TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert
ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ አካሂዶ በሁለት ጉዳዮች ውሳኔ አሳልፏል።
ውሳኔ ከተላለፈበት አንዱ ጉዳይ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ነው።
ምክር ቤቱ ፥ " በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርከቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል " ብሏል።
" ሆኖም እነዚህ አሰራሮች ፦
- በእውኀት፣
- በዕርቅ፣
- በምህረት እና በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብአዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም " ሲል ገልጿል።
በመሆኑንም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቀረቡን አስረድቷል።
ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ #በስራ_ላይ_እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
@tikvahethiopia

#NewsAlert #Tigray
" የህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ላለልተወሰነ ጊዜ የድጋፍም ይሁን የተቋውሞ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር፣ ምክትል ፕሬዜዳንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም ፤ " ፓለቲካዊ አለመግባባት ወደ ማንኛውም የፀጥታ አደጋ እንዲሸጋገር አንፈቅድም " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
" የህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ላለልተወሰነ ጊዜ የድጋፍም ይሁን የተቋውሞ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል " ያሉት ጀነራል ታደሰ ወረደ " ፓለቲካዊ ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ በቀላል እና ከባባድ ወንጀሎች ተሳትፈዋል ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የማዋል ኦፕሬሽን መጀመሩ ይታወሳል።
ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረዳ በዛሬ መግለጫቸው ላይ በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦችና ብዛታቸውን ባይገልጹም " የህግ የበላይነት ለማስከበር የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል " ሲሉ አሳውወዋል።
የዘንድሮ የአሸንዳ በዓል አከባበርና የህወሓት ጉባኤ ከመካሄድ ጋር ተያይዞ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ተገቢ እና ጥብቅ የፀጥታ ስራ ይሰራል ሲሉም ተናግረዋል።
በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ እና እየከረረ መሄዱ በርካቶችን ያሳሰበ ጉዳይ ሆኗል።
ሁኔታው የፀጥታ ስጋት ደቅኗል የሚሉ አልጠፉም።
ሌ/ጄነራል ታደሰ ግን ፓለቲካዊ ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት እንዳለበት ፤ ማንኛውም ልዩነት ወደ ፀጥታ አደጋ እንዲሸጋገር የጸጥታ አካሉ እንደማይፈቅድ አስጠንቅቀዋል።
#TikvahEthiopiaMekelle
Photo Credit - TG TV

#NewsAlert🚨
" ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር ደምስሶታል። ... ይህ ድርጊቱም የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል !! " - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
በሊቀ መንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ጉባኤውን መጀመሩ ይፋ በተደረገበት በዚህ ሰዓት ላይ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አጭር ግን ጠንካራ መልእክት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሰራጭተዋል።
በዚህም " በየትኛውም የዓለም ጥግ ያለ አገር የሚመራው በህግና በስርዓት ነው " ብለዋል።
" ህግ እና ስርዓት ከማንኛውም ሰው ፣ ተቋም ፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ፣ ቡድን፣ ስብስብ በላይ ነው። " ያሉት ለገሰ (ዶ/ር) " እነዚህ ሁሉ ከህግ እና ስርአት በታች ናቸው፤ ህግና ስርዓትን አክብሮ የማይንቀሳቀስ የትኛውም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመጨረሻ ግቡ ጥፋት ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።
ለገሰ (ዶ/ር) ፥ " የህወሓት ያለፉት ዓመታት የግትርነት ባህሪም የዚሁ ምሳሌ ነው " ያሉ ሲሆን " ህወሓት ደጋግሞ እንደመሸሸጊያ የሚያነሳው የፕሪቶሪያ ስምምነት የፌደራል ተቋማትን አሰራሮች፣ ህጎችና አካሄዶች በጥብቅ ሊያከብር ግዴታ ጥሎበታል " ብለዋል።
" ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር ደምስሶታል፡፡ " ሲሉ አሳውቀዋል።
" ድርጊቱ የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል፡፡ " ያሉት ለገሰ (ዶ/ር) " አንዴ፡ ሁለቴ፡ መሳሳት ያለንና የነበረ ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ተመሳሳይ ስህተት ሶስቴ መፈጸም ግን የመጨረሻው የጥፋት መንገድ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።
" ለዚህ ደግሞ ብቻኛ ተጠያቂ እራሱ (ህወሓት) ይሆናል " በማለት ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የጭነት ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 149/2016 አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
ምን አለ ?
- መመሪያው የሚመለከታቸው የጭነት ተሽከርካሪዎች / የጭነት አቅማቸው ከ1 ቶን ወይም 10 ኩንታል በላይ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ነው።
- እነዚህ ተሽከርካሪዎች ጠዋት ከ1:00 ሰዓት እስከ 3:00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ከሰዓት 10:30 እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ ገደብ ተጥሎባቸዋል።
- በዋና መንገዶች ላይ ማቆም፤ ጭነት ማውረድና መጫን እንዲሁም መንቀሳቀስ በክልከላው የተካተቱ ናቸው።
- አዲሱ መመሪያ ከዚህ በፊት ከነበረው የሰዓት ገደብ ላይ በቀረቡ ቅሬታዎች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ታስቦ የወጣ እንደሆነ ተመላክቷል።
- አዲሱ መመሪያ ከመስከረም 2/2017 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀናትን አይመለከትም።
የተቀመጡ የቅጣት እርከኖች ምንድናቸው ?
➡️ በተከለከለ ሰዓት በዋና ዋና መንገዶች ላይ የቆሙ የ10ሺ ብር ቅጣት፤
➡️ በተከለከለው የሰዓት ገደብ የተንቀሳቀሰ 20ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት፤
➡️ በቅጣት ሂደቱ በድጋሜ የተቀጣ አሽከርካሪ የቅጣት እርከኑን በእጥፍ የሚቀጣ ይሆናል።
➡️ በተጨማሪ የቅጣት ወረቀት በመያዝ በዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀስ ትዕዛዝ ባለማክበር ተጨማሪ ቅጣት የሚተላለፍባቸው ይሆናል ተብሏል።
ቅሬታ ያላቸው በጹሑፍ ቅሬታቸውን ለባለሥልጣኑ በማመልከቻ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን የባለሥልጣኑ ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ ይሆናል።
ይህ መመሪያ ቁጥር 149/2016 ከዚህ ቀደም የነበረውን መመሪያ ቁጥር 38/2013 እንዲሁም ሰርኩላሮች፣ ልማዳዊ አሰራሮች የሚሽር ነው።
ይህ መመሪያ ተግባራዊ የማይደረግባቸው የትኞቹ ተሽከርካሪዎች ላይ ነው ?
1ኛ. የሀገር መከላከያ፤ የፖሊስ እንዲሁም በጸጥታ አካላት ስም የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች፤
2ኛ. የድንገተኛ አደጋ ተሽከርካሪዎች፤
3ኛ. ነዳጅ የሚያመላልሱ ቦቴዎችን አይመለከትም።
ከዚህ ቀደም ወጥ አተገባበር ባልተስተዋለባቸው የውሃ አመላላሽ ቦቴዎች ላይ አዲሱ መመሪያ እንዴት ይመለከተዋል ? በሚል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላነሳው ጥያቄ ፥ በአዲሱ መመሪያ እንደሌሎች ከባድ ተሽከርካሪዎች እንደሚስተናገዱ ተገልጿል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

የአዲስ አበባ ካቢኔ ሁለት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል።
ካቢኔው " በኮሪደር ልማት አካባቢ ያሉ የግል ባለይዞታዎች የቅድሚያ የማልማት ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥበት አግባብ፣ የተጀመሩ ግንባታዎች የቦታ ማስፋፊያ ጥያቄዎች፣ ለኃይማኖት ተቋማት እና የባለ 5 ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ የቦታ ጥያቄዎች ላይ በመወያየት ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸዉ አኳያ በመመርመር እንዲፈቀድላቸውና ወደ ልማት እንዲገቡ " ሲል ውሳኔ አሳልፏል።
ሌላው የአዲስ አበባ ከተማ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ለማስተዳደርና ለማልማት የወጣው ረቂቅ ደንብን መርምሮ ለማህበረሰቡ ከሚኖራቸው የጎላ አገልግሎት አኳያ በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስተባባሪነት እንዲፈፀም መወሰኑን ታውቋል።

#Update በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ ለ4ኛ ጊዜ ቀጠሮ መሰጠቱ ተሰማ። የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ በተሰሙ የምስክሮችን ቃል መርምሮ ብይን ለመስጠት ለ4ኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ በተከሳሾች ፦ - ቄስ በላይ መኮንን፣ - በግብርና ኢንቨስትመንት…
#NewsAlert
ቀሲስ በላይ መኮንን በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ተቀጡ።
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ የቀረቡ የግራ ቀኝ ማስረጃዎችን መርምሮ በዛሬው የችሎት ቀጠሮ በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ፦
➡️ ቀሲስ በላይ መኮንን፣
በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ፣
➡️ በኮሚሽን ስራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ እና አለምገና ሳሙኤል
➡️ የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ በተባሉ ተከሳሾች ላይ ክስ አቅርቦባቸው ነበር።
ተከሳሾቹ ከአፍሪካ ህብረት ምንም አይነት የክፍያ ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ ላይ ተከሳሾች በተለያየ መጠን ክፍያ እንዲፈጸምላቸው የሚል አጠቃላይ የ6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሀሰተኛ የክፍያ ሰነድ በአንደኛ ተከሳሽ አማካኝነት ለባንኩ መቅረቡ ተጠቅሶ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ነው አቅርቦ የነበረው።
ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተከሳሾች ብቻ ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በአድራሻቸው ባለመገኘታቸውና በተደጋጋሚ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ለጊዜው ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል።
ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ክሱ እንዲሻሻልላቸው ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ ክስ መቃወሚያ ነጥቦችን ፍርድ ቤቱ መርምሮ ወደፊት በማስረጃ የሚጣራ መሆኑን ገልጾ መቃወሚያቸውን አልተቀበለውም።
ከዚህም በኋላ ተከሳሾቹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው የዕምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ አጠቃላይ ሶስት ምስክሮችን አቅርቦ ምስክርነታቸውን አሰምቶ ነበር።
ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል መርምሮ በክሱ ዝርዝር የተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን በዐቃቤ ሕግ በማስረጃ ማረጋገጡን ጠቅሶ በአንደኛው ክስ ብቻ እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን ሰጥቶ ነበር።
ሁለተኛውን ክስ በሚመለከት በሐሰተኛ ሰነድ የተፈጸመ ድርጊት መሆኑ በአንደኛውን ክስ ላይ መገለጹን ተከትሎ በሰበር ሰሚ ችሎት ትርጉም የተሰጠባቸው በተደራራቢነት የቀረቡና ተጠቃልለው ሊያስቀጡ የሚችሉ ድንጋጌዎች መኖራቸውን ፍርድ ቤቱ አብራርቶ ሁለተኛውን ክስ ውድቅ በማድረግ በአንደኛው ክስ ብቻ በከባድ አታላይነት ሙስና ወንጀል እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።
ሆኖም ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ በሰጠው ብይን የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው ማስተባበል አለመቻላቸው ተጠቅሷል።
በዚህም 1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን በሙሉ ድምጽ የጥፋተኝነት ፍርድ የተሰጠባቸው ሲሆን ፤ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በአንድ ዳኛ የሀሳብ ልዩነት በአብላጫ ድምጽ ጥፋተኛ ተብለዋል።
የሀሳብ ልዩነት ያቀረቡት አንደኛው ዳኛ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት የባንክ ሂሳባቸው በመገለጹ ብቻ የወንጀል ተግባሩ በስምምነት ተፈጽሟል ለማለት አያስችልም የሚል የሀሳብ ልዩነት እንዳላቸው ጠቅሰው ልዩነታቸውን አሳይተዋል።
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮ ዐቃቤ ሕግ ወንጀሉ የተፈጸመው በትብብር መሆኑን ጠቅሶ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ ይዟል።
በዚህም1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን ያቀረቡትን አራት የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 21 መሰረት በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት ደግሞ እያንዳንዳቸው አራት፣ አራት የቅጣት ማቅለያ አስተያየት በመያዝ በዕርከን 17 መሰረት በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
በፍርድ ቤቱ በተከሳሾች ላይ የተወሰነውን የጽኑ እስራት ውሳኔን የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እጃቸው ከተያዘ ጀምሮ ታሳቢ በማድረግ እንዲያስፈጽም ታዟል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው።

ህወሓት ለሦስት ወር ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ታገደ።
➡ በሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ ተወስኗል።
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መታገዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳወቀ።
ፓርቲው በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንሥቶ ባሉት 6 ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ ይጠበቅበት ነበር።
ቦርዱ ፥ ታኅሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በፃፈው ደብዳቤ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ የማድረጊያ ጊዜ ገደቡ ሊጠናቀቅ ከሁለት ወር ያነሰ ጊዜ አንደቀረው በመግለጽ በሕግ የተጣለበትን ግዴታ አንዲፈጽም ማሳሰቡን አስታውሷል።
ይህንን የሕግ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈጽም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሣኔ የሚሰጥ መሆኑን መግለጹንም አክሏል።
ይሁንና ፓርቲው የዐዋጁንና የመመሪያውን ደንጋጌዎችና የቦርዱን ውሣኔዎች በማክበር የጠቅላላ ጉባዔ ሳያካሄድ፣ መተዳደሪያ ደንቡን ሳያፀድቅና አመራሮቹን ሳይመርጥ በሕግ የተሰጠው የ6 ወር ጊዜ ተጠናቅቋል።
በዚህ መሠረት ቦርዱ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ጉዳዩን መርምሮ ፦
1ኛ. ፓርቲው ከፍ ዐዋጅና መመሪያ ላይ የተመለከቱ ድንጋጌዎችን ባለማክበር ጉልህ ጥሠት በመፈጸሙ ይህ ውሣኔ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ለሦስት ወራት በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዳይሣተፍ እንዲታገድ ወሥኗል።
2ኛ. ፓርቲው ለእግዱ ምክንያት የሆነውን ጥሠት በማረም፤ ዐዋጁን፣ ዐዋጁን ተከትሎ የወጣውን መመሪያ፣ የቦርዱን ውሣኔዎችና ትዕዛዞች በማክበር ፖርቲው ሊያደርግ የሚገባውን ጠቅላለ ጉባዔ ለማድረግ የሚያስችለውን የጉባዔ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለመሥራት ለቦርዱ በጽሑፍ ሲያሳውቅና ቦርዱ ይህንኑ ሲያረጋግጥ በመመሪያው መሠረት ቦርዱ ዕግዱን የሚያነሣ መሆኑን ወሥኗል።
3ኛ. ፖርቲው በተሰጠው የሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የተለየ አካሄድ ሳይከተል የፖርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ ወሥኗል።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ላይ ጊዚያዊ የእግድ ደብዳቤ ፃፉ።
እግዱ የተፃፈላቸው ከፍተኛ አመራሮች ፦
- ሜጀር ጀነራል ዮውሃንስ ወ/ጊዮርጊሰ
- ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ
- ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሃይለ ናቸው።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም የፃፉት ጊዚያዊ የእግድ ደብዳቤ ፦
" ከመንግስት ውሳኔ ውጪ መላ ህዝባችን ፣ ወጣቱን ወደ ግርግር ፤ የፀጥታ ሃይላችን ወደ እርስ በርስ ግጭት ብሎም ህዝባችን ወደ እማይወጣበት አዘቅት የሚያስገባ አደገኛ እንቅስቃሴ አልቆመም ስለሆነም እርስዎ ስርዓት ባለው አካሄድ መግባባት እስኪደረስ ድረስ ከመጋቢት 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከአዛዥነትዎ የታገዱ መሆንዎን አስታውቃለሁ " ይላል።
በትግራይ ክልል በአመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት እንዲፈታ ብዙ ጥረት ቢደረግም ምንም መፍትሄ ሳይገኝለት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ነዋሪዎችም ሁኔታው ስጋት ላይ ጥሏቸዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

#Update የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በትግራይ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዲገባ ያቀረበውን ጥሪ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት ተቃወመ። የተጀመረው " ህግ የማስከበር እርምጃ " ያለው ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በትግራይ ጉዳይ እገዛ እንዲያደርጉ ያቀረበው ጥሪ " ይፋዊ…
#NewsAlert
ከ100 ቀናት በላይ ዝግ የነበረው የመቐለ ከተማ የከንቲባ ፅሕፈት ቤት ተከፍቶ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት የመደባቸው ከንቲባ ገብተውበታል።
የምስራቃዊ ዞን እና የዓዲግራት ከተማ ከተማ አስተዳደሮችም እንዲሁ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመሩት ህወሓት ቁጥጥር ስር ውለዋል።
በደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዓዲጉዶም ፣ የሳምረ ፣ እንዲሁም የሃገረ ሰላም ከተሞች የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅሮች በህወሓት ተመራጮች መተካታቸው ተገልጿል።
ጉባኤ ያካሄደው ህወሓት የሾማቸው የመቐለ ከንቲባ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ፤ የምስራቃዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፍስሃ ሃይላይ ዛሬ መጋቢት 4/2017 ዓ.ም በህዝብ ታጅበው ወደየ ፅህፈት ቤቶቻቸው መግባታቸው አስታውቀዋል።
የዓዲግራት ከተማ የከንቲባ ፅህፈት ቤት ደግሞ ትናንተ መጋቢት 3 /2017 ዓ.ም የህወሓት ተመራጩ ከንቲባ ገብቶ ስራ መጀመሩ አስታውቀዋል።
ድርጊቱን ያወገዙት በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስና የምስራቃዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን ትኩእ ፤ ህገ-ወጥ ተግባሩ የፕሪቶሪያ የሰላም ውል የሚፃረር በመሆኑ ከማውገዝ ባለፈ እስከ መጨረሻው እንደሚታገሉት በመግለፅ ወጣቱ ከግጭት ርቆ ተደራጅቶ እንዲታገል መልእክት አስተላልፈዋል።
የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ እና የማእከላይ ዞን አስተዳደሮችም " ጉባኤ አካሂጃለሁ " ባለው ህወሓት ቁጥጥር ስር ከዋሉ ወራት ተቆጥረዋል።
የትግራይ ደቡባዊ ዞን ከተሞች እስከ አሁንዋ ሰዓትና ደቂቃ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ሹመኞች እጅ ይገኛሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው በርካታ የጊዚያዊ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች ወደ አዲስ አበባ መጓዛቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ምንጮች ገልፀዋል።

#Update የ104.4 የመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት በተመደቡ የመቐለ ከተማ አመራሮች አባላት ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል። አመራሮቹ በሰራዊት ታጅበው ሬድዮ ጣቢያውን እንደተቆጣጠሩት ተነግሯል። ምናልባትም በቀጣይ ደግሞ የድምፂ ወያነ እና ትግራይ ቴሌቪዥን ሚድያዎችን ሊያዙ እንደሚችሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከታማኝ ምንጮች ለመስማት ችሏል።…
#NewsAlert
የአሜሪካ፣ የዩናይትድ ኪንግደም፣ የኒውዚላንድ፣ የጃፓን፣ የኖርዌይ፣ የቤልጂየም፣ የቡልጋሪያ፣ የቼክ ሪፐብሊክ፣ የዴንማርክ፣ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ግሪክ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ሉክሰምበርግ፣ ሃንጋሪ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኦስትሪያ፣ ፖርቱጋል፣ ሮማኒያ፣ ስሎቬንያ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድን ኤምባሲዎች እና የአውሮፓ ህብረት ልኡክ በኢትዮጵያ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።
በዚህም መግለጫቸው ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ ለውጦችን / ሁኔታዎችን እና እየተባባሰ ያለውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
" እ.ኤ.አ. ህዳር 2022 ለተፈጸመው የግጭት ማቆም ስምምነት ሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ ደግመን አጽንኦት እንሰጣለን " ብለዋል።
ይህ ስምምነት የመሳሪያ ድምጽ ጸጥ እንዳደረገም አመልክተዋል።
በፍጹም ወደ ሁከት ፣ ግጭት ፣ ጦርነት መመለስ እንደማይገባም አስገንዝበዋል።
ሁሉም ወገኖች ተባብሰው አስቸኳይ ውይይት በማድረግ ውጥረቱን በማርገብ ስምምነቱን እንዲጠብቁ አጥብቀው አሳስበዋል።
ማንኛውም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኃላ ከአሜሪካ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እንዲሁም በአውሮፓ ህብረት አምባሳደሮች ጋር በትግራይ ስላለው ሁኔታ እና አስተዳደራቸው እየገጠመው ስላለው ፈተና ሰፋ ያለ ውይይት አድርገው ነበር።

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በምን ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ ? ከ1 ዓመት በላይ ማረሚያ ቤት ሆነዉ ጉዳያቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ፀጋዬ ቱኬ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረቡባቸው ሁለት ክሶች ጥፋተኛ ተብለዋል። አቶ ጸጋዬ ፕሮጀክቶችን " በህገ ወጥ አግባብ መርተዋል " በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። " የህዝብ እና የመንግስት ሀብት ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ "…
#NewsAlert
የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ 13 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው።
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፤ ባሳለፍነው ሳምንት በሁለት ክሶች ጥፋተኛ የተባሉት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ላይ 13 ዓመት ፅኑ እስራትና 21 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ፍርድ ማሳለፉን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ቤተሰብ አባል መረጃውን አድርሷል።
ፍርድ ቤቱ የቀድሞዉ ከንቲባ ካቀረቡት 8 የቅጣት ማቅለያዎች 4ቱን በመቀበል እና አራቱን ዉድቅ በማድረግ ነዉ የ13 ዓመት ፅኑ እስራት የፈረደባቸው።
በዚሁ በእሳቸው መዝገብ ተከሳሽ የነበሩት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ታርኩ ታመነ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እነ 41 ሺህ ብር ፤ አቶ ታፈሰ ቱናሻ በ8 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራትና 51 ሺህ ብር እንዲሁም አቶ ሰይፉ ሌሊሴ የተባሉ ግለሰብ እንደዚሁ በ8 ዓመት ከ5 ወር እና 76 ሺግ ብር የገንዘብ ቅጣት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@TIKVAHETHIOPIA