TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle 🔴 " ህወሓት መዳን ከፈለገች መልሳ ጉባኤ ማድረግ አለባት የሚል እምነት አለኝ "- ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ  ⚫️ " ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እርምጃ ውሰድ ፤ ካልሆነ በራሳችን መንገድ እንሄዳለን " - የመቐለ ከተማ ወጣቶች ዛሬ ለመቐለ ከተማ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የመከሩ ወጣቶች የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት "  ኋላቀር ለውጥ አደናቃፊ " ሲሉ …
#Tigray

" እንቅስቃሴው እጅግ አደገኛና የማያባራ ቀውስ የሚያዋልድ በመሆኑ በአስቸኳይ ይቁም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

" ' የሰራዊት አመራር ውሳኔ ' በሚል ህገ-ወጥ ጉባኤ ላካሄደ ቡድን ስልጣን ለማስረከብ የተጀመረ እንቅስቃሴ እንዲቆም " ሲል የትግራይ ክልል ጊዜዊ አስተዳደር ትእዛዝ ሰጠ።

ትእዛዙን የሰጡት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ህገ-ወጥ ተግባሩ " አስነዋሪ ፣ ለውጥ አደናቃፊና እርባና ቢስ " ሲሉ አጣጥለውታል።

ፕሬዜዳንቱ በቀጥታ ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዜዳንትና የሰራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የካቲት 26/2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ህገ-ወጥ ተግባሩ በአስቸኳይ እንዲቆም አዘዋል።

" ህገ-ወጥ ጉባኤ ያካሄደ ቡድን " ሲል የገለፁት የደብረፅዮኑ (ዶ/ር) ህወሓት የክልሉ ማእከላዊና ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የጊዚያዊ አስተዳደር መዋቅሮች በሰራዊት በመታጠቅ መቆጣጠሩ አንስቷል።

ህገ-ወጥ ድርጊቱ በተቀሩት ምስራቃዊ ፣ ደቡባዊ ፣ ደቡብ ምስራቅና መቐለ ዞኖች ለመፈፀም ያለመ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነውም ብለዋል። 

አቶ ጌታቸው ፤ " ማንኛውም ጥያቄ አለኝ የሚል የሰራዊት አመራር በህጋዊ መንገድ ጥያቄው ማቅረብ የሚችልበት ስርዓት በመጣስ በቀበሌ ፣ በወረዳ እና በመንደር ሰራዊት እያሰማሩ የመንግስት መዋቅር ለማፍረስ ማህተም ለመቀማት የሚደረግ እንቅስቃሴ ከስርዓት አልበኝነት ውጪ የሚያመጣው ፋይዳ የለም " ብለዋል።

" በተወሰኑ የሰራዊት አመራር ስም ሰራዊቱ በማሰመራት የመንግስት መዋቅሮች ህገ-ወጥ ጉባኤ ላካሄደ ቡድን ለማስረከብ የሚደረግ እንቅስቃሴ እጅግ አደገኛና የማያባራ ቀውስ የሚያዋልድ በመሆኑ በአስቸኳይ ቆሞ ህገ-ወጥ ተግባሩ እንዲፈፀም ያዘዙ የሰራዊት አመራሮች እንዲጠየቁ " ሲሉም ፕሬዜዳንቱ በደብዳቤያቸው በአፅንኦት አሳስበዋል።

ለምክትል ፕሬዜዳንትና የሰራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተፃፈው ደብዳቤ ትእዛዙ በግልባጭ ለሰላም እና የፀጥታ ቢሮ ለከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ሜጀር ጀነራል ዮውሃንስ ወ/ጊዮርጊስ ፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ አሳውቀዋል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
 
@tikvahethiopia