TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert
ህወሓት ለሦስት ወር ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ታገደ።
➡ በሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ ተወስኗል።
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መታገዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳወቀ።
ፓርቲው በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት 6 ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ ይጠበቅበት ነበር።
ቦርዱ ፥ ታኅሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በፃፈው ደብዳቤ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ የማድረጊያ ጊዜ ገደቡ ሊጠናቀቅ ከሁለት ወር ያነሰ ጊዜ አንደቀረው በመግለጽ በሕግ የተጣለበትን ግዴታ አንዲፈጽም ማሳሰቡን አስታውሷል።
ይህንን የሕግ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈጽም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሣኔ የሚሰጥ መሆኑን መግለጹንም አክሏል።
ይሁንና ፓርቲው የዐዋጁንና የመመሪያውን ደንጋጌዎችና የቦርዱን ውሣኔዎች በማክበር የጠቅላላ ጉባዔ ሳያካሄድ፣ መተዳደሪያ ደንቡን ሳያፀድቅና አመራሮቹን ሳይመርጥ በሕግ የተሰጠው የ6 ወር ጊዜ ተጠናቅቋል።
በዚህ መሠረት ቦርዱ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ጉዳዩን መርምሮ ፦
1ኛ. ፓርቲው ከፍ ዐዋጅና መመሪያ ላይ የተመለከቱ ድንጋጌዎችን ባለማክበር ጉልህ ጥሠት በመፈጸሙ ይህ ውሣኔ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ለሦስት ወራት በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዳይሣተፍ እንዲታገድ ወሥኗል።
2ኛ. ፓርቲው ለእግዱ ምክንያት የሆነውን ጥሠት በማረም፤ ዐዋጁን፣ ዐዋጁን ተከትሎ የወጣውን መመሪያ፣ የቦርዱን ውሣኔዎችና ትዕዛዞች በማክበር ፖርቲው ሊያደርግ የሚገባውን ጠቅላለ ጉባዔ ለማድረግ የሚያስችለውን የጉባዔ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለመሥራት ለቦርዱ በጽሑፍ ሲያሳውቅና ቦርዱ ይህንኑ ሲያረጋግጥ በመመሪያው መሠረት ቦርዱ ዕግዱን የሚያነሣ መሆኑን ወሥኗል።
3ኛ. ፖርቲው በተሰጠው የሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የተለየ አካሄድ ሳይከተል የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ ወሥኗል።
@tikvahethiopia