TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AU #Fraud #CBE

ቀሲስ በላይ መኮንን ከአፍሪካ ኅብረት ኦፊሳላዊ የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመጠቀም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ #ከ6_ሚሊዮን_ዶላር_በላይ (367 ሚሊዮን ብር) ለማዘዋወር ሲሞክሩ ነው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ፍድር ቤት ቀርበውም ለፖሊስ ተጨማሪ ቀን ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ ምን አሉ ?

" በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካለው የአፍሪካ ህብረት ሒሳብ የወጣ ገንዘብ የለም።

አንድ ሰው ሀሰተኛ ሰነዶችን ተጠቅሞ ለማውጣት ቢሞክርም እዛው በቦታው ላይ ተይዟል።

የማጭበርበር ሃሳብና ገንዘብ ለመውሰድ ጥረት ቢደረግም ማክሸፍ ችለናል። ይህንን የሞከሩት ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ናቸው። እኔ የማውቀው ይህን ብቻ ነው።

በመሰረቱ ጥሬ ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ሊሰጥ አይችልም። አጭበርባሪው መጥቶ  ሲጠይቅ ይህን እንኳን አያውቅም ነበር።

ሰውዬው እዚህ ሀገር የዶላር አካውንት ከሌለው ገንዘቡ ቢተላለፍም የትም ውስጥ ሊገባ አይችልም።

አጭበርባሪዎች በየቀኑ ነው ወደ ባንካችን የሚመጡት ፤ ባንክ ስለምንሰራ ይህ የተለመደ ነው። ነገር ን ሁሌም የማጭበርበር ድርጊቶቹ ከመሳካታቸው በፊት እንደርስባቸዋለን። ለፍርድም እናቀርባቸዋለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፥ የደንበኞቹን ሒሳቦች የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት ያንን እያደረግን ነው። የአፍሪካ ህብረት እስካሁን ድረስ በይፋ ቅሬታ አላቀረበብንም። "

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የአፍሪካ ኅብረት ምንጭ ምን አሉ ?

"የእኛ ሒሳብ ላይ መሰል ማጭበርበር ሲያጋጥም ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

አሁን ላይ ማጭበርበሩ #በተከበሩ_ሰዎች አማካኝነት እየተሞከረ ነው። ይህ ደግሞ በጣም አስጨንቆናል። አንድ ቀን ባለስልጣናት ተመሳሳይ ነገር ላለማድረጋቸው ምንም አይነት ዋስትና የለንም።

እምነት እያጣን ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ለደሞዝ አነስተኛ መጠን ያለው ፎሬክስ (የውጭ ምንዛሬ) ለመያዝ ወስነናል።

ይህን መሰሉ ሁኔታ የድርጅቱን ገንዘብ በውጭ ማቆየት እንድናስብ እያስገደደን ነው። "

https://telegra.ph/The-Reporter-04-21 #ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
" በታሪኬ ከታክስ በፊት ከፍተኛውን ትርፍ አግኝቻለሁ " - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2016 በጀት ዓመት 135.4 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን አሳውቋል።

በዚህ ዓመት ከታክስ በፊት የተገኘው 25.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ እንደሆነ እና በባንኩ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡን ገልጿል።

የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ1.17 ትሪሊዮን ብር የተሻገረ መሆኑን ተናግሯል።

የባንኩ የደንበኞች ቁጥር ደግሞ ከ45 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ አመልክቷል።

የተበላሸ ብድር ክምችቱ 2.6% መደረሱም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፥ ከ218 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት ማቅረቡን ጎልጾ 91% ወይም ብር 198 ቢሊዮን የሚበልጠው ለግሉ ሴክተር የተለቀቀ ብድር እንደሆነ አሳውቋል።

#CBE #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በንግድ ባንክ ዛሬ የውጭ ምንዛሬ እንዴት ዋለ ? በባንኩ የውጭ ምንዛሬ በተለይ የዶላር ዋጋ ከትላንት ከሰዓቱ የተለየ አልነበረም። ዶላር ትላንትና ከሰዓት ሲገዛ እና ሲሸጥ በነበረበት ዛሬም በዛው ውሏል። አንድ ዶላር መግዣው 80 ብር ከ0203 ሳንቲም ፤ መሸጫው 81 ብር ከ6207 ሳንቲም ሆኖ ውሏል። ዩሮም ዛሬ ከትላንቱ ያን ያህል ልዩነት አልነበረውም። መግዣው 86 ብር ከ63 ሳንቲም መሸጫው 88 ብር…
#Update

ለነገ አርብ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ አርብ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል።

በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል።

ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሆኖ ይውላል ብሏል።

ዩሮም ጨምሯል። መግዣው 90 ብር ከ5307 ሳንቲም መሸጫው 92 ብር ከ3413 ሳንቲም እንደሚሆን አሳውቋል።

የUAE ድርሃም በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ ድርሃም ነገ በ20 ብር ከ4557 ሳንቲም እየተገዛ ፤ በ20 ብር ከ8648 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል።

#TikvahEthiopia #CBE #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለነገ አርብ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ አርብ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል። በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል። ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሆኖ ይውላል ብሏል። ዩሮም ጨምሯል።…
#Update

ዶላር መሸጫው ከ100 ብር አለፈ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ ቅዳሜ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል።

በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው 101 ብር ከ4347 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል።

ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 116 ብር ከ6881 ሳንቲም ፤ መሸጫው 123 ብር ከ6894 ሆኖ ይውላል ብሏል።

ዩሮም እጅግ በጣም ጨምሯል። መግዣው 104 ብር ከ4107 ሳንቲም መሸጫው 110 ብር ከ6754 ሳንቲም እንደሚሆን አሳውቋል።

የUAE ድርሃም በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ ድርሃም ነገ በ23 ብር ከ3201 ሳንቲም እየተገዛ ፤ በ24 ብር ከ7194 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል።

#TikvahEthiopia #CBE #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
#CBE🚨

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ ተጨመረ።

መንግስት በቅርቡ ባወጣው አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግ መስረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚያቀርባቸው ምርት እና አገልግሎቶች ላይ በነበረው የአገልግሎት ክፍያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፈልባቸው መወሰኑን ገልጿል።

በዚህም ከነገ መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ. ም ጀምሮ የባንኩ ምርትና የአገልግሎት ዓይነቶች ላይ በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ የተጨመረባቸው መሆኑን ባንኩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#CBE የብድር ወለድ መጠኖች ላይ ጭማሪ ተደረገ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር ወለድ መጠኖች ላይ ጭማሪ አደረገ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከየካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ በተለያዩ የብድር ዓይነቶች ላይ ጭማሪ ማድረጉን አስታዉቋል።

ይህ ጭማሪ የመጣው መንግስት የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት አካል እንደሆነ ባንኩ ገልጿል።

በተደረገው ማስተካከያ መሰረት፦
➡️ የግብርና ብድሮች እስከ 15.5%፣
➡️ የንግድ ብድሮች እስከ 18%፣
➡️ የወጪ ንግድ ብድሮች እስከ 14%፣
➡️ የግል ብድሮች ደግሞ እስከ 15% ጭማሪ አሳይተዋል።

ይሁን እንጂ  ለኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ብድሮች የወለድ ምጣኔ በ12 በመቶ እንደነበረው ይቀጥላል ተብሏል።

የውጭ ምንዛሬ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ሰራተኞች የግል ብድሮች በስምምነቱ ውል ላይ በመመስረት ከ11 በመቶ እስከ 13 በመቶ የሚደርስ ሲሆን፣ ለየት ያለ ከፍተኛ ዋጋ ላላቸው ደንበኞች ሰራተኞች የግል ብድሮች በ12 በመቶ እንደነበረው እንደሚቀጥልም
ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

(የተሻሻለውን የብድር ወለድ መጠን ከላይ ይመለክቱ)

@tikvahethiopia