TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የውጪ ምንዛሪ ቢሮ ፍቃድ መስጠት የሚያስችለውን ሂደት መጨረሱን የብሔራዊ ባንክ አሳውቋል። ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መደበኛ ባልሆነ መንገድ የውጪ ምንዛሪ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ህጋዊ ሆነዉ ፍቃድ አውጥተዉ መስራት እንዲችሉ መፍቀዱን ተከትሎ ከወዲሁ ብዙ ሰዎችና ኩባንያዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ ገልጿል። የውጪ ምንዛሪ ገበያ ውስጥ የሚሳተፉ በፊት ባንኮች ብቻ የነበሩ ቢሆንም አሁን…
#NBE : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የስራ ፈቃድ ሰጠ።

የስራ ፍቃድ የተሰጣቸው ፦

1. Dugda Fidelity Investment PLC
2. Ethio Independent Foreign Exchange Bureau
3. Global Independent Foreign Exchange Bureau
4. Robust Independent Foreign Exchange Bureau
5. Yoga Forex Bureau ናቸው።

" እነዚህ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በሙሉ ተቀባይነት ያላቸው " ናቸው ያለው ብሔራዊ ባንክ " የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘቦችን በመግዛትና በመሸጥ እንዲሁም ከባንኮች ጋር በመቀናጀት ለወጪና ገቢ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሪ በማመቻቸት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገበያ ለማስፋፋትና ለማዳበር የሚረዳ ሚና ይኖራቸዋል " ብሏል።

የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎቹ በዋናነት የሚያካሂዱት የውጭ ምንዛሪ ሽያጭም ሆነ ግዥ ወዲያውኑ የሚፈጸም (spot transaction) ብቻ ይሆናል ተብሏል።

የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ያለ ጉምሩክ ዴክላራሲዮን ከደንበኞች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር፣ የጉምሩክ ፈቃድ ከሚያቀርቡት ደግሞ ከዚያ በላይ የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ፡፡

እንዲሁም ተፈላጊ የጉዞ መረጃ ላላቸው የግል ተጓዦች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር፣ ለንግድ ሥራ ተጓዦች ደግሞ እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይችላሉ፡፡

@tikvahethiopia
#NBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከ2 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳስቧል።

ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል።

አሁንም ቢሆን ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን ገበያ መር በሆነ መንገድ መተመናቸውን እና ይህንኑ ዋጋቸውን በተናጠል በየቀኑ ማሳወቃቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ጠቁሟል።

ባንኩ እስካሁን በነበረው አሰራር ንግድ ባንኮች ከውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚጠይቁትን ኮሚሽን ከምንዛሪ መሸጫ ጋር ደምረው ያስታውቁ እንደነበር ጠቅሶ፤ ወደፊት ግን ኮሚሽኑን ከምንዛሪ መሸጫ ጋር ሳይሆን በተናጠል ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁ አስታውቋል።

#NBE

@tikvahethiopia
#NBE : ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፤ ባንኮች እርስ በርሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ግብይት ይፋ አድርጓል።

ንግድ ባንኮች የአጭር ጊዜ ማለትም ለአንድ ቀን ወይም ለሰባት ቀናት መቆየት የሚችል ገንዘብ መበደርና ማበደር የሚችሉ መሆናቸውንም አብስሯል።

በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት መጀመሩ ፦

➡️ ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ጉድለትን በመሸፈን ወይም ትርፍ ገንዘብን ለሌሎች ባንኮች በማበደር የገንዘብ ፍሰትን በብቃት እንዲያስተዳደሩ ያስችላቸዋል።

➡️ የገንዘብ ግብይቱ የአጭር ጊዜ ማለትም የአንድ ቀን ወይንም የሰባት ቀናት የመክፈያ ጊዜ ያላቸው ብድሮችን ያካትታል ፤ ይህ ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ጉድለትን በመሸፈን ወይም ትርፍ ገንዘብን ለሌሎች ባንኮች በማበደር የገንዘብ ፍሰትን በብቃት እንዲያስተዳደሩ ያስችላቸዋል።

➡️ የገንዘብ እጥረት ስጋትን በመቀነስና በተረጋጋ የወለድ ተመን ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ሲል ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።


በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የግብይት መድረክ ላይ ብቻ እንዲሆ ብሔራዊ ባንክ ፈቅዷል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#NBE

@tikvahethiopia
#NBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለጊዜው የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ እንዳነሳ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

ለጊዜው የተነሳው ከባንክ ወደ ቴሌ ብር ለሚደርግ የገንዘብ ዝውውር ብቻ እንደሆነ ተነግሯል።

የግል ባንኮችም ይህን እንዲያስፈፅሙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዟል ተብሏል።

መንግስት የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ወደ ገበያ ማውጣቱ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ባንኮች ከአክስዮን ግዢ ጋር በተገናኘ በቀላሉ ገንዘብ እየለቀቁ እንዳልሆነ ተሰምቷል።

የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ የተነሳውም ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ያቀረበውን የአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ፥ የግል ባንኮች ህዝብ የሚጠይቀው እንዲፈፀምለትና ለኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ግዥ ግብይቶች ከባንክ ወደ ቴሌብር ዝውውሮች ሲጠየቁ እንዲፈፅሙ ተጠይቀዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ አክሲዮን ሽያጭ ተከትሎ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች እየተሸጠ መሆኑ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#NBE : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ማክሰኞ የካቲት 18 ቀን 2017 እንደሚያካሂድ አሳውቋል።

ለጨረታ የሚቀርበው የውጭ ምንዛሪ መጠን 60 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን፣ ጨረታው ለሁሉም ባንኮች ክፍት እነደሚሆን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NBE : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ማክሰኞ የካቲት 18 ቀን 2017 እንደሚያካሂድ አሳውቋል። ለጨረታ የሚቀርበው የውጭ ምንዛሪ መጠን 60 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን፣ ጨረታው ለሁሉም ባንኮች ክፍት እነደሚሆን ገልጿል። @tikvahethiopia
#NBE : ብሔራዊ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 135 ብር ዋጋ መሸጡን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት መሰረት፣ የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ የምንዛሪ ዋጋ 135 ነጥብ 6185 ብር መሆኑን ይፋ አደረገ።

በዚህ ጨረታ 27 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተሳትፎ መኖሩን ገልጿል።

ባንኩ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና ከዋጋና ከውጭ ምንዛሪ መረጋጋት ጋር በሚስማማ መልኩ ተጨማሪ ጨረታዎችን እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ይህ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ የገንዘብ ገበያውን ለማረጋጋትና የውጭ ምንዛሪ ተገኝነትን ለማሻሻል የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑ ተጠቁሟል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ትግበራ ከገባ ካለፈው ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም አንስቶ የአሁን የውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጨረታ ሲወጣ ለ2ኛ ጊዜ መሆኑ ይታወቃል ።

በዚህም በመጀመሪያዉ ዙር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን እና 27 ባንኮች በጨረታው ላይ መሳተፋቸውን ገልፆ ነበር።
#Capital

@tikvahethiopia