TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
FXD012024-FOREIGN-EXCHANGE-1-1.pdf
22.8 MB
NATIONAL BANK OF ETHIOPIA FOREIGN EXCHANGE DIRECTIVE NO. FXD/01/2024

በዚህ መመሪያ መሰረት የውጭ ምንዛሪ ማግኘት የሚችሉት እነማን ናቸው ?

➡️ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የተፈቀደላቸው የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ከኢትዮጵያ ውጭ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊውያን ወይም በአገሪቱ ውስጥ የሚኖር የውጭ ዜጎች ናቸው።

➡️ ምንዛሪ ለማግኘት የሚፈልጉ ግለሰቦች ለበዓል ፣ ለትምህርት ፣ ለህክምና ጉዞዎች እና ሌሎች የግል ጉዳዮች እንደሚጓዙ የሚያሳይ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ የመግቢያ ቪዛ እና የአየር ትኬት የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

➡️ ተጓዦች ከምንዛሪ ቢሮዎች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም የዚህ አቻ የሆነ የሌላ አገር ገንዘብ በጥሬ ወይም በክፍያ መፈጸሚያ ካርድ (debit card) አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።

➡️ የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ያላቸው ተጓዦች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድረስ ማግኘት ተፈቅዶላቸዋል።

በብሔራዊ ባንክ ካልተፈቀደ በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነዋሪ በአንድ ጉዞ ላይ ከ10,000 የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ በካሽ መያዝ አይችልም።

➡️ ለንግድ የሚጓዙ ግለሰቦችም የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ይችላሉ።

➡️ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ፓስፖርት እና የአየር ትኬት ለሚያቀርቡ ለንግድ ድርጅት ተወካዮች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ እንዲችሉ ተፈቅዷል። እነዚሁ ቢሮዎች ፦
- ለንግድ ድርጅቶች፣
- ለበጎ አድራጎት ተቋማት
- ለሃይማኖት ማኅበራት፣
- ለንግድ ትርኢቶች፣
- ለቱሪዝም
- ለባህል እና ለስፖርቶች አዘጋጆች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ ይችላሉ።

➡️ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ለመንግሥት ተጓዦች ለምግብ፣ ለማረፊያ እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ የማይበልጥ የውጭ ምንዛሬ ሊሸጡ ይችላሉ።

➡️ ነዋሪ ላልሆኑ የውጭ አገር ዜጎች እና ቱሪስቶች ብርን ወደ ውጭ ምንዛሬ ሊለውጡ የሚችሉበት አሠራርም አለ። ፓስፖርት፣ ትክክለኛ ቪዛ እና የአየር ትኬት የሚያቀርቡ ሰዎች ያለማስረጃ እስከ 500 የአሜሪካን ዶላር መለወጥ ይችላሉ። ከ500 ዶላር በላይ መለወጥ የሚፈልጉ ከሆነ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ ቪዛ፣ የአየር ትኬት እና ተመጣጣኝ የሆነው የውጭ ምንዛሪ በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገንዘብ መቀየሩን የሚያሳይ የተረጋገጠ የባንክ ማስረጃ ማቅርብ ይጠበቅባቸዋል።

ተጨማሪ ከላይ ተያያዘውን ፋይል ከፍተው ያንብቡ !

#NBE #BBC #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ለ2017 የበጀት አመት ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ይጸድቃል። የዘንድሮ በጀት 1.8 ትሪሊየን ብር እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህ መጠን ባለፈው ሰኔ ወር ለ2017 በጀት አመት ከጸደቀው 971 ቢሊየን ብር አንጻር በእጥፍ የሚጨምር ነው፡፡ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ድጋፍ ማግኘት የጀመረው መንግስት ለውጡን ተከትሎ ሊፈጠሩ የሚችሉትን ጫናዎችን ለመከላከል…
#Ethiopia

የፌደራል መንግሥት 551 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥ 240 ቢሊዮን ብሩ " ለማኅበራዊ ድጋፍ " የሚውል ነው ብለዋል።

ተጨማሪ በጀቱ የፌደራል መንግሥቱን ሰኔ ወር ላይ ያጸደቀውን የ2017 ዓ.ም. በጀት 1.5 ትሪሊዮን ብር ገደማ ያደርሰዋል።

የፌደራል መንግስት ዓመታዊ በጀትም ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1 ትሪሊዮን እንዲሻገር ያደርገዋል።

ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ምን አሉ ?

የህህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከአንድ ወር በፊት አንድ ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት ማጸዕደቁን ያታወሳል።

አሁን 551 ቢሊዮን አካባቢ የሚሆን ተጨማሪ በጀት ለምክር ቤቱ ይቀርባል።

በተጨማሪ በጀት መልክ ለፓርላማ ከሚቀርበው ግማሽ ትሪሊዮን ብር ውስጥ 240 ቢሊዮን የሚሆነው ፦
° ለማኅበራዊ ድጋፍ፣
° ለሴፍቲኔት፣
° ለሠራተኛ ደመወዝ ጭማሪ፣
° ለመድኃኒት ድጎማ፣
° ለዘይት ድጎማ፣
° ለነዳጅ ድጎማ የሚውል ነው።

ከወጪው በተጨማሪ የገቢ በጀትንም ለሕ/ተወ ምክር ቤት አቅርበን እናሳውጃለን።

563 ቢሊዮን የነበረው የፌደራል መንግሥት ገቢ ተከልሶ 851 ቢሊዮን ይሆናል። ይሄ የሚሆነው ግን አንድም የታክስ መጠን ሳይጨምረ ነው።

ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ፦

" ይሄንን ስናደርግ ተጨማሪ ታክስ በመጣል ወይም የታክስ ምጣኔ በመጨመር አይደለም መጨመር ያሰብነው። ኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን distortion ዝንፈት በማስተካከል ነው።

ታክስ ሳይከፍል ይከብር የነበረ ባለሃብት አሁን ቶሎ ወደ መስመር መግባት አለበት። ይሄንን የሚፈቅድ ነገር አይኖርም። ጠንካራ የሆነ enforcement ሥራ ይሠራል። "

#Ethiopia #FBC #BBC

@tikvahethiopia
#Telegram

" አዲሱ ደንብ መተግበሪያውን ለወንጀል የሚጠቀሙት ሰዎችን ቅስም የሚሰብር ይሆናል " - ዱሮቭ

ቴሌግራም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የደንበኞቹን መረጃዎች ለሕግ አካላት አሳልፎ ሊሰጥ ነው።

በዚህም የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ፦
➡️ ስልክ ቁጥሮች፣
➡️ የኢንተርኔት አድራሻ
➡️ ሌሎችንም መረጃዎች በፖሊስ፣ በፍርድ ቤት በመሳሰሉ የሕግ ተርጓሚዎች በሚፈለግበት ጊዜ ሊሰጥ እንደሚችል ቴሌግራም አሳውቋል።

የቴሌግራም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፔቨል ዱሮቭ ይህ አዲስ ደንብ እንደሆነው አመልክተዋል።

ይህ አዲስ ደንብ " መተግበሪያውን ለወንጀል የሚጠቀሙት ሰዎችን ቅስም የሚሰብር ይሆናል " ብለዋል።

" 99.999% የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ከወንጀል ጋር የሚያያይዛቸው አንዳችም ነገር የለም። 0.001% የሚሆኑት ግን ለድብቅ ወንጀል እየተጠቀሙበት የቴሌግራምን ዝና እና ክብርን እያጎደፉት ይገኛሉ። ይህ ደግሞ ቢሊዮን የሚጠጉ ጨዋ ተጠቃሚዎቻችን የሚጎዳ ነው " ብለዋል።

ዱሮቭ ባለፈው ወር በፈረንሳይ ፣ ፓሪስ ኤርፖርት በቁጥጥር ሥር ውለው እንደነበር አይዘነጋም።

በፖሊስ ከተያዙ በኋላ የቀረበባቸው ክስ " መተግበሪያው ለወንጀለኞች መፈንጫ እንዲሆን ፈቅደዋል " የሚል ነበር።

" ሕገ ወጥ የሕጻናት ምስሎች ዝውውርና የአደገኛ እጽ አዘዋዋሪዎችን በሚያበረታታ መልኩ መተግበሪያው ለወንጀል ተግባር እንዲውል ፈቅደዋል " በሚል የተከሰሱት ዱሮቭ ከሕግ አካላት ጋር ባለመተባበርም ተወንጅለው ነበር።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በበኩላቸው ሌሎች ለፈጸሙት ወንጀል እሳቸው ተከሳሽ መሆናቸው " አስደናቂ እና ግራ የሚያጋባ " ነገር ነው ሲሉ የፈረንሳይ ባለሥልጣናትን ወርፈው ነበር።

በኃላ ፍ/ቤት ዱሮቭ በዋስ ወጥተው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ማዘዙ ይታወሳል።

#Telegram #BBC

@tikvahethiopia
#Bitcoin

" በፍጹም ቢትኮይናችሁን አንዳትሸጡ " - ትራምፕ (በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተናገሩት)

የዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆኖ መመረጥ ለክሪፕቶ ማህበረሰቡ ትልቅ ብስራት ነው የሆነው።

ትራምፕ መመረጣቸው ከተሰማ በኃላ ቢትኮይን ታይቶ ባይታወቅ እና በማይታመን ሁኔታ ጨምሯል።

ዛሬ ላይ አንድ ቢትኮይን ከ91,000 ዶላር በላይ ገብቷል።

ልክ ትራምፕ ሲመረጡ በክሪፕቶ ማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ደስታ የተፈጠረ ሲሆን " የመጀመሪያው የክሪፕቶ ፕሬዝዳንት ተመረጠ " ነው የተባለው።

ትራምፕ የመጀመሪያው በይፋ ቢትኮይን እና ክሪፕቶከረንሲ የሚደግፉ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ናቸው።

ተመራጩ ፕሬዝደንት በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት " አሜሪካን የፕላኔታችን የክሪፕቶከረንሲ መዲና አደርጋታለሁ " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ለዲጂታል መገበያያዎች የተመቻቸ ሁኔታ እንደሚፈጥሩም ተናግረዋል። ይህን ተከትሎ በክሪፕቶ ኢንዱስትሪ ላይ የተጣለው ቁጥጥር ይላላል የሚል እምነት አለ።

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት " በፍጹም ቢትኮይናችሁን አንዳትሸጡ " ሲሉ ተናግረው ነበር።

የዓለማችን ትልቁ ክሪፕቶከረንሲ የሆነው ቢትኮይት ከትራምፕ መመረጥ በኃላ በማይታመን ሁኔታ ጨምሮ ዛሬ ላይ ከ91,000 (ዘጠና አንድ ሺህ) ዶላር በላይ ሆኗል።

ሌሎች እንደ ዶጅኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎችም ዋጋቸው ከፍ እያለ ነው። የዶናልድ ትራምፕ ቀኝ እጅ የሆነው ኢላን መስክ ዶጅኮይን በስፋት ያስተዋውቃል።

ክሪፕቶከረንሲ ምንድን ነው ?

ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ክሪፕቶከረንሲን " የገንዘብ ልውውጦችን ደኅንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ " ይለዋል።

ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ በርካታ ዓይነት ክሪፕቶካረንሲዎች አሉ።

በስፋት ከሚታወቁት መካከል ፦
- ቢትኮይን፣
- ኤቴሪያም፣
- ሪፕል እና ቢትኮይን ካሽ የሚባሉት ከበርካታ ክሪፕቶካረንሲዎች መካከል ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል + ገንዘብ + መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል።

ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የወረቀት ገንዘብ ወይም ሳንቲም ሳይሆን በበይነ መረብ ላይ የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው።

ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው።

ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። በመላው ዓለም በኔትወርክ በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች አማካኝነት ቁጥጥር ይደረግበታል።

ቢትኮይንን የፈጠረው ግለሰብ/ቡድን በዓለም ላይ 21 ሚሊዮን ቢትኮይኖች ብቻ እንዲፈጠሩ ገደብ እንዳስቀመጠ/ጡ ይታመናል።

የብሎክቼይን መረጃዎች እንደሚያሳዩት እስካሁን ከ17 ሚሊዮን ያህል ቢትኮይኖች ማይን ተደርገዋል ተብሎ ይታመናል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

#USA #Bitcoin #BBC #Mario #Crypto

@tikvahethiopia
" ግድያው የተፈጸመበት ወጣት ደረጀ አማረ ተስፋ ይባላል ፤ የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን አጠናቅቆ ወደ ቤተሰቦቹ የሄደ ነበር " - ነዋሪዎች

ቁጣን ስለቀሰቀሰው የደራው አሰቃቂ ግድያ ነዋሪዎቹ ምን አሉ ?

ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ አንድ ወጣት በታጣቂዎች ተይዞ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደል የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከታየ በኋላ በርካቶችን አስቆጥቷል።

ጉዳዩን በሚመለከት ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቃላቸውን የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች " ግድያው የተፈጸመው በአካባቢው ላይ በሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ድርጊቱ የተፈጸመው ከ2 ወራት በፊት እንደሆነም ገልጸዋል።

ግድያው የተፈጸመበት ወጣት ማነው ?

ዳንኤል ገመዳ የተባለው ግለሰብ ወደ ሰሜን ሸዋ ደራ አካባቢ አምርቶ የሟችን ቤተሰቦች ማነጋገሩን ገልጿል።

ግድያው የተፈጸመበት ወጣት ደረጀ አማረ ተስፋ እንደሚባል እና የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን አጠናቅቆ ወደ ቤተሰቦቹ የሄደ እንደነበር አስረድቷል።

በአሰቃቂው ቪዲዮ ላይ ከሚታየው የ10ኛ ክፍል ተማሪ በተጨማሪ ጓደኛው ከማል ሁሴን በአንድ ቀን መገደላቸው ተነግሯል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ በከጀማ ተራራ ሸሽተው ነበር። ደረጀ እና ሌሎች ግን በቀያቸው የቆዩት በበረት ታስረው የሚገኙትን እንስሳትን ለመጠበቅ ነበር።

በአካባቢው የነበሩ ታጣቂዎች ደረጀ እና ከማል ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የደረጀ አባት የሆኑትን አቶ አማረ ተስፋ ቶላን አግኝቼ አነጋግሬያለሁ የሚለው ዳንኤል፣ " ያን ቀን አሳድደው እግሩን ተኩሰው መትተው ከያዙት በኋላ ሳርኩላ ወደ ሚባል ቦታ ወሰዱት። እዚያ ቦታ ነው የፋኖ ታጣቂዎች በብዛት የሚንቀሳቀሱት " ይላል።

ደረጀ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ አስከሬኑ ለአውሬ የተጣለው እዚያ ቦታ መሆኑን የተናገሩት አባትየው፣ የልጃቸውን መገደል ቢሰሙም አስከሬኑን አግኝተው መቅበር አለመቻላቸውን ጨምሮ ገልጿል።

የደረጀ እናት እና አባት በልጃቸው ሞት ምክንያት አእምሮ ጤናቸው መቃወሱ ተገልጿል።

" የደረጀ እናት አእምሮአቸው ተጎድቷል እና አትናገርም። ምን ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም። ለማንም አይመልሱም። " ነው የተባለው።

ደረጀ ለቤተሰቡ ታናሽ ልጅ ሲሆን ወንድሞቹ እና እህቶቹ አግብተው ከቤት በመውጣታቸው እናት አባቱን ለማገዝ በቤት ያለ ብቸኛ ትንሽ ልጅ መሆኑ ተመላክቷል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ምንድነው ?

የግፍ ግድያውን የተመለከቱ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ ሰልፍ ወጥተው ነበር።

ምግባቸውንም ትተው በመውጣት ሀዘናቸውንና ቁጣቸውን ገልጸዋል።

ፍትህ እንዲሰፍን ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እና ወንጀለኞችም የፍትህ አደባባይ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

#ኢሰመኮ : የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጉዳዩን እንደሰማ ገልጾ ማጣራት መጀመሩን እና የደረሰበትን ውጤት ወደፊት እንደሚያሳውቅም ገልጿል።

የደራ ህዝብ እያየው ያለው የከፋ መከራ ምን ይመስላል ?

በደራ ሰላምና ደህንነት ከጠፋ ቆይቷል።

በቀጠናው በሰላም ወጥቶ መግባት ቅንጦት ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል።

ሰዎች በግፍ ይገደላሉ ፤ የሚጠየቅ አካል ግን የለም።

ለአብነት ከሳምንታት በፊት ገንዳ አረቦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሀጂ አህመድ መስጅድ ኢማም ሼይኽ ሙሀመድ መኪን ታግተው ከነበሩት 12 የሚሆኑ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ጋር በሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸው መነገሩ የቅርብ ትውስታ ነው።

ሌሎች በርካታ ግፍ እና ግድያዎች ሲፈጸሙም ቆይቷል።

በአካባቢው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (መንግሥት ሸኔ የሚላቸው) ታጣቂዎች፣ እንዲሁም የፋኖ ታጣቂዎች፣ የመንግሥት ታጣቂዎች  ይንቀሳቀሳሉ።

ህዝቡ ሰላም ከተጠማ ዓመታት አልፈዋል። ግፍ ፣ በደል ፣ ሰቆቃ መመልከት የዕለት ተዕለት ሁኔታው ሆኗል።

ዛሬ ይህ እጅግ አሰቃቂ ቪድዮ ወጥቶ በዚህ ልክ መነጋገሪያ ሆነ እንጂ በአካባቢው የሚፈጸመው ግፍ፣ የሚካሄደው ግድያ እጅግ አስከፊ ነው።

ብዙ ጊዜ ስለ አካባቢው ሁኔታ  ቢነገረም ይህ ነው የሚባል መፍትሄ አልመጣም።

ሰላም ወዳዱ ህዝብ በተለያየ አቅጣጫ በታጣቂዎች የሚያየው መከራ በቃላት የሚገለጽ አይደለም።

የአካባቢው ነዋሪዎች " መንግሥት ተቀዳሚ ስራው የሆነውን የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ስራ እየሰራ አይደለም " በሚል ብዙ ጊዜ ቅሬታቸው አቅርበዋል። አሁንም ቢሆን እያቀረቡ ነው።

#Oromia #Dera #BBC_Afaan_Oromoo

@tikvahethiopia
" ቅድሚያ የምንሰጠው ለአሜሪካ ነው። እሱ ደግሞ ነገ ይጀምራል " - ትራምፕ

ትራምፕ በመጀመሪያ የሥልጣን ቀናቸው በርካታ ትዕዛዞችን ለማስተላለፍ ቃል ገቡ።

የዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት ዛሬ የሚከናወን ሲሆን ቃለ መሐላ በፈፀሙ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ " በታሪካዊ ፍጥነት እና ጥንካሬ " እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል።

ይህ የተናገሩት በዋሺንግተን ዲሲ በሺዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎች ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።

ትራምፕ ያላቸውን ፕሬዝደንታዊ ኃይል ሁሉ ተጠቅመው ስደተኞችን በገፍ ለማባረር፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ላይ የሚያተኩሩ መመሪያዎችን ለመቀነስ እና የስብጥር (ዳይቨርሲቲ) ፕሮግራሞችን ለማስቆም ቃል ገብተዋል።

" ቅድሚያ የምንሰጠው ለአሜሪካ ነው። እሱ ደግሞ ነገ ይጀምራል " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው " ነገ ቴሌቪዥን ስትመለከቱ እንደምትዝናኑ እርግጠኛ ነኝ " ብለዋል።

ትራምፕ ከበዓለ ሲመታቸው በኋላ 200 ገደማ ትዕዛዞች ላይ ፊርማቸውን እንደሚያሰፍሩ ይጠበቃል።

አንዳንዶቹ ትዕዛዞች እንደ ሕግ የሚቆጠሩ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ፕሬዝደንታዊ መመሪያዎች ናቸው።

ትራምፕ " እኔ ሥልጣን በያዝኩ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የባይደን አስተዳደር ያስተላለፋቸው ትዕዛዞች ይሰረዛሉ " ብለዋል።

የሰው ሰራሽ ክህሎትን (AI) ዕድገት የሚያፋጥን እንዲሁም ኢላን መስክ የሚመራው ዶጅ የተባለ መሥሪያ ቤት እንዲቋቋም የሚወጣ ትዕዛዝ እንደሚፈርሙ አሳውቀዋል።

በተጨማሪ፦

➡️ እኤአ በ1963 ስለተገደሉት ጆን ኤፍ ኬኔዲ መረጃዎችን እንደሚለቁ፤

➡️ ወታደራዊ ኃይሉን 'አይረን ዶም' እንዲሠራ እንደሚያዙ፤

➡️ ብዝሀነት፣ እኩልነት እና አካታችነት የሚባሉ ፖሊሲዎችን ከጦር ሠራዊቱ እንደሚያስወግዱ፤

➡️ ፆታ የቀየሩ (ትራንስጀንደር) ሰዎች በሴቶች ስፖርት እንዳይሳተፉ እንደሚያደርጉ፤

➡️ የትምህርትን ሥልጣን ለአሜሪካ ግዛቶች አሳልፈው እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።

ትራምፕ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጋዊ ወረቀት የሌላቸውን ስደተኞች ከአሜሪካ እንደሚያባርሩ ገልጸዋል።

" እናንተን በጣም ደስተኛ የሚያደርጉ ብዙ ትዕዛዞች ማየታችሁ አይቀርም " ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል።

#BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር " - ፕሬዜዳንት ትራምፕ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን ነው " ሲሉ ወረፏቸው። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ በተባለው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው " ብለዋል። ትራምፕ…
" ይህን ተናግሬያለሁ ብዬ ማመን ይከብደኛል፤ ዘሌንስኪን በጣም ደፋር መሪ ነው " - ዶናልድ ትራምፕ

አወዛጋቢው የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም " አምባገነን " ሲሉ የጠሯቸውን የዩክሬኑን ፕሬዜዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ጀግና መሪ ነው " ሲሉ አሞካሿቸው።

ፕሬዝዳት ትራምፕ በዛሬው ዕለት ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ትራምፕ አስቀድመው በዋይት ኃውስ በሰጡት አስተያየት፤ " ለቮሊድሚር ዘለንስኪ ትልቅ ክብር አለኝ " ብለዋል።

በቅርቡ ዘለንስኪን " አምባገነን " ብለው በመጥራታቸው ይቅርታ እንደሚጠይቁ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ትራምፕ " ይህን ተናግሬያለሁ ብዬ ማመን ይከብደኛል፤ ዘሌንስኪን በጣም ደፋር መሪ " ነው ሲሉ አሞካሽተዋል።

በዛሬው እለት ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘሌንስኪ ጥሩ ውይይት እንደሚኖራቸው የገመቱት ትራምፕ፤ በዩክሬን ሰላም ለማምጣት የሚደረገው ጥረት በጥሩ ሁኔታ እና በፍጥነት እየሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ለመነጋገር እና በዩክሬን ውድ ማዕድናት ዙሪያ ስምምነት ለመፈራረም ትናንት ምሽት ወደ አሜሪካ አቅንተዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን እንዲሁም ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው " ማለታቸው ይታወሳል።

" ዘለንስኪ አሜሪካን 350 ቢሊየን ዶላር በማስውጣት መጀመር ያልነበረባቸው እና የማያሸንፉት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል " ብለዋቸው ነበር።

" ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር " ሲሉም ነበር የገለጹት።

ትራምፕ " ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል፤ ካልሆነ ግን የሚያተርፈው ሀገር አይኖርም " ብለውም ነበር።
#AlAin #BBC

@tikvahethiopia