TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update የኢትዮ ቴሌኮም ቅናች ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ቢነገርም እስካሁን ድረስ በቀደመው ታሪፍ ነው እየተሰራ የሚገኘው።

ተጨማሪ ጥያቄዎችን ይዤ ወደ ሚመለከተው አካል የስልክ ጥሪ ባደርገም አልተሳካልኝም።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️ኢትዮ ቴሌኮም ያደረገውን የታሪፍ ቅናሽ ከላይ ባሉት ምስሎች በዝርዝር ማየት ትችላላችሁ።

©EthioTelecom
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ቅናሽ ተግባራዊ የሚደረገው ከነገ ጀምሮ እንደሆነ ለማረጋገጥ ችያለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

በያዝነው ክረምት በተከዜ ወንዝ ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድባችን እየገባ ያለው የውኃ መጠን የሞላ በመሆኑ ለግድቡ ደህንነት ሲባል የውኃውን መጠን ከነሐሴ 18 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ መቀነስ አስፈልጓል፡፡

ስለሆነም ከግድቡ በታችኛው እና በላይኛው ተፋሰስ አካባቢዎች ማለትም በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር በመሃከለኛው ዞን የሚገኙ ወረዳዎች ማለትም በጣንቋአበርገሌ፣ በቆላ ተንቤን፣ በላዕላይማይጨው፣ በታህታይ ማይጨው፣ በመረብ ለሄ በሰሜን ምዕራባዊ ዞን ደግሞ በአሰገደ ጺምበላ፣ በላዕላይ አዲያቦ፣ በመደባይ ዛና፣ በታህታይ አዲያቦ፣ በታህታይ ኾራሮ፣ በፀለምቲ እንዲሁም በምዕራባዊ ዞን በካፍታ ሁመራ፣ በፀገዴ፣ በወልቃይት በተያያዘ ሁኔታም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር በዋግኽምራ ዞን ስር በአበርገሌ ወረዳ፣ በሰሜን ጎንደር ዞን በፀለምት ወረዳ በአጠቃላይ የተከዜ ወንዝ አዋሳኝ ቀበሌዎች እና በአካባቢው ነዋሪ ህዝቦች ከወዲሁ ይህንኑ #በመገንዘብ በሰውም ሆነ በእንሰሳት ላይ በሚለቀቀው #ደራሽ ውሃ #ጉዳት እንዳይደርስ ተገቢውን #ጥንቃቄ ታደርጉ ዘንድ በአክብሮት ለማሳሰብ ይወዳል፡፡

📌ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የህግ የበላይነትን በማስከበር አሁን የተጀመረውን ለውጥ ቀጣይነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በክልሉ በሁከትና ብጥብጥ ተሳትፈዋል የተባሉ 300 #ተጠርጣሪዎች #በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉም ተጠቁሟል፡፡

©የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ⬇️

በሀዋሳ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ተገንብተው የነበሩ 214 ቤቶች እንዲፈርሱ መደረጉን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ ።

የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ሱካሬ ሹዳ እንዳሉት የፈረሱት ቤቶች ባለፉት ሁለት ወራት በከተማዋ የነበረውን አለመረጋጋት ተከትሎ የተገነቡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ህገ ወጥ ተግባሩን በፈጸሙት ላይ ዛሬ የማፍረስ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡

የአስተዳደሩን እርምጃ ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያ #ግጭት ለመቀስቀስ የሚጠቀሙበት በመኖራቸው የከተማው ነዋሪ #ለሰላሙ ዘብ እንዲቆም አሳስበዋል።

በአሁኑ ወቅት ከተማዋ ወደ ሙሉ ሰላሟ የተመለሰች ሲሆን በግጭት ወቅት ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችም ሙሉ ለሙሉ የማቋቋም ስራ መጠናቀቁንም አስታውቀዋል።

©ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️ዛሬ ከጥዋት 12 ሰዓት ላይ ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ ይሄድ የነበረ ፒካፕ መኪና ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ይመጣ ከነበረ የዳንጎቴ እቃ ጫኝ መኪና ጋር በመጋጨቱ የሹፌሩን ጨምሮ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የወገኖቻችንን ነብስ ይማርልን ለቤተሰቦች ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እንመኛለን!

©BW
@tsehabwolde @tikvahethiopia
#update ኢንጂነር ታከለ ኡማ⬇️

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጀነር ታከለ ኡማ #በጎርፍ አደጋው ተከትሎ ህዝቡና ተቋማት ላደረጉት ህይወት የመታደግ ርብርብ #ምስጋና አቀረቡ፡፡

በአቃቂ ክፍለከተማ የደረሰው የጎርፍ አደጋ እጅግ ከባድና አሳዛኝ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው ሆኖም ግን በክቡራን ወገኖቻችን ህይወት ላይ ምንም አይነት የህይወት አደጋ አለመድረሱ ለሁላችንም እፎይታ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ክቡሩን የወገንን ህይወት ለማትረፍ ርብርብ ላደረጉት የኢ.ፌ.ድ.ሪ የአየር ሀይል፤ የኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት፤ ለአዲስ አበባ አሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠር ባለስልጣን፤ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽንና ከምንም በላይ ደግሞ ለአከባቢው ነዋሪና ህብረተሰብ ያላቸውን ጥልቅ የሆነ አክብሮትና ልባዊ ምስጋና ያቀረቡት ኢንጀነር ታከለ እንደ አስተዳደር ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳይከሰቱ የጥንቃቄና የመፍትሄ እርምጃዎችን ጨምሮ የከተማውን የወንዝና ተፋሰስ ስራዎችን #በማልማት ከችግር ምንጭነት ይልቅ የከተማው የውበት ምንጭ እንዲሆኑ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ አዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia