TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#አቢሲንያ_ባንክ

ወርሃዊ ክፍያዎችን በፍጥነት ባሉበት ሆነው ለመፈጸም የአቢሲንያ የሞባይል ባንኪንግ መተግበርያን ይገልገሉ። 

ሊንኩን በመጠቀም መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!

ለአንድሮይድ ስልኮች https://

play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች  https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765

ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115
ፎቶ ፦ ከትግራይ ተጉዘው አዲስ አበባ የተገኙ ከትግራይ ክልል ከተለያየ የህብረተሰቡ ክፍል የተውጣጡ ተወካዮች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መከሩ።

በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከትግራይ ክልል ተጉዘው ከመጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አሳውቀዋል።

" በትግራይ ክልል ሰላም እና ልማትን ለማስገኘት ያለን ቁርጠኝነት ሁልጊዜም ፅኑ ነው " ያሉት ጠ/ሚስትሩ " የዛሬው ውይይታችንም ይህንኑ የጋራ አላማ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚሰጥ ነው “ ብለዋል።

ዛሬ በተካሄደው የውይይት መድረክ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና የመከላከያው ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ተገኝተው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰሞኑን ከሁሉም ክልል ተወካዮች ጋር እንዲሁም ከሃይማኖት አባቶች ጋር ምክክር ሲያደርጉ ሰንብተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባገኘው መረጃ የትግራይ ተወካዮቹ ከሁሉም የትግራይ ዞኖች የተውጣጡ ሲሆኑ ብዛታቸው 200 ይጠጋል።

በቻርተር  አውሮፕላን እንዲጓዙ ተደርጎ ነው አዲስ አበባ የመጡት። አዲስ አበባ ከመጡ በኃላ ትላንት የዓድዋ መታሰቢያንን ጨምሮ ሌሎች ቦታዎችን እንዲጎበኙ ተደርጓል። ዛሬ ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

@tikvahethiopia
#ICS #Ethiopia

" በአሁን ሰዓት የተጠራቀመ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ አጠናቀናል " - ICS

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳዮች አገልግሎት በትግራይ ተቋርጦ የሚገኘውን የኢሚግሬሽን አገልግሎት ለማስጀምር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

አገልግሎቱ ትላንት በሰጠው መግለጫ ነው ይህን ያለው።

በሌላ በኩል ፤ ባለፉት 6 ወራት ከ1.1 ሚሊዮን በላይ የፓስፖርት ቡክሌቶችን ከውጭ ሀገር በማስገባት 640 ሺህ ፓስፓርት ፐርሰናላይዜሽን ህትመት በመስራት ለተጠቃሚዎች ማድረሱን አሳውቋል።

• ለአዲስ አበባ 260,371፣
• በየአካባቢው ላሉ ቅ/ጽ/ቤቶች 269,358፣
• በአስቸኳይ 35,394 እና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን 81,416 እንደሆነ አመላክቷል።

የውስጥ ህትመት አቅምን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በቀን 2 ሺህ ይታተም የነበረው አሁን ወደ 10 ሺህ በላይ ወደማተም ደረጃ መደረሱን ገልጿል።

መ/ቤቱ በአሁን ሰዓት የተጠራቀመ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ እንዳጠናቀቀ በይፋ አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ በእጁ ላይ 80 ሺህ ፓስፖርት ስላለ ያመለከቱና ተራው የደረሳቸው በስልክ በሚደርሳቸው መልዕክት መሰረት እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።

ፓስፖርት ለማውጣት ከዚህ ቀደም ይወስድ የነበረው የአንድ አመት ጊዜ ከመጋቢት 16 /2016 በኃላ እንደሚቀረፍ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳዮች አገልግሎት ገልጿል።

ከዚህ በባለፈ ፤ ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ፦
➡️ከዋና ቢሮ፣
➡️ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣
➡️ ከቦሌ፣
➡️ከኬላዎች በድምሩ 205 የሚሆኑ ሠራተኞች ውጭ ካሉ #ደላሎች ጋር በመተባበርና የአሰራር ክፍተትን በመጠቀም ከህብረተሰቡ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሰሩ መረጃ ተገኝቶባቸው ለህግ አካላት እንዲቀርቡ እንደየጥፋታቸውም ከስራ እንዲታገዱና የህግ ውሳኔ እንዲሰጣቸው መደረጉን አስረድቷል።

ህብረተሰቡ ፦

* ተመሳስለው ከተሰሩ ዌብሳይቶች ራሱን እንዲጠብቅ
* በግለሰብ አካውንት ምንም አይነት ገንዘብ ገቢ እንዳያደርግ፣
* ዜግነት ማጣራት ጋር በተያያዘ ሂደት ያለው ስለሆነ የሚጠየቁ ሰነዶችን በትዕግስት እንዲያቀርብና እንዲተባበር፣
* ፖስፖርት ውሰዱ ተብለው የጽሁፍ መልዕክት ሲደርሳቸው በተባለው ቀን እና ሰዓት እንዲወስዱ፣
* አስቸኳይ ፓስፖርት በኦንላይን የማይሰጥ ስለሆነ አስቸኳይ የሚያሰጥ ሰነድ ያላቸው ተገልጋዬች በዋናው ቢሮ ብቻ በአካል በመገኘት  መስተናገድ እንዳለባቸው አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ በአጭር ጊዜ እንደሚከፈል መግባባት ላይ ተደርሷል ” - የትግራይ መምህራን ማህበር የትግራይ መምህራን ማህበር ስራ አስፈፃሚ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ባካሄደው ውይይት ላቀረባቸው ጥያቄዎች የሚጨበጥና ተስፋ ሰጪ መልስ ማግኘቱን ለሁሉም የወረዳ መምህረን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ማህበሩ ምን አለ ? - የመምህራን መብትና ጥቅም አስመልክቶ ከሚመለከታቸው የመንግስት…
 #Update

" ለፍትሃዊ ጥያቄ ፍትሃዊ ምላሽ መሰጠት አለበት ፤ መንግስት የገባው ቃል ካልተገበረ ማህበሩ መብቱን ለማስከበር ይንቀሳቀሳል " - የትግራይ መምህራን ማህበር

የትግራይ መምህራን ማህበር የተገባለት ቃል እንዲተገበር ጠየቀ።

ማህበሩ ባወጣው መግለጫ፤ መምህሩ የተማሪው የትምህርት ጥማት ለማርካት እየሰራ ቢገኝም ላቀረበው ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ባለማግኘቱ በኑሮ ውድነት ከፉኛ እየተጎዳ ይገኛል ብሏል።

ባለፈው ጥር 2016 ከጊዚያዊ አስተዳደሩና የትምህርት ቢሮ ጋር ባደረገው ወይይት የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ በአጭር ጊዜ እንደሚከፈል መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር ይታወሳል።

በውይይቱ ላቀረባቸው ጥያቄዎች የሚጨበጥና ተስፋ ሰጪ መልስ ማግኘቱን በይፋ ለመምህራን አሳውቆም ነበር።

በወቅቱ በነበረው ውይይት የተነሱት ነጥቦች ፦
የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ፣
የ2014 ዓ.ም የ 12 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ፣
ከደደቢት ማይክሮፋይናስ ስለተወሰደ የብድር ወለድ ስለሚነሳበት ሁኔታ፣ 
የመምህራን የትራንስፖርት አገልግሎት ሰርቪስ ስለማግኘት፣ የሚሉ እንደነበሩ ይታወሳል።

በውይይቱ ፦
* በተለይ ዉዝፍ ደመወዝ የሚመለከት የ2015 ዓ.ም የ5 ወራት በአጭር ጊዜ እንደሚከፈል የ2014 ዓ.ም የ12 ወራት ዉዝፍ ደመወዝ መከፈል የሚመለከት ጥያቄ ወደ ፌደራል መንግስት መቅረቡ ፣

* ከደደቢት ማይክሮፋይናንሰ የተወሰደ የብድር ወለድ ስለሚነሳበት ሁኔታ ቀጣይ ውይይት እንደሚካሄድ ፣

* የከተማ የመምህራን ሰርቪስ የሚመለከት ጥያቄ በአጭር ጊዜ እንደሚመለስ መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር ማህበሩ ይፋ አድርጎ ነበር።

ነገር ግን እስከአሁን የተመለሰ ጥያቄ የለም ብሏል።
            
ከማህበሩ ጥያቄ አንድም ባለመመለሱ መምህራን በአኗኗራቸውን በሙያቸው አሉታዊ ጫና እንደፈጠረባቸው  የገለፀው ማህበሩ ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የገባው ቃል የማይፈፅም ከሆነ ምክር ቤት በመጥራት ችግሩ ላይ ተወያይቶ አቋም በመያዝ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል።

ማህበሩ በቀጣይ እወሰድዋለሁ ስላለው እርምጃ የሰጠው ፍንጭ የለም።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                            
@tikvahethiopia            
" ከቀን ወደ ቀን እየተበባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት ለጤና ባለሙያዎች ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል " - የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ፕሬዚዳንት አቶ ዮናታን ዳኛው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ያነሰ ትኩረት ምክንያት ብዙዎች የሚወዱትን የሙያ ዘርፍ በመልቀቅ፣ በመቀየር እንዲሁም አገር ጥለው በመውጣት ላይ ይገኛሉ " ብለዋል።

እንዲህ የሆኑት ምን ያህል የጤና ባለሙያዎች ናቸው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ዮናታን፣ " በቁጥር ይህ ነው ብዬ ባልገልጽም በonline apply እያደረጉ ብዙ ጤና ባለሙያዎች፦
- ነርሶች፣
- ሀኪሞች፣
- ሚድዋይፎች፣
- ጤና መኮነኖች በተለያዩ መንገዶች አገር ጥለው እየወጡ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" ወደ ፊላንድ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ካናዳ በህጋዊም በህገ ወጥም መንገድ ብዙ ጤና ባለሙያዎች ከአገር እየለቀቁ ነው። ብዙ የጤና ባለሙያዎች የህክምና ሙያቸውን ጥለው ወደ ንግድ እንዲሁም ወደ ተለያዩ ዘርፎች እየቀየሩ እንደሆነ ብዙ ተጨባጭ መረጃዎች አሉን። በየቀኑ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ቅሬታዎችን የምንቀበልበት አካሄድ አለን " ሲሉ አክለዋል።

“ ጤና ባለሙያዎች ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ወደ ዩንቨርስቲ የሚቀላቀሉ ቢሆኑም በተቃራኒው ግን በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮች ሆነው ይገኛሉ " ነው ያሉት አቶ ዮናታን።
 
በሥራ ላይ ያሉትም፣ " ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በሰላማዊ መንገድ የመብት ጥያቄዎችን ለመንግሥት ቢያቀርቡም እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ አለመሰጠቱ በባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል " ያሉት የማኀበሩ ፕሬዚዳንት፣ ቅሬታዎቹን እንዲጠቅሱ ሲጠየቁም፣ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ የጤና ባለሙያዎች ለመንግሥት ያቀረቧቸው ዋና ዋና ጥያቄዎች፦
* የደሞዝ ማሸሻያ፣ 
* የነፃ ህክምና፣
* የHouse allowance፣
* የRisk /ተጋላጭነት /
* የቤት፣
* የትርፍ ሰዓት ክፍያ ጥያቄዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ " በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ የመብት ጥያቄዎችን ማቅረብ እንደ ነውር ሊታይ አይገባም። የሰላማዊ ድምፆች ሊደመጡ ይገባል " ብለዋል።

" ከቀን ወደ ቀን እየተበባሰ የሚገኘዉ የኑሮ ውድነት  ለጤና ባለሙያዎች ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል" ብለው፣" መንግሥት በጤና ስርዓቱ ላይ የሚከተለውን ፓሊስ ቆም ብሎ ሊመረምረው ይገባል። የቱንም ያክል የዘመነ እና የረቀቀ የጤና ፓሊሲ ቢኖር ጤና ባለሙያዎችን መሠረት ያላደረገ ፓሊሲ ምንም ያክል እርቀት አይሄድም፣ የታቀደውንም ውጤት አያመጣም " ሲሉ አስገንዝበዋል።

“ መሠረታዊ ፍላጎቱን ማሟላት የማይችል ጤና ባለሙያ ለታካሚዎች ተገቢዉን ህክምና ይሰጣል ብሎ ማሰብ በፍፁም አይቻልም። መንግስት በጤና ባለሙያዎች ላይ እየደረሱ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እና የሚነሱ የመብት ጥያቄዎችን ችላ ከማለት ወጥቶ በአገር ላይ የከፋ ችግር ከማስከተላቸው በፊት መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ ጥሪን አቀርባለሁ ” በማለት አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ፤ " የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ ችግሮች አሉ። የእኛም ማኀበር ይህን በተመለከተ በመግለጫ ሁኔታዎች እንዲስተካከሉ ጠይቋል። ችግሩ ግን መፍትሄ አላገኘም አሁንም ብዙ ቅሬታዎች አሉ " ብለዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ነው።

@tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ 430 የጋራ መኖሪያ ቤቶች #ለመምህራን በዕጣ መተላለፋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።

ዛሬ የተላለፉት ቤቶች ከዚህ በፊት ለመምህራን ተላልፈው ከነበሩ 5,000 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ውል ሳይፈጸምባቸው የቆዩ 435 ቤቶች ከተለዩ በኃላ መሆኑን ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
አዲሱን የ5G ኔትወርክ የሚያስጠቅሙ የ ZTE ስልኮችን ከአጓጊ የጥቅል ስጦታ ጋር!

የ ZTE ብሌድ ኤ73 5ጂ ስልኮችን በመግዛት ፈጣኑን የአምስተኛውን ትውልድ ፍጥነት ያጣጥሙ ።

ስማርት ስልኮቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ሲገዙ የአንድ ዓመት 2 ጊ.ባ ወርሃዊ የዩትዩብ ጥቅልን ጨምሮ፣ ለተከታታይ ሶስት ወራት 20 ጊ.ባ ወርሃዊ ዳታ ከ 500 ደቂቃ የድምጽ ጥቅል ስጦታ ጋር አቅርበናል፡፡

በአቅራቢያዎ በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን ወይም በቴሌገበያ ድረ ገጽ https://telegebeya.ethiotelecom.et/ ይገኛሉ!

#BeyondConnectivity
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ተመልሰዋል 💥

👉የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በሱፐርስፖርት ልዩ ቻናል 240 እንዲሁም በሱፐርስፖርት ልዩ2 ቻናል 239 በ አማርኛ ኮሜንትሪ ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ በቀጥታ ይመልከቱ!

📣 አዲስ ነገር ይዘን መጥተናል!

👉ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ለቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ደንበኝነትዎን ወደ ሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ሲያሳድጉ...
እኛም ቀጣዩን የፕሪሚየም ፓኬጅ ለአንድ ወር እንጋብዝዎታለን!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#EthiopianPremierLeague #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvSelfService #DStvEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

ፒያሳ የሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ተነግሯል።

የድል መታሰቢያው የሚጎበኝበት ዋጋ ዝርዝርም ይፋ ሆኗል።

የጀግኖች ምስለ ቅርፅና ድሉን የሚያወሱ ቁሳቁሶች በመታሰቢያው ለጎብኚዎች ክፍት የሚሆኑ ሲሆን ክፍያው በቴሌ ብር፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መፈፀም ይችላል ተብሏል።

በዚህም መሰረት ፦

ለመደበኛ 150፣
ለተማሪዎች 75
ለልዩ ልዩ 550 ብር እንደሆነ ተገልጿል።

መታሰቢያው ከ2:30 እስከ 11:30 ሰዓት ተኩል ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia