TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#OFC  #OLF

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአራት ቀናት በአዲስ አበባ ከተደረገ ምክክር በኋላ በኦሮሚያ እየተከሰቱ ያሉ የፖለቲካ፣ የጸጥታ እና የሰብአዊ ቀውሶችን ለመፍታት አብሮ ለመስራት  መስማማታቸውን ኦፌኮ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ኦፌኮ በመግለጫው መፍትሔና እንደ አቋም የተወሰዱ ዋና ዋና ኃሳቦችን አጋርቷል።

በዚህም፦

- በክልሉ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለመፍታት እና ሰላም ለማስፈን ሁለቱ አካላት ማንኛውንም መንገድ በመጠቀም ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል።

- ኦፌኮ እና ኦነግ ሌሎች ዋና ዋና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሁሉን አቀፍ "የኦሮሚያ ብሔራዊ የሽግግር አንድነት መንግስት/ Transitional National Unity Government of Oromia" ለመመስረት አብረው ለመስራት ተስማምተዋል።

° የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA) የኦሮሞ ነጻነት ተዋጊዎች እንደሆኑና የሽግግር መንግሥት ውስጥ  ሰላምና ደህንነት የኦሮሚያን ወሰን የማስከበር ኃላፊነት እንዲወጣ እንደሚደረግ አመላክቷል።

- አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ መሆኗን በግልጽ እንዲቀመጥና ኦሮሚያ ከተማዋን በቀጥታ የማስተዳደር መብት እንዲኖረው እንዲሁም ከኦሮሚያ ተወስደዋል የተባሉ አከባቢዎችን በዲፕሎማሲያዊ እና ሕጋዊ መንገድ ለማስመለስ ተስማምተዋል።

- የገዳ/ ሲንቄ ሥርዓቶችን ለማጠንከርና በኦሮሞ ባህል ላይ የተመሰረተ የአስተዳደር መዋቅር ለመዘርጋት ተስማምተዋል።

- በገዳ ሥርዓት አስተምህሮ መሰረት በኦሮሚያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ብሄረሰቦች ያለምንም ፍርሃትና አድልዎ እንዲኖሩ ለማስቻል እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

- ኦሮሚያ በሁሉም የፌደራሉ መንግስት መዋቅር ማለትም በፍትሕ ተቋማት፤ በመከላከያ ሰራዊት፤ በፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የበጀት (የሀብት) ምደባ ላይ ተገቢው ድርሻ እንዲኖረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ኦፌኮ በመግለጫው ከፌዴራል መንግሥት ጋር ለመነጋገር ክፍት መሆኑን የጠቆመ ሲሆን ለሚመጡ ማስፈራሪያዎች፣ ማታለያዎች ወይም ለማይፈጸሙ ተስፋዎች ጥንቃቄ አደርጋለሁ ብሏል።

አክሎም ከመንግስት ጋር የሚደረግ ማንኛውም ስምምነት ተጨባጭ በሆነ ነገር እንዲሁም በጊዜ ገደብ መመዘን አለበት ያለ ሲሆን " ተራ ተስፋዎች አሁን ተቀባይነት የላቸውም " ሲል ገልጿል።

በሰሞነኛው የኦፌኮና ኦነግ መድረክ አባገዳዎች፣ ሃደሲንቄዎች፣ የወጣቶች ተወካዮች፣ የፓርቲ መሪዎች ፣ ታዋቂ ሰዎች ተገኝተው ነበር።

ከዚህ ባለፈ ለረጅም ጊዜ ከእይታ ርቀው የነበሩት የኦነግ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ታይተዋል።

🔗 ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM