TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🔴 “  100 ብር ከተበጀተ በኋላ ከቀረበልን ይልቅ የበፊቱ ምግብ ጥራት አለው ” - የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች

🔵 “ እንደ እውነቱ ከሆነ በ100 ብር በተሰጠው የምግብ ዝርዝር መሰረት ለማስተናገድ የማንችልበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው ” - ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ

በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ከአዲሱ የምግብ ሜኑ ጋር በተያያዘ የምግብ ጥራት ፣ የኮስት ሸሪንግ ጉዳይ ለይ ቅሬታ እንዳላቸው በመግለጽ፣ የሚመለከታቸው አካላት መመሪያውን በድጋሚ እንዲያጤኑት ጠይቀዋል።

በአዲሱ የምግብ ሜኑ መሰረት ከቀረላቸው ምግብ ይልቅ የድሮው ጥራት እንደነበረው አስረድተው፣ ማስተካከያ ካልተደረገበት ትርፉ ከፍተኛ ኮስት ሸሪንግ/ የወጪ መጋራት እዳ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት በበኩሉ፣ ከምግብ ሜኑው ትግበራ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እያቀረቡ ያሉት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሆኑ፣ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለዚህ ተጠቃሽ እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከደባርቅ ዩኒቨርቲ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አካልን ያነጋገረ ሲሆን፣ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጠተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በሰጠው ማብራሪያ ምን አለ ?

" መንግስት የተማሪ በጀት ከ22 ነበር ወደ 100 ብር ማሳደጉ ይታወቃል። 22 ብር እያለ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውንም ሌላም በጀት አጣበው እየደጎሙ አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።

ከሌላ በጀት እየተነሳ፣ እየተዘዋወረ አገልግሎት ከመስጠት ለራሱ ወጥ የሆነ የመንግስትንም ያገናዘበ የሀገሪቱን አቅም ያገናዘበ፣ በምግብ ጥራት ሊመጥን የሚችል (አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር እንዴት እንዳጠናው ባናውቅም) ብር መድቧል። 

በ100 ብር ምን መመገብ ይቻላል ? የምግብ ዓይነቱስ ምን ቢሆን ? ብሎ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ኮሚቴ ተዋቅሮ የአካባቢውን ግብዓት መሰረት ባደረገ አሰራር ዩኒቨርሲቲዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ብሎ ለአንድ ተማሪ ምን ያክል ምስር፣ ክክ፣ እንጀራ፣ ዳቦ ያስፈልጋል ብሎ የምግብ ዝርዝር ቋሚ በሆነ መልኩ አቅርቦልናል።

ለኛ የተሰጠን ስራ ግራሙን መቀየር አይደለም። ዝርዝሮቹ 10 ቢሆኑ (ለምሳሌ አዲስ አበባ፣ ደባርቅ፣ መቐለ፣ ደብረ ብርሃን የሚገኝ ሌላም) አንድ ላይሆን ስለሚችል ያን መሰረት አድርገን አገልግሎት እንሰጣለን ”
ብሏል።

ስለተማሪዎቹ ቅሬታ ዩኒቨርሲቲው ምን አለ?

“ ተማሪዎች  ‘በዚህ አንስማማም የተሰጠው የምግብ ዝርዝር የጥራት ችግር ያመጣል’ የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ነገር ግን ስራውን ከመጀመራችን ከ4 ቀን በፊት ከተማሪዎች ጋር ውይይት አድርገን መግባባት ላይ ደርሰን ነበር።

ተማሪዎቹ ጥያቄ ካላቸው በኀብረቶቻቸው አማካኝነት እንዲያቀርቡልን፣ እኛም ቀጥታ ከትምህርትና ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ጥያቄ ካለን በሰላማዊ መልኩ አቅርበን የተሻለ አገልግሎት መስጠት አለብን በማለት ተስማምተን ነው ወደ ስራ የገባነው።

ተማሪዎቹ ‘ምግቡ ድሮ 22 ብር እያለ የተሻለ የሚመስል ነገር ነበረው። ስለዚህ በጀቱ ሲጨምር የምግብ ጥራቱም በዛው ልክ መጨመር አለበት’ የሚል አመለካከት አላቸው።

እኛ ደግሞ የምግብ ጥራቱን የማንጨምርበት ምክንያት መጀመሪያም አሁን ከተመደበው በጀት እኩል/ አንዳንዴም እንደ ወቅቱ የገበያና የፀጥታ ሁኔታ እላፊ ሊሆን ይችላል እንጂ በ22 ብር ብቻ አልነበረም ሲመገቡ የነበረው።

ለምሳሌ ፦ ተማሪዎቻችንን ስንመግብ የነበረው እንጀራ በ23 ብር እየገዛን ነበር። ስለዚህ 22 ብር ብቻ በቂ አልነበረም። በተዘዋዋሪ ተማሪዎቻችን ይህን ያውቁታል። እንዲያው አመፅ ለማስነሳት ምክንያት ፈልገው ካልሆነ በስተቀር።

ሌላው ጥያቄያቸው ‘አሁን የተመደበው 100 ብር ቀጥታ ኮስት ሸሪንግ ላይ ነው የሚያርፈው’ የሚል ሲሆን፣ ይህ ከእኛ አቅም በላይ ነው። ስለዚህ ጥያቄውን ይዘን ለሚመለከተው አካል እናቀርባለን።

ነገር ግን መንግስት ‘የምግብን ኮስት ሸሪንግ ተማሪው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል’ ካለ አለ ነው። በተዘዋዋሪ 100ም ሆነ 1000 የተጠቀመውን ያክል ነው የሚከፍለው። 

የተማሪዎቹ ጥያቄ ‘ከመጣው ዝርዝር አንፃር የምግብ ጥራቱ በጣም ያንሳል’ የሚል ስለሆነ የምግብ ጥራቱ ይጨምር ከተባለም፣ በእኛ ዩኒቨርሲቲ analysis ሰርተናል። ከዝርዝሩ ውስጥ በርበሬና የሻይ ቅመም አልተካተተም።

የበርበሬና የሻይ ቅመም እንኳን ሳናስገባ ራሱ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅቶ በሰጠን መመሪያ ዋጋ ሽንኩርት ፣ ዳቦ፣ እንጀራ፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ጨው የመሳሰሉትን ግብዓቶች ለአንድ ተማሪ የገዛንበትን ዋጋ ስንሰራው 115 ብር እስከ 120 ብር ይመጣል ስለዚህ ከተማሪው በላይ ለኛ ነው ጥያቄ የሆነብን።

አንደ እውነቱ ከሆነ በ100 ብር በተሰጠው የምግብ ዝርዝር መሰረት ለማስተናገድ የማንችልበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው።

ይህ ዋጋ የተሰራው አሁን ባለንበት የገበያ ሁኔታ ሲሆን፣ ነገ ሊጨምርም ይችላል። እንኳን ኦቨር ጥራት ተማሪዎች እንደሚጠይቁት ልናደርግ በ100 ብር አጣጥመን ስናስበው ጨረታ በሰጠናቸው ውል በያዝንባቸው ከ100 ብር በላይ ነው የሚመጣው። ይህን በሰነድ ማረጋገጥ ይቻላል።

ስለዚህ በ100 ብሯ ግዴታ አብቃቅተን ማስተናገድ ይጠበቅብናል። ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ዊዝድሮውም፣ ሌላም መረጃ አለ ያንን መሰረት አድርገን ኦዲት እናደርጋለን። በዚህ መሰረት ብሩን ከፍ እናደርጋለን ቁጥጥራችን ከፍ ይላል። 

ለኛም አስጨናቂ ነው የሆነብን ተማሪው ‘አልፈልገውም’ ያለው የምግብ ዝርዝር ራሱ ከተሰጠን በጀት በላይ ነው። ስለዚህ የግንዛቤ ፈጠራዉ እንደ ሀገር አቀፍ አስተያየትም ስላልተሰጠበት ለኛ ፈተና የሆነብን ነገር ይሄ ነው።

ለጊዜው በድሮው የምግብ ዝርዝር ነው እየተጠቀምን ያለነው። እንደኛ ዩኒቨርስቲ ተጨባጭ ጥያቄ ‘አዲሱን አትጀምሩት በድሮው ይቀጥልልን’ የሚል ነው ከተማሪዎቹ የተነሳው።

ለዚህ ደግሞ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች ለስራ ጉዳይ አዲስ አበባ ነው  ያሉት ትምህርት ሚኒስቴር ጠርቷቸው። እናም ይህንን ጉዳይ ያነሱታል ብዬ አስባለሁ። 

ይህ ጉዳይ በብዙ አቅጣጫ ቢታይ ዝም ተብሎ አንድ ወገን ላይ ብቻ ጣት የሚቀሰርበት አይደለም። አሁን ላይ ተማሪው የምግብ ጥራት ይልና ኮስት ሸሪንግንም ያነሳል።

‘የምከፍል ከሆነ የምግብ ጥራቱ መጨመር አለበት ነው’ ነጥቡ። እኛ ደግሞ በ100  ብር አስተናግዱ ሲባል እንደ ምግብ ዝርዝሩ 100 ብሩ አያሰራንም አይበቃንም እያልን ነው ያለነው ” ብሏል።


መፍትሄውን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው ምን አለ ?

መንግስት የሰጠው ሜኑ አለ። ተማሪዎች ጥያቄ ካላቸው በሰላማዊ መልኩ ከዩኒቨርሲቲው ማኔጅመን፣ ከተማሪዎች ኀብረት ጋር በመሆን ጥያቄ አቅርቦ መግባባት ላይ መድረስ ነው። 

መግባባት ላይ ከተደረሰ ይህንንም ሊቀበሉ ይችላሉ። መንግስተም ኮንሲደር የሚያደርገው ነገር ሊኖር ይችላል። ስለዚህ የመንግስትን ሀሳብ በጉልበት ከመግፋት ተወያይቶ ጥያቄው ቢፈታ መልካም ነው።

ንብረት እያወደሙ፣ ትምህርት እያቋረጡ ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ በተወካዮቻቸው አማካኝተት ጥያቄያቸዌን አቅርበው ውይይት ይደረግበት ”
ሲል አስገንዝቧል።

(የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችን አስተያዬትና የትምህርት ሚኒስቴርን ምላሽ ለማካተት የተደረገው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፣ ፈቃደኞች ከሆኑ በቀጣይ እናቀርባለን)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

💥 የBoxing Day ፍልሚያዎች ዛሬ ይደረጋሉ!

የሊጉ መሪ ሊቨርፑል የነጥብ ልዩነቱን ያሰፋል ወይስ ቼልሲ፥ አርሰናልና ማን ሲቲ ልዩነቱን ያጠቡታል?

ያጓጓል!

👉እነዚህን ድንቅ ፍልሚያዎች ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ 11 ሰዎች አሁንም ያሉበት አልታወቀም። አንድ ሰው መገደሉ ተረጋግጧል ” -የሽርካ ወረዳ ቤተ ክኀነት በአርሲ ዞን፤ ሽርካ ወረዳ በታጣቂዎች ታገቱ የተባሉ በርካታ ነዋሪዎች ያሉበት እንደማይታወቅ የወረዳው ቤተ ክኀነትና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። የአካቢው ነዋሪዎች፣ “ ታጣቂዎቹ እገታውን የፈጸሙት ታኃሳስ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ/ም ነው። ከ20 በላይ ሰዎች ናቸው በታጣቂዎች…
#Update

“ ሰውኮ በየሰብሉ ውስጥ እየተገደለ እየተገኘ ነው። አንድ ሰው አስቀርተዋል። 10 ሰዎች ገንዘብ ከፍለው ተለቀዋል ” - የሽርካ ወረዳ ቤተ ክኀነት

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ ታኀሳስ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ/ም 20 ኦርቶዶክሰዊያን በታጣቂዎች እንደታገቱ፣ ከ80 በላይ ከብቶችም እየተነዱ እንደተወሰዱ ነዋሪዎችና የወረዳው ቤተ ክኀነት መግለጻቸው ይታወሳል።

ከእገታው በኋላ የወረዳ ቤተ ክኀነት ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ 9 ሰዎች ገንዘብ ከፍለው ተለቀዋል ተብሎ ነበር።

ከወረዳው ቤተ ክኀነት ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ አካል ከቀናት በፊት፣ “ አንድ ሰው መገደሉ ተረጋግጧል። 11 ሰዎች ያሉበት አይታወቅም ” ብለውን ነበር።

ያሉበት እንዳልታወቀ የተነገረላቸው ታጋቾች ተለቀቁ ?

ታጣቂዎቹ አንድ ሰው አስቀርተው አስሩን ታጋቾች ገንዘብ አስፍለው ከቀናት በፊት እንደለቀቋቸው የወረዳው ቤተ ክኀነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

“ ሰውኮ በየሰብሉ እየተገደለ እየተገኘ ነው ያለው። አንድ ሰው አስቀርተዋል። 10 ሰዎች ገንዘብ ፍለው ተለቀዋል ” ብሎ፣ “ ሌላም ሴት አዝመራ/ሰብል ውስጥ ተገድላለች ” በማለት ከታገቱት ውጪም ያሉት ላይ ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑን አስረድቷል።

“ ከታገቱት 20 ሰዎች መካከልም አንድ ሰው ገድለዋል። አንድ ሰው አስቀርተዋል። ሌላው አስፈላጊውን ገንዘብ ከፍሎ ተለቋል ” ሲልም  ገልጿል።

ችግሩ እየተደጋገመ የመጣ ነውና መፍትሄው ምንድነው ? ለሚለው ጥያቄ የወረዳው ቤተ ክኅነት ምላሽ፣ “ መልዕክት አስተላልፈን አስተላልፈን አቆቶናል ” የሚል ነው።

“ አሁንም መፍትሄ አልተገኘም። ዞሮ ዞሮ ጉዳዩ በጣም ስር የሰደደ ነው። መንግስትና የጸጥታ አካላት ይኖሩበታልና ያ ሁሉ ካልጠራ ችግሩ ሊጠፋ አይችልም ” ሲል የችግሩን ውስብስብነትና አሳሳቢነት አስረድቷል።

“ ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ እዚሁ ላይ ቢሰራና ህዝቡም ራሱን የሚከላከልበት ሞራል የሚሰጠው አካል ቢያገኝ ነው ከዚህ ችግር መውጣት የሚቻለው ” ሲልም አክሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ግብር #ተሽከርካሪዎች የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከተሽከርካሪ አስመጪዎች ለቀረበበት ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጠው ሙሉ ምላሽ ምንድን ነው? " አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ ያሉ ዋና ዋና የሚባሉ የታክስ ስወራ አለባቸው የሚባሉ ዘርፎች ተለይተው ጥናት ተደርጓል፡፡ አንዱ ከቋሚ ንብረት፣ ከቤት፣ ከሪልስቴት ጋር ሽያጭ ጋር፣ ሌላው ደግሞ ከመኪና ጋር የተገናኘ ጥናት…
#Update

🔴 “ በቡድንም ሆነው ቅሬታ እያቀረቡ ያሉ አሉ። ‘ፌደራል ጋር ስንሄድ እኔ ይህንን ጉዳይ አላወረድኩም ነው’ የሚለን ” - ተሽከርካሪ አስመጪዎች

🔵 “ ክልሎችን እንዲህ አድርጉ፣ እንዲህ አታድርጉ ብሎ ቀጥታ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እነርሱን የማዘዝ ስልጣን የለውም ” - ገቢዎች ሚኒስቴር

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ተሽከርከሪ አስመጪዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ባወረደው የደብዳቤ መመሪያ ከአቅም በላይ ግብር እየጠየቃቸው መሆኑን በተመለከተ ያደረባቸውን ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

አስመጪዎቹ፣ “ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውርዶ ከአቅማችን በላይ ግብር እየጠየቀን ነው ” ነበር ያሉት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ በወቅቱ ምላሽ የጠየቃቸው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ፣ መመሪያው የግብር ስወራን ለማስቀረት እንደወረደ፣ ይህን ማድረግም የቢሮው ማንዴት መሆኑን የሚመለከት ምላሽ ሰጥተውን ነበር።

“ ግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው ” በማለት ኃላፊው የሰጡትን ዝርዝር ማብራሪያም ማቅረባችን ይታወቃል።

አስመጪዎቹ በበኩላቸው፣ “ በቡድንም ሆነው ይህን ቅሬታ እያቀረቡ ያሉ አሉ። ፌደራል ጋር ስንሄድ 'እኔ ይህንን ጉዳይ አላወረድኩም ነው' የሚለን” ብለው ስለጉዳዩ ገቢዎች ሚኒስቴር እንዲጠየቅ አሳስበዋል።

“ ለምሳሌ የአዲስ አበባ አስመጪና የክልል አስመጪ ተመሳሳይ መኪና አምጥተው ቢሸጡ። የአዲስ አበባው 45% ግብር እየከፈለ ያኛው በድሮው በ5% ይከፍላል። ይሄ ትልቅ ልዩነት ነው የሚያመጣው ” በማለት ያለውን ሰፊ ልዩነት ሚኒስቴሩ እንዲያጤንላቸው ጠይቀዋል።

አስመጪዎቹ ተመሳሳይ ተሽከርካሪ እያመጡ እያለ አዲሱ መመሪያ የሚጠየቁት ግብር ግን አዲስ አበባ ውጪ ካሉት አስመጪዎች ስለሚለያይ መመሪያውን ገቢዎች ሚኒስቴር ያውቀው እንደሆን እንዲጠየቅላቸው መጠየቃቸውን በመግለጽ፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሚኒስቴሩን ማብራሪያ ጠይቋል።

ተሽከርካሪ አስመጪዎቹ “ ተመሳሳይ ፕሮዳክት እየመጣ እንዴት የተለያዬ ክፍያ ይኖራል ? ” የሚል ጥያቄ አላቸው፤ ቢሮው በበኩሉ የታክስ ስወራ ለማስቀረት መመሪያውን እንዳወረደና ይህን የማድረግ ማንደቱ እንዳለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፣ ማንዴቱ ለቢሮው የተሰጠ ነው ? የሚል ጥያቄ አቅርበናል።

የተሰጠው ምላሽስ ምንድን ነው ?

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው አንድ የኮሚዩኒኬሽን አካል ተከታዩን ቃል ሰጥተዋል።

“ የክልልን እና የሚኒስቴሩን ስልጣን ያስቀመጠው ህገ መንግስቱ ነው።  የሚሉትን መመሪያውንም አላወኩትም።

እነኛን መመሪያዎች ማዬት ይጠይቃል። ክልሎችን እንዲህ አድርጉ፣ እንዲህ አታድርጉ ብሎ ቀጥታ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እነርሱን የማዘዝ ስልጣን የለውም።

የጋራ መድረክ አለን። በእዛ የጋራ መድረክ ላይ አሰራራችሁ እንዴት ነው ? የማለት እንጂ በፌደራል ስርዓት የፌደራል መስሪያ ቤት የክልል መስሪያ ቤቶችን እንደዚህና እንደዛ አድርጉ ብሎ የማዘዝ ስልጣን የለውም።

የውይይት የጋራ መድረክ አለን። የክልል ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ጉዳዩን ከእነርሱ ጋር እንዲነጋርና ያሉት ጉዳይ ላይ ምንድን ነው ያለው ? አስተካክሉ የሚል የጋራ መድረክ ስላለን እዛም ላይ አንስቶ በግልም ሂዶ ሊነጋገርበት ይችላል።

መመሪያ ቁጥሩን ላኩልን። ከክልል ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ጋር እንንነጋገርበታለንና የአዲስ አበባዎች ጋር እንወያያለን። 

የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የራሳቸው ስለሆኑ፣ ግን ይሄ የተጣጣመ እንዲሆን ይሄ ቢሆን ብሎ መነጋገር ይቻላል። በዛ አግባብ ልንነጋገር እንችላን። በአዛዥና በታዛዥነት መንፈስ ሳይሆን ማለት ነው ”
ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የቅሬታ ነጥቡ መመሪያው አዲስ አበባ ያሉ ስመጪዎችን የሚጠይቀው ግብር ከአዲስ አበባ ውጪ ካሉት ተመሳሳይ ተሽከርካሪ ከሚያመጡት ጋር ሲነጻጸር ጭማሪ ያለው መሆኑ ነው፤ ሚኒስቴሩ የሚጥለው የግብር መጠን አንድ መሆን የለበትም ወይ ? የአዲስ አበባ ከተማ ብቻ የተለዬ መሆን አለበት ? የሚል ጥያቄ አቅርቧል።

እኝሁ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አካል፣ “መመሪያውን ቢለኩልንና ከእነርሱ ጋር ብንነጋገርበት ይቻላል” የሚል ምላሽ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

አስመጪዎቹ በደብዳቤ መልክ ወርዷል ያሉትን መመሪያ ከላክንላቸው በኋላ በሰጡን ምላሽ ደግሞ፣ “ መሄድ ያለብንን እንሄዳለን እንጂ ለህዝብ አሁን እንዲህ ነው እያልን ምላሽ አንሰጥም በዚህ ላይ። ለማንኛውም አየዋለሁ የሚሆነውን እናደርጋለን ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EHRC #EHRDC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ማዕከል በኢፌድሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ታግደዋል።

ስለ እግዱ ኢሰመጉ ምን አለ ?

ላለፉት 33 አመታት በሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ፥ ዲሞክራሲ እንዲስፍን እና የህግ የበላይነት እንዲከበር ከፍተኛ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ አንጋፋ ድርጅት እንደሆነ ገልጿል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሠልጣን ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም የተጻፈ ደብዳቤ በቀን ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ/ም ድርጅቱ በደረሰው መሰረት እገዳ እንደተጣለበት አመልክቷል።

ምክንያት የተባለው ምንድነው ?

ለኢሰመጉ መታገድ ምክንያት የተባለው ፤
° ከተቋቋመለት አላማ ውጪ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ፤
° ገለልተኛ እንዳልሆነ፤
° በ2023 የበጀት አመት የአስተዳደር ወጭ ገደብ ጠብቆ ባለመስራቱና ኃላፊነት በጎደለው መልኩ እየተንቀሳቀሰ ነው በሚል ነው ድርጅቱን ከማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ የታገደው።

ሆኖም ዕግዱን ተከትሎ ኢሰመጉ በጉዳዩ ላይ ለማንኛውም መገናኛ ብዙሃን የሰጠው መግለጫ የለም።

ኢሰመጉ ፤ ሁሌም ቢሆን ሕግና ስርዓትን ጠብቆ የሚንቀሳቀስ ነፃና ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ድርጅት መሆኑን ገልጾ በአሁኑ ሰዓት ዕግዱ በሚነሳበት ሁኔታ ላይ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በመነጋገር ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በዚህም ምንም አይነት መግለጫ የማውጣት ሃሳብ አልነበረውም።

ሆኖም ግን በማህበራዊ ድረገጽ ኢሰመጉ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በማድረጉ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች እንደታገደ የሚገልጹ ጽሁፎች እየተንሽራሽሩ በመሆናቸው መግለጫ ለማውጣት መገደዱን አመልክቷል።

ድርጅቱ በማሀበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተንሽራሸሩ የሚገኙት ሃሳቦች በባለስልጣኑ ስለዕግዱ ከተሰጡት ምክንያቶች ጋር ፈጽሞ የማይገናኙ የኢሰመጉን ዓላማና ተግበር የማይወክሉ እና መልካም ስራውን ለማጥፋት የሚደረጉ ሙከራዎች ናቸው ብሏቸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ምን አለ ?

ባለፉት አራት አመታት ድርጅቱ በርካታ ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየ መሆኑን በዋነኝነት ለበርካታ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት እና የውትወታ (advocacy) ስራዎችን ሲያከናውን እንደቆየ ገልጿል።

ድርጅቱ የተቋቋመለትን አላማ ሊያሳካ በሚያስችል መልኩ የአገሪቱን ህጎች ባከበረና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ እንደ አንድ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሲንቀሳቀስ የቆየ መሆኑን ጠቁሟል።

ይሁንና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን መስሪያ ቤት በፃፈው ደብዳቤ ድርጅቱ ከማንኛውም እንቅስቃሴዎች እገዳ የተጣለበት መሆኑን ገልጿል።

ምክንያት ?

" ባለስልጣኑ በድርጅቱ ላይ ባደረገው የክትትልና ግምገማ ስራዎች ድርጅቱ ከተቋቋመበት አላማ ውጭ መንቀሳቀሱ፣ ገለልተኛ አለመሆኑ፣ ግልፅ የሆነ የአደረጃጀት መዋቅር የሌለው መሆኑ እና ሃላፊነት በጎደለው መልኩ የተንቀሳቀሰ መሆኑ በተደረገ ክትትልና ግምገማ ለማረጋገጥ መቻሉ ነው " ተብሏል።

ድርጅቱ ግን ከተመስረተበት ጊዜ አንስቶ ከተቋቋመበት አላማ ውጪ በየትኛውም ያልተገባ ወይም ከህግ የሚጻረር እንቅስቃሴ ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳትፎ የማያውቅ መሆኑን ገልጿል።

ድርጅቱ በማያውቀው መልኩና ሃሳቡም በህግ አግባብ ባልተጠየቀበት ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ክትትልና ግምገማ ያካሄደ መሆኑን ገልጾ የተጣለው እገዳ አግባብነት እንደሌለው እና ህግን የተከተለ እንዳልሆነ በመግለፅ  በእግዱ ላይ በቂ ማብራሪያ እንዲሰጠው የሚጠይቅ ደብዳቤ ዛሬ ለባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ያስገባ መሆኑን አሳውቋል።

ዝርዝር ማብራሪያ የመጠየቂያ ደብዳቤ አይቶ ውሳኔ እስኪሰጠን ድረስ ድርጅታችን ከየትኛውም ሥራዎቹ ታግዶና ጽ/ቤቱም ተዘግቶ የሚቆይ መሆኑን የአገልግሎቶቻችን ተጠቃሚ ለሆኑ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች፣ ለአጋር ድርጅቶች እና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ እናሳውቃለን፡፡

እገዳ የተጣለበት ድርጅቱ ፅ/ቤቱ ተዘግቶ እንደሚቆይ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር / ኢንሳ አሳውቋል።

ኢንሳ በዛሬው ዕለት በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል አሳስቧል።

ኢንሳ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች በተለያዩ ማስገሪያ (ፊሺንግ ሊንክ) አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ ገልጷል።

በመሆኑንም ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከሚያውቁትም ሆነ ከማያውቁት) ግለሰብ ሊንክ ቢላክ መክፈት ተገቢ እንዳልሆነ እና ወዲያውኑ ማጥፋት እንደሚገባ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
" አብዛኛዎቹ ከአፍሪካ ናቸው !! "

በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈረንጆች 2024 ባሕር አቋርጠው ወደ ስፔን ለመግባት የሞከሩ ቢያንስ 10 ሺሕ 457 ስደተኞች መሞታቸውን ' ካሚናንዶ ፍሮንቴራስ '  የተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም አስታውቋል።

ካለፈው ዓመት ጋራ ሲነጻጸር በ58 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየም ድርጅቱ ጠቁሟል።

በአሐዙ መሠረት በቀን 30 ፍልሰተኞች ወደ ስፔን ለመሻገር ሲሞክሩ ሕይወታቸውን ያጣሉ። ይህም ከ2023 ጋራ ሲነጻጸር በ18 ጨምሯል።

ከሟቾቹ ውስጥ 1 ሺሕ 538 ሕጻናትና 421 ሴቶች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ድርጅቱ መረጃ መሰብሰብ ከጀመረበት ከእ.አ.አ. አቆጣጠር 2007 ወዲህ ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር የተመዘገበበት ዓመት መሆኑም ተነግሯል።

በወጉ ያልተሠሩ ጀልባዎች፣ አደገኛ የባሕር ላይ ሁኔታዎች እንዲሁም የነፍስ አድን አገልግሎት ሰጪዎች በቂ አቅም ስለሌላቸው ችግሩ ሊባባስ መቻሉንም ድርጅቱ ጠቁሟል።

ተጎጂዎቹ ከ28 ሀገራት ሲሆኑ በዋነኝነት ግን ከአፍሪካ ናቸው።

በዓመቱ 60 ሺሕ 216 ፍልሰተኞች ስፔን መግባታቸው መታወቁን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#አዲስአበባ #አሶሳ

➡️ " በስራ ዘመን ቆይታዬ ይህን ያህል ክብደት የሚመዝን ልጅ ሲወለድ የመጀመሪያው ነው " - ዶ/ር ረታ ትዕዛዙ (ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል

👉 " የ3 ቀን ጨቅላ ህፃን አንገቷ ላይ በአፈጣጠር ትልቅ እብጠት ይዛ የተወለደች ቢሆንም የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጎላታል አሁን በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ ናት " - አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል


በአዲስ አበባ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቤቴልሄም አመኑ የተባለች እናት 6 ኪሎ ግራም የሚመዝን ወንድ ልጅ በተደረገላት የቀዶ ህክምና በሰላም ተገላገለች።

የሆስፒታሉ የማህፀን ስፔሻሊስት እና የዲፓርትመንት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ረታ ትዕዛዙ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል " በስራ ዘመን ቆይታዬ ይህን ያህል ክብደት የሚመዝን ልጅ ሲወለድ የመጀመሪያው ነው " ብለዋል።

ልጆች ከ5 ኪሎ በላይ ሆነው ሲወለዱ የሚደረግላቸው ህክምና መኖሩን የገለጹት ዶ/ር " ለልጁ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ መረጃ በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጓል።

የ3 ቀን ጨቅላ ህፃን አንገቷ ላይ በአፈጣጠር ትልቅ እብጠት (Bilateral huge cystic hygroma) ይዛ የተወለደች ስትሆን  በእብጠቱ ምክንያት ጡት መጥባትም ሆነ እንደ ልቧዋ መተንፈስ አትችልም ነበር።

በ13/4/17 ዓ/ም በሆስፒታሉ የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጎላት አሁን በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል።

አሁን እንደልቧ መተንፈስ ጡት መጥባትም ጀምራለች ተብኳል።

በህክምናው ላይ የተሳተፉ ባለሞያዎች ፦
🙏 Surgeons ፦ ዶ/ር ሮቤራ ተሾመ እና ዶ/ር መብራቴ ወ/መድህን
🙏 Anaesthesiologist ፦ ዶ/ር ሲሳይ እብስቱ
🙏 Anesthesia team: ደመቀ ወ/ኪዳን፣ ተሰፋዬ አሰፋ እና ሰለሞን አዳሙ
🙏 Scrub Nurse ፦ሲ/ር ሳይሽልዋል ወርቁ (ቹቹ)
🙏 Circulator Nrs ፦ አልሃጅ ሀሰን እንደሆኑ ሆስፒታሉ አሳውቋል።


@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🔴“ 14 ተማሪዎች ታስረዋል ”  - ድርጅቱ

🔵 “ ስማቸውን ካረጋገጡልኝ እኔ ነኝ የማስፈታቸው። ግን ስምና ዲፓርትመንት አምጡ ስንል ‘አናመጣም’ ነው የሚሉት ” - ኀብረቱ

🟢 “ የታሰሩት መፈታታቸውን እንጂ ያልተፈቱ እንዳሉ መረጃው የለኝም ” - መቐለ ዩኒቨርሲቲ

ከአዲሱ የዩኒቨርሲቲዎች የምግብ ሜኑ ትግበራ ጋር ተያይዞ ተማሪዎች ቅሬታ እያነሱ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ከቀናት በፊት ከተግበራው ጋር በያያዘ ቅሬታ አድሮባቸው ግርግር ተፈጥሮ ነበር።

በግርግሩ ተማሪዎች ላይ ድብደባና እስር ፣ በንብረት ላይ ደግሞ ውድመት መድረሱን ፣ በኋላም 27 ተማሪዎች ከእስር እንደተፈቱ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል። 

ዛሬስ ምን እየተባለ ነው ?

' ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያ ' የተሰኘው ሀገር በቀል የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅት “ 14 ተማሪዎች ታመታሰራዋል ” የሚል ሪፓርት አውጥቷል።

ተማሪዎቹ ከተማሪ ተወካዮቻቸው ጋር ሲገናኙበት በነበረው የቴሌግራም ገጽ አማካኝነት ከሜኑ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ አሰምተው ከቴሌግራም ገጹ እንደታገዱ፣ በዚህም ልላ ከፈቱ የተባሉ ሁለት ተማሪዎች ታኀሳስ 15 ቀን 2017 ዓ/ም በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች እንደታሰሩ ሪፓርቱ ያወሳል።

ይህን ተከትሎ በተነሳው ተቃው ደግሞ 14 ተማሪዎች መታሰራቸውን የድርጅቱ ሪፓርት ያመለከተ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስለጉዳዩ መቐለ ዩኒቨርሲቲን ጠይቋል።

ዩኒቨርሲቲው ምን መለሰ ?

አሁንም ያልተፈቱ ተማሪዎች አሉ እንዴ ? ስንል የጠየቅናቸው አንድ የዩኒቨርቲው አካል፣ “ የታሰሩት መፈታታቸውን እንጂ ያልተፈቱ እንዳሉ መረጃው የለኝም ” ብለዋል።

እኝሁ የዩኒቨርሲቲው አካል፣ “ ምናልባት ቼክ እናድርገው ” በማለት ሁኔታውን አጣርተው ምላሽ እንደሚሰጡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃል ገብተዋል።

ከዩኒቨርሲቲው በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ከተማሪ ተወካዮቻቸው ጋር በሚገናኙት የቴሌግራም ገጹ አማካኝነት ስለምግብ ሜኑው ተቃውሞ ያነሱ ተማሪዎች ታስረዋል ? ሲል ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት ጥያቄ አቀርቧል።

ኀብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ምን አለ ?

“ ‘አንድ ዳቦ፣ ሁለት ዳቦ፣ አሸዋ አለው’ በሚለው ጉዳይ ቅሬታ ተነስቶ ነበር። 120 ግራም ነበር አንድ ዳቦ የሚጋገረው አሁን 60፣ 60 ተደርጎ ወደ ሁለት ሆኗል። ግራሙ ላይ የተጨመረ፣ የቀነሰ ነገር የለም።

ሌላው ደግሞ ትላንት 5 ሰዓት ተኩል አካባቢ እኔ ራሴ አስወጥታቸው ታስረው የነበሩ 27 ተማሪዎችን ሌሊት ላይ ግን ‘ሲቀጠቀጡ ከነበሩ የመለቐ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል አንዱ ሞቷል’ ብለው ፓስት አደረጉ።

ሌሊት ሄደን አይደር ግቢ አረጋጋግጥን ምንም እንደሌለ ሪፓርት አደረግን። ከዛ ደግሞ 8 ሰዓት ፓስት ተደረገ። ግን በእነዚህ ሦስትና አራት ቀናት በአይደር ግቢ ውስጥ የሞተ ተማሪ የለም። 

ይሄ አሉባልታ ወሬ መሆኑ መታወቅ አለበት። እሱን ሀንድል ካደረግን በኋላ ደግሞ ተመልሰው ‘የታፈኑ ተማሪዎች’ አሉ ወደሚል መጡ። የታሰሩ እንኳ አላሉም። የታሰሩ ቢሉማ ወደ ህግ ነው። ‘ታፍነዋል’ ነው እየተባለ ያለው።

ይህም አይደለም። እርግጠኛ ከሆኑ የታፈኑ ተማሪዎችን እነማን ናቸው ? የት ዲፓርትመንት ናቸው ? መቼ ተወሰዱ ? ማንስ ወሰዳቸው። የሚለውን ማጣራት ግድ ነው።

ታስረው የነበሩ ተማሪዎችን ስማቸውንና ዲፓርትመንታቸውን ስላወቅን ነው ያስፈታናቸው። አሁን ግን ' ይባላል ' ነው እየተባለ ያለው። በይባላል ስለተባለ ይሆናል ማለት አይደለም። እስር ቤት ተኪዶ ቼክ የሚደረግ ነው።

የታፈኑትን ተማሪዎች ስም ዝርዝር ስጡን ስንልም ‘አንሰጥም’ በማለት ዝም ብለው ‘ታፍነዋል’ ይላሉ። ስም ለማስጠቆር የሚሄዱት ዘዴ ነው ሌላ ምንም የተደረገ ነገር የለም።

‘ተማሪዎች ተደብድበዋል፣ ንብረት ወድሟል፣ ተማሪዎች ተፈትተዋል። ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው ”
ብሏል ኅብረቱ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያ የተሰኘው ድርጅት ያወጣውን ሪፓርት አይታችሁት ነበር ? ሲል ለኅብረቱ ተጨማሪ ጥያቄ አቅርቧል።

ኅብረቱ በምላሹ፣ “ አይቸዋለሁ። ይሄ ዝም ብሎ የለቃቀመው ነው እንጂ ትክክል አይደለም ” ብሎ፣ “ መሬት ላይ የሌለ ነገር ሆነ የሚባል ከሆነ ለቀጣይ ትውልድ ምንድን ነው የምናስተላልፈው? ” ሲል ጠይቋል።

አክሎ፣ “ እነዚህ 14 ተማሪዎች ማን ማን ይባላሉ ? ምን ድፓርትመንት ናቸው ? የስንተኛ ዓመት ናቸው ? የሚመውን ይናጋገሩ ” ሲል ገልጿል።

“ ኣዲ ሓቂ ከተማ ፓሊስ ጣቢያ ታስረዋል ” ነው የተባለውና ቼክ አድርጋችሁ ነበር ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ “ ኣዲ ሓቂ ታስረው የነበሩን አስፈትተናቸዋል ” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

“ ስማቸውን ካረጋገጡልኝ (አሁን ታስረው ያሉ) እኔ ነኝ የማስፈታቸው። ግን ስምና ዲፓርትመንት አምጡ ስንል ‘አናመጣም’ ነው የሚሉት ” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ከቴሌግራም ገጹ ተነስተዋል መባሉን በተመለከተ ማብራሪያ እንደሰጥ ስንጠይቀውም፣ ከስድስቱ ግቢዎት የተማሪዎች መገናኛ የቴሌግራም ገጽ ተነስተው ከሆነ እንዳላወቀ፣ ከዋናው ከተማሪዎች ኀብረት ግን የተቀነሰ ተማሪ እንደሌለ ገልጿል። (ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ሕብር የወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ

ከመደበኛ የቁጠባ አይነት የተሻለ ወለድ የሚያስገኝ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ጥቅሞችን የያዘ ልዩ የወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞  ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች  እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ https://yangx.top/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡

#Youthsaving #hibirYouth #Startsaving
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈 #የጤናባለሞያዎችድምጽ

🔴 " ከደመወዝ ጋር ይከፈለናል ብለን በተስፋ ስንጠብቅ አሁንም ሳይከፈለን ቀርቷል " -ቅሬታ አቅራቢ የጤና ባለሞያዎች

🔵 " ምን ያህል ይታገሱ የሚለውን አላውቅም " -የወረዳው አስተዳዳሪ

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በ9 ጤና ጣቢያ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ከግንቦት 2016 ዓ/ም ጀምሮ የተጠራቀመ የትርፍ ሰዓት ስራ (ዲዩቲ) ክፍያቸው እንዳልተከፈላቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ባለሞያዎቹ ያልተከፈላቸው የ2016 ዓ/ም የግንቦት እና የሰኔ ወር እንዲሁም በ2017 ዓ/ም የ3 ወር በጠቅላላው የ5 ወር የዱዩቲ (የትርፍ ሰዓት) የሰሩበት ክፍያ ነው።

መረጃውን ባጋራንበት ወቅት ባለሞያዎቹ ያልተከፈላቸው የ4 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ የነበረ ሲሆን በወቅቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቃሉ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ ሙህዲን አህመድን በጉዳዩ ላይ አነጋግሮ ነበር።

አስተዳዳሪው " ክፍያው የዘገየው በየጤና ጣቢያዎቹ የሚሰጠው አገልግሎት እና የሥራ ጫና የሚለያይ በመሆኑ የሚያድረው የጤና ባለሞያ ቁጥርም ይለያያል በዛ ምክንያት ደረጃ ይውጣለትና በሚሰጡት አገልግሎት እና ባለባቸው የስራ ጫና ልክ ይከፈላቸው ተብሎ ይህንን የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ በወረዳው በሚገኙ በዘጠኙም ጤና ጣቢያዎች እያጣራ ነው ሪፖርቱን እንዳቀረበ ይከፈላቸዋል " ማለታቸው ይታወሳል።

አስተዳዳሪው ይህንን ምላሽ ይስጡ እንጂ የባለሞያዎቹ የትርፍ ሰአት ክፍያ ሳይከፈል 5 ወር ማለፉን የጤና ባለሞያዎች በድጋሚ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ባለሞያዎቹ " የሰራንበትን ክፍያ እንዲከፈለን ደጋግመን ብንጠይቅም የሚሰማ አመራር በማጣታችን አሁንም ለችግር ተጋልጠናል " ብለዋል።

" በህዳር ወር መጨረሻ ከደመወዝ ጋር ይከፈለናል ብለን በተስፋ ስንጠብቅ አሁንም ሳይከፈለን ቀርቷል ለምን ? ብለን ስንጠይቅ እንደገና በወረዳው ጤና ጥበቃ ኦፊሰሮች ኮሚቴ ተዋቅሮ 9ኙም ጤና ጣቢያዎች  ቼክ ይደረጉ ተብሎ ከወረዳ አስተዳደር አቅጣጫ ተቀምጧል በዚህ ወር የሰራችሁበት አይከፈላቹም " የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወረዳውን አስተዳዳሪ የጤና ባለሞያዎቹ ምን ያህል ጊዜ ይታገሱ ሲል በድጋሚ ጠይቋል " ምን ያህል ይታገሱ የሚለውን አላውቅም በቴክኒክ ኮሚቴው ተጨማሪ ጥናት እየተደረገ ነው እሱ እንዳለቀ ይከፈላቸዋል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ወረዳው ኮሚቴዎችን አዋቅሮ በዘጠኙም ጤና ጣቢያ ጀምሮት የነበረውን የማጣራት ስራ ካጠናቀቀ በኋላ በድጋሚ ጤና ጣቢያዎቹ በራሳቸው የማጣራት ስራ ጀምረዋል ይህ ለምን ሆነ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ " ተቋማቱ (ጤና ጣቢያዎቹ) እኛም ቼክ እናድርግ አሉ እኛ ከሰራነው ጋር ያለውን mismatch (ልዩነት) እንየው ከቴክኒኩ ውጤት ጋር ይገጥማል ወይስ ልዩነት አለው የሚለውን ለማየት ፈልገው ስለሆነ እሱ እንዳለቀ ይከፈላል " ሲሉ መልሰዋል።

ሃላፊው በወረዳው ደረጃ የሰሩት የጥናት ውጤት ምን እንደሆነ ከመናገር የተቆጠቡ ሲሆን ተጨማሪ ምላሽ ለመስጠትም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዳንኤል ጋሻው ምን ምላሽ ሰጡ ?

ሃላፊው " የጤና ጣቢያዎቹ አሰራራቸውን ማየት ስላለብን በድጋሚ ጀምረናል የሚሰጡት አገልግሎት እና የባለሞያው ቁጥር ትንሽ ይጣረሳል " ብለዋል።

ጥናቱም በዚህ ሳምንት እንደሚያልቅ እና በውጤቱም መሰረት እንደሚከፈላቸው ተናግረዋል።

" ነገሩን ማስተካከል ስለሚቻል በዚህ ሳምንት ጨርሰን ያለውን ነገር ችግሮቹን ለይተን የሚከፈለው ካለ ይከፈላል ያልሰራበትንም የወሰደ ካለ በምርመራው መሰረት ያሰራውም አካል የወሰደውም አካል ተጠያቂ ይሆናል " ነው ያሉት።

" ጥናት ማድረግ የተለየ ነገር አይደለም አሰራርን መፈተሽ ያለ ነው ለሰራተኛውም ይጠቅማል የሚሰራውን እና የማይሰራውን ለመለየትም ያግዛል " ሲሉ አክለዋል።

ጥናቱን ከጨረሳችሁ በኋላ የቀረውን ክፍያ በሙሉ ትከፍላላቹ ወይስ እየቀነሳቹ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄ " እሱን ከጥናቱ በኋላ ነው የምናየው ግን የሰሩበት ይከፈላል " ብለዋል።

በውጤቱ መሰረትም በጣም ኬዝ ሎድ ኖሮባቸው ዝቅተኛ የሚከፈለው ካለ ክፍያውን ሊሻሻል እንደሚችል እና ምንም ሳይሰራ እንደ መርሐ ግብር የሚከፈለው ካለም ክፍያውን ሊያጣ እንደሚችል ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia