TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle
መቐለ ያለ ከንቲባ አንድ ወር ሆናዋታል።
በጊዚያዊ አስተዳደሩ ከተማዋ እንዲስተዳድሩ ህዳር 22/2017 ዓ.ም የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ህዳር 23/2017 ዓ.ም በአስተዳደሩ ቅጥር ግቢ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ወደ ፅህፈት ቤታቸው አልገቡም።
የከንቲባ ፅህፈት ቤት ታሽጎ በፓሊስ ጥበቃ ስር እንደሚገኝ የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል መግለጹ ይታወሳል።
ከህዳር 23 አስከ ዛሬ እሮብ ታህሳስ 23/ 2017 ዓ.ም አንድ ወር ሙሉ የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነቸው መቐለ የሚያስተዳድራት ከንቲባ የለም ፤ ተገልጋዮች ከፍተኛ መጉላላት እየደረሰባቸው እንደሆን በምሬት ይገልፃሉ።
ዛሬ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ከመቐለ እና አከባቢዋ የተወጣጡ ወጣቶች በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ ከንቲባ ስራ እንዲጀምሩ ያለመ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
ወጣት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ህጋዊው ከንቲባ ወደ ፅህፈት ቤታቸው ሳይገቡ ከቦታው ንቅንቅ እንደማይሉ ፤ ከተማዋ የግርግር እና ረብሻ ምንጭ እንድትሆን እንደማይፈቅዱ ድምፃቸው በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያቀርባል።
@tikvahethiopia

ለመቐለ የውሃ አቅርቦት በሚውል ትራንስፎርመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት አገልግሎቱ መቋረጡን የከተማዋ የውሃና ፈሳሽ አገልግሎት ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
የተዘረፈው ትራንስፎርመር ለከተማዋ በቀን 1.9 ሚሊየን ሊትር ውሃ ከጉድጓድ እንዲመነጭ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ነው።
ፓሊስ አደገኛ የስርቆት ተግባሩን " እያጣራሁት ነው " ብለዋል።
የትራንስፎርመር ስርቆቱ የካቲት 24/2017 ዓ.ም ሌሊት ፤ ሐድነት ክፍለ ከተማ አይናአለም ቀበሌ ልዩ ቦታ ' ሻፋት ' ነው የተፈፀመው።
ፅ/ቤቱ በትራንፎርመሩ ስርቆት ምክንያት በቀን 1.9 ሚሊየን ሊትር ውሃ የሚያመነጨው ጉድጓድ ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ወጪ መሆኑ ገልጾ " ህዝቡ የውሃ አቅርቦት አገልግሎቱ እስኪመለስ እንዲታገስ " ሲል ጠይቋል።
ትራንስፎርመሩ ጨምሮ ጠቅላላ የደረሰው ወድመት ከ5 ሚሊዮን ብር ላይ ይገመታል ሲልም አክሏል።
ፖሊስ ከባድ የስርቆት ተግባሩ የቦታውን ሁለት ጥበቃዎች ላይ የአካል ጉዳት በማድረስ መፈፀሙ ጠቅሶ ፈፃሚዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል የቀናጀ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።
ዘራፊዎቹ በጥበቃዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረሳቸው የተነገረ ሲሆን ተጣርጣሪዎቹ ለመያዝ በሚድረገው እንቅስቃሴ የህዝቡ ተሳትፎ እና ጥቆማ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ፓሊስ አመልክቷል።

#Tigray " ህወሓት ለበርካታ ጊዚያት በተጠራቀሙ ችግሮች ተተብትቦ ወደ ፊት መራመድ ተስኖታል " አሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የሾማቸው የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/ኢየሱስ። ከንቲባው ይህን ያሉት ከከተማዋ ወጣቶች ጋር በመከሩበት ወቅት ነው። " ህወሓት ለበርካታ ጊዚያት በተጠራቀሙ ችግሮች ተተብትቦ ወደ ፊት መራመድ ተስኖታል " ያሉት ከንቲባው " ፓርቲው ጠልፈው የጣሉት ችግሮቹ ከመፍታት ይልቅ ማሰብ አቁሞ…
#Mekelle
🔴 " ህወሓት መዳን ከፈለገች መልሳ ጉባኤ ማድረግ አለባት የሚል እምነት አለኝ "- ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ
⚫️ " ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እርምጃ ውሰድ ፤ ካልሆነ በራሳችን መንገድ እንሄዳለን " - የመቐለ ከተማ ወጣቶች
ዛሬ ለመቐለ ከተማ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የመከሩ ወጣቶች የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት " ኋላቀር ለውጥ አደናቃፊ " ሲሉ ወረፉ።
ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ ከመቐለ 7 ከፍለ ከተሞች ከተወጣጡ ወጣቶች በፅህፈት ቤታቸው የተወያዩ ሲሆን ለተነሱላቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራርያ ሰጥተዋል።
ወጣቶቹ በመድረኩ ባቀረቡት አስተያየትና አካሄድ የደብረፅዮኑ (ዶ/ር) ህወሓት " ' እኔ ባልቀደስኩት መአድ ለመብላት እጅ መሰድድ አይታሰብም ' በሚል አካሄድ ተጠምደዋል " ሲሉ ተችተዋል።
" ' እኔ ብቻ ነኝ ፈላጭ ቆራጭ ' የሚል ፈሊጥ ያለንበት ወቅት የማይዋጅ ኋላቀር " ሲሉ በስሜት የተናገሩት ወጣቶቹ የደብረፅዮኑ (ዶ/ር) ህወሓት የጠቅላይነት መንገድና አካሄድ አይሰራም ብለዋል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት " ፀረ ለውጥ " ሲሉ በፈረጁት የደብረፅዮኑ ህወሓት ላይ እርምጃ ባለመወሰዱ አምርረው የነቀፉት ወጣቶቹ " ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እርምጃ ውሰድ ፤ ካልሆነ በራሳችን መንገድ እንሄዳለን " በማለት ቁጣቸው አሰምተዋል።
" መንግስት መንግስትን በመሆን የለውጥ ጥያቄያችን ይመልስ እኛ ወጣቶች ትዕግስታችን ተሟጠዋል " ሲሉም ገልጸዋል።
ህዝቡ የአስተማማኝ ሰላም ባለቤት እንዲሆን በምርጫ የሰየመው መንግስት ሊኖረው ይገባል ሲሉ ምላሽ የሰጡት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህንን እውን እንዲሆን ከስሜት የፀዳ ትግልና አካሄድ ከወጣቱ ይጠበቃል ብለዋል።
" ህወሓት ጠላት ነው " የሚል ነገር ስህተት እንደሆነ የገለፁት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው " ፓርቲው እንዲድን ከተፈለገ እንደ አዲስ አሳታፊ ጉባኤ ማካሄድ ይጠበቅበታል " የሚል ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል።
በትግራይ ያለው ችግር በህወሓት ብቻ ይፈታል ማለት ስህተት ነው ፤/ስለሆነም ላሉት ዘርፈ በዙ ችግሮች አሳታፊ ሁሉን አቀፍ ፓለቲካ ዋነኛ ተመራጭ መንገድ ነው ሲሉ አክለዋል።
ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የመቐለ ከተማ ያለ ከንቲባ ከሦስት ወራት በላይ መቆየት፣ የDDR መቋረጥ ፣ በክልሉ የሚታዩ በርካታ የፀጥታ ችግሮች በማስመልከት ከወጣቶች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራርያ መስጠታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
Photo Credit - Tigrai TV