TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የህወሓት አመራሮች ዛሬ በመቐለ ከተማ ፊት ለፊት ተገናኝተዋል። የፊት ለፊት ግንኙነቱ በክልሉ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች የተመራ ነበር። ጥዋት በመቐለ ኖርዘርን ስታር ሆቴል አዳራሽ የነበረው የፊት ለፊት ውይይት ግማሽ ቀን የፈጀ እንደነበር ታውቋል። የሃይማኖት አባቶቹ ፥ " ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱ ባቀረብናላቸው ጥሪ መሰረት ተገናኝተው ችግራቸውን በፓለቲካዊ እና በህጋዊ አሰራር እንፈታለን…
#Tigray
" ችግሮቻቸውን በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው ለህዝቡ እፎይታ ይሰጣል " - የሃይማኖት አባቶች
የትግራይ ክልል አመራሮች በመካከላቸው የተፈጠረው የፓለቲካ ልዩነት በሰላም እና በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው የትግራይ የሃይማኖት መሪዎች አስታወቁ።
ችግሮቻቸው ለመፍታት እና ወደፊት ሊያራምዳቸው የሚችል የስነ-ምግባር ደንብ ወጥቶ መፈራረማቸውም ሰላማዊ ውይይቱን የመሩ የሃይማኖት አባቶች ዛሬ የካቲት 7/ 2017 ዓ.ም በመቐለ በሰጡት መግለጫቸው አስታውቀዋል።
የሃይማኖት አባቶቹ በመግለጫቸው " አመራሮቹን ለማቀራረብ ሲካሄድ የነበረው ሰላማዊ ውይይት ስምምነት ላይ አድርሷቸዋል " ብለዋል።
በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረው ችግር ለመፍታት ከሁለት ወር በላይ ጥረት መደረጉ ያብራሩት የሃይማኖት አባቶቹ መሪዎቹ ችግሮቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ መስማማታቸው ለህዝቡ እፎይታ ይሰጣል ሲሉ ገልጸዋል።
አመራሮቹ በመካከላቸው የተፈጠረ የፓለቲካ ልዩነት በውይይት እንዲፈቱ መስማማታቸው አስመልክቶ በሃይማኖት አባቶች የተሰጠው መግለጫ ብዙ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ያላቸው ደስታ እና ድጋፍ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚመሩ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከወራት በፊት ችግሮቻቸው ለመፍታት በሃይማኖት አባቶች ፊት ቢጨባበጡም ጠብ የሚል ለውጥ ማምጣት ባለመቻላቸው ምክንያት ህዝቡን ወደ ከፍተኛ ጭንቀት እና ወጥረት መክተታቸው የሚታወስ ነው።
አሁንስ ቃላቸው ጠብቀው ልዩነቶቻቸው ጠረጴዛ ዙሪያ በመፍታት ለህዝብ አገር እፎይታ ይሰጡ ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
ፎቶ 2 ፦ ፋይል
@tikvahethiopia

#NewsAlert ህወሓት ለሦስት ወር ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ታገደ። ➡ በሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ ተወስኗል። የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መታገዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳወቀ። ፓርቲው በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት 6 ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ…
#Update #TPLF
" ቦርዱ ከፌደራል መንግስት ጋር የጀመርነውን ተከታታይ ውይይት ከማደናቀፍ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን " - በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት 6 ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ ይጠበቅበት ነበር ፤ ይህንን ባለማድረጉ ለሦስት ወር ከፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲታደግ ፤ በሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ መወሰኑ ተከትሎ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
ህወሓት ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረ አንጋፋ ፓርቲ መሆኑ የገለፅው መግለጫው ፤ " ጥቅምት 23/2015 ዓ/ም በደቡብ አፍሪካዋ የፕሪቶሪያ ከተማ የሰላም ውል ከተፈራረመ ጀምሮ ህጋዊነት የተመለሰ ነው " ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ህወሓት ከነሃሴ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ህወሓትን በአዲስ ህግ እንደ አዲስ ፓርቲ " መዝግቤዋለሁ ማለቱን " አስገራሚ እና ተቀባይነት የሌለው ፤ ፓርቲው ከፕሪቶሪያ ስምምነት ማግስት ህጋዊነቱ ያረጋገጠ ነው " ብሏል።
" የምርጫ ቦርድ አካሄድ በመሰረቱ ተቀባይነት የሌለው ፤ ህግን መሰረት ያላደረገ ተቀባይነት የሌለው ትርጉም አልባ ውሳኔ ነው " ብሎታል።
" ህወሓት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ከኢትዮጵያ መንግስት እውቅና ተሰጣጥቶ የሰላም ውል የፈረመ ፓርቲ ነው " ያለው ህወሓት ፤ " ከኢፌዲሪ መንግስት ተከታታይ የፓለቲካ ውይይት በማካሄድ ላይ ነን። ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሰላማዊ ውይይቱ ከማደናቀፍ እንዲቆጠብ " ሲል አቋሙ ግልጿል።
ህወሓት ከኢፌዴሪ መንግስት በተከታታይ በማካሄድ ላይ ያለው ውይይት ውጤታማ በቅርቡ ወደ ፍሬ የሚቀየር መሆኑ የገለፀው ህወሓት " የምርጫ ቦርድ ይህንን መልካም ሂደት የሚፃረር አካሄድ በመሄድ ላይ ይገኛል " ሲል ከሷል።
የኢፌዴሪ መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመተግበር ህገ-መንግስቱ እንዲያከብር እና እንዲያስከብር የጠየቀው ህወሓት ፥ የምርጫ ቦርዱ ውሳኔ 50ኛው የፓርቲው የምስረታ በዓል ከማክበር እንደማያግደው በመግለፅ " ህዝቡ በዓሉ ለማክበር የጀመረው እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥል " ብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ የካቲት 11 በዓል ምን አሉ ?
" ባለፈው የከፈልነው ይብቃ ፤ ያልፈውን አልፈዋል እንዳይደገም ያለፉት ስህተቶቻችን ማረም ያስፈልጋል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) 50ኛው ዓመት የካቲት 11 በዓል በማስመልከት በትግርኛ ቋንቋ ለመላው የትግራይ ህዝብ " የእንኳን አደረሳችሁ " መልእክት አስተላልፈዋል።
በአገር ውስጥና በመላው ዓለም ለሚገኙት የትግራይ ተወላጆች እና ወዳጆች " ለ50ኛው ዓመት የካቲት 11 በዓል እንኳን አደረሳችሁ " በሚል መልዕክታቸውን ያስቀደሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ ፥ የትግራይ ህዝብ ባለፉት ዘመናት ተጋድሎ ለአገር ሉአላውነት እና ዳር ደንበር መከበር የከፈለውን መስዋእትነት በታላቅ ክብር አስታውሰዋል።
በአገራችን ታሪክ ፓለቲካዊ ልዩነቶች በህግ ወይ በመግባባት የመፍታት የዳበረ ልምድ እንዳልነበረ ጠቅሰዋል።
ይሁን እንጂ ማህበረሰቡ በየብሄሩ እና አከባቢው የሚፈጠሩት ልዩነቶች በእርቅ እና ሽምግልና መፍታት በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫዎች የተዘወተረ ነው ብለዋል።
" ይህ ሆኖ እያለ ፓለቲካው ከባህል አፈንግጦ ሁሉም ልዩነቶች በግጭት ብቻ መፍታት ፓለቲካዊ ባህል ሆኖ ለዘመናት ቆይተዋል አሁንም ፈተና ሆኖ ቀጥለዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ፓለቲካዊ ልዩነት በውይይት ፣ በእርቅ እና መግባባት ብሎም በህገ -መፈታት አለበት የሚለው አቋም ከለውጡ በኋላ እንደ መንግስት የተያዘ አቋም ነው ጠቅላአቋመያዝ በዘለለ ሕጋዊ እና ተቋማዊ አሰራር ተበጅቶለት በመተግበር ላይ እንደሚገኝ " ገልፀዋል።
" አሰራሩ ጅምር ላይ መሆኑ ልብ ማለት ይገባል " ያሉ ሲሆን የትግራይ ህዝብ ጭቆና በምክክር እና ህጋዊ አሰራር መፈታት በማይችልበት ወቅት የነበረው ብቸኛ አማራጭ ጠብመንጃ በማንሳት ዴሞክራሲ እና እኩልነት ለማስፈን ከሌሎች ህዝቦች ጋር በማበር የየካቲት 11 ትግል ለማካሄድ መገደዱን አስታውሰዋል።
" ጠበመንጃ በማንሳት የሚካሄድ የግጭት መንገድ በመሰረቱ የሚደገፍ ባይሆንም በወቅቱ የነበረው ፓለቲካዊ እና ህጋዊ ሁኔታ ግን ጠብመንጃ ለማንሳት የሚያስገድድ ነበር " ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ " የካቲት 11 የተቀጣጠለው በጠብመንጃ የታገዘ ፓለቲካዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማቆም ልየነቶች በውይይት ለመፍታት ያለመ በመኖሩ ከሱ በፊት ሲካሄዱ ከነበሩት ትግሎች ሲነፃፀር ይለያል " ብለዋል።
ስለሆነም ማንኛውም ልዩነት በጠብመንጃ ሳይሆን በውይይት እና በህጋዊ መንገድ መፍታት የየካቲት 11 ፍሬዎች መሆናቸው መገንዛብ ያሻል ሲሉ አክለዋል።
" ባለፉት የቅርብ ዓመታት ያጋጠሙን መቃቃሮች ለመፍታት የተከተልነው የግጭት መንገድ ፤ ከየካቲት 11 ዓላማዎች የወጣ መሆኑ ግልፅ ነው ፤ ይሁን እንጂ ከባድ ዋጋ ከፍለንም ቢሆን ወደ ውይይት መመለሳችን የሚደነቅ እርምጃ ነው ፤ ይሁን እንጂ አሁንም ፓለቲካዊ ልዩነት በጠንጃ ለመፍታት የመፈለግ ዝንባሌ መታየቱ አልቀረም " ብለዋል።
" ባለፈው የከፈልነው ይብቃ ፤ ያልፈውን አልፈዋል እንዳይደገም ያለፉት ስህተቶቻችን ማረም ያስፈልጋል " ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ በትግራይ አመራሮች መካከል የተጀመረው ውይይት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለውጤት እንዲበቃ ያላቸው መልካም ምኞት ገልፀዋል።
ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ፣ የተስተጓጎለው ልማት ተጠናክሮ በህዝብ ወደ ተመረጠ መንግስት ሽግግር እንዲደረግ ከልብ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።
የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ህዝብና ልሂቃን በተገለፀው የውውይት መንፈስ ማሰብ ከጀመሩ ፤ ትግራይ ወደ መደበኛ የህገ-መንግስት ስርዓት በመመለስ በሃገረ መንግስቱ ያላትን ተሳትፎ አጠንክራ የምትቀጥልበት ጊዜ በጣም አጭር እና ተጨባጭ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መልካም የየካቲት 11 በዓል እንዲሆንም በፅሁፋቸው ተመኝተዋል።

#Tigray " ችግሮቻቸውን በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው ለህዝቡ እፎይታ ይሰጣል " - የሃይማኖት አባቶች የትግራይ ክልል አመራሮች በመካከላቸው የተፈጠረው የፓለቲካ ልዩነት በሰላም እና በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው የትግራይ የሃይማኖት መሪዎች አስታወቁ። ችግሮቻቸው ለመፍታት እና ወደፊት ሊያራምዳቸው የሚችል የስነ-ምግባር ደንብ ወጥቶ መፈራረማቸውም ሰላማዊ ውይይቱን የመሩ የሃይማኖት አባቶች ዛሬ…
#Update
" በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ " የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ።
ፕሬዜዳንቱ ለእርቅ እና ሽምግልና አለመሳካት " ቡድን " ሲሉ የጠሩትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባወጡት መግለጫ " መንግስት የማያውቀው ርችት በመተኮስ የሚያጋጥም ችግር ካለ ተጠያቂው ቡድኑ ነው " ብለዋል።
አላስፈላጊ የአመፅ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸው የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ህዝቡ አከባቢውን በልዩ ሁኔታ በመጠበቅ በዓሉ እንዲያከብር አሳስበዋል።
ከቀናት በፊት ለእርቅና ሽምግልና ፍቃደኛ መሆናቸው በትግራይ የሃይማኖት አባቶች መግለጫ የተሰጠባቸው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በትናንቱ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ የሚያሳይ ፎቶ መለቀቁ ብዙዎች አስደስቶ ነበር።

ትናንተ የካቲት 12 /2017 ዓ.ም በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ በነዋሪዎችና በአከባቢው በሚገኘው የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ተከስተዋል።
በግጭቱ ምክንያት በ20 የቀበሌው ነዋሪዎችና ቁጥራቸው ባልታወቀ የትግራይ ኃይል አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ያጋጠመ ሞት የለም።
ግጭቱ እንዴት እና በምን ምክንያት አጋጠመ ?
በአዲስ አለም ቀበሌ ሁለት አስተዳዳሪዎች አሉ። አንዱ የቆየ ሲሆን ሌላው ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾመ ነው።
ሁለቱም ማህተም ይዘው በየፊናቸው " እኔ ነኝ ህጋዊ የቀበሌው አስተዳደር " በማለት ህዝቡን ለሁለት መክፈላቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ " ህዝቡ አማርሮ እንድንታደገው ጠይቆናል አዛዦቻችንም ይህንን እንድንፈፅም ልከውናል" ያሉ 9 የሰራዊት አባላት ወደ ቀበሌው ደርሰው ሁለቱ አስተዳዳሪዎች ማህተም እንዲያስረክቡ ይጠይቃሉ።
" ታስረክባላችሁ አናስረክም " በሚል እልህ በነዋሪዎች እና የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ይነሳል። ነዋሪውም ደንጋይ መወርወር ይጀምራል። የትግራይ ኃይል አባላትም ጥይት ይተኩሳሉ።
በዚህ መካከል በተተኮሰ ጥይት አንድ ሰው እጁ ላይ ተመትቶ ሆስፒታል ሲገባ ሌሎች 20 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በትግራይ ኃይል አባላት ላይም ጉዳት የደረሰባቸው አሉ።
የወረዳው አስተዳደር ለክልሉ የሰላም እና የፀጥታ ቢሮ የካቲት 11/2017 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ 13 ታጣቂዋች ወደ ወረዳው አስተዳደር በመምጣት የጊዚያዊ አስተዳደር ማህተም እና የፅህፈት ቤት ቁልፍ እንዲያስረክቡዋቸው መጠየቃቸውን እና ይህንን ህገ-ወጥ ተግባር እንዲቆም ጠይቋል።
ከህወሓት ወደ ሁለት መሰንጠቅ በኋላ የክልሉ ዋና ከተማ መቐለ ጨምሮ በተለያዩ የገጠር እና የከተማ አስተዳደሮች ተመሳሳይ ስልጣን ያላቸው ሁለት አሰተዳዳሪዎች መስማት የተለመደ ነው።
በአንዳንድ ዞኖች ያሉ ወረዳዎች በጊዚያዊ አስተዳደሩ እና የደብሪፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት የተሾሙ አስተዳዳሪዎች ለሁለት ተከፋፍለው ይተዳደራሉ።
የትግራይ መሪዎች በተለይም የህወሓት አመራሮች ከዚህ መሰል ህዝብ የሚከፋፍል አደገኛ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የሚመክሩ አስተያየት ሰጪዎች ፤ የትግራይ ኃይል አባላት አንዱን ቡድን ደግፈው ሌላው ቡድን ማውገዝ ተጨማሪ ቀውስ እና ጥፋት ስለሚያስከትል የገለልተኝነት ሚናቸው እንዱወጡ አበክረው እያሳሰቡ ናቸው።

#Tigray ትናንተ የካቲት 12 /2017 ዓ.ም በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ በነዋሪዎችና በአከባቢው በሚገኘው የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ተከስተዋል። በግጭቱ ምክንያት በ20 የቀበሌው ነዋሪዎችና ቁጥራቸው ባልታወቀ የትግራይ ኃይል አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል። ያጋጠመ ሞት የለም። ግጭቱ እንዴት እና በምን ምክንያት አጋጠመ ? በአዲስ አለም ቀበሌ ሁለት…
#UPDATE
" ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ወደ ማንወጣው ቀውስ እንደምንገባ የቅርብም የሩቁም ሊገነዘበው ይገባል " - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር
" ሃይል በመጠቀም የመንግስት መዋቅር ለማፍረስ የሚደረግ ህገ-ወጥ እርምጃ ተቀባይነት የለውም " አለ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ የካቲት 13 /2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ ገበሬ ማህበር የትግራይ ኃይል አባላት በነዋሪ አርሶ አደሮች ላይ ያደረሱትን ጥቃት አውግዟል።
" የተወሰኑ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅር ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ እየታዘብን ነው " ያለው መግለጫው " በሰሓርቲ ወረዳ የተከሰተው አሳዛኝ ተግባር እንደ አንድ ማሳያ መውሰድ ይቻላል " ብሏል።
" ሰራዊቱ የህዝብ ህልውና ለመጠበቅ እንጂ የአንድ ቡድን የስልጣን ጥማት ለማርካት የተሰለፈ አይደለም " ያለው ጊዚያዊ አስተዳደሩ " ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ወደ ማንወጣው ቀውስ እንደምንገባ የቅርብም የሩቁም ሊገነዘበው ይገባል " ሲል አስጠንቅቋል።
" ማንኛውም የህግ ወይም የአስራር ክፍተት ሲኖር የሚሊሻና የፓሊስ ሃይል ከህዝባቸው በመተባበር የሚፈቱት እና የሚያርሙት እንጂ ሰራዊት ወደ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ማሰማራት የሚያስገድድ ሁኔታ ፈፅሞ እንደሌለ የለም " ሲል ገልጿል።
" ይህንን ህገ-ወጥ አካሄድ የሚያበረታቱ እና የሚያግዙ ፓለቲከኞች እና የሰራዊት አመራሮች አደብ እንዲገዙ " ሲልም አስጠንቅቋል።

#Mekelle 🔴 " ህወሓት መዳን ከፈለገች መልሳ ጉባኤ ማድረግ አለባት የሚል እምነት አለኝ "- ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ⚫️ " ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እርምጃ ውሰድ ፤ ካልሆነ በራሳችን መንገድ እንሄዳለን " - የመቐለ ከተማ ወጣቶች ዛሬ ለመቐለ ከተማ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የመከሩ ወጣቶች የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት " ኋላቀር ለውጥ አደናቃፊ " ሲሉ …
#Tigray
" እንቅስቃሴው እጅግ አደገኛና የማያባራ ቀውስ የሚያዋልድ በመሆኑ በአስቸኳይ ይቁም " - አቶ ጌታቸው ረዳ
" ' የሰራዊት አመራር ውሳኔ ' በሚል ህገ-ወጥ ጉባኤ ላካሄደ ቡድን ስልጣን ለማስረከብ የተጀመረ እንቅስቃሴ እንዲቆም " ሲል የትግራይ ክልል ጊዜዊ አስተዳደር ትእዛዝ ሰጠ።
ትእዛዙን የሰጡት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ህገ-ወጥ ተግባሩ " አስነዋሪ ፣ ለውጥ አደናቃፊና እርባና ቢስ " ሲሉ አጣጥለውታል።
ፕሬዜዳንቱ በቀጥታ ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዜዳንትና የሰራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የካቲት 26/2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ህገ-ወጥ ተግባሩ በአስቸኳይ እንዲቆም አዘዋል።
" ህገ-ወጥ ጉባኤ ያካሄደ ቡድን " ሲል የገለፁት የደብረፅዮኑ (ዶ/ር) ህወሓት የክልሉ ማእከላዊና ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የጊዚያዊ አስተዳደር መዋቅሮች በሰራዊት በመታጠቅ መቆጣጠሩ አንስቷል።
ህገ-ወጥ ድርጊቱ በተቀሩት ምስራቃዊ ፣ ደቡባዊ ፣ ደቡብ ምስራቅና መቐለ ዞኖች ለመፈፀም ያለመ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነውም ብለዋል።
አቶ ጌታቸው ፤ " ማንኛውም ጥያቄ አለኝ የሚል የሰራዊት አመራር በህጋዊ መንገድ ጥያቄው ማቅረብ የሚችልበት ስርዓት በመጣስ በቀበሌ ፣ በወረዳ እና በመንደር ሰራዊት እያሰማሩ የመንግስት መዋቅር ለማፍረስ ማህተም ለመቀማት የሚደረግ እንቅስቃሴ ከስርዓት አልበኝነት ውጪ የሚያመጣው ፋይዳ የለም " ብለዋል።
" በተወሰኑ የሰራዊት አመራር ስም ሰራዊቱ በማሰመራት የመንግስት መዋቅሮች ህገ-ወጥ ጉባኤ ላካሄደ ቡድን ለማስረከብ የሚደረግ እንቅስቃሴ እጅግ አደገኛና የማያባራ ቀውስ የሚያዋልድ በመሆኑ በአስቸኳይ ቆሞ ህገ-ወጥ ተግባሩ እንዲፈፀም ያዘዙ የሰራዊት አመራሮች እንዲጠየቁ " ሲሉም ፕሬዜዳንቱ በደብዳቤያቸው በአፅንኦት አሳስበዋል።
ለምክትል ፕሬዜዳንትና የሰራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተፃፈው ደብዳቤ ትእዛዙ በግልባጭ ለሰላም እና የፀጥታ ቢሮ ለከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ሜጀር ጀነራል ዮውሃንስ ወ/ጊዮርጊስ ፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ አሳውቀዋል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#Tigray " እንቅስቃሴው እጅግ አደገኛና የማያባራ ቀውስ የሚያዋልድ በመሆኑ በአስቸኳይ ይቁም " - አቶ ጌታቸው ረዳ " ' የሰራዊት አመራር ውሳኔ ' በሚል ህገ-ወጥ ጉባኤ ላካሄደ ቡድን ስልጣን ለማስረከብ የተጀመረ እንቅስቃሴ እንዲቆም " ሲል የትግራይ ክልል ጊዜዊ አስተዳደር ትእዛዝ ሰጠ። ትእዛዙን የሰጡት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ህገ-ወጥ ተግባሩ " አስነዋሪ…
#Tigray
" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ያለችውን ትግራይ ማስተዳደር የማይችልበት ሁኔታ ተፈጥረዋል" - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህም የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት የተወሰኑ የሰራዊት አመራሮችን በመጠቀም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እያካሄደ እንደሆነ ተናግረዋል።
" ቡድኑ በድርጅቱ የቁጥጥር ኮሚሽንና በኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽን እውቅና የሌለው ህገ-ወጥ ጉባኤ ያካሄደ ነው " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ቡድኑ በማንኛውም መመዘኛ እና መለኪያ ወደ ስልጣን አይመለስም " ሲሉ አክለዋል።
ጥቂት የሰራዊት አመራሮች እንደ መሳሪያ በመጠቀም በየወረዳው እና ቀበሌው በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ የስራ ሃላፊዎች ማህተም በመቀማት ላይ ተጠምዷል ሲሉም ተናግረዋል።
" ይህ ህገ-ወጥ ተግባር የተረጋጋ መንግስታዊ አገልግሎትና ፀጥታ እንዳይኖር እክል ፈጥሯል " ሲሉም ገልጸዋል።
" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ያለችውን ትግራይ ማስተዳደር የማይችልበት ሁኔታ ተፈጥረዋል " ሲሉም አክለዋል።
" የክልሉን ፀጥታ በማድፍረስ የፕሪቶሪያ ስምምነት ለማፍረስ የተጀመረው እንቅስቃሴ እጅግ አደገኛና ጥፋት የሚያስከትል ነው " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ተግባሩ በአስቸኳይ እንዲቆም ሁሉ መተባበር አለበት " ብለዋል።
ሌላው አቶ ጌታቸው ረዳ በመግለጫቸው በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስታት መካከል በግልፅ የሚታይ ወጥረት አለ ብለዋል።
" ውጥረቱ ወደ ግጭት ተሸጋግሮ ትግራይ የጦርነት አውድማ እንዳትሆን መስራት ይጠበቅብናል " ሲሉ ተደምጠዋል።
ትናንት የካቲት 30 እና ዛሬ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም በትግራይ ምስራቃዊ ዞንና በመቐለ የተወሰኑ የሰራዊት አመራር ያሰማሩት ኃይል ፓትሮል በመጠቀም በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ አስተዳዳሪዎች ማህተም የመቀማት እና ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ የሚወስድ ከተማ የቁጥጥር ኬላ የመስራት ምልክቶች መታየታቸው አቶ ጌታቸው ረዳ አስታውቀዋል።
ዛሬ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም የምስራቃዊ ዞን የፀጥታና የሰላም ሃላፊ በአከባቢው በሚገኙ የሰራዊት አመራር ከሁለት ሰዓት በላይ ታግተው መለቀቃቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጠዋል።

Photo
#NewsAlert
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ላይ ጊዚያዊ የእግድ ደብዳቤ ፃፉ።
እግዱ የተፃፈላቸው ከፍተኛ አመራሮች ፦
- ሜጀር ጀነራል ዮውሃንስ ወ/ጊዮርጊሰ
- ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ
- ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሃይለ ናቸው።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም የፃፉት ጊዚያዊ የእግድ ደብዳቤ ፦
" ከመንግስት ውሳኔ ውጪ መላ ህዝባችን ፣ ወጣቱን ወደ ግርግር ፤ የፀጥታ ሃይላችን ወደ እርስ በርስ ግጭት ብሎም ህዝባችን ወደ እማይወጣበት አዘቅት የሚያስገባ አደገኛ እንቅስቃሴ አልቆመም ስለሆነም እርስዎ ስርዓት ባለው አካሄድ መግባባት እስኪደረስ ድረስ ከመጋቢት 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከአዛዥነትዎ የታገዱ መሆንዎን አስታውቃለሁ " ይላል።
በትግራይ ክልል በአመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት እንዲፈታ ብዙ ጥረት ቢደረግም ምንም መፍትሄ ሳይገኝለት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ነዋሪዎችም ሁኔታው ስጋት ላይ ጥሏቸዋል።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር " ሲል ውድቅ አደረገው።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን " አምባገነን ፕሬዜዳንት ነበር " ሲል አጣጥሏቸዋል።
ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ላይ የወሰዱት ጊዚያዊ የእግድ እርምጃ አስመልክቶ ሌሊት መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም ፕሬዜዳንቱ የወሰዱት እርምጃ " በሌለ ስልጣናቸው የወሰዱት የማይተገበር " ሲል በፅኑ ተቃውሞታል።
" እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር " ሲል ውድቅ ያደረገው መግለጫው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳን " ከስልጣቸው የኋላፊነት ቦታ ማንሳቱን " አስታውሰዋል።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን " አምባገነን ፕሬዜዳንት ነበር " ሲልም አጣጥሏቸዋል።
" የእግድ እርምጃውን የተደራጀ ሰራዊት ለማፍረስ ሲደረገው የቆየው ተንኮል አካል ነው " ያለ ሲሆን " እርምጃው አደገኛ ውጤት የሚያስከትል ነው " ሲል አስጠንቅቋል።
" መሰረተ ቢስ " ሲል የገለፀው የሦስቱ ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ጊዚያዊ እግድ ፤ የሰራዊት አባላትና ህዝቡ እንዳይቀበሉት የሚል ጥሪም አስተላልፏል።

#Update በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " እገዳው መሰረተ ቢስና የማይተገበር " ሲል ውድቅ አደረገው። ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን " አምባገነን ፕሬዜዳንት ነበር " ሲል አጣጥሏቸዋል። ደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች ላይ የወሰዱት ጊዚያዊ የእግድ እርምጃ አስመልክቶ ሌሊት መግለጫ አውጥቷል። በዚህም ፕሬዜዳንቱ…
#Update
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ትእዛዝ " አልቀበልም አልፈፅምም " አለ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ፤ " በቢሮው ስም የቀረበው መግለጫ የአንድ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አካል ሳይሆን የአንዱ ቡድን ወታደራዊ ክንፍ መሆኑ በግልፅ የሚያሳብቅና የተፈጠረውን ችግር የሚያባብስ ነው " ብሎታል።
ትናንት መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች የጣሉት ጊዚያዊ እግድ ተከትሎ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት " እገዳው መሰረተ ቢስ እና የማይተገበር " በማለት ውድቅ ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም።
ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጊዚያዊ እግድ ሙሉ በሙሉ በመፃረር ባወጣው መግለጫ ፤ በግልባጭ የተፃፈለትን ትእዘዛዝ እንደማይቀበል በመግለፅ " የህግ ማስከበር እርምጃው " ይቀጥላል ብሏል።
የሰላምና ፀጥታ ቢሮ መግለጫ ተከትሎ ከመቐለ በ115 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የዓዲግራት ከተማ በሰራዊት የታገዘ መፈንቅለ ስልጣን መካሄዱን ለማወቅ ተችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ጠዋት ወደ ምስራቃዊ ዞን የሰላምና የፀጥታ ሃላፊ ደውሎ " ከቀበሌ የተወጣጡ ጥቂት ደጋፊዎች በሰራዊት በመታገዘ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የሾማቸው ከንቲባ ሲገለገሉት የነበረው ፅሕፈት ቤት በመስበር በደብረፅዮኑ ህወሓት ለተመረጡት ከንቲባ አስረክበዋል " ብለውታል።
በትግራይ ክልል ያለው የፓለቲካና የፀጥታ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢና ተለዋዋጭ ደረጃ ላይ ይገኛል ያሉትን ሁኔታዎች እየተከታተልን እናቀርባለን።

#Peace
" እየተከተላችሁት ያለው መንገድ የተገኘውን ሰላም የሚያደፈርስ አገርን እና ህዝብን ለከባድ ቀውስ የሚያጋልጥ ነው !!! "
በትግራይ ክልል ሁኔታ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከወራት በፊት ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በላኩት የተግሳፅ ደብዳቤ ምንድነበር ያሉት ?
" ካህናት አበው ፣ የቤተክርስትያን ሊቃውንት ፣ ምእመናን ፣ የአገር ሽማግሌዎች የዕድሜ ባለፀጎች በሃዘን እያነቡ አካሄዳችሁን እንድታስተካክሉ ሲለምኗችሁ እና ሲመክሯችሁ ሰክናችሁ ማሰብ እና ማዳመጥ የተሰናችሁ ምክንያት ምን ይሆን ?
' የእኔ አካሄድ ብቻ ነው ልክ ' በሚል እልህ እና አስተሳሰብ የፈረሰ እንጂ የተገነባ ህዝብ እና አገር የለም።
የናንተ መለያየት አልበቃ ብሎ በአንድነት እና በመከባበር የኖረውን ህዝብ ለማራራቅ እየሄዳችሁበት ያለው ርቀት ህዝብን ለማገልገል መቆማችሁን ጥያቄ ውስጥ የሚከት የጥፋት እና የመጠፋፋት መንገድ በመሆኑ ቆም ብላችሁ አስቡ።
ይህ ሳይሆነ ከቀረ እየተከተላችሁት ያለው መንገድ የተገኘውንም ሰላም የሚያደፈርስ አገርን እና ህዝብን ለከባድ ቀውስ የሚያጋልጥ ነው።
ስለሆነም ህዝባችሁ የሚሰጣችሁ ምክር እና ተግሳፅ ተቀብላችሁ በስክነት እና በማስተዋል የህዝባችሁን ጥያቄ እንድትመልሱ አደራ እንላለን።
የተፈጠረው የሃሳብ አለመጣጣም ለመፍታት ከአቅም በላይ አይደለም። ችግሮቻችሁን በጥበብ እና በሰለጠነ አሰራር በመፍታት ጅምር ሰላሙን በማፅናት ህዝባችሁን እና አገራችሁን በልማት ለመካስ ከልብ እንድትተጉ የአባትነት ምክራችንን እናስተላልፋለን። "

#ትግራይ " እነዚህ ሰዎች አብደት ላይ መሆናቸውን ሊነገራቸው ይገባል " - አቶ ጌታቸው ረዳ 🚨 " እኔ ልለው የምችለው ማንም ሊገምተው ከሚችለው በላይ አስከፊ ነው !! " የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር። በዚህም ቃለ ምልልስ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ምን አሉ ? ➡️ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ጣልቃ መግባትን…
#Update
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በትግራይ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዲገባ ያቀረበውን ጥሪ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ተቃወመ።
የተጀመረው " ህግ የማስከበር እርምጃ " ያለው ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በትግራይ ጉዳይ እገዛ እንዲያደርጉ ያቀረበው ጥሪ " ይፋዊ ክህደትና የፕሪቶሪያ ስምምነት የሚያፈርስ " ሲል ውድቅ አድርጎታል።
" ህወሓት ፤ ህዝብና ሰራዊት ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሰጡትን ተልእኮዎች ለመፈፅም የሚያስችል የአመራር ማስተካከያ ይደረግ እንጂ ይፍረስ አላልኩም ብሏል " ሲልም ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ማህበረሰብ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በመተግበር የትግራይ ዘላቂ ሰላምንና መልሶ ግንባታ እውን እንዲሆን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧክ።
" መላው ህዝብ በትግራይ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት እንዲከበር ፣ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥና ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን ግዴታው ይወጣ " ሲል ህወሓት አሳስበዋል።
በተያያዘ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ሲያወጣቸው የነበሩ መግለጫዎች ወደ ህዝቡ ሲያሰራጩ የነበሩ የትግራይ ቴሌቪዥን እና ድምፂ ወያነ " የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በትግራይ ጉዳይ ጣልቃ እንዲገባ " የሚጠይቀውን መግለጫ ሳያስተናግዱት ቀርተዋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ምንጮች ፤ ለ104.4 የመቐለ ኤፍኤምና ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን አዲስ ስራ አስኪያጆች መመደባቸው ተናግረዋል።