TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#SafaricomEthiopia

ምን ትጠብቂያለሽ? የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ ጥቂት ቀናቶች ብቻ ቀርቶታል! ፍጠኝ ቲሸርትሽን በእጅሽ አስገቢ!

ከ M-PESA ላይ በመግዛት የ540 ብር ቲሸርት በ389 ብቻ ታገኛለሽ።

#Andegna #1Wedefit #FurtherAheadTogether
#Afar #Somali #Iftar

ዛሬ የአፋር እና ሶማሌ ወንድማማች ህዝቦች የኢፍጣር መርሐ ግብር በጅግጅጋ እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሃጂ አወል አርባ፣ የሰላም ሚንስትሩ አቶ መሀመድ እድሪስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።

#SomaliRegionGovCommunication

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE #NGAT ትምህርት ሚኒስቴር የሶስተኛውን ዙር የ2017 ዓ.ም የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ይፋ አደረገ። ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ በ https://ngat.ethernet.edu.et/registration የመመዝገቢያ ሊንክ በኩል…
#Update #MoE

" እስከምሽት ድረስ እየሞከሩ መቆየት ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

ሀገር አቀፍ የ2017 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የአመልካቾች ምዝገባ ከ የካቲት 27/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ እንደሚከናወን የትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ዛሬ በሚያበቃው የአመልካቾች የምዝገባ ሂደት ለመመዝገብ የሞከሩ ተፈታኞች የመመዝገቢያው ማስፈንጠሪያ ወይም ሊንክ እየሰራ አይደለም የሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

ከምዝገባ ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሚል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስቀመጣቸው ስልኮች ቢኖሩም እየሰሩ አለመሆኑንም ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን ዶ/ር ኤባ ሚጀናን ማብራሪያ ጠይቋል።

በምላሻቸውም " የኔትወርክ ችግር ይሆናል እንጂ ሲስተሙ ይሰራል ደጋግማቹ ሞክሩ " ብለዋል።

አክለውም " ሁሉም ሳይሆን የተወሰኑ ሰዎች ናቸው ለመመዝገብ እክል የገጠማቸው በርካታ ሰዎች አሁንም እየተመዘገቡ ነው " ያሉ ሲሆን እስካሁን ባለው 8 ሺ የሚጠጋ ሰው መመዝገቡን ጠቁመዋል።

" ፕሮሲጀሩን መከተል ግድ ይላል ከዘለሉ ላይሰራ ይችላል ነገር ግን ሁል ጊዜ ብዙ ሰው በመጨረሻ ነው የሚመዘገበው ፣መጨናነቅ ይኖራል እንዳይዘጋ በሚል በርካታ ሰዎች በአንድ ላይ ስለሚሞክሩ ጫና ይኖራል በዚህ ምክንያት ካልሆነ በቀር ምንም ችግር የለበትም " ነው ያሉት።

ሊራዘም የሚችልበት አጋጣሚ ይኖራል ወይ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄም " መራዘም ሳይሆን እስከምሽት ድረስ እየሞከሩ መቆየት ይችላሉ ኔትወርክ ያለበት አካባቢ በመሆን ደጋግመው ይሞክሩ " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተፈታኞች የመፈተኛ 'User Name' እና 'Password' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ መሆኑን እና የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም እንደሚጠበቅባቸው ማስታወቁ ይታወሳል።

ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን በቀጣይ እንደሚገልጽ አሳውቋል፡፡

መመዝገቢያ ፦
https://ngat.ethernet.edu.et/registration

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " እንቅስቃሴው እጅግ አደገኛና የማያባራ ቀውስ የሚያዋልድ በመሆኑ በአስቸኳይ ይቁም " - አቶ ጌታቸው ረዳ " ' የሰራዊት አመራር ውሳኔ ' በሚል ህገ-ወጥ ጉባኤ ላካሄደ ቡድን ስልጣን ለማስረከብ የተጀመረ እንቅስቃሴ እንዲቆም " ሲል የትግራይ ክልል ጊዜዊ አስተዳደር ትእዛዝ ሰጠ። ትእዛዙን የሰጡት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ህገ-ወጥ ተግባሩ " አስነዋሪ…
#Tigray

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ያለችውን ትግራይ ማስተዳደር የማይችልበት ሁኔታ ተፈጥረዋል" - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት የተወሰኑ የሰራዊት አመራሮችን በመጠቀም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እያካሄደ እንደሆነ ተናግረዋል።

" ቡድኑ በድርጅቱ የቁጥጥር ኮሚሽንና በኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽን እውቅና የሌለው ህገ-ወጥ ጉባኤ ያካሄደ ነው "  ያሉት ፕሬዜዳንቱ  " ቡድኑ በማንኛውም መመዘኛ እና መለኪያ ወደ ስልጣን አይመለስም " ሲሉ አክለዋል።

ጥቂት የሰራዊት አመራሮች እንደ መሳሪያ በመጠቀም በየወረዳው እና ቀበሌው በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ የስራ ሃላፊዎች ማህተም በመቀማት ላይ ተጠምዷል ሲሉም ተናግረዋል።

" ይህ ህገ-ወጥ ተግባር የተረጋጋ መንግስታዊ አገልግሎትና ፀጥታ እንዳይኖር እክል ፈጥሯል
" ሲሉም ገልጸዋል።

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ያለችውን ትግራይ ማስተዳደር የማይችልበት ሁኔታ ተፈጥረዋል " ሲሉም አክለዋል።

" የክልሉን ፀጥታ በማድፍረስ የፕሪቶሪያ ስምምነት ለማፍረስ የተጀመረው እንቅስቃሴ እጅግ አደገኛና ጥፋት የሚያስከትል ነው " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ተግባሩ በአስቸኳይ እንዲቆም ሁሉ መተባበር አለበት " ብለዋል። 

ሌላው አቶ ጌታቸው ረዳ በመግለጫቸው በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስታት መካከል በግልፅ የሚታይ ወጥረት አለ ብለዋል።

" ውጥረቱ ወደ ግጭት ተሸጋግሮ ትግራይ የጦርነት አውድማ እንዳትሆን መስራት ይጠበቅብናል " ሲሉ ተደምጠዋል።

ትናንት የካቲት 30 እና ዛሬ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም በትግራይ ምስራቃዊ ዞንና በመቐለ የተወሰኑ የሰራዊት አመራር ያሰማሩት ኃይል ፓትሮል በመጠቀም በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ አስተዳዳሪዎች ማህተም የመቀማት እና ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ የሚወስድ ከተማ የቁጥጥር ኬላ የመስራት ምልክቶች መታየታቸው አቶ ጌታቸው ረዳ አስታውቀዋል።

ዛሬ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም የምስራቃዊ ዞን የፀጥታና የሰላም ሃላፊ በአከባቢው በሚገኙ የሰራዊት አመራር ከሁለት ሰዓት በላይ ታግተው መለቀቃቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጠዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ላይ ጊዚያዊ የእግድ ደብዳቤ ፃፉ።

እግዱ የተፃፈላቸው ከፍተኛ አመራሮች ፦
- ሜጀር ጀነራል ዮውሃንስ ወ/ጊዮርጊሰ
- ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ
- ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሃይለ ናቸው።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም የፃፉት ጊዚያዊ የእግድ ደብዳቤ ፦

" ከመንግስት ውሳኔ ውጪ መላ ህዝባችን ፣ ወጣቱን ወደ ግርግር  ፤ የፀጥታ ሃይላችን ወደ እርስ በርስ ግጭት ብሎም ህዝባችን ወደ እማይወጣበት አዘቅት የሚያስገባ አደገኛ እንቅስቃሴ አልቆመም ስለሆነም እርስዎ ስርዓት ባለው አካሄድ መግባባት እስኪደረስ ድረስ ከመጋቢት 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከአዛዥነትዎ የታገዱ መሆንዎን አስታውቃለሁ " ይላል።

በትግራይ ክልል በአመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት እንዲፈታ ብዙ ጥረት ቢደረግም ምንም መፍትሄ ሳይገኝለት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ነዋሪዎችም ሁኔታው ስጋት ላይ ጥሏቸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia