TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#US #Egypt

የዴሞክራት ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ ተቀብለው በአሜሪካ ሴኔት ውስጥ የግብፅን አጀንዳ በማራመድና በሌሎች ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ። 

በሴናተሩ ላይ የቀረቡትን ክሶች የተመለከተው የኒውዮርክ ፍ/ቤት በመጪው ጥቅምት ወር የቅጣት ውሳኔ ለማሳለፍ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል። 

ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ በአሜሪካ ሴኔት ውስጥ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ በነበሩበት ወቅት፣ ለዓመታት የግብፅን አጀንዳ በሴኔት ውስጥ ሲያራምዱ እንደነበር ለዚህም ከግብፅ መንግሥት ክፍያ ማግኘታቸውን ዓቃቤ ሕግ የሰነድ ማስረጃና የሰው ምስክሮችን በማቅረብ አረጋግጧል።

የሴናተር ሜኔንዴዝ ባለቤት የሆነችው ናዲኔ ሜኔንዴዝ  እ.ኤ.አ. በማርች 2020 ገደማ ባለቤቷ ሴናተር ሜኔንዴዝ ከአንድ የግብፅ ጦር ጄኔራል ጋር እንዲገናኙ ፕሮግራም ማዘጋጀቷንና በፕሮግራሙ ላይም ሴናተሩ ከግብፅ ጄኔራል ጋር ተገናኝተው በወቅቱ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በግብፅ፣ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ይካሄድ ስለነበረው ድርድር መወያየታቸውን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል።

በወቅቱም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዋነኛ የትኩረት አጀንዳ ተደርጎ ይወሰድ እንደነበር የምርመራ ሰነዱ ይገልጻል።

ሴናተሩ ከግብፅ ጄኔራል ጋር በተገናኙ በቀጣዩ ወር ውስጥ (በኤፕሪል 2020 ወይም ገደማ)፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ለሚሳተፉት ለወቅቱ የአሜሪካ ግምጃ ቤት ፀሐፊና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደብዳቤ መጻፋቸውን ያትታል።

በደብዳቤያቸው መግቢያ ላይም፣ " እኔ ይህንን ደብዳቤ የምጽፈው ግብፅ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን በግድቡ ዙሪያ ያደርጉት የነበረው ድርድር መቋረጥ እንዳሳሰበኝ ለመግለጽ ነው " ማለታቸውን ያስረዳል።

በማከልም፣ " የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በግድቡ ድርድር ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሳድግ እጠይቃለሁ "ማለታቸውን የምርመራ መዝገቡ ይጠቅሳል።

እ.ኤ.አ. በ2021 መገባደጃ ላይ የሴናተር ሜኔንዴዝ ባለቤት የሆነችው ናዲኔ ሜኔንዴዝ አዘውትራ ከምትገናኘው ከግብፅ ጄኔራል ጋር በመነጋገር እሷና ባለቤቷ ሜኔንዴዝ ወደ ግብፅ እንዲጓዙ ፕሮግራም ማመቻቸቷንና ጉዞውም በጥቅምት 2021 መደረጉን ያስረዳል። 

በመጀመሪያ ጉዞው መደበኛ ያልሆነ ወይም ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቁጥጥር ውጭ እንዲካሄድ የታቀደ መሆኑን የሚያለክተው የምርመራ መዝገቡ፣ በኋላ ላይ አንድ የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ባልደረባ በካይሮ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ በማነጋገር ጉዞው በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እውቅናና ቁጥጥር የሚደረግበት መደበኛ የኮንግረንስ ልዑክ የሥራ ጉብኝት እንዲሆን ማነጋገሩን ይጠቅሳል።

ነገር ግን ይህ ጥያቄ መቅረቡን ያወቀው የግብፅ ባለሥልጣን እንደዚያ ሊሆን እንደማይችል የሚገልጽ መልዕክት ለናዲን ሜኔንዴዝ መላኩንና ናዲን ሜኔንዴዝም ምልዕክቱን ለሴናተር ሜኔንዴዝ መላኳን በዚህም ምክንያት ሴናተሩና ባለቤታቸው ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እውቅና ውጪ እንደተካሄደ በምርመራ መዝገቡ ተጠቅሷል።

ሜኔንዴዝና ባለቤታቸው ወደ ግብፅ ከተጓዙ በኋላም በካይሮ ከበርካታ የግብፅ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተውና በአንድ ከፍተኛ የግብፅ የስለላ መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን የግል መኖሪያ ቤት እራት መብላታቸውን ያስረዳል።

በእነዚህ ወቅቶችም ልዩ መለያ ቁጥር የተከተበባቸው ባለ አንድ ወቄት የሚመዝኑ 22 የወርቅ ባሮችን (አሞሌዎችን) ከግብፅ መንግሥት በክፍያ (በጉቦ) መልክ ማግኘታቸውን፣ በዚያ ወቅት የገበያ ዋጋ መሠረት አንዱ ወቄት የወርቅ ባር 1,800 ዶላር እንደነበርና ክስ ከተመሠረተ በኋላ በወጣ የፍርድ ቤት የብርበራ ማዘዣ ሁለት የወርቅ አሞሌዎች በመኖሪያ ቤታቸው መገኘቱን የምርምራ መዝገቡ ያስረዳል።

የአሜሪካ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንደገለጸው፣ ሴናተር ሜኔንዴዝ በተለያዩ ጊዜያት ከግብፅ የስለላ ባለሥልጣናት ጋር መገናኘታቸውን፣ ከእነዚህም መካከል በአሜሪካ የምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ሚስጥራዊ ክትትል በተደረገበት በሞርተን ሬስቶራንት ውስጥ ከግብፅ የስለላ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው እራት በመብላት ለግብፅ መረጃ አሳልፈው መስጠታቸውን እንዲሁም ለግብፅ ምቹ ወታደራዊ የጦር መሣሪያ ድጋፍ ለማስገኘት ማሴራቸውን ይገልጻል።

ሜኔንዴዝ ለግብፅ መንግሥት ራሳቸው ደብዳቤ አዘጋጅተው ከሰጡ በኋላ ይህንኑ ደብዳቤ በመጠቀም በግብፅ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ሌሎች የኮንግረስ አባላት ያላቸውን ሥጋት ለማግባባት እንደተጠቀሙበት የአሜሪካ ፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የክስ ሰነድ ያስረዳል።

በጥቅሉ የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ እ.ኤ.አ. በጁን 16 ቀን 2022 ከሜኔንዴዝ ቤት በድምሩ 486,461 ዶላር፣ አንድ ወቄት የሚመዝኑ 11 የወርቅ አሞሌዎችንና አንድ ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ሁለት የወርቅ አሞሌዎችን በቁጥጥር ሥር አውሏል።

በአጠቃላይ የኒው ጀርሲው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የውጭ መንግሥት ፍላጎትን ለመፈጸም ሥልጣናቸውን መጠቀም፣ ጉቦ መቀበል፣ ማጭበርበር፣ ፍትሕን ማደናቀፍን ጨምሮ በ16 የወንጀል ድርጊቶች የተከሰሱ ሲሆን፣ ባለፈው ማክሰኞ በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ ተብለው ተበይኖባቸዋል።

የቅጣት ውሳኔውን ለማስተላለፍ ለመጪው ጥቅም ወር 2017 ዓ.ም. ቀጠሮ የተያዘ ሲሆን፣ ሴናተሩ በትንሹ ከ20 ዓመት በላይ እስር ሊፈረድባቸው እንደሚችል ሲኤንኤንን ጨምሮ የተለያዩ የአሜሪካ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

Credit - Reporter Newspaper

@tikvahethiopia
#Egypt #Somalia : የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ' ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ' ብለው ግብፅ ይገኛሉ።

የፕሬዜዳንቱ ቢሮ እንዳለው በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ግንኙነታቸው በማጠናከር ላይ ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር መክረዋል።

ስምምነታቸው ይዘቱ ምን እንደሆነ በዝርዝር ባይታወቅም ሀገራቱ #ወታደራዊ ትብብር ፕሮቶኮል ስምምነትም ተፈራርመዋል።

ግብፅ በሞቃዲሾ ኤምባሲ መክፈቷም ተነግሯል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ወደ ፕሬዜዳንትነት ስልጣን ከመጡ በኃላ ከግብፅ ጋር የተለየ ወዳጅነት ለመመስረት ሲሰሩ ታይቷል።

በተለይም ደግሞ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች በኋላና ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነቷ ከሻከረ በኃላ ወደ ግብፅ ብዙ ጊዜ እየተመላሳለሱ ይገኛሉ።

Photo Credit - Villa Somalia

Via @thiqahEth
TIKVAH-ETHIOPIA
ግብፅ ? ግብፅ፣ ሶማሊያን እያስታጠቀች ነው። ሶማሊያ የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ከግብፅ እንደተሰጧትና ተጨማሪ መሳሪያዎችን በቀጣይነት እንደምትጠብቅ አንድ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለሥልጣን ተናግረዋል። ስማቸው ሳይጠቀስ ለቢቢሲ ሶማሊኛ የተናገሩ ባለሥልጣን ባለፉት ቀናት በመርከብ ተጭነው ወደ ሞቃዲሾ ወደብ የደረሱት የጦር መሳሪያዎች እንዳሉ ጠቁመዋል። እነዚህ መሳሪያዎች የሶማሊያ መንግሥት ጦር የሚታጠቃቸው…
" ... ግብፆች መርዳት ከፈለጉ ለምን ፍልስጤሞችንና ሌሎች ዓረብ አገሮችን አይረዱም ? " - አምባሳደር አብዱላሂ መሐመድ ዱአሌ

አምባሳደር አብዱላሂ መሐመድ ዱአሌ ፤ የሶማሌላንድ የአፍሪካ ኅብረትና የኢጋድ ልዩ መልዕክተኛ ግብፅ በቀጣናው ስለምታደርገው እንቅስቃሴ ምን አሉ ?

(ለሪፖርተር ጋዜጣ ከተናገሩት የተወሰደ)

" የግብፅ እንቅስቃሴ በግልጽ ጣልቃ ገብነት ነው፡፡ ግብፅ ወደ ሶማሊያ መሣሪያ እያሠራጨች ነው፡፡

በመሣሪያ እየታመሰ ባለ ቀጣና ውስጥ ሌላ መሣሪያ እንዲመጣ አንፈልግም፣ በሶማሊያ እያንዳንዱ ግዛት መሣሪያ ተበትኗል፡፡ ነገር ግን ሶማሊያውያን መሣሪያ የተራቡ አይደሉም፡፡

ሶማሊያን ለመጠበቅ በርካታ አገሮች ማለትም ኢትዮጵያ፣ ብሩንዲ፣ ኡጋንዳና ሌሎች ልጆቻቸውን ገብረዋል፣ ውድ ቤተሰቦቻቸውን፣ ገብረዋል፡፡ አሁን በድንገት ግብፅ መጥታ አለሁላችሁ ብትል አይሠራም፡፡

ሶማሊያ የምትባል አገር መጀመሪያ የራሷን የቤት ሥራ ትሥራ፣ ቤቷን ትጠብቅ፡፡

ሶማሌላንዶች ከሕዝብ ገንዘብ ሰብስበን በጀት መድበን አገር እያስተዳደርን ያለን ሰላማዊ አገር ነን፡፡ ከማንም ለምነን አይደለም አገር የምንመራው፡፡

ሶማሊያን ተመልከት ማን እንደሚደግፋቸው፡፡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ናቸው፡፡

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ኢትዮጵያንም ሶማሌላንድንም ከማን ጋር ስምምነት መፈጸም እንዳለባቸው ሊነግሯቸው አይገባም፡፡

ግብፆች መርዳት ከፈለጉ ለምን ፍልስጤሞችንና ሌሎች ዓረብ አገሮችን አይረዱም ? አሁን ግብፅ መሣሪያና ወታደር በአውሮፕላን እየጫኑ እያመጡ ነው፡፡

ይህ የግብጽ ጣልቃ ገብነት ትልቅ ሥጋት ነው፡፡ ለሶማሌላንድ ጭምር አደጋ ነው፡፡ ይህን ሥጋት ለአፍሪካ ኅብረትና ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ፣ እንዲሁም ለኢጋድ አሳውቀናል፡፡ "


#Somaliland #Egypt

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Somalia #Egypt

የሶማሊያ ናሽናል ኢንተለጀንስ ኤንድ ሴኪዩሪቲ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አብዱላሂ ሞሐመድ ዓሊ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

አብዱላሂ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር መክረዋል።

ውይይቱ የአንካራውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ከሁለቱ ሀገራት አቻ ተቋማት የሚጠበቁ የትብብርና የአጋርነት መስኮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

በውይይቱ የኢትዮጵያና ሶማሊያ የደኅንነትና የጸጥታ ተቋማት ስምምነቱ ተግባራዊ እንዳይሆን እንቅፋት የሚፈጥሩ አካላትን ለመከላከል የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመወጣት የጋራ መግባባት እና ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነግሯል።

በሌላ በኩል ፥ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ኢትዮጽያ ይገኛሉ።

በውይይታቸው ሁለቱ ወገኖች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማሻሻል እና በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ማስጠበቅ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዋን ወደ ኢትዮጵያ በላከችበት በዚህ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ግብፅ ካይሮ ልካለች።

ሚኒስትሯ አሕመድ ፊቂ ከግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባድር አብደላቲ ጋር ከመከሩ በኃላ የጋራ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚሁ መግለጫ ፤ የግብፁ ሚኒስትር " የቀይ ባሕርን ዳርቻ መጠቀም የሚችሉት ከባሕሩ ጋር የሚዋሰኑ አገራት ብቻ መሆን ይገባል ፤ የቀይ ባሕር ዳርቻ አዋሳኝ ላልሆኑ ሀገሮች ክፍት ሊሆን አይችልም " በማለት መናገራቸውን " ኢጂፕት ዴይሊ " ዘግቧል።

ግብፅ ይህን አስተያየት የሰጠችው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ኢትዮጵያ የባህር በርን ልታገኝ የምትችልበትን ስምምነት ፈርመው ፊርማ ሳይደርቅ ነው። በቀጣይ ወር ደግሞ ለዚሁ ጉዳይ ንግግር እንደሚጀመር ይታወቃል።

ከዚህ ባለፈ የግብፁ ሚኒስትር ፤ " የሱማሊያ ፌደራል መንግሥት መላው የሀገሪቱን ግዛቶች ሙሉ እንዲቆጣጠር " በሚችልበት አግባብ ላይ መምክራቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ ግብፅ የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ በሚያደረገው ተልዕኮ " ወታደሮቼን አወጣላሁ " ብላለች።

የሶማሊያው ሚኒስትር በሰጡት አስተያየት " ግንኙነታቸን ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሸጋገር ተስማምተናል " ሲሉ መናገራቸውን ኢጂይፕት ዴይሊ አስነብቧል።

#Ethiopia #Somalia #Egypt

@tikvahethiopia