TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ጥምቀት

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ! በዓሉ በደስትና በረከት የተሞላ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

መልካም የጥምቀት በዓል !

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ፈጣሪ ይጠብቀን እንጂ የዛሬውስ እጅግ ያስፈራ ነበር " - ነዋሪዎች

ለሊት ከ8:46-8:48 ባለው ጊዜ ከወትሮ የተለየ በርካታ ሰዎችን ከተኙበት ጥንልቅ እንቅልፍ ሁሉ ሳይቀር የቀሰቀሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

እስካሁን ባለው መጠኑን  የዓለም አቀፍ ተቋማት ከ5.0 - 5.3 በሬክተር ስኬል መዝግበውታል።

የጀርመን ጂኦ ሳይንስ ጥናትና ምርምር ማዕከል መንቀጥቀጡ ከጭሮ ሰሜን ምዕራብ 60 ኪሎሜትር ላይ የተከሰተ ነው ብሏል።

የአሜሪካው ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ደግሞ ቦታውን በተመሳሳይ ገልጾ መጠኑ በሬክተር ስኬል 5.3 ነው ሲል አመልክቷል።

በርካታ አፋርና አካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች መልዕክታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።

" አላህ ይጠብቀን ምን አይነት አስፈሪ መንቀጥቀጥ እንደነበር በቦታው ያለ ሰው ብቻ ያውቀዋል " ሲል አንድ የቤተሰባችን አባል ክስተቱን ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከሌሎች በርካታ ከተሞችም ከቤተሰቦቹ መልዕክቶችን እየተቀበለ ይገኛል።

ንዝረት ከነበረባቸው ከተሞች መካከል አዲስ አበባ እና አካባቢዋ ዋነኞቹ ናቸው።

የሽሮ ሜዳ፣ ጎሮ፣ ፊሊዶሮ፣ ፓስተር ፓውሎስ ሆስፒታል፣ አባዶ፣ አያት ፣ ጀሞ፣ ሰፈራ፣ ጋርመንት ፣ ፈንሳይ፣ ሰሚት ፣ ባልደራስ ፣ ገርጂ፣ ኮዬ ፈጬ፣ ላፍቶ፣ ሰሜን ማዘጋጃ ፣ ቱሉ ዲምቱ፣ ኮዬ ፈጬ ... ሌሎችም አብዛኛው የአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ሰፈሮች የሚኖሩ ነዋሪዎች ንዝረቱ ከፍ ብሎ ተሰምቷቸዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል 5ኛ ፎቅ ላይ እንደምትኖር ገልጻ " እጅግ ያስፈራ ነበር የዛሬው ከሁሉም ነው የተለየብኝ ህንፃው ተደረመሰ እያልኩ ነው ያለፈው " ብላለች።

ሌላኛው ፤ " ፈጣሪ ይጠብቀን እንጂ የዛሬው ያስፈራ ነበር። እኔ አልጋው እየተነቃነቀ መስሎኝም ነበር ከዚህ በፊት እንዲህ ተሰምቶኝ አያውቅም በድንገት መሆኑ ደሞ ሁላችንንም አስፈርቶ ነበር " ብሏል።

ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል ደሞ ፥ " እኔን ጨምሮ ሁሉም ቤት ውስጥ ያለነው ተነስተን ቁጭ ለማለት ተገደናል ፤ እንዲህ ተሰምቶን ስለማያውቅ ተደናግጠናል በተለይ የህንፃው ከፍተኛው ወለል ላይ ስሜቱ ያስታውቅ ነበር " ብሏል።

ምንም እንኳን የዓለም አቀፍ ተቋማት መጠኑን ከ5. 0 እስከ 5.3 በሬክተር ስኬል ቢመዘግቡትም ስሜቱ ግን ከወትሮ የተለየና ጠንካራ ነበር።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
መልካም የዐቢይ ጾም !

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለውድ ቤተሰቦቹና ለመላ ምዕመናን መልካም የዐቢይ ጾም እንዲሆን ይመኛል።

ጾሙ የፈጣሪን በረከት ፣ ዕርቅ ፣ ምህረት ፤ ለመላው ሀገራችን ፍጹም ሰላምና ዘላቂ መረጋጋትን የሚያመጣ እንዲሆን ከልብ ይመኛል።

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጾመ ኢያሱስ ሱባዔ (ዐቢይ ጾም) መልዕክት የተወሰደ ፦

" ከጌታችን ጾም የምንወስደው ብዙ ትምህርት አለ ፤ ከሁሉ በፊት ሰው በሕይወት መኖር የሚችለው በእንጀራ ብቻ ኣይደለም ብሎናል።

ይህ ኣባባል በሕይወት ለመኖር እንጀራ አያስፈልግም ማለት ኣይደለም፤ ሕይወትን ማኖር የሚቻለው በእንጀራ ብቻ እንደ ሆነ አድርገን እንዳናስብ ግን ቃሉ ያስተምራል ፤ ይህም በዓለማችን በየዕለቱ የምናውቀው ሓቅ ነው፤ ብዙ ሰዎች እንጀራን ሳያጡ በየዕለቱ ሕይወትን ያጣሉ፤ ምክንያቱም በሕይወት ለመኖር የእግዚአብሔር ቃልም እንጂ እንጀራ ብቻው በቂ አይደለምና ነው።

ዓለማት ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ሁኑ ተብለው በቃሉ እንደተፈጠሩ፤ በቃሉም ጸንተው እንደሚኖሩ ኋላም በቃሉ እንደሚያልፉ ሁሉ የሰው ሕይወትም በዚህ ቃል ይወሰናል።

እንጀራ ኖረም አልኖረ ቃሉ በቃ ካለ ያበቃል ፤ ኑር ካለ ደግሞ እንጀራ ባይኖርም ይኖራል፤ ስለዚህ በሕይወታችን ወሳኝ ሥልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል እንጂ፣ እንጀራ ብቻ ኣለመሆኑ ጌታችን በዚህ ኣስተምሮናል።

ጾመ ኢየሱስ እያልን በየዓመቱ የምንጾመው የታላቁ ጾማችን ዓላማ ዲያብሎስን ለማሸነፍ ነው፤ የዲያብሎስ ማሸነፊያ ስልት የመልካም ኅሊና ልዕልና ነው። "

መልካም የዐቢይ ጾም !

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia