TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update አማራ ክልል⬇️

በአማራ ክልል በዚህ ዓመት በትራፊክ አደጋ የ1 ሺህ 1 መቶ ሀምሳ ሁለት(1152) ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ ባለፈው አመት በክልሉ በታራፊክ አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ከጠፋ ሰዎች ቁጥር አንፃር የዘንድሮው በልጦ ተገኝቷል። ባለፈው ዓመት በትራፊክ አደጋ 1 ሺህ ዘጠና ስድስት(1096) ሰዎች ህይወታቸው ያለፈው፡፡

በሌላ በኩል⬇️

▪️በክልሉ በዚህ አመት 8 መቶ 57(857) ተሸከርካሪዎች አደጋ አድርሰዋል። ባለፈው ዓመት ደግሞ 7መቶ 96(796) ተሸከርካሪዎች አደጋ አድርሰዋል፡፡

የችግሩን አሳሳቢነት ለማሳወቅ ፣ ለመጠየቅ እና እውቅና ለመፍጠር ከህጻን እስከ አዋቂ የሚሳተፍበት #ሰልፍ ነገ በዋና ከተማዋ #ባህርዳር መዘጋጀቱን ከአማራ ክልል የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር መረጃ📌አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ነገ፣ መስከረም 9/2018 ዓ.ም. #ዝግ እንደሚሆን አስታውቋል።

ኤምባሲው ለነገ አገልግሎቱን የሚያቋርጠው በከተማዪቱ ውስጥ በሚካሄደው “ግዙፍ ሊሆን ይችላል” ባለው #ሰልፍ ምክንያት የተጠናከረ ጥንቃቄ ለመውሰድ ሲባል መሆኑን ገልጿል።

ቀደም ሲል ተይዘው የነበሩ የቪዛ ቀጠሮዎችና ኤምባሲው ለአሜሪካዊያን ዜጎች ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ለነገ መስከረም 9/2018 ዓ.ም /19 September 2018/ ተቀጥረው የነበሩ ጉዳዮች በሙሉ የተሠረዙ መሆናቸውን አስታውቋል።

አሜሪካዊያን በኤምባሲው ዌብሳይት አማካይነት አዲስ ቀጠሮ እንዲይዙ መክሯል።

ከኢሚግራንት ቪዛ ጠያቂዎች ጋር ተለዋጭ ቀጠሮ ለማድረግ ኤምባሲው በቅርቡ የሚያገኛቸው መሆኑንና ነን-ኢሚግራንት ቪዛ ለማግኘት ያመለከቱ ደግሞ በኤምባሲው ዌብሳይት ላይ አዲስ ቀጠሮ እንዲጠይቁ አሳስቧል።

አጣዳፊ አገልግሎት የሚፈልጉ አሜሪካዊያን ዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ዌብሳይት ላይ ያለውን የአድራሻ/የመገናኛ መረጃ እንዲያዩ መክሯል።

ከኤምባሲው መደበኛ አገልግሎቶች በተጨማሪ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የአሜሪካ ማዕከል እና ዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ውስጥ የሚገኘው ሳችሞ ማዕከልም ነገ ዝግ ሆነው እንደሚውሉ አስታውቋል።

በሰልፉ ላይ #የሚሣተፉ ሁሉ ሃሣቦቻቸውንና ፍላጎቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለፃቸውን እንደሚያበረታታም ኤምባሲው ገልጿል።

©VOA 24(የአማርኛው አገልግሎት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

በአዲስ አበባ #ለዛሬ የተጠራ ምንም ዓይነት #ሰልፍ አለመኖሩን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

ኮሚሽኑ ለfbc እንደገለፀው፥ ህብረተሰቡ በመዲናዋ ምንም ዓይነት የተጠራ ሰልፍ አለመኖሩን አውቆ #መደበኛ የእለት ተእለት እንቅስቃሴውን እንዲያከናውን አሳስቧል።

መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ለረቡዕ በአዲስ አበባ የተጠራ ሰልፍ አለ በሚል ያወጡት መረጃ ሙሉ በሙሉ #የተሳሳተም ነው ብሏል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia