TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
60K photos
1.52K videos
215 files
4.17K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Afar #Somali #Iftar

ዛሬ የአፋር እና ሶማሌ ወንድማማች ህዝቦች የኢፍጣር መርሐ ግብር በጅግጅጋ እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሃጂ አወል አርባ፣ የሰላም ሚንስትሩ አቶ መሀመድ እድሪስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።

#SomaliRegionGovCommunication

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አፋር #ቤንዚን “አንድ ሊትር ቤንዚን በብላክ ማርኬት ከ250 ብር በላይ ገዝተን ሰርትን መተዳደር በጣም ከብዶናል” - የሰመራ ከተማ አሽከርካሪዎች “ባለፉት ስድስትና ሰባት ቀናት ውስጥ በጣም ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት አለ” - የአፋር ክልል ንግድ ቢሮ በአፋር ክልል በተለይም ሰመራ ከተማ ያሉ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ቤንዚን ከማደያ እንዳይቀዱ በመከልከላቸው አንድ ሊትር ቤንዚን በችርቻሮ…
#Afar

🔴 “ ቤንዚን ማግኘት አልቻልንም፤ ባጃጅ ማሽከርከር እንደስራ አይቆጠርም ? ወይስ ተፈላጊ አይደለንም?” - የአፋር ክልል አሽከርካሪዎች

➡️ “ ባጃጅ ሰርቭ እናደርጋለን ብለን ከተማ ሊቃጠል ይችላል፤ እንደዛ እንዳይሆን ስጋት ስላለብን ነው ” - ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን

በአፋር ክልል በተለይ ሰመራና ዴቸቶ የሚገኙ የባለሦስት እግር አሽከርካሪዎች ሰሞኑን በጥቁር ገበያ እንኳ ቤንዚን ማግኘት እንዳልቻሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ከማደያ መቅዳት ስላልተፈቀደ አንድ ሊትር ቤንዚን በችርቻሮ 250 ብር ለመግዛት መገዳዳቸውን ከቀናት በፊት ገልጸው ነበር፣ አሁን ደግሞ “ቤንዚን ማግኘት አልቻልንም፤ ባጃጅ ማሽከርከር እንደስራ አይቆጠርም? ወይስ ተፈላጊ አይደለንም?” ሲሉ ጠይቀዋል።

“እባካችሁ ስቃያችንን እዩልን። እኛ ቤተሰብ ጭምር የምናስተዳድረው በባጃጅ ሰርተን በምናገኘው ገቢ ነው። ነገር ግን ጭራሽ ማዳያ ላይ እንዳንቀዳ ነው የተደረግነው፤ እንዴት እንኑር?” ሲሉም አማረዋል።

የክልሉ ንግድ ቢሮም ሰመራ ሙቀት ስለሆነ ቤንዚን ማደያ ላይ መቅዳት እንደማይቻል፣ የነዳጅ እጥረት እንዳጋጠመው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጾ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ሙቀት ባለባቸው ከተሞች ቤንዚን ከማደያ እንደማይቀዳ ተገልጿል፤ ይህ ለአሽከርካሪዎቹም ችግር ሆኗል። ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው? ሲል የኢትዮጵያ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ምላሽ ጠይቋል። 

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዲላሂ ምን መለሱ ?

“ ሙቀት ስለሆነ በጣም ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ባጃጅ ሰርቭ እናደርጋለን ብለን ከተማ ሊቃጠል ይችላል። እንደዛ እንዳይሆን ስጋት ስላለብን ነው።

በአካባቢ ያሉ ካምፓኒዎች ‘እናቅርብ’ ሲሉ ታንከሮቻችሁን ማስተካከል አለባችሁ ብለናቸዋል። እነርሱም ተቀብለዋል። ምክንያቱም ማንም ሪስክ አይወስድም።

ሙሉ ማደያ ብቻ ሳይሆን ከተማው ነው የሚያቃጥለው። ቀዝቀዝ የሚሉ ከተሞችን ምረጡ ብለናቸዋል። እነርሱ ሚሌን መርጠዋል። እዛ ላይ ሰርቭ እየተደረጉ ነው። በተረፈ ግን እንደ ክልል ሌሎች አማራጮችን ፈልጉ ብለናቸዋል።

ለምሳሌ በጀሪካን፣ በበርሜል ካልን ወደ ኮንትሮባንድ ንግድ ይሄዳል። ግን እነዚህ ባጃጆች ማሃ፣ ሁልበረግም ሌሎች አካባቢዎችንም በሳምንት 2 ሰርቭ እያደረገ ነው። ለእዛ አካባቢ ማደያዎች ስታንዳርድ አውጥተናል። ከ2016 ዓ/ም ጀምሮ ጸድቋል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ ምን ያክል ማደያዎች ስታንዳርዱን ጠብቀዋል? ምን ያክሎቹስ አላሟሉም? ያላሟሉትስ ምን ያክል ጊዜ ብንሰጣቸው ያሟላሉ? የሚሉትን እየሰራን ነው። 

የዲስፔንሰርና የታንከርንም አካተናል። ለምሳሌ ከዚህ በፊት የሚገጠሙ ታንከሮች ብረት የነበሩና ዝገት ሲያመጡ መሬት ላይ ሲቀበሩ ስታንዳርዱ ላይ የተቀመጠ ሜዠርመንት አለ። ለምሳሌ ታንከሩና ከላይ ያለው ኮንክሪት ከተቀራረበ ከባድ መኪና በሚያልፍበት ጊዜ አደጋ ሊፈጥር ስለሚችል ከነዚህ ነገሮች አኳያ ነው ስታንዳርዱን ያዘጋጀነው።

ከዚህ በኋላ በስታንዳርዱት እንዲገነቡ፣ የሚስተካከሉት እንዲያስተካክሉ ለማድረግ እየተሰራ ነው። ለምሳሌ አንዳንድ ቦታ ላይ ታንከሮች እየተበላሹ ውስጥ ለውስጥ የአርሶ አደር መሬት እስከማቃጠል የደረሱ አሉ” ብለዋል።

ሙቀት ባለባቸው አካባቢዎች ያሉ ሹፌሮች ቤንዚን እንደተቸገሩና ጥቁር ገበያውም እንደናረ ገልጸል፤ ታዲያ በምን መልኩ ነው ቤንዚን እያገኙ ያሉት? የሚል ጥያቄም አቆርበናል።

ዋና ዳይሬክተሯ በምላሻቸው፦

“ሚሌ ላይ ጠይቀው ፈቅደናል። ከሚሌ ወስደው ወደ ሰመራና ሌሎች አካባቢዎች በጥንቃቄ ቢያንስ ግማሽ፣ ግማሽ ቦቴ እያደረጉ ሰዓቱ ቀዝቀዝ ሲል እንዲያራግፉና በዚያን ወቅት እንዲጠቀሙ ነው ያልናቸው። 

ሚሌ ላይ ፈቅደንላቸው ኦፊሻሌ እየጫኑ ነው። ሰመራ እና ዴቸቶ አካባቢ በጣም ሙቀት አለ። ግን በዚያ ሙቀት ውስጥ ሆነንም ግማሽ፣ ግማሽ ቦቴ አድርገው ኩባንያዎች እየጫኑላቸው ነው። የክልሉ ንግድ ቢሮ ደብዳቤ ጽፎ ለምሳሌ መሃ በሚባል ጉባንያ በኩል ቤንዚን ያቅርብልን ብሎ ፈቃድ ሰጥተናል” ሲሉ ተናግረዋል።

የክልሉ ንግድ ቢሮ የነዳጅ እጥረት እደገጠመወ ገልጿል፤ ማቅረብ አልተቻለም? በሚል ስንጠይቃቸው ለክልሉ በልዩ ሁኔታ እንደሚጫን፣ ሰሞኑንም እንደተጫነ፣ ባለፉት ቀናት ግን ችግር ገጥሟቸው እንደነበር ገልጸዋል።

ወ/ሮ ሳህረላ፣ “አፋር ላይ ዋና ዋና የሚባሉት ሰመራ ዴቸቶ አና አዋሽ ናቸው አብዛኛው የመኪና አንቅስቃሴም ያለው የናፍጣ አዋሽ ላይ ራሱ የተባበሩት ጭኗል በፈረጆቹ 26። ከፈረንጆቸለ 27 ጀምሮ ሦስት አራት ቀናት ችግር ገጥሞን ነበር። በኋላ ግን ማስተካከል ተችሏል” ነው ያሉት። 

የገጠማችሁ ችግር ምን ነበር? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ምላሻቸው፣ “ሆራይዘን የማሽን ብልሽት ገጥሞን ስለነበረ ነው” ብለው፣ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከቀን 2 እስከ 11 የተለያዩ ካምፓኒዎች በተከታይይ መጫናቸውን የዳታውን ዝርዝር አስረድተዋል።

በዘርፉ የሚስተዋሉ ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን በተመለከተ ጠይቀናቸው ዋና ዳይሬክተሯ ማብራሪያዎች የሰጡን ሲሆን፣ በቀጣይ በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia