TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
60K photos
1.52K videos
215 files
4.17K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ ጥያቄ አላቀረብንም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ ጥያቄ አላቀረብንም ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አስታውቀዋል።

ክልሉ ላይ " የህግ ተቀባይነት ያጡ እና ከጦርነት ትርፍ እናገኛለን የሚሉና በጥቅም የተሳሰሩ የተወሰኑ የህወሃት አንጃዎች የተወሰኑ ከፍተኛ መኮንኖችን በመያዝ ክልሉን አደጋ ላይ እየከተቱ ነው " ብለዋል።

" ይህ እንቅስቃሴ ትግራይን ወደ ሌላ የትርምስ ምእራፍ እየወሰደ ይገኛል  " ሲሉ ገልጸዋል።

ይህንን አስመልክቶ የፌዴራል መንግስት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራውን እንዲሰራ ደጋፍ እንዲያደርግ እንጂ ጦር አዝምቶ ጣልቃ እንዲገባ ጥያቄ አላቀረብንም ብለዋል።

በዚህ ደረጃ ጥያቄ ለማቅረብ የሚያስችል ሁኔታም የለም ሲሉ ገልጸዋል።

" ክልሉ ወደ ሌላ ጦርነት መግባት የለበትም።  ጊዜያዊ አስተዳደሩ የፌዴራል መንግስቱ ውሳኔ አካል ነው። የፌዴራል መንግስቱ አግባብነት ያለው ሃላፊነት መውሰድ ይኖርበታል " ብለዋል።

የትግራህ ህዝብ ዳግም ወደ ግጭት እንዳይገባና ሰላምን መፍጠር የሚቻልባቸው እድሎችን ማጽናት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
#EPA

@tikvahethiopia