TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ፎቶ🔝በአማራ ክልል #ደብረብርሃን ከተማ የተዘያዙት 52 ህገወጥ የጦር መሣሪያዎች ከላይ በፎቶው የምትመለከቷቸው ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ኢትዮጵያውያን የጠበበን ቦታ ሳይሆን #ፍቅር ነው፡፡›› በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የሀይማኖት መሪ የሆኑት ሃጂ #ሙስባ_ሙሃመድ_አሚን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ🔝

"ሀዋሳ ዛሬ 12:00 ገደማ ቅዱስ ገብርኤል አካባቢ የትራፊክ አደጋ ተከስቷል። አደጋው የተከሰተው ሞተር እና መኪና ተጋጭተው ሲሆን ሞተር ላይ አንድ ቤተሰብ ናቸው ያሉት አባት፣ እናት እና ልጅ ናቸው። ህፃኑ ልጅ ላይ ከባድ ጉዳት ነው የደረሰው። የአደጋውን ምክንያት ፖሊስ እያጣራው ነው። የመኪና አደጋ አስከፊነት ጨምሯል። ቤቢ ከሀዋሳ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ‼️

በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በምትገኘው ሸካ ዞን የተለያዩ ግጭቶች መሰማት ከጀመሩ ጥቂት ወራቶችን አስቆጠሩ።

ይህም አለመረጋጋት #በሚዛን_ቴፒ_ዩኒቨርስቲ የተመደቡ ተማሪዎችን የትምህርት ጉዳይ አስተጓጉሏል።

የዚህ ችግር መንስኤ በነዚህ ጥቂት ወራት የተከሰተ ሳይሆን ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ የሸኮ ሕዝብ ራሳችን በራሳችን እናስተዳድር የሚለው ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱ እንደሆነ በሥራ ምክንያት ነዋሪነቱን አዲስ አበባ ያደረገውና የአካባዊው ተወላጅ #ኮስትር_ሙልዬ ይናገራል።

የያደገበትን አካባቢ 'ትንሿ ኢትዮጵያ' ሲል የሚጠራው ኮስትር የሸካ ዞን የብዙ ህዘቦች መናኸሪያም እንደሆነች ይናገራል።

በተለይም ከጥቂት ጊዜ ወራት በፊት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪያት ከማል የአካባቢውን ሕዝብ ሊያናግሩ ከመጡ ወዲህ ደግሞ ነገሮች መባባሳቸውን የከተማዋ ሰላም ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ መንገሻ አዲስ ይናገራሉ።

የሸካ ዞን የመዠንገር፣ ሸካ እና ሸኮ ብሔሮች የሚኖሩበት ሲሆን፤ ከአፈ ጉባዔዋ ጋር በነበረው ውይይት ላይ የተሳተፉት ሰዎች እኛን የማይወክሉ ናቸው በሚል መንስዔ ችግሩ እንደተባባሰ ኮስትር ለቢቢሲ ገልጿል።

«አፈ ጉባዔዋ ውይይት ላይ ሳሉ፤ ከአዳራሹ ውጭ ያሉ ወጣቶች ተቃውሞ በማሰማታቸው ወጥተው አነጋግረዋቸዋል። ቢሆንም ጉዳዩ
ሊፈታ ስላልቻለ የአካባቢው ሕዝብ ተቃውሞውን በሥራ ማቆም አድማ እየገለፀ ነው፤ ትምህርት ቤቶችም ዝግ ናቸው» ብሏል ኮስትር።

በቴፒ ከተማ እና የኪ በተሰኘችው ወረዳ ከሆስፒታል በቀር ሌሎች የመንግሥት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሥራ ላይ እንዳልሆኑ ከነዋሪዎችና ከቴፒ ከተማ ፀጥታና ፍትህ ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ ተሥፋዬ አለም ሰምተናል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ጉዳዩን ለክልልም ሆነ ለፌዴራል መንግሥት እንዳቀረቡና ምንም አይነት ምላሽ እንዳልተሰጣቸውም ምሬታቸውን አሰምተዋል።

ከተማዋ ባለመረጋጋቷና የንግድም ሆነ ሌሎች እንቅስቃሴዎች በመቆማቸው ምክንያት ልጆቻቸውን አዲስ አበባ ድረስ ልከው እያስተማሩ ያሉ ነዋሪዎች እንዳሉ ኮስትር ያስረዳል።

«እንግዲህ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ አሁንም ተቸግሮ ነው ያለው፤ የቴፒ ዩኒቨርሲቲም ተማሪዎችን ያልጠራበት ምክንያት ይህ ነው።» ይላል

የአካባቢው ሕዝብ ትኩረት እንዲሰጠው ነው እንቅስቃሴዎችን ወደማቆም የተገባው ሲል ኮስትር ሁኔታውን ያስረዳል፤ «ቢያንስ የፌዴራል ቢሮ ዝግ ሲሆን ለምን ሆነ ብሎ የሚመጣ አካል ይኖራል በሚል" እንደሆነ የሚናገረው ኮስትር «አዲሱ የክልሉ አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስም ጉዳዩን ያውቁታል፤ ሶስት ወር ገደማ ሆነው። ነገር ግን ምንም ዓይነት ምላሽ አላገኘንም።» ብሏል።

ጥያቄው ምንድነው?

የደቡብ ክልል መንግሥት የዞን እና ክልል እንሁን ጥያቄዎችን በመመለስ እና በመመርመር የተጠመደ ይመስላል።

«የክልሉ መንግሥት ጉዳዩን በደንብ ያውቀዋል፤ በቅርቡ ዞኖችን እንደ አዲስ ሲያዋቅር እንኳ የእኛን አካባቢ ጥያቄ ችላ ብሎታል» በማለት ኮስትር ቅሬታውን ያሰማል።

የሸካ ዞን በዋናነት የሶስት ብሔር ተወላጆች ይኖሩበታል፤ ሸካ፣ ሸኮ እና መዠንገር።

ከእነዚህ ብሔሮች መሃል የሸካ የበላይነት ስላለ እኛ ራሳችን በራሳችን እንደ ዞን ማስተዳደር እንድንችል ይሁን ዋነኛው ጥያቄ እንደሆነ ኮስትር እና አቶ መንገሻ ያስረዳሉ።

ትላንት ረፋዱ ላይ በቴፒ ከተማ አለመረጋጋት ነበር የሚሉት አቶ መንገሻ፤ ጥያቄያቸው ከራስን ማስተዳደር ወደ መሠረተ ልማት ጥያቄ ወርዷል።

ጥያቄያቸውንም ለክልል ምክር ቤት እንዲሁም ለፌዴሬሽን እንዳቀረቡ ገልፀዋል።

"በጣም በርካታ ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ጩኸቱን አሰምቷል። አሁንም ቢሮዎች አገልግሎት እየሰጡ አይደሉም። በሺዎች የሚቆጠሩ የሸኮ እና የመዠንገር ተወላጆች ዛሬ ወደ ከተማ ወጥተው አወያዩን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥያቄያችንን የመሠረተ ልማት ነው ማለቱ ተገቢ አይደለም ብለው ወጥተዋል።» ብለዋል፥

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ዋና አማካሪ የሆኑት #አኔሳ_መልኮ ሁኔታውን አጥንተን ምላሽ እንሰጣለን ብንልም የሚሰማን ማግኘት አልቻልንም ይላሉ።

«ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድር የሚሉ አሉ። እኛ ይህ ትክክል ነው ብለን ዛሬውን ምላሽ መስጠት አንችልም። በጥናት ወደፊት ይታያል ተብሎ ተነግሯቸዋል። ዛሬውኑ ይደረገልን፤ ዛሬውኑ ይጠና የሚሉ አሉ" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል
አቶ አኔሳ የአቶ ሚሊዮን አስተዳደር ሁኔታውን በማረጋጋት ሥራ ላይ መጠመዱን ይናገራሉ።

«አመራሩ የማረጋጋት ሥራ ላይ ነው፤ ከዚህ ውጭ የሆነ ነገር እንዳይኖር ነው የምንሰጋው። ዋናው ሰላምና መረጋጋት ነው።»

ለአለመረጋጋቱ ዋናው መንስዔ የሕዝቡ ጥያቄ አለመመለስ ሆኖ ሳለ ጥያቄው መፍትሄ ሳይበጅለት ሰላም ማምጣት አይከብድም ወይ የሚል ጥያቄ ለአማካሪው ሰንዝረንላቸው ነበር።

«ጥናት ይካሄዳል ብያለሁ እኮ፤ አጥኚ ቡድኑም በሰላም መንቀሳቀስ መቻል አለበት። መደማመጥ ከሌለ፤ እኔ ያልኩት ብቻ ይሰማ የሚል ባለበት እንዴት መሥራት ይቻላል?» በማለት ጥያቄ ያነሳሉ የደቡብ ክልል የገጠር ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ አክሊሉ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለማነጋገር ትላንት በሥፍራው ቢገኙም ሰዎች እየመረጡ እንጂ ሁላችንንም አላነገሩንም ሲሉ ነዋሪዎቹ ይወቅሳሉ።

ኃላፊውን ለማግኘት ቢቢሲ በተደጋጋሚ ስልክ ቢደውልም ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ሊነሳ አልቻለም።

በአካባቢው የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች ተሰማርተው ፀጥታ ለማስከበር እየጣሩ እንደሆነና፤ አከባቢው አሁንም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደማይስተዋልበት ኮስትር ይናገራል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

ሜድሮክ ፒያሳ አካባቢ ያጠረውን ጨምሮ በመዲናዋ ለዓመታት ያለስራ ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን አጥር #የማፍረስ ስራ ነገ በይፋ ይጀመራል።

በነገው እለት አጥር የማፍረስ ስራ ከሚጀመርባቸው ውስጥ ሜድሮክ ኢትዮጵያ ፒያሳ አካባቢ ለግዙፍ የገበያ ማእከል ግንባታ ከተረከበው በኋላ ለዓመታት አጥሮ ያቅመጠው ቦታ አንዱ ነው።

ሜድሮክ ፒያሳ አካባቢ ያለውን ስፍራ ለልማት ከተረከበ በኋላ ያለምንም ስራ ከ20 ዓመት በላይ አጥሮ ማስቀመጡም አይዘነጋም።

በተጨማሪም በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች በልማት ስም መሬት ከወሰዱ በኋላ ሳያለሙ ለበርካታ ዓመታት ታጥረው የተቀጡ መሬቶች ላይ ያሉ አጥሮችም ከነገ ጀምሮ መፍረስ ይጀምራሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለረጅም ጊዜ ታጥረው በቆዩ ቦታዎች ንብረታቸውን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ባላነሱት ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ተከትሎ ነው አጥሮቹ የሚፈርሱት።

የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት የደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን እርምጃ መውሰድ የጀመሩት።

አስተዳደሩ ባልለሙ ቦታዎች ላይ ንብረቶቻቸውን ያስቀመጡ አካላት ንብረታቸውን እንዲያነሱ ከሳምንት በፊት መግለጫ መስጠቱ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጅ እነዚህ አካላት ንብረቶቻቸውን ማንሳት ባለመጀመራቸው ምክንያት አስተዳደሩ ወደ እርምጃ የገባው።

አስተዳደሩ የህዝብን ሃብት ለተገቢው ልማትና ለነዋሪዎች ተጠቃሚነት እንዲውል በጀመረው ተግባር ህገ ወጥነትን እንደማይታገስና፥ ህግ የማስከበር ሃላፊነቱን እንደሚወጣ መግለጹም ይታወሳል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ‼️

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተከሰተ #ግጭት ጉዳት መድረሱ ተገለፀ።

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በትላንትናው ዕለት በሁለት ተማሪዎች መካከል የተከሰተ ግጭት ሰፍቶ ለተማሪዎች #መጎዳትና ለትምህርት መስተጓጎል ምክንያት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ሐይማኖት_ዲሳሳ ለኢቢሲ እንደገለፁት ግጭቱ መጀመሪያ ላይ የግል ቢሆንም ወደ ኃላ ላይ ሰፍቶ ወደ ሁከት ተሸጋግሮ ትናንትና ዛሬ 34 ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ከተጎችዎቹ ውስጥ 29ቱ ቀላል ጉዳት በመሆኑ ወዲያው ህክምና ተደርጎላቸው ተመልሰዋል፡፡5 ያህሉ ደግሞ በአሶሳ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡

አሁን ላይ ተፈጥሮ የነበረው ሁከት #በመብረዱ ተማሪዎችን ጭምር በማወያየት ችግር ፈጣሪዎቹን ለመለየት እየተሰራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሐይማኖት ተናግረዋል፡፡

የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስም በስፍራው ተገኝተው የማረጋጋቱን ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኙም ተዉቋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በርበራ‼️

የኢትዮጵያ መንግሥት በራስ ገዟ ሱማሌላንድ የሚገኙትን ዲፕሎማቲክ ልዑኩን #ጠርቷል፡፡

በበርበራ የኢትዮጵያ ቆንስላ ሃላፊው በርሄ ተስፋይ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱም All East Africa የተሰኘው ዜና ወኪል ዛሬ በድረገጽ አስነብቧል፡፡

የቆንስሉ መጠራት በቀጠናው የአሰላለፍ ለውጥ በመምጣቱ እና ኢትዮጵያ ከሱማሊያ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት በመጥበቋ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

“ምናልባት ጠቅላይ ሚንስትር #ዐቢይ_አሕመድ ከሱማሌላንድ ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማቀዝቀዝ እንደሚፈልጉ አንድ ምልክት ሊሆን ይችላል” ሲሉ የሱማሌላንድ ፓርላማ አባል ኢስማኤል አብዲራህማን ለዜና አገልግሎቱ ተናግረዋል፡፡

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት #ሞሃመድ_ፎርማጆ በቅርቡ ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳያችን ከመግባት ትቆጠብ ሲሉ ማሳሰባቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በትግራይ ክልል የሚነገሩ ቋንቋዎችን መሰረት ያደረገ አገር አቀፍ ሲምፖዝየም በመቀሌ ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ የትግራይ ቋንቋዎች አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር #ዳንኤል_ተክሉ ዛሬ እንደገለፁት ከህዳር 14 ቀን 2011 ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚካሄደው ሲምፖዝየም ዋና አላማው በክልሉ የሚነገሩ ቋንቋዎች ስነ ልሳን፣ ስነ ቃልና ስነ ጽሁፍ እድገት ዙሪያ ለመወያየት ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባኤ  አቶ #ገዙ_አሰፋ ዞኑን በምክትል ዋና አስተዳዳሪነት እንደመሩ ሾሟል፡፡

©ena(ዲላ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH_ETH v2.apk
4.3 MB
TIKVAH-ETH የሞባይል መተግበሪያ!
#UpdateSport በአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣርያ ከሶማሊያ ጋር ጅቡቲ ላይ የመልስ ጨዋውን ያደረገው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ቡድን 1-0 ተሸንፏል፡፡ በዚህም በድምር ውጤት 4-1 አሸንፎ ወደ ሁለተኛው ዙር ማጣርያ ማለፍ ችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ቀጣይ ተጋጣሚ ማሊ ስትሆን በመጋቢት ወር ላይ የሚከናወን ይሆናል፡፡

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ🔝

ለዘመናት በአንድነትና በፍቅር የቆዩ በወላይታና ሲዳማ ብሔረሰቦች መካከል ተከስተው የነበረውን አለመግባባትን በማስወገድ በፍቅር፣ በይቅርታና በዕርቅ አንድነታቸውን ዳግም እንዲቀጥሉ የሚያስችል #የዕርቀ_ሰላም_ኮንፈረንስ በወላይታ ሶዶ ተካሂዷል፡፡

ኮንፈረንሱ ከቀናት በፊት በሲዳማ ዞን የተጀመረ ሲሆን በተቀመጠለት መርሃ ግብሩ መሠረት በወላይታ ሶዶም ከሁለቱም ብሔረሰብ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተደርጓል፡፡

የወላይታ ዞን ተጠባባቂ አስተዳደር አቶ #ዳጋቶ_ኩምቤ በኮንፈራንሱ መክፈቻ እንደተናገሩት በወላይታና ሲዳማ ብሔረሰብ መካከል ያለው አንድነት ከብረት የተጠናከረ ነው፤ በመሆኑም ዛሬ በሚናደርገው መድረክ አንድነታቸውን እናስቀጥላለን እንጅ አንፈጥርም ብለዋል፡፡ ስለሆነም ተከስተው የነበረውን አለመግባባትን በማስወገድ፤ ያለፈውን በመተው ወደፊት በመጓዝ ሁላችንም በሁሉም ዘርፍ አስፈላጊ ለሆነው ሠላም ዘብ መቆም ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ሚሊዮን_ማትዎስ በኮንፈረንሱ ተገኝተው እንደተናገሩት ሁለቱም ብሔረሰቦች ሠላም ፈላጊ ናቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የህዛባችን ሠላም የሚያደፈርሱ የትኛውም ኃይል ለሠላም ጤንቅ ናቸውና ፈልፍለን እያወጣን ለሁለቱም ህዝቦች ጋራ ተጠቃሚነት፣ ለሠላምና ለዴሞክራሲ መስፈን እንሠራለን ብለዋል፡፡

የኢፌዴሪ ሠላም ሚኒስተር ወ/ሮ #ሙፈሪያት_ካሚል እንደተናገሩት ስለ ሠላም የሁለቱም ህዘቦችና ሽማግሌዎች ያዉቃሉ፤ ጥበብ ጥበበኞች ዘንድ ትገኛለች፤ ዕዉቀትም በአስተማር ዘንድ፡፡ በመሆኑም ዛሬ በሁለቱ ህዝቦች ሠላም ፍላጎት መሠረት የዕርቅ ማዕድ ተቋዳሽ ሆነናል፡፡ ለሁላችንም እንኳን ደስ አለን ብለው የወላይታና ሲዳማ አንድነት አይበጠስም፣ አይሰበርም ይልቁንስ ሊበጥስ የሚጥር ኃይል ይበጠሳል እንጅ በማለት አንድነት ይበልጥ ይጠናከራል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ ገልለተኛ አካል የሆነ የዕርቅ ሽማግሌም ከሐምሌ 23/2010 ዓ.ም ጀምረው የተሠራውን የዕርቅ ሂደቱንና ከሁለቱም ህዝቦች በኩል የተነሱና በጋራ መስማማት የተዳረሱ ጉዳዮችን በሪፖርት መልክ አቅርበዋል፡፡ በተነሱ ሀሳቦችም ሁለቱም በኩል የተገኑ ሽማግሌዎች ይቀር መባባላቸውን ዕርቅና ፍቅር እናውርድ ብለው በመስማማታቸው መሠረት ዕርቁ ልፈፀም መቻሉንም አስረድተዋል፡፡

ሽማግሌዎችም ከሁሉ በላይ ከጌታ ጋር ያለንን አንድነታችን ስናጣክር ሌላው ሁሉ ይሆናል የመንግስት አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ወደ ፈጣር እንቅርብ ፣ ያለፈውን እንተው ወደ ፊት እንጓዝ በማለት መክረዋል፡፡

በመድረኩም ከሁሉም ቤተ ክርሲቲያን የተገኙ መሪዎችም የፀሎትና ቃል ስብከት ፕሮግራም አድርገዋል ይህም የወላይታና ሲዳማ የጥንት መሠረቱ ወንጌል ነው ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻ ከሁለቱም ብሔረሰብ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን የሰጡት ላለፈው ይቅር ተባብለዋል፡፡ በመሆኑ የባህላዊ ዕርቅ ሥርዓትም ተደርጓል፡፡

ምንጭ፦ የወላይታ ሶዶ ከተማ ባ/ቱ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️
ሰብዓዊነት⁉️

ለ30 ደቂቃ በየቤታችሁ ተወያዩ!!
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ በየዶርማችሁ!!

#ሰብዓዊነት ከምንም ነገር ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። ሰው ሲሞት፣ ሲደበደብ፣ ሲጎዳ፣ ሲሰደድ ስናይ ልባችን ሊደማ የሚገባው የኛ ወገን እና ብሄር ተወላጅ ስለሆነ ብቻ መሆን የለበትም። የሰው #ስቃይ እና #መከራ እንደሰውነቱ ካልተሰማን በህይወት መኖራችን ትርጉም አልባ ነው። ሰው ሲኖር ነው ሀገር፣ ብሄር፣ ዘር፣ ክልል፣ ባንዲራ የሚኖረው። ሰው በሰውነቱ ብቻ የሚከበርባትን ታላቅ ሀገር ለመፍጠር እኛ አስተዋፅኦ እያደረግን ነው???

3 እና ከዚያ በላይ ሆናችሁ በያላችሁበት ተወያዩ!! ውይይታቹ ላይ የተነሱ ሀሳቦችን ላኩልኝ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia