TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የመሬት መንቀጥቀጡ የቦታ ለውጥ አድርጓል ?

" በአንድ አካባቢ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው ያለው እንጂ የቀረበ ነገር የለም " - ፕ/ር አታላይ አየለ

በትላንትናው ዕለት በቀን፣ በምሽትና በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ተደጋጋሚ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጦች መከሰታቸው ዓለም አቀፍ ጁኦሎጂካል ተቋማት ዘግበዋል።

ትላንት ምሽት 2:10 የተከሰተው እና ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ከተሰማው በሬክተር ስኬል 5.0 ሆኖ ከተመዘገበው መንቀጥቀጥ በተጨማሪ ለሊት 7:20 ላይ 5.1 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አስታውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በተጠቀሰው መጠን መከሰቱን እና ዛሬ ጠዋት 2:11 ላይም ሌላ መንቀጥቀጥ በመታየቱ የመተንተን ስራ እየተሰራ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ህዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም፤ የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር አታላይ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ትላንት ለሊት 7:20 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከደብረ ሲና 52 ኪሜ ርቀት ላይ ምሽት ላይ የተከሰተው ደግሞ ከአዋሽ 14 ኪሜ ርቀት ላይ የተከሰተ ነው መባሉ ከዚህ ቀደም ይከሰት ከነበረበት የአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የቦታ ለውጥ አለ ማለት አለመሆኑን አስረድተዋል።

ተመራማሪው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ ?

" ትላንትና ከሰዓት ጀምሮ በጣም የተደጋጋመ ከፍተኛ መጠን ያለው ከ4.6 ጀምሮ እስከ 5.0 የተመዘገበ መንቀጥቀጥ ተከስቷል ፤ ነገር ግን ደብረ ሲና ሲል ከፈንታሌ በወፍ በረር ሲለካ ነው ከተለያየ አቅጣጫ በማየት ነው እንጂ መነሻው ስለተቀየረ አይደለም።

አንድ አካባቢ ላይ መሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት በአቅራቢያው ያለው ከተማ የትኛው ነው ? የሚለው ይታያል ከዛ የተለያዩ ከተሞችን እንደ ሪፈረንስ ይጠቅስና ከዛ ከተማ ምን ያህል ነው የሚርቀው የሚለውን ሪፈር ያደርጋል፤ እንደዛ ሲሆን ሌላ ሰው መንቀጥቀጡ ለዛ ከተማ ቀርቧል ማለት ነው የሚል ስጋት ሊያድርበት ይችላል ነገር ግን እስካሁን የተቀየረ ነገር የለም፤ ፈንታሌ ዙሪያ ነው እንቅስቃሴው እየተታየ ያለው።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ እና የጀርመኑ የጂኦ ሳይንስ ተቋማት የሚጠቀሙት ዳታ አውቶማቲክ ነው ሲስተሙ ቶሎ አናላይዝ አድርጎ የተከሰተበትን መጠን እና አካባቢ ከርቀት ጋር ይናገራል ነገር ግን ይህ አይነቱን አዘጋገብ የሚከተሉት ለማህበረሰቡ በምን ያህል ርቀት ላይ ነው የተከሰተው የሚለውን ለማስረዳት ነው።

ለምሳሌ፦  አንድ ብቻ አይደለም የተለያዩ ቦታዎች ይጠቅሳሉ  ከመተሃራ፣ከደብረሲና ፣ከደብረ ብርሃን እና ከአዲስ አበባስ ምን ያህል ርቀት ላይ ይገኛል ሊል ይችላል በአንድ አካባቢ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው ያለው እንጂ የቀረበ ነገር የለም።

አዲስ ነገር አይደለም ስንመዘግብ የኖርነው ነገር ነው ነገር ግን መሃንዲስም፣ ኢንቨስተርም ሆነ የሚመለከተው አካል ጆሮ ሰጥቶ ጥንቃቄ አድርጎ አያውቅም አሁን የሚከሰተውንም መአት እንደተከሰተ አድርጎ የሚያወራ አለ እንደዛ አይደለም በተለያየ ጊዜ ይመዘገባል።

በ1997 በአፋር ታይቶ የማይታወቅ የቅልጥ አለት እንቅስቃሴ ነበር ብዙ አለም አቀፍ ሳይንቲስቶች ሁሉ መጥተው አብረን የሰራናቸው ስራዎች አሉ፣ ፈንታሌም በፈረንጂዎቹ 1981 እንደ አሁኑ 3 እና 4 ወር የቆየ የቅልጥ አለት እንቅስቃሴ ነበር።

የመረጃ ውንዥብር እየተፈጠረ ነው ሳይንቲስት የምንለው ማነው ? ታማኝነቱስ ምን ያህል ነው ?የሚለው አስቸጋሪ ሆኗል ያልሆነውን ሆኗል እያሉ የሚያወናብደውም ብዝቷል ተማረ የምንለውም መሬት ላይ ያለውም ህብረተሰብ።

መሬት በራሷ ጉዞ እየሄደች የምታስተነፍሰው ሃይል ነው ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም ቦታውም፣ በምን ያህል ርቀት ላይ እንደሆነ ይታወቃል በተለይ አዲስ አበባ ያለ ሰው ምንም ሊደነግጥ አይገባም።

ከትላንት እኩለ ቀን ጀምሮ ጎላ ጎላ ያሉት መንቀጥቀጦች የመደጋገም ፍጥነታቸው ጨምሯል ቀጣይነትም ያለው ሊሆን ይችላል እየተከታተልን እየመዘገብን እንገኛለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#AAU
#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia