TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፣ በአትሌት ዴሬሳ ገለታ ፣ በአትሌት ታምራት ቶላ የተወከለችበት የፓሪስ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር እየተካሄደ ይገኛል። Via @tikvahethsport @tikvahethiopia
#Ethiopia የወንዶች ማራቶን ሊጠናቀቅ 9 ኪሎ ሜትር ይቀረዋል።

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ታምራት ቶላ እና ደሬሳ ገለታ ውድድሩን ከፊት ሆነው በመምራት ላይ ይገኛሉ።

ወቅታዊ ደረጃቸው 1ኛ ታምራት ቶላ ደሬሳ ገለታ 2ኛ ናቸው።

ታምራት በርቀት እየመራ ነው። ጥሩ ጥንካሬና ጉልበት ያለውም ይመስላል።

መጨረሻውን ያሳምረው። ውድድሩ በዚህ ካለቀ የወርቅ ሜዳሊያ ልናገኝ እንችላለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ 🥇 ወርቅ አገኘች !! @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ወርቅ አገኘች።

ሀገራችን በኦሎምፒኩ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ በማራቶን በጀግናው አትሌትላችን ታምራት ቶላ አማካኝነት አግኝታለች።

ምንም እንኳን በፓሪስ እየተመዘገበ ያለው ውጤት አንገት የሚያስደፋ ቢሆንም ዛሬ በወንዶች ማራቶን የተገኘው ውጤት የሚያኮራ ነው።

አትሌት ታምራት እጅግ በሚደንቅ ብቃት ነው ወርቁን ወደ ኢትዮጵያ እጅ ያስገባው።

አትሌት ታምራት ተጠባባቂ የነበረ ሲሆን የአትሌት ሲሳይ ለማን መጎዳት ተከትሎ ነው በውድድሩ ሊሳተፍ የቻለው።

@tikvahethiopia @tikvahethsport
#Ethiopia

በማራቶን ውድድር ላይ " ተጠባባቂ ነህ " ተብሎ የተያዘውና ለውድድሩ የተመረጠ ሌላ አትሌት መጎዳቱን ተከትሎ ሀገሩን ወክሎ የተሳተፈው ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ ለሀገሩ ኢትዮጵያ ወርቅ ማምጣት ብቻ ሳይሆን በሚደንቅ ብቃት የኦሎምፒክ ሪከርድም ጭምር ነው የሰበረው።

ጀግናው አትሌት ታምራት ከአትሌት ገዛኸኝ አበራ በኋላ (ከ24 ዓመታት በኃላ) ነው የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ለሀገራችን ያስገኘው።

ሌላው አንጋፋው ኢትዮጵያ ሁል ጊዜ በስራው የምታመሰግነው የ42 ዓመቱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 39ኛ ደረጃ ይዞ እጅግ ከባድ የነበረውን የፓሪስ ማራቶን አጠናቋል።

አትሌት ደሬሳ ገለታም 5ተኛ ደረጃ በመውጣት እጅግ በጣም አበረታችና ተስፋ ሰጪ ውጤት አስመዝግቧል።

ምንም እንኳን ዛሬ በወንዶች ማራቶን የተገኘው ውጤት አስደሳችንና የሚያኮራ ቢሆንም በፓሪስ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ኢትዮጵያን የሚመጥናት አይደለም።

በጭቅጭቅና ንትርክ በተሞላው በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ ያገኘችው እስካሁን 3 ሜዳሊያ ብቻ ነው። 1 ወርቅ እና 2 ብር ብቻ።

የአትሌቲክሱ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ ያሉ ችግሮች እና ኢትዮጵያን ዝቅ ያደረጉ ነገሮች ሁሉ ተፈትሸው መለወጥ እንዳለባቸው የፓሪስ ኦሎምፒክ በግልጽ አመላክቷል።

ከሚዲያ በዘለለ ስለዚህ ሀገር አትሌቲክስ ሁሉም " የሀገር ክብር ያሳስበኛል " የሚል ቁጭ ብሎ ተነጋግሮ በአስቸኳይ ለውጥ ማምጣት አለበት። እንዲህ ከቀጠለ በዓለም ደረጃ የነበረን ክብር የማናጣበት ምክንያት የለም።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

" የተወሰኑ ግለሰቦች ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን የላኩት ማስረጃ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( #ህወሓት ) ምክትል ሊቀመንበርና  የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅሬታ ደብደቤ አቀረቡ።

ምክትል ሊቀ-መንበሩ ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም በህወሓት " በልዩ ሁኔታ " የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ዙሪያ ነው ለቦርዱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት።

" በህወሓት የምዝገባ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተላከው ደብዳቤ ማእከላዊ ኮሚቴ የማያውቀው በግለሰቦች የተላከ ነው " ብለዋል።

ም/ ሊቀ መንበሩ አቶ ጌታቸው ፥ " የተወሰኑ ግለሰቦች ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን በመሆን የፈረሙት እንጂ እኛ ለምዝገባ ብለን የፈረምነው ማንኛውም ሰነድ የለም " ሲሉ አክለዋል።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት አስመልክቶ ለተወሰኑ ግለሰቦች የሰጠው እውቅና የተጭበረበረ በመሆኑ ዳግም ሊያጤነው ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የአንዲት ታዳጊ ህይወት አልፏል !

በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የሐዋሳ ቅርንጫፍ በመደበኛው የፓይለት ስልጠና ልምምድ ላይ የነበረ ቀላል የተማሪዎች መለማመጃ አውሮፕላን (Dimond DA40NG) አየር ላይ ሳለ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አርሲ ነጌሌ አካባቢ ለማረፍ መገደዱን የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ ገልጿል።

" ይህንን ተከትሎ በመደበኛ ስልጠናው ላይ የነበሩት አስተማሪውና ተማሪው የመለማመጃ አውሮፕላኑ ሕብረተሰቡ ላይ አደጋ በማያደርስ ሁኔታ ለማሳረፍ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም ለማረፍ በተደረገው ጥረት መሬት ላይ በነበረች አንዲት ታዳጊ ላይ ጉዳት ደርሷል " ብሏል።

በዚህም የታዳጊዋ ህይወት አልፏል።

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ፥ የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ በሚመለከታቸው አካላት በመጣራት ላይ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
Within the Jasiri Talent Investor Program, you’ll meet like-minded individuals and potential co-founders from diverse backgrounds, and together, you will form a co-founding team to build high growth venture from scratch. 🤝🚀

Apply today to join cohort 7 at https://jasiri.org/jasiri-talent-investor/.

Follow our telegram channel @Jasiri4Africa
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰጥቶታል። @tikvahethiopia
#TPLF

" አልቀበልም ! " - ህወሓት

ህወሓት የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ የሰጠውን የምዝገባ ውሳኔ አልቀበልም አለ።

ድርጅቱ " የተሰጠኝ የምዝገባ ውሳኔ ከተካሄዱት የሁለትዮሽ ወይይቶችና መግባባት ወጪ ነው፤ ስለሆነም ወደ ነባሩ እውቅናዬ የማይመልስ ውሳኔ አልቀበልም " ብሏል ዛሬ ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም ባወጣው ባለ ሁለት ገፅ የፅሑፍ መግለጫ።

ህወሓት ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዞ ቀርቧል።

ትላንትና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፓርቲዎች " በልዩ " ሁኔታ ሲመዘገቡ የሚሰጥ ሕጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠቱ ይታወሳል።

ይህን ውሳኔ ነው ህወሓት " አልቀበልም " ብሎ መግለጫ ያወጣው። " እኛ የምፈልገው የተሰረዘው ህጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስልን ብቻ ነው " ብሏል።

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የወንዶች 5000 ሜትር ፍፃሜ እየተካሄደ ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ፦ 🇪🇹 በአትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት 🇪🇹 በአትሌት አዲሱ ይሁኔ 🇪🇹 በአትሌት ቢኒያም መሀሪ ተወከላለች። መልካም ዕድል ! More @tikvahethsport @tikvahethiopia
ሜዳሊያ ውስጥ አልገባንም።

ኖርዌይ ወርቅ፣ ኬንያ ብር፣ አሜሪካ ነሐስ አግኝተዋል።

የሀገራችን አትሌቶች ሀጎስ ገብረህይወት 5ኛ፣ ቢንያም መሀሪ 6ኛ ፣ አዲስ ይሁኔ ደግሞ 14ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የሴቶች 1500 ሜትር ፍፃሜ ጀምሯል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ፦ 🇪🇹 በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 🇪🇹 በአትሌት ድርቤ ወልተጂ ተወከላለች። እስቲ በዚህ እንኳን ይቅናን 🙏 @tikvahethiopia
በዚህም ምንም ሜዳሊያ አላገኘንም።

የኬንያዋ ኪፕዬጎን ወርቁን ወስዳዋለች።

አውስትራሊያ ብር እንዲሁም እንግሊዝ ነሐስ አግኝተዋል።

ድርቤ ወልተጂ 4ኛ እንዲሁም ጉዳፍ ፀጋይ 12ኛ በመሆን አጠናቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በዚህም ምንም ሜዳሊያ አላገኘንም። የኬንያዋ ኪፕዬጎን ወርቁን ወስዳዋለች። አውስትራሊያ ብር እንዲሁም እንግሊዝ ነሐስ አግኝተዋል። ድርቤ ወልተጂ 4ኛ እንዲሁም ጉዳፍ ፀጋይ 12ኛ በመሆን አጠናቀዋል። @tikvahethiopia
#Kipyegon : የኬንያዋ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን በሶስት (3) ተከታታይ ኦሎምፒክ በ1500 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሯ ገቢ በማድረግ ታሪክ ሰርታለች።

ዛሬ በ 3:51.29 በመግባት የኦሎምፒክ ሪከርድ ሰብራለች።

አትሌቷ የ1500 ሜትር የዓለም ሪከርድ ባለቤትም ናት።

#TikvahEthiopia #WA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ፤ " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ " ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ህወሓት ባወጣው መግለጫ ፥ " የስራ ኃላፊዎቼ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማካሄድ ሕጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል።

" በአፍሪካ ህብረት ፓናል ውይይትም ይህ ጉዳይ ተነስቶ ህጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት ስምምነት ተደርሶበታል " ሲል ገልጿል።

ይህን ተከትሎ " ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ ሰውነታችን ወደነበረበት እንዲመለስልን ብቻ በሀምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጥያቄ አቅርበናል " ብሏል።

ሆኖም " ቦርዱ የፕሪቶሪያውን ስምምነት፣ ከዚህ በፊት በሌሎች የፌደራል ተቋማት የተሰጡትን ውሳኔዎች፣ ሌሎች ህጎችና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረሱ መግባባቶች ወደጎን በመተው ጥያቄውን ' በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ' መልሷል " ሲል ገልጿል።

ይህን ተከትሎ ህወሓት " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ ሆኗል " በማለት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ " አልቀበልም " ሲል አሳውቋል።

" በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ የተካተቱት ዝርዝር ይዘቶች አዲስ በወጣው ማሻሻያ ህግ መሰረት የተቀመጡና ካቀረብነው ጥያቄ ጋር የማይገናኙ ናቸው " ሲልም አክሏል።

" የቦርዱ ውሳኔ ህጋዊ ሰውነቴን ወደነበረበት እንዲመለስ የቀረበውን ጥያቄ የማይመልስ ፤ የነበሩ ውይይቶችን የሚቃረኑ ዝርዝር ይዘቶች የሚጭንብን በመሆኑ አልተቀበልኩትም " ያለው ህወሓት " ጥያቄያችን እስኪመለስ ድረስ የፓርቲው ሕገ ደንብ በሚፈቅድልን መልኩ ተያያዥ ስራዎችን እናከናውናለን " ብሏል።

የፌደራል መንግስቱም የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመከሩበት ወቅት ፦

- TPLF እና መሰል ፓርቲዎች በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ሕጋዊ ፓርቲ እንዲሆኑ አዋጅ መሻሻሉ፤
- አቃቤ ህግ ለምርጫ ቦርድ መጻፍ የነበረበትን ማለትም ስራውን ሰርቶ የሚያጣራውን አጣርቶ በሕጋዊ መንገድ እንዲፈቅድላቸው፤
- የአስፈጻሚውን ስራ 100% መሰራቱን፤
- ፓርቲ ለፓርቲ ፤ የመንግሥት ለመንግሥት ውይይቶች ላይ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ እንደተሰጠ፤
- TPLF ምርጫ ቦርድ ሄዶ የሚጠበቅበትን ዶክመንት አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ጉባኤ ማድረግ እንዳለበት ፤ ይህን ባያደርግ ምርጫ ቦርድም ካልተቀበለው፤ TPLFን ሕጋዊ ፓርቲ ካላለው ፦
በምርጫ ሊሳተፍ እንደማይችል ፤
መንግሥትም ሊሆን እንደማይችል ይህ ደግሞ ተመልሶ ጦርነት ውስጥ የሚያስገባ እንደሆነ፤
- ተመልሶ ጦርነት ውስጥ ከመግባት በተበጀው ሕግ ፤ በተደረሰው ስምምነት ህወሓት የቀረውን ጉዳይ አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ጉባኤ አካሂዶ ፓርቲውን መልሶ ወደ ፖለቲካ ስርዓት መመለስ እንዳለበት መግለጻቸው ይታወሳል።

#Ethiopia #TPLF #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia