#ዛሬ
" ዝክረ አድዋ ኢትዮጵያዊነት "
“ ዝክረ አድዋ ኢትዮጵያዊነት ” የተሰኘ ልዩ የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር፣ ዛሬ አርብ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በአድዋ ሙዚየም ይካሄዳል፡፡
የመርሃ ግብሩ አዘጋጅ አብርሃም ግዛው ኢንተርቴይንመንት ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ ‹‹ኢትዮጵያዊነት ዝክረ አድዋ” የተሰኘ ጥናታዊ ፅሁፍና ዲስኩር በምሁራን ይቀርባል ብሏል።
የግጥም ምሽትና የስታንዳፕ ኮሜዲም እንደተሰናዳ ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ፖለቲከኞች በሰላምና አንድነት ዙሪያ አነቃቂ ንግግር፣ እንዲሁም ጀግኖች አርበኞች ሽለላና ፉከራ በባህላዊ ባንድ ታጅበው ያቀርባሉ ተብሏል።
በመርሃ ግብሩ ፦
- ደራሲ፣ ገጣሚና ፀሀፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣
- አምባሣደር ዲና ሙፍቲ፣
- ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ፣
- ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣
- መምህር ዲያቆን ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣
- ጋዜጠኛና ደራሲ ጥበቡ በለጠ፣
- መጋቢ ቸርነት በላይነህ ፣
- አርቲስት ተስፋዬ ሲማ፣
- አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤልና ሌሎችም እንደሚሳተፉ ተነግሯል፡፡
የመግቢያ ዋጋ መደበኛ 300 ብር፣ VIP ደግሞ 500 ብር እንደሆነ አዘጋጆቹ ጠቁመዋል። ትኬቱን በቴሌ ብር፣ በጃፋር ቤተ-መፅሐፍት፣ በ2 ሺህ ሐበሻ የባህል ምግብ አዳራሽ እንደሚገኝ አብርሃም ግዛው ኢንተርቴንመንት ጠቁሟል፡፡

TIKVAH-ETHIOPIA
" ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር " - ፕሬዜዳንት ትራምፕ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን ነው " ሲሉ ወረፏቸው። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ በተባለው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው " ብለዋል። ትራምፕ…
" ይህን ተናግሬያለሁ ብዬ ማመን ይከብደኛል፤ ዘሌንስኪን በጣም ደፋር መሪ ነው " - ዶናልድ ትራምፕ
አወዛጋቢው የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም " አምባገነን " ሲሉ የጠሯቸውን የዩክሬኑን ፕሬዜዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ጀግና መሪ ነው " ሲሉ አሞካሿቸው።
ፕሬዝዳት ትራምፕ በዛሬው ዕለት ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
ትራምፕ አስቀድመው በዋይት ኃውስ በሰጡት አስተያየት፤ " ለቮሊድሚር ዘለንስኪ ትልቅ ክብር አለኝ " ብለዋል።
በቅርቡ ዘለንስኪን " አምባገነን " ብለው በመጥራታቸው ይቅርታ እንደሚጠይቁ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ትራምፕ " ይህን ተናግሬያለሁ ብዬ ማመን ይከብደኛል፤ ዘሌንስኪን በጣም ደፋር መሪ " ነው ሲሉ አሞካሽተዋል።
በዛሬው እለት ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘሌንስኪ ጥሩ ውይይት እንደሚኖራቸው የገመቱት ትራምፕ፤ በዩክሬን ሰላም ለማምጣት የሚደረገው ጥረት በጥሩ ሁኔታ እና በፍጥነት እየሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ለመነጋገር እና በዩክሬን ውድ ማዕድናት ዙሪያ ስምምነት ለመፈራረም ትናንት ምሽት ወደ አሜሪካ አቅንተዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን እንዲሁም ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው " ማለታቸው ይታወሳል።
" ዘለንስኪ አሜሪካን 350 ቢሊየን ዶላር በማስውጣት መጀመር ያልነበረባቸው እና የማያሸንፉት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል " ብለዋቸው ነበር።
" ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር " ሲሉም ነበር የገለጹት።
ትራምፕ " ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል፤ ካልሆነ ግን የሚያተርፈው ሀገር አይኖርም " ብለውም ነበር። #AlAin #BBC
@tikvahethiopia

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ በመጪው ዓመት / 2018 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለትምህርት ለመመዝገብ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ወይንም ፋይዳ መያዝ አስገዳጅ ሆነባቸው፡፡
የከተማው ትምህርት ቢሮ የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ይፋ አድርጓል።
ተማሪዎች የፋይዳ ምዝገባ አንዲያካሂዱ በዘመቻ መልክ ለመሰራት የታሰበ ሲሆን እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በላይ የሆናቸው ህፃናትን ምዘገባ በዘመቻ እንደሚከናወን መነገሩን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

Photo
" በነገው ዕለት አንድ ቡድን ወደ ስፍራው ያቀናል " - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ ፤ በማይናማር ታግተው የነበሩ 246 ዜጎችን በቀጣይ ሳምንት ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ነው አሳውቀዋል።
" በማይናማር በከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለማስወጣት በቶኪዮ እና በኒውዴሊ ባሉ ኤምባሲዎች በኩል ሥራዎች እየተሠሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" አሁን ላይ 246 ኢትዮጵያዊያን ከማይናማር ወጥተው ወደ ታይላንድ ደርሰዋል " ሲሉ ጠቅሰዋል።
" እነሱን ለመርዳትና የማጣራት ሥራ ለመሥራት በነገው ዕለት አንድ ቡድን ወደ ስፍራው ያቀናል " ብለዋል።
በተመሳሳይ በመካከለኛው ምስራቅ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለማስወጣት የሚደረገው ጥረት ቀጣይነት እንዳለውም ጠቁመዋል። #ኤፍኤምሲ

#ረመዷን
ታላቁ እና የተቀደሰው የረመዷን ጾም ነገ ቅዳሜ ይጀምራል።
በሳኡዲ አረቢያ የረመዷን ጨረቃ ታይታለች።
ዛሬ የተራዊህ ሶላት የሚጀመር ሲሆን ነገ ቅዳሜ የረመዷን ጾም ይጀምራል።
#Haramain

" የግብፅ እና ኢትዮጵያ ጨዋታ የኪሳራ ጨዋታዎች ናቸው። ... ለመሸነፍ ለመሸነፍ ብዙ ወጣት ተጫዋቾች አሉን " - መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር በፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ በተላለፉ ወሳኔዎች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ በትላንትናው ዕለት ሰጥቶ ነበር።
የሊጉ አክስዮን ማህበር የፋይናንስ አጣሪ ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የፋይናንስ ደንቡን በጣሱ ክለቦች እና ተጨዋቾች ላይ የቅጣት ውሳኔ ከቀናት በፊት አስተላልፎ የነበረ ሲሆን በተላለፈው ቅጣትም 4 ክለቦች እና 15 ተጫዋቾች ላይ ባደረገው ምርመራ ክለቦቹ የቅድመ ክፍያ(በሶስተኛ ወገን) ከፍለዋል በማለት 45 ሚልዮን ብር ቀጥቷል።
የአክስዮን ማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በሰሞነኛ የክለቦች የዝውውር ክፍያ ስርዓት ላይ በተሰጠ መግለጫ የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች እንደሚቀጡ አስረግጠው ተናግረዋል።
ከጋዜጠኞች ይቀጣሉ ወይ ? ተብሎ ለተነሳላቸው ጥያቄ " አዎ ይቀጣሉ " ሲሉ መልሰዋል።
በቀጣይ ከግብፅ ጋር ስለሚደረግ ጨዋታ ሲጠየቁም " እሱን ግጥሚያ ብለህ ትጠራለህ ? ማሟያ ነው " ብለዋል።
መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ አያይዘውም " ካፍ ስላስገደደን ነው የምንሄደው የኪሰራ ጨዋታዎች ናቸው ፣ ለመሸነፍ ለመሸነፍ ብዙ ወጣት ተጫዋቾች አሉን " የሚል ምላሽን ለጋዜጠኞች ሰጥተዋል።
ዋልያዎቹ ከሶስት ሳምንት በኃላ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ መርሐ ግብር በሞሮኮ ካሳብላንካ ዛውል አል አረቢ ስታዲየም የግብፅ አቻውን ይገጥማል።
ዋልያዎቹ ለመጨረሻ ጊዜ ከሁለት ዓመት በፊት በሜዳቸው ማድረግ የነበረባቸውን መርሐ ግብር በማላዊ ባደረጉበት ወቅት በሽመልስ በቀለ እና ዳዋ ሆቴሳ ጎሎች 2ለ0 ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው።
#TikvahEthiopia

" ይህን ተናግሬያለሁ ብዬ ማመን ይከብደኛል፤ ዘሌንስኪን በጣም ደፋር መሪ ነው " - ዶናልድ ትራምፕ አወዛጋቢው የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም " አምባገነን " ሲሉ የጠሯቸውን የዩክሬኑን ፕሬዜዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ጀግና መሪ ነው " ሲሉ አሞካሿቸው። ፕሬዝዳት ትራምፕ በዛሬው ዕለት ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ትራምፕ አስቀድመው በዋይት…
" በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ላይ ቁማር እየተጫወትክ ነው " - ትራምፕ
ዛሬ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ አሜሪካ ሄደው ከፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተገናኝተዋል።
" ውይይት አደረጉ " ለማለት በሚያስቸግር ሁኔታ ትራምፕ እና ባለስልጣኖቻቸው ዜሌንስኪን ሲገስጹ ፣ ንግግራቸውን ሲያቋርጡ፣ ሲመክሯቸው ታይተዋል።
ትራምፕ ዜሌንስኪን ከሩስያ ጋር የገቡበት ጦርነት የሚያቆምበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋቸዋል።
" አሁን አንተ የምትወስንበት አቋም ላይ አይደለህም " ሲሉም ትራምፕ እና ጄዲ ቫንስ ዘለንስኪን ሲገስፁ ነበር።
የገቡበት ጦርነት ያለ ቀድሞው ፕሬዜዳንት ባይደን እና 350 ቢሊዮን ዶላር የአሜሪካ ድጋፍ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ያበቃ ነበር ሲሉም ነግረዋቸዋል።
ትራምፕ " በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ላይ ቁማር እየተጫወትክ ነው። በሶስተኛው የዓለም ጦርነት ቁማር እየተጫወትክ ነው " ሲሉ ዜሌንስኪን ተናግረዋቸዋል።
" ሀገርህ ችግር ላይ ናት "ም ብለዋቸዋል።
" ደግሞ አመስጋኝ አይደለህም ፤ያ ጥሩ ነገር አይደለም " ሲሉም ገስጸዋቸዋል።
" ወይ ስምምነት ፍጠር ካልሆነ እኛ ከዚህ እንወጣለን። አሁን ምንም የቀረህ የምትመዘው ካርድ የለህም " ሲሉም ተናግረዋቸዋል።
ዘለንስኪ ከትራምፕ ጋር ከነበራቸው የጋለ የቃላት ልውውጥ በኋላ አስቀድመው ዋይት ሃውስን ለቀው ወጥተዋል።
ሁለቱ መሪዎች በጋራ መስጠት የነበረባቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰርዟል።
ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር የጋለ ንግግር ካደረጉ በኋላ በትሩዝ ትስስር ገጻቸው ላይ " ዘለንስኪ ለሰላም ዝግጁ አይደለም። ለሰላም ሲዘጋጅ ተመልሶ መምጣት ይችላል " ብለዋል።
ኢሎን መስክ በX ገጹ ላይ " ዘለንስኪ በአሜሪካ ሕዝብ ፊት እራሱን አዋርዷል " ሲል ፅፏል። #SputnikNews

ሕብረት ባንክ እንኳን ለ1446 ዓ.ሒ የሐጅ ጉዞ በሰላም አደረሳችሁ እያለ፤ የሐጅ ጉዞ ክፍያዎን በአቅራቢያዎ በሚገኙ ቅርንጫፎቻችን በልዩ መስተንግዶ እንዲፈጽሙ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡
በዚህ አጋጣሚ የሸሪዓውን መርህ መሰረት ያደረገ ሕብር ሀቅ የተሰኘ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎታችን ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡
ሐጀን መብሩር!
ሕብር ሀቅ
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ https://yangx.top/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡

#MPESASafaricom
ከUSA ገንዘብ በM-PESA እንቀበል 10% ስጦታ እና 1 ጊ.ባ ኢንተርኔት ተጨማሪ አሁኑኑ እናግኝ! ቪዛ ፣ ማስተርካርድ ወይም አሜክስ ካርድ በመጠቀም በካሽ ጎን በኩል እንላክ።
በምንዛሬ ተመን
1 USD = 137 ብር
ካሽ ጎን ይህንን ሊንክ ተጠቅመን ማውረድ እንችላለን፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo
ገንዘቦን በዳሽን ባንክ እለታዊ ምንዛሬ ያግኙ + 10%ስጦታ ።
#MPESAEthiopia #MPESASafaricom

#Update ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ የሕክምና ትምህርቱን እንዲቀጥል ተወስኗል። የተማሪ ቢንያም ኢሳያስን ትምህርት በተመለከተ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው ፤ የተማሪ ቢንያም ኢሳያስን ትምህርት በተመለከተ ለተማሪው የትምህርት ሂደት ይረዳሉ ያሏቸውን አማራጮች መቅረቡን አስታውሷል። ሆኖም ተማሪ ቢንያም ብቸኛ ፍላጎቱ የሕክምና ትምህርትን መማር እንደሆነ…
#DrBinyamEsayas
ዶክተር ቢኒያም ኢሳያስ በከፍተኛ ውጤት ተመረቀ።
ዛሬ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 179 ተማሪዎች አስመርቋል።
ከተመራቂዎቹ አንዱ ዶክተር ቢኒያም ኢሳያስ ነው።
በትምህርት ቆይታው ያጋጥሙትን ውስብስብ ችግሮች በማሸንፍ ለበርካቶች አርአያ የሆነው ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ በከፍተኛ ወጤት ተመርቋል።
ዶክተር ቢኒያም በትምህርት ቆይታው ያጋጥሙትን ውስብስብ ችግሮች አልፎ ዛሬ ለደረሰበት ስኬት በመብቃቱ መደሰቱን ገልጿል።
ዶክተር ቢኒያም እናትና አባትም ልጃቸው ከልጅነቱ ጀምሮ ጎበዝ ተማሪ መሆኑን ገልጸው፤ ለህልሙ መሳካት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣታቸውን ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ኮሚሽን በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ የሕክምና ትምህርቱን እንዲቀጥል መወሰኑ ይታወሳል።
#EPA