TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Somalia ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የ #AUSSOM ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳወቀ። በመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሶማሊያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጉ ተነግሯል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሰራጨው መረጃ ፥ የልዑካን ቡድኑ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ማህሙድ ጋር ውጤታማ ውይይት…
#Ethiopia 🤝 #Somalia
በሶማሊያ በሁለትዮሽ ስምምነት መሠረት ተሰማርቶ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሁኔታን በተመለከተ አሠራር ለመዘርጋት የሁለቱ አገራት የጦር አዛዦች ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
በኢትዮጵያው መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና በሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ኃይሎች የመከላከያ ሠራዊት አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ኦዳዋ ዩሱፍ ራጌ መካከል የተደረሰው ስምምነት በሶማሊያ ያለው የኢትዮጵያ ጦር ስምሪትን፣ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም አጠቃላይ ክንዋኔዎች የሚመለከተውን 'ስታተስ ኦፍ ፎርስ አግሪመንት' ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ነው።
አንዲት አገር ጦሯን በሌላ ውጭ አገር በምታሰማራበት ወቅት የጦሩ ስምሪት፣ ተግባራት፣ ኃላፊነት፣ መብቶችን የሚመለከተው በአገራቱ መካከል የሚደረስ አሳሪ (ሕጋዊ ስምምነት) ስታተስ ኦፍ ፎርስ አግሪመንት ይሰኛል።
ይህ 'ስታተስ ኦፍ ፎርስ' ስምምነት በአውሮፓውያኑ 2023 በአገራቱ መካከል የተፈረመው የመከላከያ ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ዋና አካል እንደሚሆን ተነግሯል።
በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሚመራ ልዑክ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ የካቲት 15/2017 ዓ.ም. ባደረገው የአንድ ቀን ይፋዊ ጉብኝት ይህንን ስምምነት ጨምሮ ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በሶማሊያ እና በቀጠናው ሰላም፣ ደኅንነት፣ ፀጥታ እና የመረጋጋት ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ሁለቱ የጦር አዛዦች የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (ኤዩሶም) ጅማሮ አድንቀው ከዚህ ቀደም በነበረው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት አትሚስ ስኬቶች ማስቀጠል አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በኤዩሶም ስምሪት ላይ እንዲካተት የጦር አዛዦቹ በዚህ ወቅት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።
በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ውዝግብ በአንካራ ስምምነት መፈታቱን ተከትሎ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮችን በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ (ኤዩሶም) ውስጥ ላለማካተት አሳልፋው የነበረውን ውሳኔ ልትቀለብስ እና በተልዕኮው ለማካተት እያጤነች እንደሆነ ከዚህ ቀደም ተዘግቦ ነበር።
#SomaliaNationalTV #BBCAMAHRIC
@tikvahethiopia

#Ethiopia #Somalia
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ረፋድ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።
ሁለቱ ሀገራት ገብተውበት ከነበረው የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ውጥረት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑ ነው።
የሶማሊያው ፕሬዚደንት ሐሰን ሼክ መሐሙድም ቱርክ ሁለቱን ሀገራት አንካራ ላይ ካስማማች በኋላ ባለፈው ጥር 3 ቀን አዲስ አበባን ጎብኝተዋል።
አስከትለውም በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ታድመው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተነጋግረዋል።
በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በጋራ በወጣው መግለጫ " ይህ ጉብኝት ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ የተደረጉ ተከታታይ ግንኙነቶችን የተከተለ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነትም ወደ መደበኛ ሁኔታ የሚመልስ ነው " ብሏል።
ሁለቱ መሪዎች ለጋራ ጥቅም ትብብራቸውን ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን ስለማረጋገጣቸው እና በዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትብብር " መተማመንን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል " ተብሏል።
የዚህ ጉብኝት እንደምታን በሚመለከት ቃላቸውን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ የሰጡት ፤ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት የአፍሪካ ጉዳዮች የሥራ ክፍል ኃላፊ እና ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ግዛቸው አስራት ፥ ሁለቱ ሀገራት መተማመን በሚያስችል ሁኔታ መነጋገር የሚችሉበት ዕድል እንደሚሆን ገልፀዋል።
" የቴክኒክ ቡድኑ (የአንካራ ስምምነት) ከሁለት ሳምንት በፊት አንካራ ላይ ተገናኝቶ ሲነጋገር ተመልክተናል። መስማማቶች እና መግባባቶች ላይ የደረሱበት፣ መተማመን በሚያስችል ሁኔታ ንግግሮች እያደረጉ ያሉበት ሂደት ነው " ብለዋል።
" የቱርክ መንግሥት አካባቢውን ካላስፈላጊ ውጥረት ታድጓል " ያሉት ተመራማሪው እንዲህ ያሉ መልካም ልምዶች በዚህ ቀጣና ብዙም አይታዩም ብለዋል። ይህን መሳይ የውይይት፣ የድርድር እና የሰላም መንገዶች ሲታዩ ማመስገን ያስፈልጋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጋራ ጥቅሞችን በማሳደግ፣ ሰላምና ደህንነትን በማስፈን እና የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በማጠናከር ለዜጎቻቸውና ለሰፊው የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውም ጉብኝቱን ተከትሎ በወጣው የጋራ መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።
ዶክተር ግዛቸው አስራት " ቀጣናዊ ትብብርን " የተመለከቱ ውይይቶች እንደሚኖሩ ገልፀዋል።
የዛሬውን ጉብኝት በሚመለከት አስቀድመው የወጡ ዘገባዎች ሞቃዲሾ ውስጥ ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ መደረጉን ያመለክታሉ። #DW
@TIKVAHETHIOPIA