TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
60K photos
1.52K videos
215 files
4.18K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ከ3,000 ወጣቶች ወደ 130 የሚሆኑት ወጡ ተብሎ ዝም የሚባል ከሆነ ለቀሪዎቹ አደጋ ነው " - የወላጆች ኮሚቴ ሰርተው ለመለወጥ በሚል ከኢትዮጵያ የተሰደዱ ዜጎች በማይናማር በአጋቾች የከፋ ስቃይ እያሳለፉ በመሆኑ መንግስት ከስቃይ እንዲታደጋቸው በተደጋጋሚ መጠየቁ አይዘነጋም።  የወላጆች ኮሚቴ፣ ኢትዮጵያዊያኑ በታገቱበት የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ አጋቾች ልጆቹን ዶላር ማጭበርበር…
#Update

🔴 “ መንግስት እንዲመጡ ስላላደረገ ከእገታው የወጡት ኢትዮጵያዊያንም በፓሊስ ተመልሰው እየተወሰዱ ነው። እስካሁን ሰባት ልጆች ተወስደዋል ” - ቤተሰብ

🔵
እኛ ዜጎች አይደለንም እንዴ? መንግስት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትዕዛዝ መስጠት አይችልም? ” - ኢትዮጵያዊ በታይላንድ

➡️ “ ልጆቻችን በረሃብ ሊያልቁብን ነው ” - የወላጆች ኮሚቴ

ሰርተው ለመለወጥ ሲሉ ተታለው ወደ ታይላንድ የተሰደዱና በታጣቂዎች በማይናማር ታግተው ቆይተው የወጡና አሁንም በእገታ ያሉ ኢትዮጵያዊያን መንግስት እንዲደርስላቸው በተደጋጋሚ መጠየቁ ይታወሳል።

በሺዎች ከሚቆጠሩት ኢትዮጵያዊያን ታጋቾች ውስጥ 13ዐ የሚሆኑት ከሳምንታት በፊት ከእገታ እንደተለቀቁ፣ ሌሎች በርካቶች ደግሞ ገና ከእገታው እንዳልወጡ፣ የወጡትም ሆኑ ያልወጡት የመንግስትን ድጋፍ እየተጠባበቁ መሆኑን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

በታይላንድ ያሉ ኢትዮጵያዊያኑ አሁንስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

“ ከመግደል ያላነሰ ድብድባ ነው የሚካሄደውኮ። እኛ ዜጎች አይደለንም እንዴ? መንግስት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትዕዛዝ መስጠት አይችልም ?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታይላንድ በረራ እንዳለው እያየን ነው። እሺ ገበያውም አይዘጋበት ቢያንስ ሰው ይዞ ወደ ታይላንድ መጥቶ ሲመለስ የተወሰኑ ሰዎችን እየቀላቀለ ቢመልሰን ማቃለል አይችልም ? 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኛ አይደለም እንዴ ? ለሥራ ብለን ነው የመጣነዎኮ ስለተቸገርን ገንዘብ ለማግኘት። ገንዘብ ይዘን ደግሞ ወደ ሀገራችን ለመመለስ። 

‘መንግስት አላችሁ?’ ተብለን እስከምንጠየቅ መድረሳችን በጣም ያሳፍራል። የኢትዮጵያ መንግስት ለሌላ አገር ‘ገንዘብ ረዳሁ’ ብሎ ከሚያወራ እዚህ ያሉትን ዜጓቹን አያስወጣም እንዴ ? 

እኛስ መቼም ምግብ ባይቀርብልም ከነበርንበት ሁኔታ አንጻር ምንም አይመስለንም። ትኩረት የሚሹት በማይናማር ከእገታ ያልወጡት እኛ ባለን መረጃ ብቻ እንኳ ከ400 በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያዊያን ነው። እነርሱ የሚወጡት ደግሞ እኛ ቦታውን ስንለቅላቸው ነው።

እኛ ማይናማር ቦርደር ላይ ነው ያለነው። ሞኤ የሚባል ወንዝ እንደተሻገን። በጣም ሐበሻዎች አሉ። ከአንድ ካምፓኒ ብቻ እስከ 500 የሚደርሱ ሐበሻዎች አሉ።

አብዛኛው ኢትዮጵያ ያለበት አንዱ ካምፓኒ ‘ወደ ሌላ ቦታ እንስዳችኋለሁ’ እያለን ነው። ሌላ ቦታ የሚወስደን ሁሉንም ነገሮች ቁጥጥሩ ለማድረግ ነው። አሁን ያለንበት ቦታ ላይ ደኀንነታችን የተጠበቀ ነው። 

ማይናማር ግን ብዙ ሰው እየተጎዳ፣ እየተሰቃዬ ያለበት ፎረይን ፓሊሶች የሌሉበት አካባቢ ነው። ያለንበትን ካምፓኒ አቋርጠን ለመውጣት 2,500 ዶላር ይከፈላል። ያለንበት ግቢ እስከ 25 ካምፓኒዎች አሉ። ወደ ሌላ ግቢ ላለመሄድ ነው ጥረት እያደረግን ያለነው።

ሐበሾችን እየጠበቅን ነው ገና ከእገታ ያልወጡ ስላሉ። አመት ድረስ የቆዩ አሉ። በራሳችን ፈቃድ ስለማያስወጡን። 

እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ ያልመጣንበት ዋነኛው ምክንያት ሙሉ ወጪ መሸፈን ስላማይችል ነው። 

ምክንያቱም ወደ ኢትዮጵያ መንግስት ደብዳቤ ልከው ከኢትዮጵያ መንግስት ምንም አይነት ምላሽ እንዳላገኙ ነው መረጃ የሰጡን። የታይላንድ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት ደብዳቤ ልኳል። ግን እስከ ሳምንት ምላሽ አልተሰጠም።

ካለንበት ካምፕ ወጥተን ወደ ታይላንድ/ሜኢሶት ኤርፓርት ነው መሄድ ያለብን። ከታይላንድ መንግስት ጋር በመነጋገር ወንዝ ያሻግሩናል። ፓስፓርት የሌለው አንድ ወር መቆየት እንደሚችል ነው የተነገረው። 

የተጎዱ ሀበሿች፣ ጀርባቸው ላይ ለምጥ ያለ፣ የታመሙ፣ የተደበደቡ በሙሉ ካምፕ ነው ያሉት። እኛን ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ነው ያልጠየቁን እንጂ ህንዶችን፣ ቻይናዎችን ‘አለንላችሁ’ የሚሉ አሉ። 

ምን እያደረጉ እንደሆነ የምናውቀው ነገር የለም። የምናውቀው ዘገባ እያደረጉና ዜግነታችንን ለይተው ብዙ ነገር እየጠየቁ እንደሆነ ነው። 

የኢትዮጵያ ዜጎች ብቻ ናቸው የቀሩት። ከኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ ስላላገኙ። ምላሽ ቢያገኙ ይወጡ ነበር የሚቆዩበት ምክንያት የለም። ለኛም ስጋት የሆነው እነርሱ ባለመሄዳቸው የተነሳ ምናልባት የታይላንድ መንግስት ላይቀበለን ይችላል ” ሲሉ ተናግረዋል። 

የኢትዮጵያዊያኑ ቤተሰቦችስ በሰጡን ቃል ምን አሉ ?

“ ከእገታው ያልወጡ ኢትዮጵያዋያን ስቃይ ላይ ናቸው። ከእገታ ከወጡት 261 ዜጎች 138 ኢትዮጵያዊያ ናቸው። ከማይናማር ተነስተው ታክ በሚባል ካምፕ ነው ያሉት፤ ከቦርደሩ 82፣ ለባንኮክ 377 ኪሎ ሜትር ርቀት።

ቦታው አሁን ለደኀንነታቸው አስተማማኝ እየሆነ አይደለም። ምክንያቱም ከወጡት 261 የ18 ሀገራት ዜጎች በስምንት ቀናት ሁሉም ወደ ሀገራቸው ሂደዋል። የቀሩት የኢትዮጵያ ዜጎች ብቻ ናቸው።

ከእገታው እንደወጡ ኢንተርቪው ተደገው ነበር በዛው አካባቢው አካላት፣ የደረሰባቸውን ስቃይ ተናግረው ነበር። ቃለመጠይቁን የሰሙ የታይላንድ ፓሊሶችም መልሰው ወስደዋቸዋል። መንግስት እንዲመጡ ስላላደረገ የወጡት ኢትዮጵያዊንም በፓሊስ ተመልሰው እየተወሰዱ ነው። እስካሁን ሰባት ልጆች ተወስደዋል። የተመለሰ የለም።

የሌሎቹ ሀገሪት ዜጎችም ኢንተርቪው ተደርገው የነበር፤ ነገር ግን ኤምባሲዎች ሂደው በቀናት ውስጥ ነው የወሰዷቸው። 138ቱ ኢትዮጵያዊን ከእገታው ቢወጡም ወደ ኢትዮጵያ ስላልወጡ አደጋ ላይ ናቸው።

በታይላንድ ካምፕ ላይ ያሉት 138፣ በሌላ ጉዳይ ምክንያት በታይላንድ ፓሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ፣ ገና ቦርደር ላይ እየጠበበቁ ያሉ 100 በአጠቃላይ 259 ኢትዮጵያዊያን ስም ዝርዝራቸው እንደተላከለት ውጪ ጉዳይ ነግሮናል።

በስም ዝርዝራቸው መሠረት መረጃዎችን እያደራጀ እንደሆነ ቢገልጽልንም እስካሁን ድረስ ግን ምንም አይነት ተጨባጭ የሆነ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተሰራ ነገር የለም።

የወጡት ኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ መንግስት የሚጠብቁት ምን እንደሆነ፥ የአገልግሎት ጊዜው ያለቀ ፓርፓርት ያላቸው ልጆች ስላሉ ማንንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ወደ ታይላንድ መንግስት እንዲልክላቸው፣ የበረራ ትኬቶች እንዲስተካክልላቸው ነው” ብለዋል።

የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ ፦

“ የታይላንድ መንግስት ‘ዜጎቻችሁን ውሰዱ’ ካለ በኋላ ብዙ ሀገራት ልጆቻቸውን አስወጥተዋል። የኢትዮጵያ ልጆች ግን እየተሰቃዩ ነው ያሉት።

የተወሰኑት አምልጠው ሲወጡ ተከትለው ለወጣት የምከሩ ኢትዮጵያዊያን ማይናማር በወታደሮች ካምፕ ታጉረዋል። ከእገታ የወጡት ወደ ሀገቸው ስላልመጡ ሌሎች ያልወጡት ታጋቾችም እየተሰቃዩ ነው።

አሁንም ወታደራዊ ካምፕ ያሉ ኢትዮጵያዊያኑ ብቻ ናቸው። ምግብም እየተሰጣቸው አይደለም። ልጆቻችን በረሃብ ሊያልቁብን ነው። ልጆቹ ያልወጡበት ምክንያት ያገራችን መንግስት ባለመቀበሉ ብቻ ነው” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለምን ከእገታ የማጡት ኢትዮጵያዊንን በአፋጣኝ ማምጣትና የታገቱትን ወገኖች ለማስለቀቅ ለምን እንዳልተቻለ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥያቄ ቢያቀርብም እስካሁን ምላሽ አላገኘም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔊 #የጤናባለሙያዎችድምጽ 🔴 “ የጸጥታ አካላት ሆስፒታል ድረስ በመምጣት ድብደባ ፈጽመዋል፣ ዘጠኝ ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላትን አስረዋል ” - የሆስፒታሉ ሠራተኞች ➡️ “ እነርሱ ጋ ብቻ አይደለም ያልተከፈለው፤ ከ2000 በላይ ሠራተኞች እንደ ዞን ያልተከፈላቸው አሉ ”  - የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ፣ የይርጋጨፌ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ባለሙያዎች “ በጸጥታ…
#Update

🔴 “ ወደ አራት ጤና ባለሙያዎች ገና አልተፈቱም። የጠየቁት መብታቸውን ስለሆነ ሊፈቱ ይገባል ” - ቤተሰቦች

➡️ “ ሰልፍ ላይ ስለተገኙ ብቻ ነው የተያዙት ” - ጤና ባለሙያ


የአራት ወራት አዲሱ ደወመዝ ክፍያ ስላልተፈጸመላቸው የሥራ ማቆም አድማ በመምታታቸው ከታሰሩት የይርጋጨፌ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች መካከል አራቱ እንዳልተፈቱ ቤተሰቦቻቸውና የጤና ባለሙያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

መጀመሪያ የታሰሩት ዘጠኝ እንደነበሩ ሠራተኞቹ ከቀናት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ እስራቱ ቀጥሎ በአጠቃላይ 12 ሰዎች ታስረው እንደነበርና አራቱ እንዳልተፈቱ ነግረውናል።

የታሳሪ ቤተሰቦችና ጤና ባለሙያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

አንድ ጤና ባለሙያ በሰጡን ቃል፤ “ የተፈቱና ሌሎቹም በሥራ ገበታ ላይ ናቸው። የነዚህ የአራቱ አለመፈታት ግን እስካሁን ምስጢር ሆኖብናል። ሰልፍ ላይ ስለተገኙ ብቻ ነው የታሰሩት ” ሲሉ ተናግረዋል።

የታሳሪ ቤተሰቦች በበኩላቸው “ አራት ጤና ባለሙያዎች ገና አልተፈቱም። የጠየቁት መብታቸውን ስለሆነ ሊፈቱ ይገባል ” ብለዋል።

“ ጥያቄው የሆስፒታሉ አካላት ሁሉ ነው። የፓለቲካ ጉዳይ የሌለበት የደመወዝ ጥያቄም ነው። ከደመወዝ ይከፈለን ውጪ ያነሱት ጥያቄ የለሞ ” ሲሉም ሞግተዋል።

አንዲት የታሳሪ ቤተሰብ በሰጡን ቃል፣ ባለቤታቸው ከታሰሩ ቀናት እንዳስቆጠሩ፣ እስካሁንም እንዳልተፈቱ፣ ያሉበትን ሁኔታም እንደማያውቁ ገልጸዋል።

ሌላኛው የታሳሪዋ የቅርብ ሰው የ10 ወር ጨቅላ ህፃን ያላት ጤና ባለሙያ እንደታሰረች ገልጸው፣ በዋስ እንደትለቀቅ እንኳ ቢሞከር ፈቃደኛ አካል አለመኖሩን ጠቁመዋል።

“ አጥቢ ከመሆኗ አንፃር ቀነ ገደብ ተጠይቆ ነበር። ፍርድ ቤት ዋስትና እንዲሰጣት ውሳኔ ቢያስተላልፍም እንዳትወጣ በፓሊስ ተከልክላለች ” ሲሉ ነው የወቀሱት።

የታሳሪ ቤተሰቦች፣ የታሰሩት የጤና ባለሙያዎች እንደሆኑ፣ ብዙ የህክምና ተገልጋዮች መጉላላታቸውም ከግምት ሊገባ እንደሚገባ አሳስበው፣ በፍጥነት እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

የታሰሩት ለምን እንዳልተፈቱ ምላሽ ለማግኘት የጸጥታ አካላትን ለማካተት የተደረገው መከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኞች ባለሆናቸው ለጊዜው አልተሳካም።

የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ከዚህ ቀደም  ጠይቀነው፣ በሌሎች ሆስፒታሎችም ጭምር ከ2000 በላይ ሠራተኞች ክፍያው እንዳልተፈጸመላቸው፣ የታሰሩትን ለማስፈታትም እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🔴 " ሙሉ ፓትሮል መኪና መጣብን፡፡ እኛ ሮጠን አመለጥን ሌሎች 5 ሰዎች ታስረዋል " - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች

➡️ " እየለፉ እስከሆነ ድረስ ቢጨመርላቸው ደስ ይለናል " - የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

⚫️ " የማውቀው ጉዳይ የለም " - የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን

ከማኀበራት ተውጣጥተው በሀዋሳ የኒቨርሲቲ በምገባና ሌሎች ስራዎች ለዓመታት ሰራን ያሉ ወደ 800 ሠራተኞች ደመወዝ እንዲጨመርና ቋሚ ቅጥረኛ እንዲሆኑ ጥያቄ በማቅረባቸው፣ ዩኒቨርሲቲው ከሥራ ሊያሰናብታቸው መሆኑን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አቤት ብለው ነበር።

ሠራተኞቹ ዛሬ በሰጡን ቃልስ ምን አሉ ?

“ ደመወዝን በተመለከተ ቅሬችንን ለመግለጥ ወደ ደቡብ ኤፍኤፍ እየሄድን በነበረበት የተወሰኑ ሰዎች ታስረዋል መብታቸውን ስለጠቁ ታስረዋል፡፡ አንዱ ታሳሪ ታሟል፡፡

ጠዋት ደቡብ ኤፍኤም ቀጥሮን ነበር፡፡ 2 ሰዓት ተኩል ወደ ጣቢያው ስንሄድ ሙሉ ፓትሮል መኪና መጣብን፡፡ እኛ ሮጠን አመለጥን ሌሎች 5 ሰዎች ታደስረዋል፡፡ ጠዋት ነው የታሰሩት አሁን ስንሄድ ቃላቸውን የሚቀበላቸው የለም። እኛንም እየፈለጉን ነው ካፓስ ውጪ ነን። 

ሰዎቹ የታሰሩት ሀዋሳ 01 ፖሊስ ጣቢያ ነው፡፡ ምንም አላጠፋንም፡፡ ‘ለምን ተሰባሰባችሁ’? ሲሉን የደመወዝ ጭማሪ አልደረሰንም፡፡ በ1,000 ብር ደመወዝ እየሰራን ኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻልንም፡፡ መንግስት እንዲመለከተን ለሚዲያ ቃላችንን ልንሰጥ ነው የመጣነው አልናቸው፡፡

ከዚያ በኋላ ‘እንዴት ስማችን ይጠፋል? ለምንድን ነው የምታስተላልፉት’? ብለው ነው ወንዶቹን አተኩረው ያሰሯቸው። የታሰሩት ሠራተኞች እንጨት ሲፈልጡ ለትርፍ አንጀት በሽታ ተጋልጠው ቀዶ ጥገና የተሰሩ ናቸው፡፡ አንዱ መኪና ላይ ሲወረውሩት ራሱን አያውቅም።

መንግስት ይየን፡፡ ፍትህ ይደረግልን፡፡ የኑሮ ውድነት እኛን አልነካም? እኛ ልጆች የሉንም? ለምንድን ነው መንግስት የማያየን? የኑሮ ወድነቱን አልቻልንም፡፡ ተንከራተን ነው የምንኖረው፡፡ ልጆቻችን እየተራቡ፣ እየተጠሙ ነው፡፡

24 ሰዓት ነው ግቢ ውስጥ የምንሰራው፡፡ ከግቢ ወጥተን ሌላ ሥራ ለመስራትም ጊዜ የለንም፡፡ ሁሉም በችግር ላይ ነው። በዛ ላይ ወጥ የተደፋባቸው፣ እጃቸውን ማሽን የቆረጣቸው አሉ። አካል ጉዳተኞቹንም ለማሳየት ነበር ወደ ሚዲያ የሄድነው፡፡ ግን መብታችን ተረግጧል፡፡ ዲሞክራሲም የለም፡፡

አካል ጉዳተኞች 50 በላይ ይሆናሉ፡፡ እናቶች መንቀሳቀስ ስለማይችሉ ቤት ውስጥ ነው ያሉት፡፡ የሚያሰሩት ሰዎችን 600 ብር ቀጥረው ነው፡፡ መስራት ስላማችሉ፡፡ ከታሰረው እንዱ ራሱ ወጥ ተደፍቶበት እግሩ ተቃጥሏል፡፡

እንጨት ከጫካ ተሸክመን አምጥተን ፈልጠን በዬኩሽናው እናደርስ ነበር። እንደዚህ ደክሞን ውለን የምንታጠብበት ሳሙና አልነበረንም። ችግር ከትክሻችን አልወርድ አለ። 

ለሌሎች ደመወዝ ሲጨመር የኛስ ድካም ለምን አይታይም? ልጆች እናስተምራለን፣ የቤት ኪራይ አለብን። 'ደመወዝ ተጨምሯል' ሲባልም የቤት ኪራይ ተጨምሮብን 'ቅድሚያ ካልከፈላችሁ ውጡ’ እየተባልን ነው፤ ተጨንቀናል ” ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች አማረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የሠራተኞችን ቅሬታ ይዞ ፤ ሰዎቹ የመብት ጥያቄ ስላነሱ ለምን ታሰሩ ? ይህን ማድረግ አግባብ ነው ? ሲል የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮን ጠይቋል።

አንድ የቢሮው አካል በሰጡት ምላሽ፣ የደመወዝ ጭማሬና ቋሚ ሰራተኛ መሆንን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው የራሱ መተዳደሪያ ደንብ እንዳለው፣ ጭማሬው ለቋሚ ሠራተኞች እንጅ ለጊዜያዊ እንደማይሆን ገልጸዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ለሰዎቹ ደመወዝ የመጨመርና ቋሚ ሠራተኛ ማድረግን የሚመለከተው ዩኒቨርሲቲው ሆኖ እያለ፣ ሠራተኞቹ የመብት ጥያቄ በማቅረባቸው መታሰታቸው አግባብ ነው ? ሲል ለእኝሁ አካል በድጋሚ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

እሳቸው በምላሻቸው፣ ከክልል ይታሰሩ እንዳልተባለ ገልጸው፣ " አንተ እንዳልከው እኛ ደመወዝ ይጨመርላቸው፤ አይጨመርላቸው የመተዳደሪያ ደንብ ስላላቸው እነርሱ ናቸው የሚያስተካክሉት " ብለዋል፡፡

" ቢጨምሩላቸው እኛም ደስ ይለናል፡፡ እየለፉ እስከሆነ ድረስ ቢጨመርላቸው ደስ ይለናል፡፡ ግን እነዚህ ሰዎች ታስረዋል ? ማነው ያሰራቸው ? የሚለውን ለመጠየቅ እየሞከርኩኝ ነው፡፡ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ናቸው፡፡ ሲወጡ እንዴት ታሰሩ ? የሚለውን አጣራለሁ " ብለዋል፡፡

በተጨማሪም፣ ሠራተኞችን ለምን እንደታሰሩ ማብራሪያ  የጠየቅናቸው የሲዳማ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ካሳ ጩቦ በሰጡን ቃል፣ " የማውቀው ነገር የለም " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
 
(የክልሉ ፓሊስና ጸጥታ ቢሮ ተጨማሪ አጥጋቢ ምላሽ  ከሰጡን የምናቀርብ ሲሆን፣ ጉዳዩንም እስከ ጥግ እንከታተለዋልን)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በአስር ቀናት ዉስጥ የ19 ሰዎች ሕይወት አልፏል " - የኑዌር ዞን ጤና መምሪያ በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን አኮቦ ወረዳ ከቀናት በፊት እንደተከሰተ በተነገረዉ የኮሌራ በሽታ በጥቂት ቀናት ብቻ 19 ሰዎች ሲሞቱ ከ280 በላይ ሰዎች ላይ በበሽታዉ መያዛቸውን የኑዌር ዞን ጤና መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታዉቋል። ከደቡብ ሱዳን እንደገባ በተገመተዉ ይህ የኮሌራ በሽታ የካቲት 3/2017 ዓ/ም በጋምቤላ…
#Update #HealthAlert

" የሟቾች ቀጥር ከ30 በልጧል " - ዞን ጤና መምሪያ

በጋምቤላ ክልል በኑዌር ዞን በተከሠተው የኮሌራ ወረርሽኝ፣ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ30 በላይ እንደደረሰ የዞኑ ጤና መምሪያ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል አሳውቋል።

በዞኑ ከ1 ሺሕ በላይ የሚደርሱ ሰዎች በበሽታው መታመማቸው ተመላክቷል።

የኑዌር ዞን ጤና መምሪያ ሓላፊ አቶ ጋትቤል ግርማ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤ ወረርሽኙ ቀድሞ የተከሠተባቸው ዋንታዎ እና አኮቦ ወረዳዎች፣ አሁንም ስርጭቱ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሰው፣ መድኃኒትም በበቂ ሁኔታ አልቀረበም ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴 " ሙሉ ፓትሮል መኪና መጣብን፡፡ እኛ ሮጠን አመለጥን ሌሎች 5 ሰዎች ታስረዋል " - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች ➡️ " እየለፉ እስከሆነ ድረስ ቢጨመርላቸው ደስ ይለናል " - የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ⚫️ " የማውቀው ጉዳይ የለም " - የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ከማኀበራት ተውጣጥተው በሀዋሳ የኒቨርሲቲ በምገባና ሌሎች ስራዎች ለዓመታት ሰራን ያሉ ወደ 800 ሠራተኞች ደመወዝ እንዲጨመርና…
#Update

🔴 “ የታሰሩት ተፈትተዋል፡፡ የመብት ጥያቄ በማቅረብችን ነው ያሰሩን፡፡ 10 ሠራተኞች ሥራ ተከልክለናል ” - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች

➡️ “ ቅሬታ እንዳለባቸው አውቃለሁ፡፡ ያንን ማሰማት መብታቸው ነው፡፡ የሰሩት ወንጀል የለም ” - የከተማው ጸጥታ መምሪያ

በዛ ቢባል 1,100 ብር ደመወዝተኛ ለ20 ዓመታት ምገባና ሌሎች ሥራዎችን የሰሩ 800 የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው ዩኒቨርሲቲውን ሲጠይቁ ‘እንዲያውም አሰናብታችኋላሁ’ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት ተናግረው ነበር።

ሠራተኞቹ ከዚያ በኋላ በገለጹት መሰረት፣ ቅሬታቸውን ለሚዲያ ለማቅረብ በሄዱበት ወቅት ደግሞ የተወሰኑት ሠራተኞች በፖሊስ እንደታሰሩ ነበር የነገሩን።

የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ ጉዳዩን እንደሚያጣራና ሠራተኞቹ ደመወዝ ቢጨመርላቸውም እንደማይከፋው፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዩን እንደማያውቅ ስለጉዳዩ ከቲክቫህ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተው ነበር።

ታሰሩ የተባሉት ሠራተኞች ተፈቱ ?

የታሰሩት ሠራተኞች ትላንት ጠዋት በዋስ እንደተፈቱ፣ ገና ወደ ሥራ እንዳልገቡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ታስረው ከነበሩና ከቅሬታ አቅራቢ ሠራተኞቹ ገለጻ ለማወቅ ችሏል፡፡

ሠራተኞቹ በሰጡን ቃል፣ “የታሰሩት ተፈትተዋል፡፡ የመብት ጥያቄ በማቅረብችን ነው ያሰሩን፡፡ ከ10 በላይ ሠራተኞች ሥራ ተከልክለናል” ነው ያሉት።

የመብት ጥያቄ ለማቅረብ ከመሞከር ውጪ ጥፋት እንዳልፈጸሙ፣ ሆኖም በዩኒቨርሲቲ በሚገኘው 01 ቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከቆዩ በኋላ በመታወቂያ ዋስ እንደተለቀቁ ሠራተኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል፣ ቅሬታ ካቀረቡት የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች መካከል 10 የሚሆኑት “ወደ ዩኒቨርሲቲው ለሥራ አትግቡ” ተብለው እንደተከለኩ ገልጸው፣ መብታቸው እንዲከበርላቸው በድጋሚ ጠይቀዋል፡፡

ታሳሪዎቹን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጥ ሰሞኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲጠይቀው የነበረው የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ፣ ጉዳዩን አጣርቶ ምላሽ ለመስጠት ገልጾ ነበር፡፡

መምሪያው ትላንት በሰጠን ምላሽ፣ “ምንም የታሰረ አካል የለም፡፡ የተፈጠረ ነገርም የለምኮ ለምንድን ነው የሚያታሰሩት?” ብሏል።

“ ቅሬታ እንዳለባቸው አውቃለሁ፡፡ ያንን ማሰማት መብታቸው ነው፡፡ የሰሩት ወንጀል የለም፡፡ የሚያሳስራቸው ጉዳይም የለም ” ሲል ተናግሯል።

የተፈጠረ ነገርማ አለ፤ ሠራተኞች እንደታሰሩ ተናግረዋል፣ ለመሆኑ ከከተማው 01 ቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ ሄዳችሁ አጣርታችሁ ነበር ? ስንል ላቀረብለት ጥያቄ ደግሞ፣ “ ቼክ አድረገናል፡፡ ወንጀል የለባቸውም፡፡ ዩኒቨርሲቲውም ለኛ ያመለከተን ጉዳይ የለም ” ብሏል።

ሠራተኞቹ በበኩላቸው፣ “ እነርሱማ እውነት ነው አይሉም ” ሲሉ ወቅሰዋል።

(ክትትሉ ይቀጥላል)


#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከጀርባዋ " ኤሌክትሮኒክ ቁስ ተሸክማ ስትበር ተያዘች " የተባለችው ወፍ ምንድነች ? 🔴 “ ምርመራ እየተደረገ ነው ፤ ገና አላለቀም ” - የቤንሻንጉል ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ➡️ “ ምርመራ እየተደረገ ነው። ሲያልቅ እናሳውቃለን ” - የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን እና ሰላምና ጸጥታ ቢሮ  በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ ጉሬ ቀበሌ “ በጀርባዋ ላይ ኤሌክቶርኒክስ ቁስ ተገጥሞባታል ” የተባለችና…
#Update

“በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አዕዋፋት ይመጣሉ። ባለፍኩበት የስራ ዘመን እንደዚህ አይነቱን አሰራር ለስለላ ተጠቅመውበት አያውቁም” - በዘርፉ 40 ዓመታት የሰሩ የአዕዋፍ ሳይንቲስት

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ በጀርባዋ የኤሌክትሮኒክ ቁስ ተሸክማ ስትበር ተገኘች የተባለችው ወፍ የብዙዎችን ቀልብ ስባለች።

ብዙዎች “ለስለላ የተላከች ወፍ ነች” የሚል ስጋታቸውን በማኀበራዊ ሚዲያ ሲያንጸባርቁ የተስተዋሉ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም የክልሉን አካላት ስለጉዳዩ ጠይቆ ገና በምርመራ መሆናቸውን ከመግለጽ ውጪ ያሉት የለም።

የወፏ ጉዳይ እውነትም ስለላ ሊሆን ይችላል ይሆን ? እስከዛሬ በነበሩ መሰል ክስተቶች በወፍ አማካኝነት ስለላ ተደርጎ ያውቃል ? ስንል የአዕዋፋት ሳይንቲስት አቶ ይልማ ደለለኝን ማብራሪያ ጠይቋል። 

በዘርፉ የ40 ዓመት ልምድ ያላቸው ባለሙያ ምን መለሱ ?

አሁን በግላቸው የአካባቢ ጥበቃ ላይ፣ ከዚህ ቀደም በዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የሰሩት አቶ ይልማ እንዳሉት፣ ሰምንኛው የወፏ ጉዳይ በየዓመቱ የሚስተዋልና ሥጋት ሊደቅን የማይችል የተለመደ ሁነት ነው።

ባለሙያው፣ ከጀርባቸው ሶላር ጂፒኤስ፣ ከእግራቸው ቀለበት የተገጠመላቸው ወፎች የሆነ ወቅት ቅዝቃዜን በመሸሽ ከአውሮፓ ሀገራት 7000 ድረስ ኪሎ ሜትር አቋርጠው በየዓመቱ የሚመጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ወፎች ላይ ቀለበትና ሶላር ጂፒኤስ ገጥሞ መላክ ታዲያ ለምን አስፈለገ? የሚለውን ጥያቄ ሲያብራሩም፣ ከጀርባቸው ያለው ሶላር ጂፒኤስ ወፎች የት እንዳሉ፣ በምን ያህል ከፍታ እየበረሩ እንደሆነ፣ ወደየትኛው አገር እንደሄዱ አውሮፓያውያኑ የሚከታተሉበት እንደሆነ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ባለዎት ልምድ መሰረትና እንደብዙኅኑ ስጋት ቀለበትና ሶላር ጂፒኤስ በተገጠመላቸው ወፎች ስለላ ተደርጎ አያውቅም? የሚል ጥያቄ ለባለሙያው አቅርቧል።

አቶ ይልማ ምን መለሱ ?

ሰዎች ይህንን ከፖለቲካ ጋር ያያይዙታል። ነገር ግን ፒዩርሊ የሳይንስ ስራ ነው። እኔም ብዙ ጊዜ ወፎች ላይ ቀለበትና ጂፒኤስ ትራከር አስሪያለሁ። 

ኢትዮጵያ እንኳን በሚመጡበት ወቅት ያን ቀለበትና ጂፒኤስ አስረን የት ድረስ እንደሚሄዱ የምንከታትልበት ሲስተም አለ። ሳይንቲስቶች ከእውቀት ጉጉት የሚያደርጉት ነው እንጂ በፍፁም የስለላ ተግባር እንዳልሆነ ነው የምረዳው። 

ያው ኢትዮጵያ ውስጥ ያን ያክል ጥልቅ እውቀት ስለሌለና አሁን ያለንበት የሰላም ሁኔታ ጋር ተደማምሮ ሰዎች እንደዚህ እንዲያስቡ አድርጓቸዋል። እውነት ለመናገር ለስለላ ቢሆን ኖሮ ወፍ ሳይሆን ድሮን ላይ በተገጠመ ነበር። ምክንያቱም የተፈጥሮ ወፍን እንቅስቃሴ መቆጣጠር አይቻልም።

በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አዕዋፋት ይመጣሉ። እነርሱ (አውሮፓውያኑ) ከኛ የተሻለ ፍለጎቱ፣ እውቀቱ፣ አቆርቦቱ፣ የገንዘብ አቅሙም ስላላቸው በአዕዋፍ እንደዚህ ያደርጋሉ እንደዚህ ዓይነቱ ስራ ደግሞ ከገንዘብ በተጨማሪ ብዙ ጊዜና ክትትል ይፈልጋል።

ከዚህ ቀደምም በደርግ ዘመን የኢትዮ - ኤርትራና የካራማራ ጦርነት በነበረበት ወቅት ደርግም ደግሞ ኮሚኒስት ከመሆኑ የተነሳ ከአሜሪካና ከአውሮፖ ሀገራት ‘የተላከ ሰላይ ነው’ በሚል ብዙ ጭንቅላት የሚያዞር ችግር ነበር፤ እኛም ይህን ለማስረዳት ሞክረናል። 

አሁንም ሰዎች ይህን ቢሉ እኔ አልፈርድም ምክንያቱም እኛ ባለሙያዎችም ብንሆን እንደዚህ አይነቱን ነገር ቀድመን ለማህበረሰቡ ማሳወቅ ይጠበቅብናል።

ባለፍኩበት የስራ ዘመን እንደዚህ አይነቱን አሰራር ለስለላ ብዙም ተጠቅመውበት አያውቁም። በእርግጥ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የወፎች እግር መልዕክት ይደረግላቸውና መልዕክት የሚላላኩትን ሰዎች ቤት እርግቧ ስለምታውቅ ከአንዱ ወደ ልላኛው ስታስተላልፋል።

በዛ ጊዜ የተጠቀለለ ወረቀት በትንሽየ እቃ አድርገው በወፍ ጀርባ ላይ ያደርጉትና ለሚፈለገው አካል ይደርስ ነበር። ምክንያቱም ወፍ ላይ መልዕክት ይኖራል ተብሎ ስለማታይ ጠላት ባለበት ጎራም አልፈው ወገን ጋር ሊያደርሱ ይችላሉ።

በወፎች ስለሚደረገው ስለላ ይህን ብቻ ነው የማውቀው ይኸውም ያኔ እንደአሁኑ ቴሌግራም፣ ፌስቡክን የመሳሰሉ የመልዕክት መለዋወጫዎች ስላልነበሩ ነው። አሁን ወፎች ለስላላ ጥቅም አይውሉም፤ አንዲያውም ጂፒኤስ የሚደረግባቸው ወፎች ረጅም ርቀት በመጓዝ በመጓዛቸው፣ በርሀብና በጥም ምክንያት 75% ይሞታሉ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🔴 " ዛሬ ጠዋት 32 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል " - የወላጆች ኮሚቴ

➡️ " የታይላንድ መንግስት ያልተቀበላቸው ወደ 300 ልጆች ማይናማር ካምፕ ውስጥ አሉ። 32 ልጆች መጥተናል " - ተመላሽ ኢትዮጵያዊ

ከማይናማሩ እገታ ወጥተው ታይላንድ ካምፕ ከነበሩት ኢትዮጵያውያን መካከል 32 የሚሆኑት ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን የወላጆች ኮሚቴና ተመላሾቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

የወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " ዛሬ ጠዋት 32 ኢትዮጵያውን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል " ብሏል።

ልጆቹን ለሀገራቸው እንዲበቁ ላደረጓቸው ምስጋና አቅርቦ፣ ከእገታ ወጥተው በታይላንድ ያሉ፣ በማይናማር ገና ከእገታ ያልወጡና ወጥተው ወደ ታይላንድ ያልተሻገሩ፣ ጭራሹንም ያሉበት የማይታወቅ በርካታ ኢትዮጵያውያንን መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቋል።

ከተመላሾቹ መካከል አንዱ፣ 32 ልጆች መምጣታቸውን አረጋግጦ፣ " የታይላንድ መንግስት ያልተቀበላቸው ወደ 300 ልጆች ማይናማር ካምፕ ውስጥ አሉ። 32 ልጆች መጥተናል " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

የውጩ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ 32 ልጆች እንደመጡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት አረጋግጧል። 

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፣ ከማይናማሩ እገታ ወጥተው ወደ ታይላንድ ከተሻገሩ 133 ኢትዮጵያ መካከል 32ቱ ዛሬ ወደ አገራቸው ገልጾ፣ " 43  ኢትዮጵያውያንን ደግሞ ዛሬ ምሽት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል " ብሏል።

" ቀሪዎቹ በታይላንድ ማቆያ የሚገኙ 58 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ኤምባሲው ጥረት እያደረገ ይገኛል " ሲልም አክሏል።

ጃፓን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ወደ ታይላንድ በማሻገር ወደ  አገራቸው ለመመለስ  ጥረት እያደረገ ይገኛል ሲልም አክሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE #NGAT ትምህርት ሚኒስቴር የሶስተኛውን ዙር የ2017 ዓ.ም የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ይፋ አደረገ። ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ በ https://ngat.ethernet.edu.et/registration የመመዝገቢያ ሊንክ በኩል…
#Update #MoE

" እስከምሽት ድረስ እየሞከሩ መቆየት ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

ሀገር አቀፍ የ2017 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የአመልካቾች ምዝገባ ከ የካቲት 27/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ እንደሚከናወን የትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ዛሬ በሚያበቃው የአመልካቾች የምዝገባ ሂደት ለመመዝገብ የሞከሩ ተፈታኞች የመመዝገቢያው ማስፈንጠሪያ ወይም ሊንክ እየሰራ አይደለም የሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

ከምዝገባ ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሚል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስቀመጣቸው ስልኮች ቢኖሩም እየሰሩ አለመሆኑንም ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን ዶ/ር ኤባ ሚጀናን ማብራሪያ ጠይቋል።

በምላሻቸውም " የኔትወርክ ችግር ይሆናል እንጂ ሲስተሙ ይሰራል ደጋግማቹ ሞክሩ " ብለዋል።

አክለውም " ሁሉም ሳይሆን የተወሰኑ ሰዎች ናቸው ለመመዝገብ እክል የገጠማቸው በርካታ ሰዎች አሁንም እየተመዘገቡ ነው " ያሉ ሲሆን እስካሁን ባለው 8 ሺ የሚጠጋ ሰው መመዝገቡን ጠቁመዋል።

" ፕሮሲጀሩን መከተል ግድ ይላል ከዘለሉ ላይሰራ ይችላል ነገር ግን ሁል ጊዜ ብዙ ሰው በመጨረሻ ነው የሚመዘገበው ፣መጨናነቅ ይኖራል እንዳይዘጋ በሚል በርካታ ሰዎች በአንድ ላይ ስለሚሞክሩ ጫና ይኖራል በዚህ ምክንያት ካልሆነ በቀር ምንም ችግር የለበትም " ነው ያሉት።

ሊራዘም የሚችልበት አጋጣሚ ይኖራል ወይ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄም " መራዘም ሳይሆን እስከምሽት ድረስ እየሞከሩ መቆየት ይችላሉ ኔትወርክ ያለበት አካባቢ በመሆን ደጋግመው ይሞክሩ " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተፈታኞች የመፈተኛ 'User Name' እና 'Password' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ መሆኑን እና የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም እንደሚጠበቅባቸው ማስታወቁ ይታወሳል።

ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን በቀጣይ እንደሚገልጽ አሳውቋል፡፡

መመዝገቢያ ፦
https://ngat.ethernet.edu.et/registration

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር " ሲል ውድቅ አደረገው። 

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን " አምባገነን ፕሬዜዳንት ነበር " ሲል አጣጥሏቸዋል።

ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ላይ የወሰዱት ጊዚያዊ የእግድ እርምጃ አስመልክቶ ሌሊት መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም ፕሬዜዳንቱ የወሰዱት እርምጃ " በሌለ ስልጣናቸው የወሰዱት የማይተገበር " ሲል በፅኑ ተቃውሞታል።

" እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር " ሲል ውድቅ ያደረገው መግለጫው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳን " ከስልጣቸው የኋላፊነት ቦታ ማንሳቱን " አስታውሰዋል። 

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን " አምባገነን ፕሬዜዳንት ነበር " ሲልም አጣጥሏቸዋል።

" የእግድ እርምጃውን የተደራጀ ሰራዊት ለማፍረስ ሲደረገው የቆየው ተንኮል አካል ነው " ያለ ሲሆን " እርምጃው አደገኛ ውጤት የሚያስከትል ነው " ሲል አስጠንቅቋል። 

" መሰረተ ቢስ " ሲል የገለፀው የሦስቱ ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ጊዚያዊ እግድ ፤ የሰራዊት አባላትና ህዝቡ እንዳይቀበሉት የሚል ጥሪም አስተላልፏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #MoE " እስከምሽት ድረስ እየሞከሩ መቆየት ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የ2017 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የአመልካቾች ምዝገባ ከ የካቲት 27/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ እንደሚከናወን የትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ዛሬ በሚያበቃው የአመልካቾች የምዝገባ ሂደት ለመመዝገብ…
#Update #NGAT

የብሄራዊ ድህረ-ምረቃ (NGAT) መግቢያ ፈተና መጋቢት 5 እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም የሶስተኛ ዙር የNGAT አመልካቾች ምዘገባ መጠናቀቁን ገልጿን።

ፈተናው የሚሰጠው ዓርብ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ መሆኑንም አሳውቋል።

ተፈታኞች  በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በሚመደቡበት የፈተና ማዕከላት እንዲገኙ ብሏል።

➡️ ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከል በሚሄዱበት ወቅት ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

➡️ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከመጀመሩ 3 ደቂቃ በፊት በፈተና ማዕከል መገኘት ይጠበቅበታል፡፡

➡️ የሞባይል ስልክ ይዞ በፈተና ማዕከል መገኘት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

➡️ የፈተና ማዕከላት ምደባ በምዝገባ ፕላትፎርም የሚገለጽ ይሆናል፡፡

#MoE

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር " ሲል ውድቅ አደረገው።  ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን " አምባገነን ፕሬዜዳንት ነበር " ሲል አጣጥሏቸዋል። ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ላይ የወሰዱት ጊዚያዊ የእግድ እርምጃ አስመልክቶ ሌሊት መግለጫ አውጥቷል። በዚህም ፕሬዜዳንቱ…
#Update

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ትእዛዝ " አልቀበልም አልፈፅምም " አለ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ፤ " በቢሮው ስም የቀረበው መግለጫ የአንድ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አካል ሳይሆን የአንዱ ቡድን ወታደራዊ ክንፍ መሆኑ በግልፅ የሚያሳብቅና የተፈጠረውን ችግር የሚያባብስ ነው " ብሎታል።

ትናንት መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች የጣሉት ጊዚያዊ እግድ ተከትሎ  ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት  " እገዳው መሰረተ ቢስ እና የማይተገበር " በማለት ውድቅ ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም።

ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጊዚያዊ እግድ ሙሉ በሙሉ በመፃረር ባወጣው መግለጫ ፤ በግልባጭ የተፃፈለትን ትእዘዛዝ እንደማይቀበል በመግለፅ " የህግ ማስከበር እርምጃው  " ይቀጥላል ብሏል።

የሰላምና ፀጥታ ቢሮ መግለጫ ተከትሎ ከመቐለ በ115 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የዓዲግራት ከተማ በሰራዊት የታገዘ መፈንቅለ ስልጣን መካሄዱን ለማወቅ ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ጠዋት ወደ ምስራቃዊ ዞን የሰላምና የፀጥታ ሃላፊ ደውሎ " ከቀበሌ የተወጣጡ ጥቂት ደጋፊዎች በሰራዊት በመታገዘ ጊዚያዊ  አስተዳደሩ የሾማቸው ከንቲባ ሲገለገሉት የነበረው ፅሕፈት ቤት በመስበር በደብረፅዮኑ ህወሓት ለተመረጡት ከንቲባ አስረክበዋል " ብለውታል።

በትግራይ ክልል ያለው የፓለቲካና የፀጥታ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢና ተለዋዋጭ ደረጃ ላይ ይገኛል  ያሉትን ሁኔታዎች እየተከታተልን እናቀርባለን።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " እነዚህ ሰዎች አብደት ላይ መሆናቸውን ሊነገራቸው ይገባል " - አቶ ጌታቸው ረዳ 🚨 " እኔ ልለው የምችለው ማንም ሊገምተው ከሚችለው በላይ አስከፊ ነው !! " የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር። በዚህም ቃለ ምልልስ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ምን አሉ ? ➡️ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ጣልቃ መግባትን…
#Update

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ  ማህበረሰብ በትግራይ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዲገባ ያቀረበውን ጥሪ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ተቃወመ።

የተጀመረው " ህግ የማስከበር እርምጃ " ያለው ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በትግራይ ጉዳይ እገዛ እንዲያደርጉ ያቀረበው ጥሪ " ይፋዊ ክህደትና የፕሪቶሪያ ስምምነት የሚያፈርስ " ሲል ውድቅ አድርጎታል።

" ህወሓት ፤ ህዝብና ሰራዊት ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሰጡትን ተልእኮዎች ለመፈፅም የሚያስችል የአመራር ማስተካከያ ይደረግ እንጂ ይፍረስ አላልኩም ብሏል " ሲልም ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ማህበረሰብ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በመተግበር የትግራይ ዘላቂ ሰላምንና መልሶ ግንባታ እውን እንዲሆን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧክ።

" መላው ህዝብ በትግራይ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት እንዲከበር ፣ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥና ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን ግዴታው ይወጣ " ሲል ህወሓት አሳስበዋል።

በተያያዘ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ሲያወጣቸው የነበሩ መግለጫዎች ወደ ህዝቡ ሲያሰራጩ የነበሩ የትግራይ ቴሌቪዥን እና ድምፂ ወያነ " የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በትግራይ ጉዳይ ጣልቃ እንዲገባ " የሚጠይቀውን መግለጫ ሳያስተናግዱት ቀርተዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ምንጮች ፤ ለ104.4 የመቐለ ኤፍኤምና ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን አዲስ ስራ አስኪያጆች መመደባቸው ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ከ100 ቀናት በላይ ዝግ የነበረው የመቐለ ከተማ የከንቲባ ፅሕፈት ቤት ተከፍቶ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት የመደባቸው ከንቲባ ገብተውበታል። የምስራቃዊ ዞን እና የዓዲግራት ከተማ ከተማ አስተዳደሮችም እንዲሁ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመሩት ህወሓት ቁጥጥር ስር ውለዋል። በደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዓዲጉዶም ፣ የሳምረ ፣ እንዲሁም የሃገረ ሰላም ከተሞች የጊዚያዊ…
#Update

የ104.4 የመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት በተመደቡ የመቐለ ከተማ አመራሮች አባላት ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

አመራሮቹ በሰራዊት ታጅበው ሬድዮ ጣቢያውን እንደተቆጣጠሩት ተነግሯል።

ምናልባትም በቀጣይ ደግሞ የድምፂ ወያነ እና ትግራይ ቴሌቪዥን ሚድያዎችን ሊያዙ እንደሚችሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከታማኝ ምንጮች ለመስማት ችሏል።

መገናኛ ብዙሃኑ ዛሬ ከአዲስ አበባ የተሰጠውን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን መግለጫ እስካሁን አላስተላለፉም።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በአደጋዉ እስካሁን የ14ሰዎች ሕይወት አልፏል" - የወላይታ ዞን ፖሊስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ ባዴሳ ከተማ አከባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን ባለው የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ንጋቱ ጌታቸዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። አደጋዉ ዛሬ 11 :30 አከባቢ እንደደረሰ ገልጸዋል። ከአርባ ምንጭ ወደ ሻሸመኔ ይጓዝ የነበረ ሰሌዳ…
#Update

ዛሬ ወላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ ባዴሳ ከተማ አከባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን ባለው የ15 ወገኖቻችን ህይወት አልፏል።

የዞኑ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ተጨማሪ መረጃ ፤ አደጋዉ የደረሰባቸው ወደ አርባ ምንጭ ዚጊቲ ደብረ ሠላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ጉዞ አድርገው ሲመለሱ የነበሩ ምዕመናን ላይ ነው።

መኪናው ፍሬን በመበጠሱ ምክንያት በወረዳው በዴሳ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ደደሳ ወንዝ ተገልብጦ በመግባቱ ነው አደጋው የደረሰው።

መኪናው 46 የሻሸመኔ ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ወጣቶች የያዘ ነበር።


#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔴 " ዛሬ ጠዋት 32 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል " - የወላጆች ኮሚቴ ➡️ " የታይላንድ መንግስት ያልተቀበላቸው ወደ 300 ልጆች ማይናማር ካምፕ ውስጥ አሉ። 32 ልጆች መጥተናል " - ተመላሽ ኢትዮጵያዊ ከማይናማሩ እገታ ወጥተው ታይላንድ ካምፕ ከነበሩት ኢትዮጵያውያን መካከል 32 የሚሆኑት ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን የወላጆች ኮሚቴና ተመላሾቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።…
#Update

🔴 “ 23 ኢትዮጵያውያን ዛሬ መጥተዋል። ጠዋት 12 ሰዓት 30 ነው ቦሌ ኤርፓርት የደረሱት ” - ቤተሰብ

➡️ “ ቦታው ለሰው ልጅ የሚሆን አይደለም። በጣም አስከፊ ቦታ ነው። የምንወጣ አልመሰለንም ነበር ” - ተመላሽ
 

ከማይናማሩ እገታ ከወጡ በኋላ በታይላድ ካምፕ ከነበሩ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 23ቱ ዛሬ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ቤተሰብና ተመላሾቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ቤተሰብ፣ “23 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ዛሬ መጥተዋል። ጠዋት 12 ሰዓት 30 ነው ቦሌ ኤርፓርት የደረሱት” ብለው፣ ደስታቸውን ገልጸዋል።

ዛሬ ከመጡት መካከል 3 ሴቶች 20 የሚሆኑት ወንዶች እንደሆኑ፤ ነገ ከ26 እስከ 30 ታይላንድ ያሉ ኢትዮጵያውያን ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያውያኑ በምን መልኩ እንደተመለሱ የጠየቅነው ተመላሽም፣ “የበረራ ትኬታቸው አንድ አመት ያላለፈ ልጆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ተነጋግረው ነው የመጡት። እኛ ግን ‘መንግስት ለእናንተ በጀት የለኝም’ ብሎን በመጨረሻም ኤንጂኦዎች ከፍለውልን ነው የመጣነው” ብሏል።

የቀሩት ወገኖች በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? ምንስ መደረግ አለበት? ለሚለው ጥያቄ በምላሹ፣ “ማይናማር ካምፕ በአርሚው ስር ያሉት እንዲመለሱ ፕሮሰስ እየተደረገላቸው ነው፤ ግን ከኋላቸው የቀሩ አሉ” ሲል ተናግሯል።

“በኔ እውቅና እንኳ ወደ 20 ልጆች በየቀኑ የሚገረፉ አሉ። መንግስት እነርሱ ላይ ቢሰራና ቢያወጣቸው ጥሩ ነው። ጨለማ ላይ ነው ያሉት። የእነርሱ ህይወት በጣም አስቸጋሪ ነው” ሲልም አሳስቧል። 

ሌላኛው ተመላሽ በሰጠን ቃል፣ “ቦታው ለሰው ልጅ የሚሆን አይደለም። በጣም አስከፊ ቦታ ነው። በጣም አረመኔዎች ናቸው። ጥፍር ይነቅላሉ፤ ይገርፋሉ፤ አንድም ሁለትም አመት ያለ ደመወዝ ያሰራሉ። ብቻ ቦታው ለሰው ልጅ የሚሆን አይደለም። እግዚአብሔር ረድቶን ወጣን፤ የምንወጣ አልመሰለንም ነበር” ብሏል።

ሰሞኑን በመጀመሪያ 32፣ ቀጥለው 45 ኢትዮጵያዎያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ከታይላንድና ማይናማር ወደ ሀገራቸው ያልተመለሱ ወገኖች አሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ዛሬ ምሽት 3:55 ገደማ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ ተከስቷል። በአዲስ አበባ ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ጠንከር ያለ ንዝረትም ተሰምቷል። @tikvahethiopia
#Update

🚨የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 5.1 ተለክቷል !!

ባለፉት ሳምንታት ትንሽ ጋብ ብሎ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ጠንክሮ ተሰምቷል።

የአዋሽ አካባቢ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ በርካታ አከባቢዎች እጅግ የጠነከረ ንዝረትም ለሰከንዶች ነበር።

" እኛ የተሰማን ከወትሮው የተለየ ነበር " ያለው አንድ የቤተሰባችን አባል " ያለሁበት ህንጻ ላይ ከፍተኛ መነቃነቅ ተሰምቶናል ፤ እጅግ ያስፈራም ያስደግጥም ነበር " ሲል ገልጿል።

በርካቶችም በተመሳሳይ ህንጻ ላይ የነበረው ስሜት ከፍተኛ እንደነበር ጠቁመዋል።

ከአዲስ አበባ ውጭም በርካታ ከተሞች ላይ ንዝረቱ በደምብ ተሰምቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ጠቁሟል።

በሬክተር ስኬልም 5.1 መለካቱን አመላክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ “ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መጥተው ከድልድዩ ቆመው አይተው ሄዱ ተመልሰው ” - የቦታው ነዋሪ “ ምናልባት በኛ የማይሰራ ከሆነ ብዬ እንደዛም ገምቼ ነው፡፡ ይነግሩኝ ነበር ከሄዱ አሳውቃለሁ ” - ኮሚሽኑ  አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11፣ ቀጠና 2፣ “ወይናምባ ማርያም” የተሰኘ አካባቢ ነዋሪዎች፣ የአካባቢው ወንዝ በአፈር በመዘጋቱ ትላንት የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ…
#Update

“ እስካቫተር አግኝተን አፈሩን እያዛቅን ነው። ለ105 ሰዎች ከ600 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት የቁሳቀስ ድጋፍ አድርገናል ” - አቶ ንጋቱ ማሞ

“ መጥተው አፈሩን እያነሱ ነው። ድጋፍም እየሰጡን ነው ” - ነዋሪዎቹ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11፣ ቀጠና 2፣ የ“ወይናምባ ማርያም” ነዋሪዎች ከቀናት በፊት በጣለው ዝናብ የአካባቢው ትልቅ ወንዝ በአፈር በመዘጋቱ ሙሉ ንብረት እንደወደመባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም በማግስቱ፣ ጉዳዩን እንደሰማ ለእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ጥቆማ አድርሶ ነበር።

በዚህም አቶ ንጋቱ፣ ለሚመለከው የኮሚሽኑ ክፍል መልዕክት እንዳስተላለፉ፣ መልዕክቱ የደረሳቸው አካላት በቦታው መሄድና አለመሄዳቸውን እንደሚገልጹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃል ገብተው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቆይታ በኋላ፣ የእሳት አደጋ ሠራተኞች መጡ? ሲል ነዋሪዎቹን ጠይቆ የነበረ ሲሆን፣ “ አይተው ተመልሰው ሄዱ” የሚል ምላሽ ነበር የሰጡት።

ይህን ተከትሎም ኮሚሽኑ ምን ምላሽ እንዳለው ቲክቫህ በድጋሚ ለመጠየቅ ቢሞክርም በወቅቱ ምላሽ አላገኘም ነበር።

ዛሬስ ጉዳዩ ከምን ደረሰ?

የእሳትና ሥራ አመራር ኮሚሽኑ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ “ እስካቫተር አግኝተን አፈሩን እያዛቅን ነው። ንብረት ለተጎዳባቸው ድጋፍም ተደርጓል ” ሲሉ ነግረውናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የእሳት አደጋ ሠራተኞች መጥዋል? ሲል ነዋሪዎቹን ዛሬም የጠየቀ ሲሆን፣ “ መጥተው አፈሩን እያነሱ ነው። ድጋፍም እየሰጡን ነው። በቀጣይነት ግን አፈሩ ሙሉ ለሙሉ መነሳት አለበት ” ብለዋል።

ኮሚሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

“ ኮሚሽኑ ከተሰጡት ተግባሮች መካከል በአደጋ ምላሽ ዘርፋችን እሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች በአጋጠሙ ጊዜና ጥሪዉ እንደደረሰ በቦታው በፍጥነት በመድረስ በሰውና በንብረት ላይ ሊደርስ የሚችልን አደጋ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ነው።

በሌላ በኩልም በደረሱ አደጋዎች ምክንያት ከቤት ንብረታቸዉ ለተፈናቀሉ ተጎጂዎች አልባሳት ፣ የምግብ ማብሰያና የንጽህና መጠበያ ቁሳቁሶችን በጊዜያዊነት ይደግፋል።

በዚህ መሰረት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ቀጠና 2፣ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ/ም በጣለው ዝናብ የጎርፍ አደጋ ተከስቶ ተከስቶ የነበረ ቢሆንም ነዋሪዎች አደጋው አጋጥሞ ጉዳት ካደረሰባቸው በኋላ በማግስቱ መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ/ም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን አድርሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ለኮሚሽኑ መረጃውን በማድረሱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በማሰማራት ሂደት ውስጥ የኮሚሽኑ አመራርና ባለሞያዎች የተጋላጭ ቦታ ልየታ የመስክ ጉብኝት እያደረጉ በነበረበት አጋጣሚ አደጋው ደርሷል በተባለው ቦታ ነዋሪዎችን አግኝተው አነጋግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ኮሚሽኑ ችግሩ መኖሩን እንደተረዳ በአፈሩ ተደፍኖ የነበረውን የውሃ መውረጃ መስመር ከባለድርሻ አካላት ጋር በእስካቫተር እንዲጸዳ በማድረግ የተጠራቀመው ውሃ ቦታውን እንዲለቅ፣ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም የማቅለያ እርምጃ ሰርቷል።

በሌላ በኩልም በጎርፍ አደጋው ጉዳት ለደረሰባቸዉ 105 ተጎጂዎች የዋጋ ግምታቸው ከ600 መቶ ሺሕ ብር በላይ የሆነ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።

ህብረተሰቡ ማናቸውም አደጋዎች በአጋጠሙ ጊዜ  በነጻ የስልክ መስመር 939 ላይ በመደወል እንዲያሳውቅም ኮሚሽን መ/ቤቱ ያሳስባል ” ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ በቦታው ቅኝት አድርጎ ሲመለከት ነዋሪዎቹ ስለገለጹት ቀጣይ ስጋትና ሌሎች ጥያቄዎች ለኮሚሽኑ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ማብራሪያው በቀጣይ ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia