TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #Axum

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማሳሰቢያ ፥ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ዛሬ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።

" ያልተመዘገበ አይፈተንም " ማለቱ ይታወሳል።

ከሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ መልበስ ጋር ተያይዞ በአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተነሳው ውዝግብ ባለመግባባት ተቋጭቷል።

159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል አገር አገር አቀፍ ፈተና ለማሳተፍ የሚያስችላቸው ፎርም ሳይሞሉ የተሰጠው የምዝገበ ቀነ ገደብ ዛሬ አልቋል።

ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተለው የቆየው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ጥር 6 ቀን 2017 ከሰዓት በኋላ ወደ አክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር  ስዩም ካሕሳይ ደውሎ አግኝቷቸዋል።

ርእሰ መምህር ስዩም ካሕሳይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" - በትምህርት ቤታችን ከተለመደው የአለባበስ ስርዓት የተለየ የተሰጠ የአለባበስ ትእዛዝ የለም።

- ሴት ሙስሊም ተማሪዎቻችን እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ከትምህርት ቤቱ አመራር በአካል በመምጣት እንዲወያዩ ማስታወቅያ በመለጠፍና ስልክ በመደወል ጥረት ተደርጓል ለመምጣት ፍቃደኛ ኣይደሉም።

- የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አመራሮች ጉዳዩ እንዲረግብ ከትምህርት ቤታችን ፣ ከከተማዋ ከንቲባ ከአገር ሽማግሌ እና ከክልል ትምህርት ቢሮ ሰላማዊ ልመና ቢቅርብላቸውም ጉዳዩ ለማርገብ ፍቃደኛ አልሆኑም።

- በአጠቃላይ የፈተና ፎርም ያለ መሙላትና ያለ መፈተን ፍላጎቱ ከተማሪዎቻች ፍላጎት ውጪ የውጭ ተፅእኖ እና ግፊት አለበት።

- ልጆቻችን በቀላሉ በመግባባት ሊፈታ በሚችል ጉዳይ ከፈተና ውጪ መሆናቸው እንደ ርእሰ መምህርና ወላጅ እጅግ እሞኛል አበሳጭቶኛል " ... ብለዋል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ታህሳስ 22 ቀን 2017 ከህገ-መግስት ከሃይማኖታዊ ስርዓት ክልከላ ውጪ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች " ሂጃብ " እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላ እና የመብት ጥሰት አስመልክቶ ባወጣው ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ  ፥ " ፍትሃዊ ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የክልላችን የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመምከር በቀጣይ የምንወስዳቸው ሰላማዊ የትግል እርምጃዎችን ለህዝባችን እናሳውቃለን " ማለቱ ይታወሳል። 

ም/ቤቱ ባወጣው መግለጫ መሰረት ጥያቄዎቹ በሚመለከተው አካል ጀሮ ዳባ ልበስ መባላቸውን በማረጋገጡ በታህሳስ 30 ቀን 2017 ባወጣው አጭር መግለጫ ጉዳዩ በህግ እንዲታይ ክስ መመስረቱ ግልጽ አድርጓል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አመራሮች ስለ ጉዳዩ አሁናዊ ሁኔታ ተጨማሪ ማብራርያ እንዲሰጡ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

ከ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጭ የሆኑት 159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ጉዳይ ወዴት ያመራ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያቀርባል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" መላው የሎስ አንጀለስ ግዛት በእሳት ስጋት ውስጥ ይገኛል " - ባለስልጣናት በአሜሪካ ፤ ሎስ አንጀለስ የተነሳው ሰደድ እሳት አሁንም መቆጣጠር ያልተቻለ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም ወደ 24 ከፍ ብሏል። 16 ሰዎች ደግሞ የገቡበት አይታወቅም። በሎስ አንጀለስ ዙሪያ 3 አካባቢዎች መቃጠላቸውን ቀጥለዋል። በአሁኑ ላይ ትልቁ እሣት ሚገኘው በፓሊሳድስ ሲሆን 9307 ሔክታር መሬትን ሲያቃጥል 11 በመቶውን መቆጣጠር…
#Update

በአሜሪካ ፤ ሎስ አንጀለስ የተነሳው ከፍተኛ ሰደድ እሳት አሁንም መቆጣጠር ያልተቻለ ሲሆን እሳቱ አሁንም ሎስ አንጀለስን ማንደዱን ቀጥሏል።

እሳቱ እስካሁን ካደረሰው ውድመት በላይ ሊያደርስ ይችላል ተብሏል።

በአካባቢው ያለው የንፋስ ሁኔታ እሳቱን እያባባሰው ነው ተብሏል።

ከተነሱት ሰደድ እሳቶች አንዱን ብቻ ነው ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የተቻለው።

ባለስልጣናት
#ቀጣዮቹ ንፋሶች አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ የንፋስ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ በማለት መላው የሎስ አንጀለስ ግዛት በእሳት ስጋት ውስጥ እንደሚገኝ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።

እስከ ትላንት ባለው 24 ሰዎች ሲሞቱ 16 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም።

የግል ትንበያ ተቋም የሆነው " አኩዌዘር " እስከ ትላንት ባለው በእሳት ቃጠሎ የተነሳ የደረሰው ኪሳራ ግምት ከ250 እስከ 275 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ብሏል።

@tikvahethiopia
#AsiyaKelifa🇪🇹

ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ አሲያ ኽሊፋ የ2025 ሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደር ሆና ተመረጠች።

የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ዓመታዊ የስልጠና መርሃ ግብር፣ ከሁዋዌ ታዋቂ የማኅበራዊ ኃላፊነት ስራዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

ይህ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት የ2025 የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደሮችን መርጦ አሳውቋል።

ከተመረጡት 12 አምባሳደሮች መካከል በኢትዮጵያ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ የሆነችው አሲያ ኽሊፋ ትገኛለች።

ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ዓላማውን ያደረገው በዓለም ዙሪያ ያሉ ወጣት ተማሪዎችን በአጭር ጊዜ ስልጠና የዲጂታል ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን አረዳዳቸውን ማሳደግ ነው።

ለዚህም አጫጭር ስልጠናዎችን፣ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እና የተመራቂዎች ማህበር እንቅስቃሴዎች (አልሙናይ) ተሳትፎ እንዲጎለብት ይሰራል።

የባህል ልውውጦች አስፈላጊነት እና የስራ ፈጣሪነት መንፈስ ማዳበር ላይም ትኩረት ያደረገ ሲሆን ከተሳታፊዎች መካከልም ከአንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑትን ሴቶች በማድረግ የተለያዩ ልዩነቶችን ለማስተናገድና ለማካተት ቁርጠኛ ሆኖ ይሰራል።

የአሲያ የአለምአቀፍ አምባሳደር ሆና ለመመረጧ በሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር 2024 ፕሮግራም ስኬታማ ተሳትፎ ማድረጓ አስተዋጻኦ ያደረግ ሲሆን ይሄውም እ.ኤ.አ. በ2025 በቻይና ውስጥ በሚካሄደው የአይሲቲ ታለንት ዲጂታል ጉብኝት በአካል እንድትሳተፍና የተግባር ልምድ እንድታገኝ፣ እንዲሁም በሌሎች ትልልቅ አለም አቀፍ ዝግጅቶች ላይ ተገኝታ የቴክኖሎጂ ተግባራዊ እውቀት እንድትካፈል እድል ይሰጣታል።

የአለምአቀፍ አምባሳደር ፕሮግራም የተቀረጸው የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር እ.ኤ.አ. ከ2008 ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ያሉትን የፕሮግራሙን ተሳታፊዎች ግንኙነት ለማጠናከር ነው።

የፕሮግራሙን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ለማስፋትና የተሳታፊዎች መማማርና ትስስር እድሎችን ለመፍጠር ያተኮረ ነው። ፕሮግራሙ ወጣት መሪዎች የፕሮግራሙን ዋና እሴቶች የሆኑትን ዲጂታላይዜሽን፣ ፈጠራ፣ ስራ ፈጠራ እና ዘላቂነትን እንዲላበሱ ይሰራል።

የአለምአቀፍ አምባሳደሮችን የመምረጥ ሂደት በፕሮግራሙ ድህረ ገጽ በኩል ማመልከቻ በማስገባት የሚጀመር ሲሆን፣ እጩዎች ግንዛቤያቸውን እና አመለካከታቸውን ለመገምገም የታለሙ ስድስት ቃለ መጠይቆች ላይ በመሳተፍ ምላሽ ይሰጣሉ። ከዚያም የዳኞች ቡድን ሁሉንም ማመልከቻዎችና ምላሾች ይገመግማል፣ አመልካቾች ስለ ዓለም አቀፍ አምባሳደር መርሃ ግብር ያላቸው ግንዛቤ፣ የመግባባት ችሎታ፣ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ተሳትፎ እና ለድርጊት ያላቸው ቁርጠኝነት ላይ በመመርኮዝ የእጩዎች መረጣን ያከናውናል።

መረጃው ትምህርት ሚኒስቴር ነው።

#አሲያኽሊፋ 👏 #AsiyaKelifa

@tikvahethiopia
1.ICT Consulting(ICT Infrastructure and Support)
2.Structured Network Cabling (Design/Installation/Documenting & Testing)
3.ICT Infrastructure (Enterprise Grade CCTV, Wireless, Time Attendance)
4.ICT Support (Endpoint Protection)
5.Email Security(SPF/DMARC/DKIM)
6.Business Website Design (Maintenance & Updates | Security & Backups)
7.Visual Branding and Advertising Design (Logo Design | Product Catalog)

Miniapp => http://yangx.top/SeventechSolutionsBot/app
Phone => +251-717-73-23-73
Chat => https://yangx.top/seventechsolutions
🔈 #የተማሪዎችድምጽ

" በዩኒቨርሲቲው አመራር ለደህንነታችን ስጋት ወደ ሆነ አካባቢ ትሄዳላችሁ ተብለናል "- ተማሪዎች

በቁጥር 1,300 አካባቢ ይሆናሉ የተባሉ የደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ከዋናው ግቢ 5 ኪ/ሜ ያህል ርቆ ወደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ትዘዋወራላችሁ መባላቸው ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ የሚዘዋወሩበት ግቢ " በመንግስት እና በታጣቂዎች መካከል አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ የሚደረግበት አካባቢ ነው " ያሉ ሲሆን " በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች እየለቀቁ ባለበት ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው ለደህንነታችን ስጋት ወደ ሆነ አካባቢ ትሄዳላችሁ ብሎናል " ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ ከደብረማርቆስ ከተማ በ5 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በ2015 ዓ/ም ህዳር ወር ጀምሮ ለ7ወር አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ በክልሉ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ከየካቲት 7/2016 ዓም ጀምሮ ተማሪዎቹን ወደ ዋናው ግቢ በማዘዋወር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አደርጎ ነበር።

እስከ አሁን በዋናው ግቢ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት የጤና ተማሪዎች " ከሚመጣው ቅዳሜ 10/05/17 ዓም ጀምሮ ወደ ቀድሞ ግቢ እንደምንዘዋወር ተነግሮናል " ብለዋል።

ተማሪዎቹ ትዘዋወራላቹ የሚል ውሳኔ ከሰሙበት ቀን ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር በተደጋጋሚ ሲጠይቁ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል።

በ 02/05/2017 ዓም የጤና ኮሌጅ ዲን አና ሌሎች የጤና ትምህርት ክፍል ተጠሪዎች በተገኙበት ባደረጉት ስብሰባም " ለሚደርስባቹ የህይወት አደጋ ዩኒቨርሲቲው ምንም አይነት ኃላፊነት አይወስድም እርስ በእርሳቹ ተጠባበቁ አናንተ ስትሄዱ የቦታዉ ሰላም ይረጋገጣል " መባላቸውን ተናግረዋል።

በትላንትናው ዕለት የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት ጨምሮ የሚመለከታቸው የክፍል ተጠሪዎች በተገኙበት በድጋሚ ባደረጉት ስብሰባ ተማሪዎች ውሳኔያቸውን እስከ አርብ እንዲያሳውቁ እና ከቅዳሜ ጀምሮ እንደሚዘዋወሩ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ምን ምላሽ ሰጠ ?

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ስሜ አይጠቀስ ያሉ የዩኒቨርሲቲው አመራር ዝርዝር
ማብራሪያ ጠጥተዋል።


ምን አሉ ?

" እንዲሄዱ የሚደረግው የቦታ ጥበት በመኖሩ ነው ተማሪዎቹ መጀመሪያ ግቢያቸው ይህ አልነበረም ተደርበው ነው ያሉት።

የትምህርት ማቴሪያሎቻቸው በሙሉ እዛ ነው የሚገኙት ዩኒቨርሲቲውም የሚቀበላቸው አዳዲስ ተማሪዎች አሉ ይሄ ሁሉ ተጨማምሮ የመማሪያ ክፍል እጥረት ስላለ እና ጸጥታውም በአንጻራዊነት መሻሻል ስለሚያሳይ ነው እንዲሄዱ የተወሰነው።

ተማሪዎቹ ' እንሂድ ' ብለው ሰኔ ወር ላይ ጠይቀው ነበር እንዲዘገዩ ያደረግነው እኛ ነን በወቅቱ ጸጥታው ይህንን ለማድረግ የማያስችል በመሆኑ አሁን እንሂድ ስንል ነው ቅሬታ የተፈጠረው " ብለዋል።

በአካባቢው በሚታየው የጸጥታ ችግር አካባቢያቸውን የሚለቁ ሰዎች እንዳሉ ተሰምቷል ምን አስተማማኝ የጸጥታ ሁኔታዎች ኖረው ነው ተማሪዎቹ የሚዘዋወሩት ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ አመራሩን ጠይቋል።

እሳቸውም ፦

" አካባቢውን እየለቀቀ ያለ ሰው አለ የሚለው ውሸት ነው የሚለቅ ሰው ሊኖር ይችላል ክረምት እና ከክረምት በፊት በፍርሃት የሚወጡ ነዋሪዎች ነበሩ አሁን ግን ነዋሪውን በአካል አወያይተናል ነዋሪውም መምጣታቸውን ይፈልጋል።

ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ነው ልል አልችልም ካለው ተለዋዋጭ ሁኔታ አንፃር አሁን ያለንበትም ተቋም ቤቱም ሆነ ከተማው ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም ግን የተለየ ስጋት የለም የሚል ድምዳሜ ነው ያለው " ብለዋል።


በዋናው ግቢ ቆይተው ቢማሩ ለደህንነታቸው የበለጠ አስተማማኝ አይሆንም ወይ ? ስንል ጥያቄ አንሰተናል።

" እዚህም ቢሆኑ እዛም ቢሄዱ ችግር የሚመጣ ከሆነ ሊደርስባቸው ይችላል ' ያኛው ግቢ የበለጠ ለአደጋ ተጋላጭ ያደርገናል ' ብለው ቢያስቡ እንኳ በአሁኑ ሰዓት በዋናው ግቢ ትምህርቱን ለማስቀጠል የማያስችሉ ሁኔታዎች አሉ ትምህርቱ እየተጎዳ ስለሆነ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" 16.3 ቢሊዮን ብር ሰብስበናል ! " - ICS

" ባለፋት ስድስት ወራት 10 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅደን ከ16.3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስበናል። ከ721 ሺህ 623 በላይ ፓስፖርቶችን የማተም ስራም ተሰርቷል። ከታተመው 98 በመቶው ለተገልጋዮች ተሰጥቷል " - ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት (የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር) #EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሂጃብሂጃብ #አክሱም

" ተከሳሾች የሰጡት አስተዳደራዊ ትእዛዝ መዝገቡ እልባት እስኪያገኝ ወይም ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥበት ድረስ #እንዳይተገበር ለጊዜው በእግድ እንዲቆይ ታዟል " - ፍርድ ቤት

በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎችን ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ክልከላ አድርገዋል በተባሉት አካላት ላይ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ህጋዊ ክስ መስርቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን ከምክር ቤቱ ጠበቃ አረጋግጧል።

በተመሰረተው ክስ መሰረት ተከሳሾች ለጥር 16/2017 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸው እንዲሰጡ የመጥሪያ ትእዛዝ ተፅፎላቸዋል።

የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት ለተከሳሾች የፃፈው የመጥሪያ ትእዛዝ ሙሉ ይዘት ምን ይላል ?

ከሳሽ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሲሆን ተከሳሾች ደግሞ :- 
የአክሱም ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት
የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 
አብራሃ ወ አፅብሃ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ወርዒ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ክንደያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ናቸው።

በዚሁ ደብዳቤ ላይ ተከሳሾች በወሰኑት አስተዳደራዊ ውሳኔ መሰረት የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን በቀረበቅ ማመልከቻ መረዳት እንደተቻለ ተገልጿል።

ፍርድ ቤቱ ፤ የተሰጠው አስተዳደራዊ ውሳኔ እግድ ካለተጣለበት በሴት ተማሪዎቹ ላይ የማይመለስ የመብት ጥሰት ሊያጋጥም ስለሚችል ተከሳሾች የሰጡት አስተዳደራዊ ትእዛዝ መዝገቡ እልባት እስኪያገኝ ወይም ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥበት ድረስ እንዳይተገበር ለጊዜው በእግድ እንዲቆይ አዟል።

ተከሳሾችም በቀረበው የእግድ ማመልከቻ መሰረት ቀርበው ቃል እንዲሰጡ በፍርድ ቤቱ ለቀን 16/05/2017 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት ተቀጥረዋል።

NB. ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደብዳቤውን ትክክለኝነት ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠበቃ ማረጋገጥ ችሏል።

159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከሂጃብ ክልከላ በተያያዘ ትናንት የተጠናቀቀውን 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን የሚያስችላቸውን ፎርም ሳይሞሉ መቀረታቸውን የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መግለጹ ይታወሳል።

ጉዳዩን እስከመጨረሻውን የምንከታተለው ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ የሰፈር ወሮበላ ነው " - ጠ/ሚ ኤዲ ራማ ከሳምንታት በፊት አልባንያ ውስጥ አንድ የ14 ዓመት ታዳጊ በስለት ተወግቶ መገደሉን ተከትሎ አልባንያ ቲክቶክን ለማገድ ልታስብ እንደምትችል መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤዲ ራማ ሀገራቸው ለ1 ዓመት ቲክቶክን እንደምታግድ ተናግረዋል። ባለፈው ወር የ14 ዓመቱ ታዳጊ ከተገደለ በኋላ ማኅበራዊ ሚዲያ ልጆች ላይ…
#TikTok

' ቲክቶክ ' የተሰኘው መተግበሪያ አልባኒያ ውስጥ ለአንድ አመት እንደሚታገድ መገለጹ ይታወሳል።

" እገዳው በኦንላይ የንግድ ስራ የሚሰሩ / ማርኬቲንግ ላይ ያሉ እንዲሁም የንግግርና ሃሳብ ነጻነት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያመጣል " በሚል የመብት ተሟጋች ነን በሚሉ አካላት እገዳው ቢተችም የሀገሪቱ መንግሥት እገዳውን ተግባራዊ ያደርጋል ተብሏል።

ቲክቶክ በቀጣይ ሳምንታት ይወርዳል ተብሏል።

ሀገሪቱ ' ቲክቶክ 'ን ለማገድ ውሳኔ ያሳለፈችው ከሳምንታት በፊት በኦንላይን በተነሳ ፀብ አንድ የ14 ዓመት ታዳጊ በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተወግቶ መገደሉን ተከትሎ ነው።

በቅርቡ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤዲ ራማ በአልባንያ መዲና ቲራና ከመምህራን፣ ወላጆችና የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ፥ " ቲክቶክ የሰፈር ወሮበላ ነው። ለአንድ ዓመት ቲክቶክ እናግዳለን። ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ዕድገት የሚከታተሉበት አሠራር እንዘረጋለን " ሲሉ ተናግረው ነበር።

" በቻይና ቲክቶክ የሚያገለግለው ለልጆች ትምህርት፣ ለተፈጥሮ ጥበቃና ባህልን ለመጠበቅ ነው። ከቻይና ውጭ ያለው ቲክቶክ ግን ርካሽና አሳሳች ነው። ይሄን ለምን እንፈልጋለን ታዲያ ? " ሲሉም ገልጸው ነበር።

' ቲክቶክ ' የተሰኘው መተግበሪያ ፤ አልጎሪዝሙ ልቅና ሱስ የሚያሲዝ ተድርጎ የተሰራ ፤ ቁጥጥር የሌለው ፤ ለማህበረሰብ ግንኙነት ለልጆች ፣ ወጣቶች ጠንቅ ፤ በቻይና ያለውና በሌላው የተቀረው ዓለም ላይ ያለው ይዘት ልዩነት ያለው በሚል ይተቻል።

አሜሪካ ደግሞ ከቻይና የመረጃ ምንተፋ ጋር በማገናኘት እስከመጨረሻው ድረስ ከሀገሪቱ ለማገድ ጫፍ ደርሳ እግዱን ተግባራዊ የምታደርግበትን ቀን እየጠበቀች ነው።

ባይትዳንስ የተባለው የቲክቶክ ፈጣሪ ድርጅት በተለያየ ጊዜ የሚቀርብበትን ክሶች ሁሉ ውድቅ ሲያደርግ እንደነበር አይዘነጋም።

#TikTok

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

ዛሬውኑ የKimem Itel Pro ስልክ ከሳፋሪኮም ወስደው፣ ክፍያውን ቀስ እያሉ ይክፈሉ። እስከ 3000 ብር ቅድሚያ ክፍያ በመክፈል ቀሪዉን አመቺ በሆኑ የክፍያ አማራጮች እየከፈሉ በ10,747ብር ይግዙት። ለበለጠ መረጃ ወደ 700 ወይም *777*6# ይደዉሉ። እንዳያመልጥዎ!
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://yangx.top/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #1Wedefit #Furtheraheadtogether
EFMA

ድርጅታችን የኢትዮጵያ ፈርኒቸር አምራች ኢንዱስትሪ ማህበር ከተመሰረተ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ በሴክተሩ ሳሱ አምራቾች ድምፅ በመሆን በርካታ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ዓመት መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም. አባለቱ በተገኙበት አራተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን አካሄዷል፡፡

ማህበሩ ዋና ዋና የሚባሉ ፐፈርኒቸር አምራቾችን አባል በማድረግ የሚሰራ ሲሆን በየቀኑም አዳዲስ አባላት ማህበሩን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ ፤ ለእርስዎም በፈርኒቸር እና ተዛማች ስራዎችና ምርቶች ላይ ተሰማርተዉ የሚሰሩ ከሆነ የማህበሩ አባል በመሆን በርካታ ጥቅሞችን ያግኙ፤ የማህበሩን አላና እና ስራዎች ለማየት የማህበሩን ዌብሳይት ይጎብኙ።
https://efma.topbestsimilar.com/
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ዛሬ ጥር 5/2017 ዓ.ም ተፈናቃዮች " ይበቃል ወደ ቄያችን መልሱን ! " በሚል የጀመሩትን ሰላማዊ ሰልፍ የሚደግፍ መግለጫ አውጥተዋል።  " ይበቃል ወደ ቄያችን መልሱን በሚል መሪ ቃል በተፈናቃዮች የተጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ቀናና የሚደገፍ " ብሎታል ጊዚያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው።  " የተፈናቃዮች መከራ ተገቢ ምላሽ አልተሰጠውም " ያለው መግለጫው…
#Update

" ያለፈው ይብቃ አሁን የተጣለባችሁን ሃላፊነት በአስቸኳይ ፈፅሙ " - ተፈናቃዮች

" ይበቃል ! ወደ ቄያችን መልሱን ! " በሚል መቐለ ውስጥ ሲካሄድ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ አበቃ።

ሰልፉ 3 ተከታታይ ቀናት የተካሄደ ሲሆን የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀቀው።

በዚህም ተፈናቃዮች " የፌደራል መንግስት ለፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ታማኝ እና ተገዢ በመሆን ስምምነቱን በሙሉነት እንዲያስፈፅም " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የፕሪቶሪያ የሰላም ውል እንዲፈረም ያሳየው ቁርጠኝነት ተግባራዊ እንዲሆንም ሚናውን ማጉላት አለበት ብለዋል።

ሰልፈኞቹ የትግራይ ክልል የቀድሞ ይዞት በህገመንግስቱ መሰረት ወደነበረበት እስከሚመለስ ሰላማዊ ተቃውሞ ማሰማታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር በተለይ ደግሞ ለሁለት የተሰነጠቁት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ለስልጣን እና ወንበራቸው ሲሯሯጡ የተፈናቃዮች ስቃይ መዘንጋታቸው በምሬት የነቀፉት ሰልፈኞቹ " ያለፈው ይብቃ አሁን የተጣለባችሁ ሃላፊነት በአስቸኳይ ፈፅሙ " በማለት ጥሪ አቅርበዋል ።

" ይበቃል ! ወደ ቄያችን መልሱን ! " ሰላማዊ የተቃውሞ ስልፍ ተሳታፊዎች ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፣ ለህወሓት እንዲሁም በክልሉ ለሚገኙ የተለያዩ የተባበሩት መንግስት የእርዳታ ድርጅቶች የአቋም መግለጫቸው አድርሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMeKelle

@tikvahethiopia