TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
🔈#ለጥንቃቄ

ከአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ፦

" በቅርብ ጊዚያት ውስጥ በቦሌ ቡልብላ የጨለማ ዝርፊያ በብዛት እየሰማን ነው።

ከሳምንት በፊት ሊናጋጋ ሲል 11:30 አከባቢ የቅርብ ወዳጄ የአምልኮ ተግባሩን አከናውኖ ሲመለስ ነበር ቪትዝ መኪና በርቀት በማቆም ከጀርባ መጥተው በማነቅ እና እራሱን  ስቶ እንዲወድቅ በማድረግ በኪሱ የነበረውን እስከ 60 ሺህ የሚገመት ሞባይል ወሰዱበት።

ተመሳሳይ ወንጀል በተለያየ ሰዓት በአከባቢው ሲከሰት በ15 ቀን ውስጥ ለ4ተኛ ጊዜ እንደሆነ ከተለያዩ ነዋሪዎች ጋር በነበረን ውይይት መገንዘብ ችየለሁ።

በተለይ በምሽት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ አስጠንቅቁልን። "


ከዚህ ቀደም መሰል ድርጊቶች በአዲስ አበባ ከተማ ሲፈጸሙ እንደነበር ይታወሳል።

አሁን አሁንማ መኪና በመጠቀም የሚፈጸም ዝርፊያ እየተለመደ ነው።

ከወራት በፊት መካኒሳ አካባቢ አንድ ግለሰብ ለስራ ሲወጣ እዛው ሰፈሩ ላይ በቪትዝ መኪና የመጡ ሰዎች አንገቱን ይዘው መሬት ላይ ከጣሉት በኃላ ዘርፊያ ፈጽመው እንደሄዱ መግለጻችን ይታወሳል።

እንዲሁም ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ በነጭ የቤት መኪና ታርጋ ባለው ዲኤክስ መኪና የመጡ በቁጥር 5 የሚሆኑ ስለት ያያዙ ጎረምሶች ምሽር ላይ አንድ ሰው አስቁመው ንብረት ዘርፈው መሰወራቸውንም ነግረናችሁ ነበር።

መኪና በመያዝ የሚፈጸም ዝርፊያ ስላለ የጸጥታ አካላት ልዩ ክትትል ቢያደርጉ መልካም ነው።

ውድ ቤተሰቦቻችን ሆይ እናተም በመንገዳችሁ ላይ ጥንቃቄ አድርጉ። ሁሌም ቢሆን ዙሪያ ገባችሁን ቃኙ። መኪና ይዞ የሚንቀሳቀስ ሁሉ ሃብታም ነው ማለት አይደለም። ስትንቀሳቀሱ በአትኩሮት ይሁን።

በተቻለ አቅምም የምትጠራጠሩትን ማንኛውም እንቅስቃሴ መኪና ታርጋ በቃል ለመያዝም መሞከሩ አይከፋም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ለጥንቃቄ🚨

" ሰሞኑን የተከሰተው ጉንፋን መሰል በሽታ ለመከላከል ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት " - የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ

ሰሞኑን በስፋት የሚስተዋለውን ጉንፋን መሰል በሽታ ለመከላከል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡

ቢሮ ለኢፕድ እንደገለጸው " ከሰሞኑ በስፋት የተከሰተው የጉንፋን በሽታ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነው " ብሏል።

በሽታውን ለመከላከልና እንዳይስፋፋ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ሲልም አሳስቧል።

የተከሰተው ጉንፋን መሰል በሽታ በዋነኝነት በተለይ የኢንፍሉዌንዛ ቫይረሶች አማካኝነት የሚከሰት መሆኑን ገልጾ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም ፦
- አፍንጫን፣
- ጉሮሮን
- የአየር መተላለፊያ ባንቧን እንደሚያጠቃ ቢሮው አመልክቷል።

ከወቅታዊው የቅዝቃዜና ደረቅ የአየር ፀባይ ጋር ተያይዞ ለቫይረሶች ምቹ የመራቢያ ወቅት በመሆኑ በስፋት የሚሰራጭ መሆኑ ተጠቅሷል።

ትምህርት ቤቶችና ክረምቱን ተከትሎ የሚዘጉ የሥራ ተቋማት በመከፈታቸው የሰዎች ግንኙነት ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ ስርጭቱ የጨመረ መሆኑ ተመላክቷል።

° ሳል፣
° ትኩሳት፣
° ራስ ምታት፣
° ጉሮሮን መከርከር፣
° ማስነጠስ፣
° የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣
° ከፍተኛ ድካም፣
° ብርድ ብርድ ማለት፣
° የትንፋሽ ማጠር እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ምልክቶች ናቸዉ ተብሏል።

ቫይረሱ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን በቫይረሱ የተጠቃ ግለሰብ በሚያስልበት እና በሚያስነጥስበት ጊዜ ከሚወጡ ጠብታዎች  ጋር ንክኪ፣ ቫይረሱ ያረፈበትን ቁሳቁስ ንክኪ ማድረግ ዋነኛ መተላለፊያ መንገዶች ናቸው።

በመሆኑም ፦
🔴 የእጅና የቁሳቁስ ንጽህናን በመጠበቅ፣
🔴 ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል በማድረግ፣
🔴 ስፖርታዊ እንቅስቃዜን ማዘወትር፣
🔴 መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር ማድረግ
🔴 በቂ የጸሀይ ብርሀን ማግኘትና አትክልትና ፍራፍሬ በመመገብ በሽታውን መከላከል እንደሚገባ ቢሮው ገልጿል።

በሽታው በሁሉም ሰው ላይ የሚከሰት ቢሆንም በተለይም እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት፣ አዛውንቶችና እና ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ላይ የሚጠነክር በመሆኑም በትኩረት መከላከልና ከተያዙ አስፈላጊው ክትትልና የህክምና ድጋፍ ሊያገኙ ይገባል ሲል አሳስቧል።

በመከላከያ መንገዶች ላይ ትኩረት ማድረግ በሽታውን ከመከላከል ጀምሮ በህመሙ ከተያዙ በቤት ውስጥ ከሚደረጉ ክትትሎች እና ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ማግኘት ይገባል ተብሏል።

#EPA

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

በጥንቃቄ ጉድለት ሊደርሱ የሚችሉ የተለያዩ ድንገተኛ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ሲል የአዲስ አበባ እሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መልዕክት አስተላልፏል።

ኮሚሽኑ ፤ በሰው ልጅ ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ከሚያደርሱ ድንገተኛ አደጋዎች መካከል አብዛኞቹ በጥንቃቄ ጉድለትና በመዘናጋት የሚከሰቱ ናቸው ብሏል።

በመሆኑም ለአደጋ መንስኤ የሚሆኑ የአሰራርና የአጠቃቀም ግድፈቶችን በማስወገድ ህይወትንና ንብረትን ከጉዳት ለመታደግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባራት ማከናወን እንደሚገባ ገልጿል።

➡️ በምግብ ማብሰያ /ማዕድቤት/ አካባቢ የኤሌክትሪክ፣ የቡታ ጋዝ፣ የጧፍና የከሰል ምድጃዎችን በአግባቡና በጥንቃቄ ይጠቀሙ።

➡️ በገበያ ማእከላት የገበያተኛውን ቀልብ ለመሳብ የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክስ ዲኮሬሽኖች ቃጠሎ እንዳያስነሱ ይጠንቀቁ።

➡️ ሻማና ጧፍ በሚጠቀሙበት ወቅት ከተቀጣጣይ ነገር ያርቁት።

➡️ ካም ፋየር የሚያዘጋጁ ከሆነ ከአካባቢው ከመራቅዎ በፊት በደንብ መጥፋቱን ያረጋግጡ።

➡️ በኤሌክትሪክ እሳት የተነሳ እሳትን ሃይሉን ከምንጩ ሳያቋርጡ በወሃ ለማጥፋት አይሞክሩ።

➡️ ርችቶችን ሲተኩሱ በነዳጅ ማደያ ፣ በሳር ቤቶችና በሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች ላይ እንዳያርፍ ይጠንቀቁ።

➡️ ጠጥተው አያሽከርክሩ ለመዝናናትዎ በገደብ ይስጡ።

➡️ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ የተለያዩ መሳሪያዎች በአንድ ሶኬት ላይ ደራርበው አይጠቀሙ።

➡️ ለአደጋ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን በማስወገድ/በመፍታት የሰው ህይዎትን እና ንብረትን መታደግ ያስፈልጋል።

ኮሚሽኑ ከአቅም በላይ ለሆነ ማንኛውም የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም የአምቡላንስ አገልግሎትን በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ሳምንቱን ሙሉ 24 ሰዓት በመደወል ማግኘት እንደሚቻል አሳውቋል።

° ነፃ የስልክ መስመር 👉 939
° ማዕከል 0111568601/0111555300

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር / ኢንሳ አሳውቋል።

ኢንሳ በዛሬው ዕለት በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል አሳስቧል።

ኢንሳ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች በተለያዩ ማስገሪያ (ፊሺንግ ሊንክ) አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ ገልጷል።

በመሆኑንም ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከሚያውቁትም ሆነ ከማያውቁት) ግለሰብ ሊንክ ቢላክ መክፈት ተገቢ እንዳልሆነ እና ወዲያውኑ ማጥፋት እንደሚገባ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake በድጋሚ የአዋሽና አካባቢው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " አስፈሪ ነበር " ያሉት የመሬት መንቀጥቀጥ ከደቂቃዎች በፊት መከሰቱን ጠቁመዋል። " የመሬት መንቀጥቀጥ ድግግሞሹ እየባሰበት ነው " ያሉ ሲሆን " አላህ ይዘንልን ምናደርገው ጠፋን " ሲሉ ገልጸዋል። " ነገሩ አዲስ አበባ እና ሌሎችም ቦታዎች ካልተሰማ ትኩረት እያገኘ አይደለም። ድግግሞሹ እኮ ብዙ ነው በሚዲያ ከሚገለጸውም…
#ለጥንቃቄ🚨

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ?

➡️ ከቤት ውጭ ከሆኑ ፦ ከዛፎች ፣ ከሕንፃዎች ፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።

➡️ በቤት ውስጥ ከሆኑ ፦ በበር መቃኖች ፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

➡️ በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር ፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

➡️ መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ ፦ የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።


#Ethiopia
#የአአእሳትናአደጋስራአመራርኮሚሽን

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

(በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቀረበ)

ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ምንድነው ?

ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ስልካችን ላይ ከማህበራዊ ትስስር ድረ-ገፆች በምንጭናቸው መተግበሪያዎች አማካኝነት ወደ ስልካችን ሰርጎ የሚገባ ሲሆን እንደ ቴሌግራም፣ ዋትስአፕ፣ የመሳሰሉ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በስፋት እየተሰራጨ ጥቃትን የሚሰነዝር
#መተግበሪያ ነው፡፡

ጉዳቱ ምንድነው ?

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመረጃ ሥርዓት ደህንነት ክፍል ፋርማ ፕላስ (Pharma+) የተሰኘውን መተግበሪያ ጉዳት አምጪ እንደሆነ ገልጿል።

ፋርማ ፕላስ (Pharma+) ከማህበራዊ ትስስር ገጾች አውርደን በምንጭናቸው ሌሎች መተግበሪያዎች ጋር በመለጠፍ ወደ ስልካችን ሰርጎ በመግባት ፦
- የስልካችንን ስክሪን ማየት፤
- አጭር የጽሑፍ መልዕክቶችን ማንበብ፣
- ሀሰተኛ የመግቢያ ገጾቸን በማዘጋጀት
- የይለፍ ቃሎችን መመንተፍ እና የመሳሰሉ የግል መረጃዎችን የሚሰርቅ መተግበሪያ ነው፡፡

የፋይናንሻል ግብይቶችን ከተጠቂው እውቅና ውጪ መፈፅሙ እና ስልካችን ላይ ተጭነው ካሉት መተግበሪያዎች ውስጥ መደበቁ ማየት ስለማንችል ለመከላከል በጣም አዳጋች ነው።

እንዴት ራሳችንን ከፋርማ ፕላስ (Pharma+) እንጠብቅ ?

➡️ ካልታመኑ ምጮቾች ማንኛውንም መተግበሪያ ስልኮት ላይ አይጫኑ፤
➡️ በማህበራው ገጽ አማካኝነት የሚላክሎትን ማንኛውንም ማስፈንጠሪያ ወይም መተግበሪያ ምንነቱን ሳያረጋግጡ አይክፈቱ፤
➡️ ብቅ ባይ (Pop up) ማስታወቂያዎችን ወይም አጠራጣሪ ገጾችን በፍጹም አይክፈቱ፤
➡️ እንደ ጎግል ፕሌይ፣ አማዞን፣ አፕስቶር ወይም ሳምሰንግጋላክሲ ስቶር ጥብቅ የደህንነት ፍተሻዎችን የሚያደርጉ ይፋዊ የመተግበሪያ ማከማቻዎችን ብቻ ይጠቀሙ።

ትክክለኛ የስልክ መተግበሪያዎችን በመጠቀም እራስዎትን ይጠብቁ።

(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

" የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ስላሉ ተጠንቀቁ " - ፖሊስ

በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስና የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው በተለምዶው " ሿሿ " የተባለውን ወንጀል ፈፅመዋል የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ተጠርጣሪዎቹ  ብዛታቸው 4 ሲሆን የወንጀል ድርጊቱን ፈፅመዋል ተብለው በቁጥጥር ስር  የዋሉት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አካባቢ ነው።

የግል ተበዳይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቄራ  እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሄደው የጤና ምርመራ ለማድረግ ዘነበወርቅ አደባባይ ትራንስፖርት እየጠበቁ ነበር።

ግለሰቦቹም በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 B-13788 አ.አ በሆነ የቤት መኪና የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለውና የግል ተበዳይን ተሽከርካሪው ውስጥ ያገቧቸዋል።

በኃላም " ቄራ ድረስ ከምትሄጂ እዚሁ ቅርብ ቦታ የጤና ምርመራ ማድረግ ትችያለሽ  እናሳይሻለን " በማለት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ታቦት ማደሪያ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ ቅያስ ውስጥ ይገባሉ።

እዛም በማስገባት በእጅ ቦርሳ ውስጥ የነበረ 7,900 ጥሬ ገንዘብ ይዘው ለመሰወር ሙከራ ሲያደርጉ በአየር ጤና አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ግለሰቦቹ ወንጀሉን ፈፅመው በተሽከርካሪ ለማምለጥ በሚሞክሩበት ሰዓትም  አንድ ግለሰብ ላይ አደጋ ማድረሳቸው ተጠቁሟል።

ከተያዙት 4 ተጠርጣሪዎች ውስጥ አንዷ ሴት ስትሆን አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ግለሰቦቹ ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ወንጀል በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፓስተር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደነበርና ደጋጋሚ ወንጀል ፈፃሚዎች መሆናቸውን ጅምር የምርመራ መዝገቡ ያመለክታል ተብሏል።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለውና የተለያዩ ማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀም ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦችን በህግ ለማስቀጣት ህብረተሰቡ የራሱን ጥንቃቄ እንዲያደርግና ጥቆማ በመስጠት የተለመደውን ትብብር  እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia