TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ረቂቅ በጀቱ ነገ ይፀድቃል! ዛሬ ውይይት የተካሄደበት ረቂቅ በጀቱ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት ይፀድቃል።

*ዛሬ ጥዋት ኦነግ፣ኦብነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ በይፋ ተሰርዘዋል።

#ነገ ዓርብ ዶክተር አብይ ምክር ቤት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ📌ዛሬ ውይይት የተካሄደበት ረቂቅ በጀቱ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት ይፀድቃል።

*ዛሬ ጥዋት ኦነግ፣ኦብነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ በይፋ ተሰርዘዋል።

#ነገ ዓርብ ዶክተር አብይ ምክር ቤት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

በአዲስ አበባ የሚገኙት 10 ክፍለ ከተሞች ምክር ቤቶች #ነገ አስቸኳይ ጉባኤዎቻቸውን ያካሂዳሉ። ምክር ቤቶቹ በአስቸካይ ጉባኤዎቻቸው የክፍለ ከተሞቹን ዋና #አመራር ሹም ሽር እንደሚያደርጉ የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ነገ ስናድግ በሰላም እንድንኖር #ዘረኝነትን አታውርሱን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮ-ኤርትራ⬇️

ወደ ጦርነት ገብተው ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ግንኙነታቸውን አቋርጠው የኖሩት እና በቅርቡ ግኑኝነታቸውን ያደሱት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ #ነገ በሳዑዲ አረቢያ በሚካሄድ ስነ ስርዓት በቅርቡ የገቧቸውን #የሰላም ስምምነቶች የሚያጠናክር ስምምነት ይፈራረማሉ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይን ጠቅሰው የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡትም በሪያድ በሚካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓት ላይ የተመድ ዋና ፀሃፊ #አንቶኒዮ_ጉተሬዝ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ እንዲሁም የሳዑዲ አረቢያው ንጉስ #ሳልማን ይገኛሉ ተብሏል።

📌የስምምነቱ ዝርዝር ይዘት ይፋ አልተደረገም።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ⬇️

በአዲስ አበባ ነገ እውቅና የተሰጠው #ሰልፍ አለመኖሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በከተማው ሕገ ወጥ ሰልፍ የሚደረግ ከሆነ በሕግ አግባብ #እርምጃ እንደሚወሰድም ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

አንዳንድ ግለሰቦች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ #መሟለት ያለባቸውን መስፈርቶች ማለትም የሰልፉ አስተባባሪዎች ማንነትና አድራሻ፣ እንዲሁም ሰልፉ ላይ የሚገኝ የሰው ብዛት ሳያሳውቁ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰልፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ለህብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት ሲባል አብዛኛው የጸጥታ ኃይል በሌላ የጸጥታ ስራ ላይ በተሰማረበት በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ አለመኖሩን ኮሚሽኑ አስታውቆ፣ #ነገ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ መሟለት ያለባቸውን
መስፈርቶች ሳያሟሉ ሰልፍ ለማድረግ የተዘጋጁ አካላት ከሕገ ወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባና ይህንን ማሳሰቢያ ተላልፈው በሚወጡ አካላት ላይ ኮሚሽኑ በሕግ አግባብ #እርምጃ ለመውሰድ እንሚገደድ አስታውቋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia