TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray : በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት የራሱን ምክር ቤት አቋቁሟል።

" የሃላቀርነት እና ወንጀል ቡድን " ሲል የገለፀውን በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን የህወሓት ቡድን በፅኑ ለመታገል ቆርጦ እንደተነሳ ገልጿል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት እስከ ቀጣዩ 14ኛው የደርጅቱ መደበኛ ጉባኤ የሚቆዩ ሊቀመንበር እና ምክትል ያቀፈ 7 አባላት ባሉት አስተባባሪ ኮሚቴ የሚመራ ም/ቤት አቋቁሟል።

የደርጅቱን ምክትል ሊቀመንበር ማን አድርጎ እንደሰየመ ያልገለፀው መግለጫው  ፤ አስተባባሪ ኮሚቴው የቀጣይ 3 ወራት እቅድ ማዘጋጀቱ አስታውቋል።

ደርጅቱ 14 ኛ ጉባኤውን መቼ እንደሚያካሂድ ያልገለፀ ሲሆን የተመሰረተው ምክር ቤት አባላት ሁሉም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከሚመራው ህወሓት " አንሰለፍም " ብለው የተቆራረጡ ናቸው።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት በከተማና ገጠር ከክልል ፣ ዞን ፣ ወረዳ እና እስከ ቀበሌ ድረስ አደራጃጀቶች በመዘርጋት " የኃላቀርነት እና ወንጀል ቡድን " ሲል የገለፀውን በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን ህወሓት በፅኑ ለመታገል ቆርጦ መነሳቱ ገልጿል።

መላው የትግራይ ህዝብ ፣ የህወሓት አባላት ፣ የፀጥታ ሃይሎች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ በተለይ ወጣቶች ፣ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች እና የዳያስፓራ ማህበረሰብ ከጎኑ እንዲሰለፉ ጥሪ ያቀረበው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " በሰላማዊ ትግል የትግራይን ህዝብ ጥቅም ለማስክበር እታገላለሁ " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ' ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን ብቻ እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን ' ብለዋል " - ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ከድምጺ ወያነ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ፤ የትግራይ አመራሮች በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐበይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በወቅታዊ ጉዳይ በነበራቸው ቆይታ በክልሉ ጉዳይ የሃሳብ ልዩነት አልነበራቸውም ብለዋል፡፡

ነገር ግን " የትግራይ ፓለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ እያመራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" የፀጥታ ሃይሎች ከማንኛውም ጫና ነፃ ሆነው የህዝቡ ብሄራዊ ጥቅም ማረጋገጥ ይገባቸዋል " ሲሉ አክለዋል፡፡

በአዲስ አበባው ውይይት በደብረፅዮን (ዶ/ር) ይሁን በአቶ ጌታቸው የሚመሩት የህወሓት ልኡካን እንዲሁም የጊዚያዊ አስተዳደሩ ተወካዮች መካከል በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታና ችግሮች ዙሪካ ያለልዩነት መስማማታቸውን ገልጸዋል።

በወቅቱ " የፌደራል መንግሰት የትግራይ ችግሮች እንዲፈቱ አላገዝክም " በማለት ወቀሳ ማቅረባቸውን ጠቁመዋል።

" የፌደራል መንግስት ' ጉባኤ እንድናካሂድ ፤ የትግራይ ፓለቲካ እንድናስተካክል ጊዜ ስጠን በማለት ዕድል እና ጊዚያችሁን አባክናቹሃል ' በማለት መልሶልናል " ሲሉ አብራርተዋል።

ሌተናል ጄነራሉ ፥ " በመሃከላችን እየታየ ያለው ክፉኛ መሳሳብ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት እንዳይረጋገጥ ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቁያቸው እንዳይመለሱ አደገኛ መሰናክል ሆኗል " ብለዋል።

የፕሪቶሪያ ውል በይፋ የተቃወመ የለም ፤ በተግባር ግን ውሉን የሚያደናቅፍ አሉታዊ ተግባር የሚፈፀሙ አካላት አሉ ብለዋል።

" የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ በመተግበር ብቻ ነው አቃፊ መንግስት ማቋቋም የሚቻለው " በማለትም አስረግጠዋል።

" እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ' ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን ብቻ እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን ' ብለዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" እኛም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የፌደራል መንግስት ዓለምአቀፋዊ ወሰኖች የመጠበቅ እና የማስከበር ስልጣን አለው፤ ይህንኑ ስልጣኑ ተጠቅሞ በቦታው የሚገኙ የውጭ ሃይሎች አውጥቶ የግዛት አንድነት እንዲያረጋግጥ በአፅንኦት ጠይቀናል " ብለዋል።

በዚህ ምክንያት " ' ከሃዲዎች ' በሚል ስማችንን ማጠልሸት ተገቢ አይደለም " ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በፌደራል መ/ቤቶች የትግራይ ውክልና ባለመኖሩ ምክንያት የህዝቡ ድምፅ በተገቢው መንገድ ሊሰማ ባለመቻሉ ምክንያት ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልሉ ውክልና እንዲመለስ ለፌደራል መንግስት ጥያቄ መቅረቡን  ሌተናል ጀነራሉ አሳውቀዋል።

በተጨማሪ ፤ " የፕሪቶሪያ ውል አንቀፅ 8 ዓለምቀፍ ወሰኖች በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ ስለሚያዝ ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ከኤርትራ እና ከሱዳን የሚያገናኙ ወሰኖች ጠባቂ ስለሌላቸው የውጭ ሃይሎች እየገቡ ግፎች እየፈፀሙ ፣ ወርቅ ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች ህገ-ወጥ ወንጀሎች እየተፈፀመባቸው በመሆኑ ወሰኖቹ በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ " ሲሉ መጠየቃቸውን አሳውቀዋል።

#Tigray #TPLF

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ሚመራው የህወሓት ቡድን በቀጣይ " አዲስ እና ሰላማዊ የትግል ስልት እከተላለሁ " ብሏል።

ቡድኑ በቀጣይ አጠቃላይ አባላቶቹ በመጠቀም " የእምቢተኝነት ዘመቻ " ያለውን እንቅስቃሴ ለማድረግ እንዳቀደ ተነግሯል።

ለዚህ ዘመቻ " እምቢ ለብሔራዊ ክህደት፣ ለአገዛዝ እና ብተና " የሚል መፈክር እንደሰጠው ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ትላንት እና እና ዛሬ የደብረፅዮን (ዶ/ር) ቡድን ከፍተኛ ካድሬዎቹ ስብሰባ ተቀምጠው ነው የዋሉት።

@tikvahethiopia
#Tigray

በወርቅ ማዕድን ቁፋሮ እና ዝውውር ዙሪያ መረጃዎች በማሰባሰብ ላይ የነበሩ የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በታጣቂዎች መታገታቸውን ተቋሙ አስታወቀ።

የታገቱት ጋዜጠኞች ብዛት 3 እንደሆነ የገለፀው የሚድያ ተቋሙ ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ መደረጉን ጨምሮ ገልጿል። 

ትግራይ ቴሌቪዥን " በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ እና ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ለማጥራት የተሰማሩ ጋዜጠኞች ናቸው በታጣቂዎች የታገቱት " ሲል አሳውቋል።

ሦስት አባላት የያዘ የጋዜጠኞች ቡድን ዛሬ ታህሳስ 20/ 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 3:00 ጀምሮ በአስገዳ ወረዳ ' ሜይሊ ' ተብሎ ከሚጠራ ልዩ ቦታ በምትገኘው መንደር ነው የታገቱት ተብሏል።

ጋዜጠኞቹ በአከባቢው ስላለው ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና ዝውውር በማስመልከት በአካል ቦታው ድረስ በመሄድ የአከባቢውን ነዋሪዎች ፣ አርሶ አደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ሲያነጋግሩ እንደሰነበቱ የገለፀው የትግራይ ቴሌቪዥን " የጋዜጠኞች ቡድኑ በስራ እያለ በታጣቂዎች ሊታገት እና ሊታሰር ችሏል " ሲል አመልክቷል።

የታገቱት የጋዜጠኞች ቡድን ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ በመደረጉ ምክንያት ያሉበት ሁኔታ እና ድህንነታቸው ማረጋገጥ እንዳልተቻለ አመልክቷል።

ጋዜጠኞቹን የሚመለከት መረጃ ለመጠይቅ በአከባቢው ለሚገኙ የመንግስት አመራሮች ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም እንዳልተሳከለት የትግራይ ቴሌቪዥን አሳውቋል።

እገታውን ስለፈጸሙ ታጣቂዎች ማንነት በዝርዝር የተባለ ነገር የለም።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የትግራይ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቃዎች ታግተዋል " የተባሉት  3 የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ሜይሊ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚገኝ እስር ቤት እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቪዥን ከደቂቃዎች በፊት ማረጋገጡ ይታወሳል። አሁን ከስፍራው በተገኘው መረጃ ሦስቱ ጋዜጠኞች ከእስር ተለቀዋል። የጋዜጠኞቹ መፈታት በማስመልከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፥ ጋዜጠኞቹ መረጃ…
#Tigray

የትግራይ የፀጥታና የሰላም ቢሮ " ትግራይ ቴሌቪዥን " ይቅርታ ይጠይቅ አለ።

ቢሮው ይህን ያለድ ለአንድ ቀን ያህል በእገታና አስር ቆይተው ተለቀቁ በተባሉት ሦስት የትግራይ ቴሌቪዥን ባለሙያዎች ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ነው።

የቢሮው መግለጫ የሚድያ ባለሙያዎቹ እገታ እና እስር አስመልክቶ የተሰራጨውን መረጃ የሚቃወም እንድምታ አለው። 

ተስፋዝጊ ዓስበይ ፣ ኢሳያስ በየነ እና ኣታኽልቲ የተባሉ የትግራይ ቴሌቪዥን የሚድያ ባለሙያዎች  ታግተውበታል ወደ ተባለው ቦታ መሄዳቸው የወረዳ ፣ የቀበሌ እና የመንደር አመራሮች መረጃ አልነበራቸውም ብሏል።

ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ' ታግተናል ታስረናል ' ማለታቸው ልክ እንዳልሆነ አመላክቷል።  

" ጋዜጠኞቹ ወደ ቦታው እንዲንቀሳቀሱ የቀበሌ እና የመንደር አመራሮች መረጃ እንዲኖራቸው የግድ ነው ወይ ? " የሚል ጥያቄን ግን የቢሮው መግለጫ አለመለሰም።

" ሊበሉዋት የፈለጓትን አሞራ  ቆቅ ናት ይሉዋታል " ብሎ የተረተው የሰላምና የፀጥታ ቢሮ መግለጫ ፤ ተገቢ ማጣራት ሳይደረግ የሚድያ ባለሙያዎቹ ' ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ታግተዋል ፤ ታፍነዋል ' ተብሎ  የተሰራጨው መረጃ መስተካከል እና የትግራይ ቴሌቪዥን ይቅርታ ሊጠየቅበት እንደሚገባ አስገንዝቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋዜጠኞች እና የሚድያ ባለሙያዎች የሙያ ነፃነታቸው ተከብሮ በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም ቦታ ተዘዋውረው መረጃ በማሰባሰብ ለህዝብ የማድረስ መብት እንዳላቸው የገለጸው የትግራይ ጋዜጠኞች ማህበር ፤ በትግራይ ቴሌቪዥን የሚድያ ባለሙያዎች ላይ የተደረገው ወከባ አፈና ፣ እስር እና እንግልት በፅኑ ኮንነዋል።

ጋዜጠኞቹ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር ለህዝብ እና ለአገር መረጃ ለማቅረብ ሲንቀሳቀሱ ተገቢ የፀጥታ ጥብቃ ሊድረግላቸው እንደሚገባ ያሳሰበው የማህበሩ መግለጫ ፤ ህግ እና ስርዓት አክብረው ተገቢ የሙያ ተግባራቸው በሚከውኑ የሚድያ ባለሙያዎች ላይ የሚድረግ ማንኛውም ዓይነት አፈና ፣ በደል ፣ ክልከላ እና ወከባ በጥብቅ እንቃወማለን ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል። ምርጫ ቦርድ ፤ ህወሓት በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር መሠረት በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን አስታውሷል። ፖርቲው ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ…
#TPLF #Tigray

ለሁለት ቡድን የተከፈሉት የህወሓት አመራሮች አሸናፊ እና ተሸናፊ በሌለበት የፓለቲካ ችግሮቻቸውን ለመፍታት የተደረገው ተደጋጋሚ ድርድር አልተሳካም አለ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር።

ሁለቱ ቡድኖች ፓለቲካዊ ልዩነታቸው እንዲፈታ ከመጣር ይልቅ ፤ አንዱ ሌላውን ጠርጎ ለማጥፋት በሚል እሳቤ መጠመዳቸው ለድርድሩ አለማሳካት አንዱ እና ዋነኛ ምክንያት ነው ተብሏል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?

- የፓለቲካ ልዩነቱ ዋና መነሻ ከፍተኛ አመራሩ በመሆኑ ችግሩ በድርድር እንዲፈታ ጥረት የተደረገው በከፍተኛ አመራሩ ነው ብለዋል።

- የክልሉ የፀጥታ ሃይል ጨምሮ ሌሎች አካላት " ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ችግሮቻቸው ፓለቲካዊ ነው መፈታት ያለበትም በፓለቲካዊ መግባባት ነው " በሚል ለማደራደር በርካታ ጥረት ተደርጓል።

- በሁለቱ ቡድኖች መካከል የተፈጠረ የፓለቲካ ልዩነት አሁን የተፈጠረ ሳይሆን በወቅቱ ሳይፈታ ለዓመታት እየተከማቸ የመጣ መሆኑ ቡድኖቹ ለማቀራረብ አዳጋች አድርጎታል።

- በሁለቱን ቡድኖች ያለው ፓለቲካዊ መሳሳብ  አሁንም ፓለቲካዊ መፍትሄ ያሻዋል። የፀጥታ ሃይሉ  " የኛ ደጋፊ ነው " የሚል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚናገረው ተቀባይነት የለውም።

- የፀጥታ ሃይሉ የክልሉ እና የህዝቡ ፀጥታ እና ሰላም ከማስከበር ባለፈ አንዱን ቡድን በመደገፍ ሊቆም አይችልም። ህዝቡ ሁለቱ ቡድኖቹ ችግራቸው በጠረጴዛ ውይይት እንዲፈቱ ጫናውን ማሳደር ይጠበቅበታል።

- የፀጥታ ሃይሉ የአንዱ ደጋፊ ለማሰመሰል የሚደረግ ጥላሸት የመቀባት ተግባር ልክ አይደለም። ይህን መሰል በሬ ወለደ ውሸት የሚያራግቡ አካላትም ሆነ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባቸዋለን።

መረጃውን የትግራይ የመገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ የላከው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray " በየመዋቅሩ ያሉ ም/ቤቶች ጊዚያቸው ያለፈ እና ህጋዊ መሰረታቸው ያበቃ በመሆኑ መሾምና መሻር አይችሉም " ብሎ የነበረው የትግራይ  ክልልጊዚያዊ  አስተዳደር ምክር ቤቶቹ ህጋዊ መሰረት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ደንብ አፅድቀዋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ የወረዳ ምክር ቤቶች የሚያጠናክር እና ህጋዊ መሰረት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ያለውን ደንብ ከሰሞኑን አፅድቋል።

" የፀደቀው ደንብ የወረዳ ም/ቤቶች ተጠናክረው የህዝቡ ተሳትፎ እና ውክልና በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል የተፈጠረው አለመግባባት የሚቀርፍ ሁሉን በሚያግባባ መልኩ ስራቸው እንዲፈፅሙ የሚያስችላቸው ነው "  ብሏል።

ደንቡ ተፈፃሚነት እንዲኖረው ሁሉም የበኩሉ እንዲወጣ ያሳሰበው  የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፤ አስከታች ድረስ ያለው መንግስታዊ እና አስተዳዳራዊ መዋቅር ተጠናክሮ ህዝቡ የሚገባውን አገልግሎት ማግኘት አለበት ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

ዛሬ በደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች በኩል የፓሊስ ትእዛዝ የጣሱ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።

በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራቸው ሰልፈኞች ፥ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  ጥር 14/2017 ዓ.ም የወጣውን የውሳኔ ሃሳብ የሚደግፉና እና ሌሎች መፈክሮች አስተጋብተዋል።

በራሳቸው ተነሳሽነት ሰልፍ መውጣታቸው የሚናገሩት በብዛት ወጣቶች ያካተቱ ሰልፈኞች ደግሞ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  የተሰጠው ውሳኔ ተፈፃሚነት (null and void እንዲሆን) እንዳይኖረው ፤ ጦርነት የሚፀየፉና ጅምር ሰላም እና ለውጡ እንዲቀጥል የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል።

በሰሜናዊ ምዕራብ ፣ ማእከላዊ ዞኖች መቐለ ከተማ በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት ብቻ የጠራቸው ሰልፎች ሲካሄዱ ፤ በምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች በደጋፊ እና ተቃዋሚ በአንድ ጊዜ የተጠሩ ሰልፎች ተከናውነዋል።

በውቅሮ ከተማ የፀጥታ አካላት በራስ ተነሳሽነት ለመውጣት በሞከሩት ላይ ለመበተን የሞከሩ ሲሆን ፤ በዓዲግራት የነበሩት የለውጥ ደጋፊዎች ላይ ግን ለመበተን የተደረገ ሙከራ እንደሌለ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዘግቧል።

ትናንት ጥር 17/2017 ዓ.ም  በደቡባዊ ዞን የተለያዩ ከተሞች " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  የተሰጠው ውሳኔ የሚቃወም ጦርነት የሚያወግዝ ሰላምና ለውጥ የሚደግፍ ሰላማዊ ስልፍ የተካሄደ ሲሆን ዛሬ እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት የጠራው ሰልፍ በዞኑ አልተካሄደም።

በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት በጠራው ሰልፍ የተደመጡ መፈክሮች ምን ይመስላሉ ?

- የትግራይ ሰራዊት ውሳኔ ይተግበር !!
- የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በአስቸኳይ ይስተካከል !!
- የፕሪቶሪያ ውል ይተግበር !!
- የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር !!
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!
- የህወሓት ህጋዊነት በአስቸኳይ ይመለስ !!
- የውጭ ጣልቃ ገብነት አንቀበልም !!
- ሰራዊታችን ለማፍረስ እየተደረገ ያለው ሴራ አንቀበልም !!
- የፕሪቶሪያ ስምምነት መተግበር ለትግራይ እና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ዋስትና ነው !!

በራስ ተነሳሽነት ወጣቶች በብዛት በተሳተፉባቸው ሰልፎች የተደመጡ መፈክሮች ምን ይመስላሉ ?

- የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም !!
- የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች የህዝብ አገልጋዮች እንጂ የአንድ ቡድን ከለላ አይደሉም ! 
- የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ይከበር !!
- የሚቆም ትግል እና ለውጥ የለም !!
- ወጣቶች ለልማት እንጂ ለጦርነት አንሰልፍም!!
- የተረጋጋ መንግስት ለመትከል የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው !!
-ጊዚያዊ አስተዳደሩ ወደ መደበኛ መንግስት የሚያሸጋግረን በቸኛ ህጋዊ ተቋም ነው !!
- የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዲፀና እንፈልጋለን !!

... ሲሉ ተደምጠዋል።

በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ፤ ዛሬ ጥር 18/2017 ዓ.ም መቐለ ጨምሮ በመላው ትግራይ የሚካሄደው ሰልፍ መግባባት የተደረገበት እና የተሟላ ጥበቃ የሚደረገበት ነው ያለ ሲሆን ጊዚያዊ አስተዳደሩ በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት በኩል ጥር 17/2017 ዓ.ም  ባወጣው መግለጫ ለእሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም የተጠራ እና የተፈቀደ ሰልፍ የለም ብሎ ነበር።

የትግራይ ፓሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ህወሓት ለእሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በቂ ጥበቃ ለመስጠት በመቸገሩ ምክንያተት ቀን እንዲቀየርለት ሲጠይቅ : የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ  ትእዛዝ ተላልፈው ስበብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ በሚያካሂዱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ማስጠንቀቁ መዘገባችን ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ እስከ አሁን ባለው መረጃ በድጋፍ እና በተቃውሞ በኩል የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ሰላማዊ የነበሩ ሲሆን ከክልሉ ፓሊስ እንዲሁም የሰላም እና  የፀጥታ ቢሮ የሚሰጥ መረጃ ካለ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#Tigray

በእንዳስላሴ ሽረ ከተማ በህዝብ መዝናኛ ስፍራ በተጣለ የእጅ ቦምብ 10 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉደት ደረሰባቸው።

የሰው ህይወት አለማለፉን ለመረዳት ተችሏል።

የቦምብ ጥቃቱ አድራሾች እና ግብረ አበሮቻቸው ለመያዝ የተጠናከረ ክትትል እና ምርመራ እያደረግኩ ነው ብሏል ፖሊስ።

ጥቃቱ መቼና ? የት ? እንዴት አጋጠመ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ፤ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞችን አግኝቶ አነጋግሯል።

ጥቃቱ የካቲት 3/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 1:40 ቀበሌ 05 በሚገኝ የአንድ ግለሰብ የመዝናኛ ስፍራ ነው የደረሰው።

የመዝናኛ ቤቱ ባለቤት ሰሞኑን ከማያወቀው ሰው በሞባይል እየተደወለ የማስፈራርያ መልእክት ይደርሰው እንደነበር ፤ የመልእክቱ አንኳር ነጥብ " እስከ 400 ሺህ ብር እንዲከፍል " ይህንን ካላደረገ ግን አደጋ እንደሚደርስበት የሚገልጽ ማስጠንቀቅያ ነው።

ግለደቡ የማስፈራርያ ዛቻውን በሰዓቱ ለፓሊስ ያደርስ እንደነበረ ነው የተነገረ ሲሆን ጥቃቱ ከመድረሱ ከአንድ ቀን በፊት ሳይቀር ዛቻውን ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር።

የመዝናኛ ቤቱ ባለቤት ስጋቱ አይሎበት ፓሊስ ጣብያ ድረስ በመሄድ የጉዳዩን አሳሲበነት አስረድቶ ፓሊስ በተባለው አከባቢ ከየካቲት 2/2017 ዓ.ም በመከታተል እያለ ቦምቡ መጣሉ ከከተማው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ ያመልክታል።

የተጣለው ቦምብ በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን አንድ ሴት የምትገኝባቸው ሦስት ሰዎች ላይ  ከባድ ፡ ሰባት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የከተማው ፓሊስ ተጠርጣሪዎች ከግብረ አበሮቻቸው ጋር ለመያዝ ክትትል እና ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉ ገልፆ ህዝቡ መረጃ በመስጠት ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርቧል።

ከቀናት በፊትም በከተማዋ በአስፋልት ዳር ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች አንድ ሰው ተገድሎ መገኘቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃውን አጋርቶናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የህወሓት አመራሮች ዛሬ በመቐለ ከተማ ፊት ለፊት ተገናኝተዋል። የፊት ለፊት ግንኙነቱ በክልሉ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች የተመራ ነበር። ጥዋት በመቐለ ኖርዘርን ስታር ሆቴል አዳራሽ  የነበረው የፊት ለፊት ውይይት ግማሽ ቀን የፈጀ እንደነበር ታውቋል። የሃይማኖት አባቶቹ ፥ " ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱ ባቀረብናላቸው ጥሪ መሰረት ተገናኝተው ችግራቸውን በፓለቲካዊ እና በህጋዊ አሰራር እንፈታለን…
#Tigray

" ችግሮቻቸውን በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው ለህዝቡ እፎይታ ይሰጣል " - የሃይማኖት አባቶች

የትግራይ ክልል አመራሮች በመካከላቸው የተፈጠረው የፓለቲካ ልዩነት በሰላም እና በውይይት ለመፍታት መስማማታቸው የትግራይ የሃይማኖት መሪዎች አስታወቁ።

ችግሮቻቸው ለመፍታት እና ወደፊት ሊያራምዳቸው የሚችል የስነ-ምግባር ደንብ ወጥቶ መፈራረማቸውም ሰላማዊ ውይይቱን የመሩ የሃይማኖት አባቶች ዛሬ የካቲት 7/ 2017 ዓ.ም በመቐለ በሰጡት መግለጫቸው አስታውቀዋል።

የሃይማኖት አባቶቹ በመግለጫቸው " አመራሮቹን ለማቀራረብ ሲካሄድ የነበረው ሰላማዊ ውይይት ስምምነት ላይ አድርሷቸዋል " ብለዋል።

በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረው ችግር ለመፍታት ከሁለት ወር በላይ ጥረት መደረጉ ያብራሩት የሃይማኖት አባቶቹ መሪዎቹ ችግሮቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ መስማማታቸው ለህዝቡ እፎይታ ይሰጣል ሲሉ ገልጸዋል።

አመራሮቹ በመካከላቸው የተፈጠረ የፓለቲካ ልዩነት በውይይት እንዲፈቱ መስማማታቸው አስመልክቶ በሃይማኖት አባቶች የተሰጠው መግለጫ ብዙ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ያላቸው ደስታ እና ድጋፍ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚመሩ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከወራት በፊት ችግሮቻቸው ለመፍታት በሃይማኖት አባቶች ፊት ቢጨባበጡም ጠብ የሚል ለውጥ ማምጣት ባለመቻላቸው ምክንያት ህዝቡን ወደ ከፍተኛ ጭንቀት እና ወጥረት መክተታቸው የሚታወስ ነው።

አሁንስ ቃላቸው ጠብቀው ልዩነቶቻቸው ጠረጴዛ ዙሪያ በመፍታት ለህዝብ አገር እፎይታ ይሰጡ ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

ፎቶ 2 ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#Tigray

ትናንተ የካቲት 12 /2017 ዓ.ም በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ በነዋሪዎችና በአከባቢው በሚገኘው የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ተከስተዋል።

በግጭቱ ምክንያት በ20 የቀበሌው ነዋሪዎችና ቁጥራቸው ባልታወቀ የትግራይ ኃይል አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ያጋጠመ ሞት የለም።

ግጭቱ እንዴት እና በምን ምክንያት አጋጠመ ? 

በአዲስ አለም ቀበሌ ሁለት አስተዳዳሪዎች አሉ። አንዱ የቆየ ሲሆን ሌላው ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾመ ነው።

ሁለቱም ማህተም ይዘው በየፊናቸው " እኔ ነኝ ህጋዊ የቀበሌው አስተዳደር " በማለት ህዝቡን ለሁለት መክፈላቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ " ህዝቡ አማርሮ እንድንታደገው ጠይቆናል አዛዦቻችንም ይህንን እንድንፈፅም ልከውናል" ያሉ 9 የሰራዊት አባላት ወደ ቀበሌው ደርሰው ሁለቱ አስተዳዳሪዎች ማህተም እንዲያስረክቡ ይጠይቃሉ።

" ታስረክባላችሁ አናስረክም " በሚል እልህ በነዋሪዎች እና የትግራይ ኃይል አባላት መካከል ግጭት ይነሳል። ነዋሪውም ደንጋይ መወርወር ይጀምራል። የትግራይ ኃይል አባላትም ጥይት ይተኩሳሉ።

በዚህ መካከል በተተኮሰ ጥይት አንድ ሰው እጁ ላይ ተመትቶ ሆስፒታል ሲገባ ሌሎች 20 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በትግራይ ኃይል አባላት ላይም ጉዳት የደረሰባቸው አሉ። 

የወረዳው አስተዳደር ለክልሉ የሰላም እና የፀጥታ ቢሮ የካቲት 11/2017 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ 13 ታጣቂዋች ወደ ወረዳው አስተዳደር በመምጣት የጊዚያዊ አስተዳደር ማህተም እና የፅህፈት ቤት ቁልፍ እንዲያስረክቡዋቸው መጠየቃቸውን እና ይህንን ህገ-ወጥ ተግባር እንዲቆም ጠይቋል።

ከህወሓት ወደ ሁለት መሰንጠቅ በኋላ የክልሉ ዋና ከተማ መቐለ ጨምሮ በተለያዩ የገጠር እና የከተማ አስተዳደሮች ተመሳሳይ ስልጣን ያላቸው ሁለት አሰተዳዳሪዎች መስማት የተለመደ ነው።

በአንዳንድ ዞኖች ያሉ ወረዳዎች በጊዚያዊ አስተዳደሩ እና የደብሪፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት የተሾሙ አስተዳዳሪዎች ለሁለት ተከፋፍለው ይተዳደራሉ።

የትግራይ መሪዎች በተለይም የህወሓት አመራሮች ከዚህ መሰል ህዝብ የሚከፋፍል አደገኛ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የሚመክሩ አስተያየት ሰጪዎች ፤ የትግራይ ኃይል አባላት አንዱን ቡድን ደግፈው ሌላው ቡድን ማውገዝ ተጨማሪ ቀውስ እና ጥፋት ስለሚያስከትል የገለልተኝነት ሚናቸው እንዱወጡ አበክረው እያሳሰቡ ናቸው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
" የህግ ተጠያቂነት እስኪረጋገጥ ድረስ በአስቸኳይ ከአከባቢያችን ይልቀቁ " - ነዋሪዎች " ተጠቅተናል " የትግራይ የሳምረ ሰሓርቲ ወረዳ 400 የህዝብ ተወካዮች ዛሬ የካቲት 14/2017 ዓ.ም ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት እና ምክትል ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በመቐለ ከተማ መክረዋል። ተወካዮቹ የህግ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እና ጥቃት አደረሰብን ያሉት የትግራይ ኃይል…
#Tigray

" ህወሓት ለበርካታ ጊዚያት በተጠራቀሙ ችግሮች ተተብትቦ ወደ ፊት መራመድ ተስኖታል " አሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የሾማቸው የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/ኢየሱስ።

ከንቲባው ይህን ያሉት ከከተማዋ ወጣቶች ጋር በመከሩበት ወቅት ነው።

" ህወሓት ለበርካታ ጊዚያት በተጠራቀሙ ችግሮች ተተብትቦ ወደ ፊት መራመድ ተስኖታል " ያሉት ከንቲባው " ፓርቲው ጠልፈው የጣሉት ችግሮቹ ከመፍታት ይልቅ ማሰብ አቁሞ ህዝቡን ወደ ከባድ ስቃይ አስገብቶታል " ሲሉ ጠቁመዋል።

" ' ራሴን በራሴ አስተዳድራለሁ፤ የሚሆነኝን እመርጣለሁ ' ያለ ትግራዋይ ማንኛውም ጥቃት ሊደርስበት አይገባም " ያሉት ከንቲባው " ከፌደራል መንግስት የሚያገናኘን የፕሪቶሪያ ውል ማደናቀፍ ማለት እንደ ህዝብ አደጋ ላይ የሚጥል ነው " ሲሉ አክለዋል።  


ከህዳር 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ  በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ይሁንታ የመቐለ ከንቲባ በመሆን የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ እስከ አሁን ወደ ፅህፈት ቤታቸው ባይገቡም ከተማዋ በሚመለከቱ በተለያዩ ህዝባዊ ስብሰባ እና ውይይቶች በመገኘት በከንቲባ መዓርግ መልእክት ያስተላልፋሉ።

በደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት እና ጊዚያዊ አስተዳደር ሁለት ከንቲባ የተሾሙባት መቐለ በፓለቲካ አመራሮቹ በተፈጠረው አለመጣጣም ላለፉት 86 ቀናት ፅህፈት ቤት ገብቶ ህዝብ የሚያገለግል ከንቲባ የላትም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከምንጮቹ ባገኘው መረጃ የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን በፀጥታ ሃይሎች ጥበቃ ስር የሚገኘው የከንቲባው ፅህፈት ቤት አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ እንዲረከቡት ወደ መቐለ ፓሊስ ትእዛዝ ቢፅፍም አልተተገበረም።

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle 🔴 " ህወሓት መዳን ከፈለገች መልሳ ጉባኤ ማድረግ አለባት የሚል እምነት አለኝ "- ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ  ⚫️ " ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እርምጃ ውሰድ ፤ ካልሆነ በራሳችን መንገድ እንሄዳለን " - የመቐለ ከተማ ወጣቶች ዛሬ ለመቐለ ከተማ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የመከሩ ወጣቶች የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት "  ኋላቀር ለውጥ አደናቃፊ " ሲሉ …
#Tigray

" እንቅስቃሴው እጅግ አደገኛና የማያባራ ቀውስ የሚያዋልድ በመሆኑ በአስቸኳይ ይቁም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

" ' የሰራዊት አመራር ውሳኔ ' በሚል ህገ-ወጥ ጉባኤ ላካሄደ ቡድን ስልጣን ለማስረከብ የተጀመረ እንቅስቃሴ እንዲቆም " ሲል የትግራይ ክልል ጊዜዊ አስተዳደር ትእዛዝ ሰጠ።

ትእዛዙን የሰጡት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ህገ-ወጥ ተግባሩ " አስነዋሪ ፣ ለውጥ አደናቃፊና እርባና ቢስ " ሲሉ አጣጥለውታል።

ፕሬዜዳንቱ በቀጥታ ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዜዳንትና የሰራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የካቲት 26/2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ህገ-ወጥ ተግባሩ በአስቸኳይ እንዲቆም አዘዋል።

" ህገ-ወጥ ጉባኤ ያካሄደ ቡድን " ሲል የገለፁት የደብረፅዮኑ (ዶ/ር) ህወሓት የክልሉ ማእከላዊና ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የጊዚያዊ አስተዳደር መዋቅሮች በሰራዊት በመታጠቅ መቆጣጠሩ አንስቷል።

ህገ-ወጥ ድርጊቱ በተቀሩት ምስራቃዊ ፣ ደቡባዊ ፣ ደቡብ ምስራቅና መቐለ ዞኖች ለመፈፀም ያለመ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነውም ብለዋል። 

አቶ ጌታቸው ፤ " ማንኛውም ጥያቄ አለኝ የሚል የሰራዊት አመራር በህጋዊ መንገድ ጥያቄው ማቅረብ የሚችልበት ስርዓት በመጣስ በቀበሌ ፣ በወረዳ እና በመንደር ሰራዊት እያሰማሩ የመንግስት መዋቅር ለማፍረስ ማህተም ለመቀማት የሚደረግ እንቅስቃሴ ከስርዓት አልበኝነት ውጪ የሚያመጣው ፋይዳ የለም " ብለዋል።

" በተወሰኑ የሰራዊት አመራር ስም ሰራዊቱ በማሰመራት የመንግስት መዋቅሮች ህገ-ወጥ ጉባኤ ላካሄደ ቡድን ለማስረከብ የሚደረግ እንቅስቃሴ እጅግ አደገኛና የማያባራ ቀውስ የሚያዋልድ በመሆኑ በአስቸኳይ ቆሞ ህገ-ወጥ ተግባሩ እንዲፈፀም ያዘዙ የሰራዊት አመራሮች እንዲጠየቁ " ሲሉም ፕሬዜዳንቱ በደብዳቤያቸው በአፅንኦት አሳስበዋል።

ለምክትል ፕሬዜዳንትና የሰራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተፃፈው ደብዳቤ ትእዛዙ በግልባጭ ለሰላም እና የፀጥታ ቢሮ ለከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ሜጀር ጀነራል ዮውሃንስ ወ/ጊዮርጊስ ፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ አሳውቀዋል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
 
@tikvahethiopia