TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
መቐለ ? የመቐለ ከተማ ም/ቤት ዛሬ አካሂዶታል በተባለ ሰብሰባ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው ህወሓት ውስጥ የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው የተመረጡትን ዶ/ር ረዳኢ በርሀ የከተማዋ ከንቲባ ሆኖው እንዲያገለግሉ በ1 የተቃውሞ በ5 ድምፀ ተአቅቦ እንደመረጣቸው ተሰምቷል። የከተማዋ ም/ቤት ከተማዋ በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት በዶ/ር ደብረፅዮን በሚመራው ህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ…
#መቐለ

" የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚፃረር አቋም በመያዝ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር ያለን መዋቅር መምራት አትችሉም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አዲሱን የመቐለ ከንቲባ ከስራ አገዱ።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ " ለዶ/ር ረዳኢ በርሀ " በማለት ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ፤ አዲሱ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ ህጋዊ ያልሆነ ተግባራቸውን እንዲያቆሙ አሳስበዋል።

" የመቐለ ከተማ ምክር ቤት መጠቀምያ በማድረግ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራ የሚፃረር ተግባር መፈፀም አይቻልም " ያለው የፕሬዜዳንቱ ደብዳቤ የአዲሱ ከንቲባ ሹመት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ተቀባይነት እንደሌለው አስረድቷል።

አቶ ጌታቸው " የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚፃረር አቋም በመያዝ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር ያለን መዋቅር መምራት አትችሉም ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩም ከእርስዎ ጋር መሰራት አይችልም " ብለዋል።

በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች " ህጋዊ አይደሉም " የተባሉት ከንቲባ የሚሰጡዋቸው አመራሮች እና ትእዛዞች ተቀብለው እንዳይፈፅሙ ፕሬዜዳንቱ አስጠንቅቀዋል።

አዲሱ የመቐለ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ ፤ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት ህወሓት የስራ አስፈፃሚ ሆነው የተመረጡ ናቸው።

በያዝነው ወር መጀመሪያ ሳምንት ደግሞ የቀድሞውን ከንቲባ አቶ ይትባረክ አምሃ በመተካት ከንቲባ ሆነው እንዲመሩ በመቐለ ከተማ ምክር ቤት መሾማቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መዘገቡ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሌሊት 10 ሰዓት ነው በትዳር አጋሯ የተገደለችው ፤ አንቆ ነው የገደላት " - የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ በትግራይ፣ በውቕሮ ከተማ ድል ባለ ሰርግ ከተሞሸረች በኃላ በአራተኛው ቀን በትዳር አጋሯ ታንቃ ስለተገደለችው ሊዲያ ዓለም ጉዳይ የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ አስተያየቱን ሰጥቷል። ለቢቢሲ አማርኛው ቃላቸውን የሰጡት የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ ኮማንደር ሙሉ ብርሃን ካህሳይ ፥ " ሊዲያ ረቡዕ፣ጥቅምት…
#መቐለ

መቐለ ከተማ ውስጥ በጭካኔ የተገደለች እንስት አስከሬንዋ ከ2 ቀን በኋላ መገኘቱን ፓሊስ አስታውቋል።

የጭካኔ ተግባሩ የት ፣ መቼ ፣ እንዴት ተፈፀመ ?

የጭካኔ ተግባሩ በትግራይ ፣ መቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ሰፈር በሚገኝ የአንድ ሆቴል ክፍል ነው የተፈፀመው።

ሓበን የማነ የ19 ዓመት ወጣት ስትሆን በሆቴል ክፍል #በቢላዋ ተገድላ መገኘትዋና ጥቅምት 20 /2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ የቀብርዋ ስነ-ሰርዓት መከናወኑ ተሰምቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የጭካኔ ተግባሩ የሚመለከት ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት ወደ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፓሊስ ፅህፈት ተጉዟል።

ፓሊስ የጭካኔ ተግባሩ የሚመለከት ዝርዝር መረጃ በማሰብባሰብ ላይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የጭካኔ ግድያ ተግባሩ በፍቅኛሞች መካከል መፈፀሙን እና በግድያ ወንጀል የተጠረጠረ ዳዊት ዘርኡ የተባለ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ህዝቡ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጠይቋል። 

በተያያዘ በያዝነው ወር የመጀመሪያ ሳምንት ውቕሮ ከተማ ላይ እሁድ ጥቅምት 5 ተድራ ሓሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም በባሏ በጭካኔ የተገደለችው ሙሽሪት ሊድያ ጉዳይ ተጣርቶ ወደ አቃቤ ህግ መተላለፉን የወቕሮ ከተማ ፓሊስ አሳውቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መቐለ መቐለ ከተማ ውስጥ በጭካኔ የተገደለች እንስት አስከሬንዋ ከ2 ቀን በኋላ መገኘቱን ፓሊስ አስታውቋል። የጭካኔ ተግባሩ የት ፣ መቼ ፣ እንዴት ተፈፀመ ? የጭካኔ ተግባሩ በትግራይ ፣ መቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ሰፈር በሚገኝ የአንድ ሆቴል ክፍል ነው የተፈፀመው። ሓበን የማነ የ19 ዓመት ወጣት ስትሆን በሆቴል ክፍል #በቢላዋ ተገድላ መገኘትዋና ጥቅምት 20 /2017…
#መቐለ

" ተጠርጣሪው ተይዞ ለክልሉ ፖሊስ ተላለልፎ ተሰጥቷል " - ፖሊስ

የ19 ዓመትዋን ወጣት በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ በፓሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

የመቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፓሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጸው ፥ ጥቅምት 19 /2017 ዓ.ም ሓበን የማነ የተባለች ፍቅረኛውን በተከራዩት የሆቴል ክፍል በጬቤ በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ ከቀናት ፍለጋ በኃላ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

በአሰቃቂ የግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ዳዊት ዘርኡ ተወልደ የተባለው ግለሰብ አሰቃቂ ተግባሩን ፈፅሞ በመሰወሩ ሲፈለግ ቆይቷል።

የሟች ቤተሰብ ጨምሮ በርካታ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች በከባድ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ ከትግራይ ክልል ወጥቶ በአማራ ክልል በኩል ሊያመልጥ ሲል በደሴ ከተማ መያዙን ፅፈዋል።

የመረጃው ትክክለኝነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያረጋገጡት የሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፓሲስ አዛዥ ሞገስ ወርቁ ፥ ተጠርጣሪው በዛሬው ቀን ጥቅምት  27/2017 ዓ.ም ለክልሉ ፓሊስ ተላለልፎ መሰጠቱን ገልፀዋል።

ግለሰቡ ደሴ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ለፖሊስ ጥቆማ በመድረሱ ነው ሊያዝ የቻለው።

ከክልል ፖሊስ በተገኘው መረጃ ደግሞ ግለሰቡ በአላማጣ አድርጎ ነው ወደ ደሴ የተጓዘው። ወደዛ የሄደውም በረዳት ሹፌርነት ነው።

አንድ ለሊትም በደሴ ከተማ ካሳለፈ በኃላ ሰውነቱ ላይ ያለውን ንቅሳት የሚሸፍን ልብስ ገዝቶ ወደ ያዘው መኝታ ክፍል ሲገባ በደረሰ ጥቆማ ሊያዝ ችሏል። ከዛም መቐለ ፖሊስ አባላቱን በመላክ ተጠርጣሪው ወደ መቐለ እንዲመጣ አድርጓል።

የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም የደሴ ህዝብ ላደረገው ትብብር ምስጋና አቅርቧል።

በከባድ የግድያ ተግባር የተጠረጠረው ግለሰብ አስመልክቶ በማህበራዊ የትስስር ገፆች የተሰራጨው አጭር ቪድዮ እንደሚያመለክተው ፥ ተጠርጣሪው ፍቅረኛውን በጬቤ ከገደላት በኋላ ተፀፅቶ ራሱ ለመግደል ሞኩሮ ሳይሳካለት መቅረቱ በአንደበቱ ይገልፃል።

የሟች ወጣት ሓበን የማነ አባት አቶ የማነ ንጉስ ልጃቸው በጭካኔ በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ በአጭር ጊዜ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ለተባበሩ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

የፎቶ ባለቤት ፦ የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን

@tikvahethiopia 
#መቐለ

መቐለ ውስጥ ባለፉት 3 ወራት ብቻ 1,088 ወንጀሎች መፈፀማቸው የመቐለ ከተማ ፓሊስ አስታውቋል።

ከተፈፀሙት ወንጀሎች መካከል ፦
➡️ 16 የግድያ
➡️ 47 የግድያ ሙከራ
➡️ 16 የሴቶች አስገድዶ መድፈር ይገኙበታል።

በሩብ አመቱ የተመዘገበው የወንጀል ተግባር አሳሳቢና ህዝብ ያሳተፈ የመከላከል ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላካች ነው ብሏል።

ፖሊስ የወንጀል ተግባራቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ 3 ወራት ሲነፃፃር የቀነሰ ቢሆንም አሁንም ቢሆን ህዝቡ ከወንጀልና የወንጀል ስጋት ነፃ እንዳልሆነ አመላካች ነው ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia