TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF " እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ?  "  - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ ሰጥተው ነበር። አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ? - የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት…
#Tigray #TPLF

"ሊካሄድ በታቀደው ጉባኤ አልሳተፍም ! " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር ፕሬዜዳንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ ዛሬ ዓርብ ነሀሴ 3/2016 ዓ.ም ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፣ ለድርጅቱ የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ተኽለብርሃን ኣርኣያ በፃፉት ደብዳቤ በጉባኤው እንደማይሳተፉ አረጋግጠዋል።

ፕሬዜዳንቱ በደብዳቤያቸው የድርጅቱን ከፍተኛ አመራሮች ውሳኔ በጣሰው ጉባኤና የምዝገባ ሂደት እንደማይሳተፉ በመግለፅ " ህወሓት መዳን የሚችለው አባላቱና አመራሩ በሚያካሂዱት ጤናማ እንቅሰቃሴ ነው " ሲሉ አስታውቀዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰጥቶታል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
አቢሲንያ በየዕለቱ እያስገረመን ነው፤ አሁን ATM ካርድ ቢረሳ ስልክ የATM ካርድን ስራ ይሰራል።
መተግበሪያውን በማውረድ ካርዶትን ዲጂታል ቪዛ ካርድ ያድርጉ።

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#DigitalVisacard #Visa #ApolloVisacard #BoAVisacard #Visacard #Digitalethiopia #Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#Ethiopia

የ10,000ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ጀምሯል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ፦
🇪🇹 በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 በአትሌት ጽጌ ገብረሰላማ እና
🇪🇹 በአትሌት ፎቴን ተስፋይ ተወክላለች።

መልካም ዕድል ! ይቅናን !

@tikvahethiopia
ዛሬም ያው ነው ! ሜዳሊያ ውስጥ አልገባንም።

ኬንያ ወርቁን ወስዳዋለች።

ጣልያን ብሩን አግኝታለች።

ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፋን ሀሰን 3ኛ በመውጣት ነሀስ ለሀገሯ አስገኝታለች።

ከቀናት በፊት ሲፋን ለሀገሯ የነሃስ ሜዳሊያ ማስገኘቷ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬም ያው ነው ! ሜዳሊያ ውስጥ አልገባንም። ኬንያ ወርቁን ወስዳዋለች። ጣልያን ብሩን አግኝታለች። ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፋን ሀሰን 3ኛ በመውጣት ነሀስ ለሀገሯ አስገኝታለች። ከቀናት በፊት ሲፋን ለሀገሯ የነሃስ ሜዳሊያ ማስገኘቷ አይዘነጋም። @tikvahethiopia
#Ethiopia

በሴቶች የ10,000 ሜትር ፍጻሜ ላይ ምንም አይነት ሜዳሊያ አለማግኘታችን ብቻ ሳይሆን ደረጃችን እጅግ በጣም ዝቅ ያለ ነው።

ጉዳፍ ፀጋይ 6ኛ ፣ ፎቴን ተስፋይ 7ኛ እንዲሁም ጽጌ ገብረሰላማ 10ኛ ደረጃን በመያዝ ነው ያጠናቀቁት።

በዘንድሮ የፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚይዟቸው ደረጃዎች እጅግ በጣም የሚያስደነግጡ ናቸው።

በአትሌቲክሱ ዓለም ሀገራችን #ኢትዮጵያ ስሟ በዚህ መልኩ አይታወቅም ነበር።

@tikvahethiopia
አሁን ፓሪስ ላይ ምን ቀረን ?

እስካሁን ያለው የፓሪስ ኦሎምፒክ ለእኛ አንገታችንን ያስደፋን ነው።

ውድድሩ ሊጠናቀቅ የቀናት እድሜ ነው የቀሩት።

በኦሎምፒኩ እስካሁን ድረስ ሜዳሊያ ውስጥ የገቡት 80 ሀገራት ሲሆኑ ሀገራችን ኢትዮጵያ በሁለት የብር ሜዳሊያ 67ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ሁለቷም የብር ሜዳሊያ የመጣችው በበሪሁ አረጋዊ እና ፅጌ ድጉማ ነው።

የቀረን ውድድር ፦
➡️ የሴት እና ወንድ ማራቶን
➡️ 5000ሜትር ወንድ ፍጻሜ
➡️ 1500ሜትር ሴቶች ፍጻሜ ብቻ ነው።

Via
@tikvahethsport 
ቪድዮ ፦ በብራዚል 58 መንገደኞችንና 4 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ የነበረ አውሮፕላን ተከስክሶ የሁሉም ህይወት አልፏል።

አውሮፕላኑ ንብረትነቱ የቫፖስ ሲሆን የተከሰከሰው በሳኦፖሎ ግዛት ነው።

ከካስካቬል ወደ ሳኦፖሎ ከተማ ወደሚገኝ ዋናው ኤርፖርት ሲበር ነበር።

አውሮፕላኑ ' ቪንሄዶ ' የተባለ ከተማ ላይ ሲደርስ በቪድዮው እንደሚታየው ከላይ ወደታች ወርዶ ተከስክሷል።

በዚህም አንድም የተረፈ ሰው የለም።

የአደጋው መንስኤ ለጊዜው አልታወቀም።

ቪድዮ ክሬዲት ፦ BNO News

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ዘንባባውን ገጭቶ ጉዳት ስላደረሰ 347 ሺህ 262 ብር ቀጥተነዋል " - መንግሥት

በአዲስ አበባ፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02 ቦሌ መንገድ በተለምዶ ' ቦሌ ማተሚያ ' እየተባለ በሚጠራው ቦታ በሀምሌ 29/2016 ዓ.ም አንድ ተሽከርካሪ ዘንባባ ገጭቷል።

አደጋው እንዴት ? እና በምን ሁኔታ ? እንደተፈጠረ ምንም የምርመራ ውጤት ይፋ አልሆነም።

ነገር ግን " በተሰራው የኮሪደር ልማት ላይ ዘንባባ ገጭቶ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት አድርሷል " የተባለው አሽከርካሪ በዛሬው እለት በህግ ጥሰት መቀጣቱን ወረዳው አሳውቋል።

በዚህም፣ አሽከርካሪው በ347 ሺህ 262 ብር እንደተቀጣና ቅጣቱንም በባንክ እንዳስገባ ነው የተገለጸው።

(ገንዘቡ የገባበት እና ለማን እንደገባ የሚያሳይ ደረሰኝ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

⚽️የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከ5 ቀናት በኋላ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ!

አዳዲሱ ተጫዋቾች ያስፈረሙት ቡድኖች ሊጉን ለመጀመር ዝግጁነታችውን አሳውቀዋል!

🤔እናንተስ ከሊጉ የትኛውን ተጫዋች ለማየት ጓግታችኋል?

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን  ወደ ሜዳ ያሳድጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#Ethiopia

ዛሬ ፓሪስ ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት ሦስት የፍጻሜ ውድድሮች ይደረጋሉ።

አሁን 3:00 ለይ የወንዶች የማራቶን ውድድር የሚካሄድ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ፦

🇪🇹 በአንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
🇪🇹 በአትሌት ዴሬሳ ገለታ
🇪🇹 በአትሌት ታምራት ቶላ ትወከላለች።

ምሽት 2:50 የወንዶች 5000 ሜትር ፍፃሜ የሚካሄድ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ፦

🇪🇹 በአትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት
🇪🇹 በአትሌት አዲሱ ይሁኔ
🇪🇹 በአትሌት ቢኒያም መሀሪ ትወከላለች።

ምሽት 3:15 የሴቶች 1500 ሜትር ፍፃሜ ይደረጋል ፤ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ
🇪🇹 በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 በአትሌት ድርቤ ወልተጂ ትወከላለች።

@tikvahethiopia @tikvahethsport