#Ethiopia 🤝 #Somaliland
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) ኢትዮጵያ በሱማሌላንድ በምትወስደው የወደብ ስፍራ ላይ ልማት ለማከናወን ሲዘጋጅ መቆየቱን አስታውቋል።
ትላንት የተፈረመው ስምምነት ለስራችን ትልቅ ዜና ነው ያሉት የኢባትሎ ዋና ስራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር)፤ በድርጅቱ ስራ ላይ ትልቅ እመርታ የሚያመጣ ነው ብለውታል።
በተለይ ከዋጋ እና አላስፈላጊ ወጪ ጋር በተገናኘ እንደ አገር ትልቅ እፎይታ የሚያመጣ ነው ሲሉ ስምምነቱን አሞግሰዋል።
ድርጅታቸውም በተወሰደው ቦታ ላይ መሰረተልማት ለማከናወን ሲዘጋጅ እንዲሁም የሚያስተዳድራቸውን መርከቦች መጠን ለመጨመር ሲሰራ እንደቆየ ነው የገለፁት።
ትላንት ይፋ በተደረገው ስምምነት ኢትዮጵያ በሱማሌላንድ የበርበራ ከተማ በስተ ሰሜን አቅጣጫ በሚገኝ የባህር ዳርቻ የራሷን የጦር ሰፈር እና የንግድ ወደብ እንደምታለማ ተገልፀጿል።
Via CAPITAL
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ ይፋዊ መግለጫ ወጥቷል። በዚህም መግለጫ ስምምነቱ ታሪካዊ ነው ተብሏል። ይህ ታሪካዊ ስምምነት ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እውቅና በመስጠት በሊዝ የባህር በር / ለባህርኃይሎቿ የባህር መዳረሻ እንደምታገኝ መግለጫው ይገልጻል። " ስምምነቱ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ነው " ያለው መግለጫው ለኢትዮጵያ የባህር ኃይል ተጠቃሚነት 20 ኪሎሜትር የባህር በር እንደሚሰጥ…
#Ethiopia #Somaliland
አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ምን አሉ ?
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ የኢትዮጵያ የባህር በር መዳረሻ መኖር ለቀጠናዊ ውህደት ቁልፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ከሶማሊላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት ቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም አሳውቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ " የሶማሌላንድ መንግስት ያወጣውን መግለጫ በደስታ እንቀበላለን። " ብለዋል።
የሶማሊላንድ መንግስት ዛሬ ጥዋት ባወጣው መግላጫ ኢትዮጵያ በሊዝ የባህር ወደብ እንድታገኝ በምላሹ ደግሞ ለሶማሊላንድ እውቅና እንድትሰጣት የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙን አሳውቋል።

#Update ሶማሊያ በኢትዮጵያ ያሉትን አምባሳደሯን መጥራቷን ተከትሎ አምባሳደር አብዱላሂ ዋርፋ ወደ #ሞቃዲሾ ማቅናታቸው ተሰምቷል። በሌላ በኩል ደግሞ ፤ የሶማሊያ ሁለቱ የፌደራል ፓርላማ ምክር ቤቶች በአሁን ሰዓት አስቸኳይ የጋራ ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን በዚህ ስብሰባ ላይ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል። ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ የወደብ እና…
#Somalia #Somaliland
" የሶማሊያ ደካማ መንግስት ይሄን ታሪካዊ ስምምነት ለማስቆም ምንም አይነት ሕጋዊነት የለውም " - አብዱላሂ አርሼ (የሶማሊላንድ ባለስልጣን)
የቀድሞ የሶማሊላንድ " የሀገር ውስጥ " ሚኒስትር አማካሪ እና በአሁን ሰዓት በሶማሌላንድ " የሀገር ውስጥ " ሚኒስቴር የሚዲያ እና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አብዱላሂ አርሼ የሶማሊያን መንግሥት " ደካማ መንግሥት " ሲሉ ጠርተው በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ ሪፐብሊክ መካከል የተፈረመውን #ታሪካዊ_ስምምነት ለማስቆም ምንም አይነት ሕጋዊነት የለውም ብለዋል።
" የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና የሰጠው የሶማሊያ ስርዓት እንደ ወቀደ መንግስት ነው፣ ሞቃዲሾ ውስጥ የአስተዳደር ስርዓት የለም። " ሲሉ ጠንካራ ትችት ሰንዝረዋል።
ኢስማኤል ሺርዋክ የተባሉ የሶማሊላንድ ዲፕሎማት ደግሞ ፤ " ሀገራችን አንድ እርምጃ ወደፊት ስትሄድ ሶማሊያ በታሪክ ግልፅ የሆነ ጥላቻ አሳይታለች። " ያሉ ሲሆን " ሶማሌላንድ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (#UAE) ስምምነት ላይ ሲደርሱ ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል፣ ነገር ግን ምንም አይነት ውጤት አላመጣም። " ብለዋል።
" እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር የዜጎቻችንን ጥቅም መሰረት አድርገን የሚያስፈልገውን እንወስናል " ሲሉ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ ለሁለቱ የፌዴራል ም/ቤት አባላት ንግግር ማድረጋቸው የተሰማ ሲሆን የሶማሊላንድ እና የኢትዮጵያን የትብብር ስምምነት ሰነድ ተቃውመዋል።
" አንድም ኢንች የሶማሊያ ግዛት በማንም ሊፈረም አይችልም ፤ሉዓላዊነታችንንና የግዛት አንድነታችንን እንጠብቃለን ፤ በዓለም አቀፍ ህጎች መሰረት እናስከብራለን፤ እያንዳንዱን ኢንች መሬት እንጠብቃለን፤ ሶማሊያ የሶማሊያውያን ነች ፤ ይሄ የመጨረሻው ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" አቶ መለስ ዜናዊ በሶማሊያ ውስጥ የገቡት ጣልቃ ገብነት የአልሸባብን መነሳት አስከትሏል " ሲሉ የተደመጡት ፕሬዜዳንቱ " የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እርምጃም ያሸነፍነውን አልሸባብ ዳግም እንዲነሳሳ ሌላ ዕድል የሚሰጥ ነው " ብለዋል።
" የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጥር 1 ከያዙት መንገድ እንዲመለሱ " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ያላቸው አማራጭ አንድ ብቻ ነው እሱም በሰላም መኖር ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።
የሶማሊንላንድ ባለልስጣናት ስምምነቱን የደገፉ ሲሆን በሶማሊያ ባለስልጣናት ላይም ጠንክራ ትችት እየሰነዘሩ ይገኛሉ። ስምምነቱን የማስቆም ምንም አይነት አቅም የላቸውም ሲሉ እየተደመጡ ናቸው።

ቪድዮ ፦ የጃፓን አየርመንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ዛሬ በቶኪዮ ሃኔዳ አውሮፕላን ማረፊያ እንዳረፈ #በእሳት ተያይዟል።
12 የበረራ ቡድን አባላትን ጨምሮ 379 ሰዎችን ያሳፈረው አውሮፕላን በእሳት ቢያያዝም አንድም ሰው ህይወቱ ሳያልፍ ከእሳት አደጋው ማትረፍ ተችሏል።
367 መንገደኞችን ያሳፈረው የጃፓን አየርመንገድ አውሮፕላን መነሻው በሆካይዶ ደሴት ሺን ቺቶሴ ከተባለ አካባቢ እንደነበር ተገልጿል።
አውሮፕላኑ 6 ሰዎችን አሳፍሮ ከነበረ ሌላ የጃፓን ባህር ዘብ ትንሽ አውሮፕላን ጋር መጋጨቱ ተነግሯል። ከ6ቱ አምስቱ ሲሞቱ ፓይለቱ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በህይወት ተርፏል።
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ግን የአደጋውን መንስኤና የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ቡድን አቋቁመዋል።
የመረጃ ምንጭ፦ ሮይተርስ፣ አልአይን፣ ዶቼቨለ ናቸው።
ቪድዮ ፦ ከማበራዊ ሚዲያ

ለገና በዓል ከባህር ማዶ ከወዳጅ ዘመድ በዌስተርን ዩኒየን ዓለም-አቀፍ ሃዋላ የሚላክልዎትን ገንዘብ አቅራቢያዎ በሚገኝ የኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ይቀበሉ፤ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ በማስተላለፍ ተጨማሪ የ10% ስጦታ ያግኙ!
እንዲሁም ከባህር ማዶ በአጋሮቻችን በኩል በቴሌብር ዓለም-አቀፍ ሃዋላ ገንዘብ ሲላክልዎ፤ የተላከልዎትን መጠን 10% በስጦታ ያገኛሉ!
መልካም በዓል!
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

Photo
“ ‘ልጆቼን ልያቸው’ ብሎ ማታ ሲመጣ ከሁለት አቅጣጫ ተተኮሰበት ሞተ። " - የመተሃራ ነዋሪ
ከታህሳስ 19/2016 ዓ/ም ወዲህ ባሉት ቀናት ብቻ በተለያዩ ቦታዎች ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ አሽከርካሪዎችን ጨምሮ ስምንት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን፣ ከአሥር በላይ ተጓዦች መታገታቸውን፣ እንዲሁም ስምንት ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን የዓይን እማኞችና የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አንድ የመተሃራ ከተማ ነዋሪ በመተሃራ በኩል የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተ በሰጡት ቃል፣ “ በቀን 19 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት ላይ መኪናውን አዋሽ ሰባት አቁሞ በሌላ መኪና ተለጥፎ ‘ልጆቼን ልያቸው ብሎ ማታ ሲመጣ ከሁለት አቅጣጫ ተተኮሰበት ሞተ ” ነው ያሉት።
“ ግድያውን የፈጸሙት ታጣቂዎች ናቸው ” ያሉት ነዋሪው፣ ሟቹ ተወልዶ ያደገው መተሃራ እንደሆነ፣ ተሽከርካሪ ገዝቶ በአፋር ክልል በኩል ከአዋሽ ሰባት - መተሀራ ባለው መንገድ የሽንኩርት ጭነት ሥራ ይሰራ እንደነበር፣ ግድያው የተፈጸመው በአዋሽ ፓርክ ወደ መተሃራ ወረድ ብሎ በሚገኝ ጫካማ ስፍራ መሆኑን አስረድተዋል።
ሌላኛው የመተሃራ ከተማ ነዋሪ በበከላቸው፣ “ ከቁልቢ ገብርኤል በዓለ ንግስ ደርሰው ሲመለሱ በተጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 6 ደርሷል። እስካሁን ባለው መረጃ ከ10 በላይ ሰዎች ታግተዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።
ግድያው የተፈፀመባቸው ከአቃቂ ባቡር ጣቢያ መጋላ ሰፈር የሄዱ ሲሆኑ ከተገደሉትና ከታገቱት ሰዎች ባሻገር ጉዳት የደረሰባቸው ሴት ተጓዦች መኖራቸውንም አክለዋል።
በሌላ በኩል ሌላኛው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጭ ታህሳስ 21 ቀን 2016 ዓ/ም ወደ ሀዋሳ በሚወስደው ፈጣን መንገድ ምሽት ላይ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል ብለዋል።
ከተቃጠሉት ተሽከርካሪዎች መካከል የአንዱን አይሱዙ ባለቤት እንደሚያቁት፣ አይሱዙው ከተገዛ ገና 6 ወራት እንደሆነው፣ ተኩስ ሲከፈትበት ሹፌሩ ሸሽቶ እንዳመለጠና የጫነውን ሙሉ ንብረት ጨምሮ ተሽከርካሪዎው እንደተቃጠለ አስረድተዋል።
ከሀዋሳ አዲስ አበባ ያለው ፈጣን መንገድ ከባቱ (ዝዋይ) ጀምሮ እስከ ሞጆ ባለው መስመር ከዚህ ቀደም ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት ማድረሳቸውን አስታውሰዋል።
" በዚሁ መስመር ሚሊሻ የሚባሉት ራሱ ከታጣቂዎች ባልተናነሰ ነው አሽከርካሪዎችን ያሰቃያሉ ” ሲሉ አስረድተዋል።
ሌላኛው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጭ በበኩላቸው የላኩትን ምስል መሠረት በማድረግ በሰጡን ገለጻ፣ “ ሰሞኑ 20 ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል። ቦታውም ከአዲስ አበባ ወደ ቡታጅራ በሚወስደው መንገድ ከሌመን ጀምሮ እስከ ጢያ ድንበር ድረስ ነው ፤ ይህ ሁሉ በአንድ ቀን የተቃጠለ መኪና ነው " ሲሉ " ገለጸዋል።
አክለውም፣ “ ከዛም ውስጥ አንድ ሹፌር ለማምለጥ ሲሞክር አብሮ የተቃጠለበት ሁኔታ ነው ያለው። የተቃጠለው ሹፌር የቡታጅራ ልጅ ሲሆን፣ ከዚህ በፊት በተራ አስከባሪነት ህይወቱን ይመራ ነበር። በክስተቱ ብዙ ተሳፋሪዎች የታገቱ ሲሆን፣ ምስሉን ወደ አዲስ አበባ ሂጄ በሦስተኛ ቀኔ ስመለስ ያነሳሁት ነው። ስሄድ ሰላም የነበረ አገር በዬ ከተማው እስከ 6 መኪና ተቃጥሎ ደረስኩ ” ብለዋል።
በአሽከርካራዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ ምን እየሰሩ እንደሆነ ከባለድርሻ አካላት ሁሉ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሰባት አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች እንደተገደሉ፣ ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ የተገደሉት ደግሞ 70 እንደሚሆኑ መዘገባችን አይዘነጋም።
ዘገባውን የላከው የአዲስ አበባ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

#INDIA #UAE
ህንድ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ዛሬ በህንድ ሰሜን ምዕራብ በምትገኘው ራጃስታን ግዛት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ መጀመራቸው ተሰምቷል።
ወታደራዊ ልምምዱ " Desert Cyclone " በሚል ለቀጣይ ሁለት ሳምንት የሚዘልቅ ሲሆን በሀገራቱ መካከል ያለውን ወታደራዊ ልምድ እንዲለዋወጡ እንደሚያስችል እና ያላቸውን ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ተነግሯል።
የተባባሩት አረብ አሜሬትስ (UAE) ፤ ህንድ ያለችበትን የBRICS አባል ሀገራት በትላንትናው ዕለት ከነ #ኢትዮጵያ ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ እና ኢራን ጋር በይፋ መቀላቀሏ ይታወሳል።