TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
60K photos
1.52K videos
215 files
4.17K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#NEBE

ወ/ሮ ሜላተወርቅ እና አቶ ታደሰ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት የመጨረሻ እጩዎች ሆነው መለየታቸው ተነገረ።

በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እጩ መልማይ ኮሚቴ ከህዳር 3 እስከ 13 ድረስ 56 ጥቆማዎችን በተለያዩ የጥቆማ መንገዶች መቀበሉን ገልጿል። ከእነዚህ መካከል 52ቱ ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 4 ደግሞ ሴቶች እንደነበሩ አመልክቷል።

በዚህም በተለያዩ ሶስት ዙሮች በተለያዩ መስፈርቶች 5 ግለሰቦች የተለዩ ሲሆን በመጨረሻም መስፈርቱን ያሟሉ ሁለት እጩዎች መለየታቸው ገልጿል።

በዚህም መሰረት ፦

- ወይዘሮ ሜላተወርቅ ሃይሉ

- አቶ ታደሰ ለማ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት የመጨረሻ እጩዎች ሆነው መመረጣቸውን ይፋ አድርጓል።

ሁለቱ እጩዎች የተመረጡት ባላቸው ልምድና ተሞክሮ የፖለቲካ ገለልተኝነት እና ሌሎች መስፈርቶችን አሟልተው በመገኘታቸው ነው ብሏል።

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አንድ ሰብሳቢ የሚያስፈልገው በመሆኑ ሁለቱ እጩዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይቀርባሉ።

በመጨረሻ ፤ ከሁለቱ አንዱ የቦርዱ ሰብሳቢ እንደሚሆኑና ሹመቱም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚፀድቅ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE ወ/ሮ ሜላተወርቅ እና አቶ ታደሰ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት የመጨረሻ እጩዎች ሆነው መለየታቸው ተነገረ። በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እጩ መልማይ ኮሚቴ ከህዳር 3 እስከ 13 ድረስ 56 ጥቆማዎችን በተለያዩ የጥቆማ መንገዶች መቀበሉን ገልጿል። ከእነዚህ መካከል 52ቱ ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 4 ደግሞ ሴቶች እንደነበሩ አመልክቷል። በዚህም በተለያዩ ሶስት ዙሮች በተለያዩ…
#NEBE

ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ወ/ሮ ምዕላተወርቅ ሀይሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል ።

ምክር ቤቱ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ የሾመው በ1 ድምፀ ተዓቅቦ በአበላጫ ድምፅ ነው።

ወ/ሮ ሜላተወርቅ ማናቸው ?

- ወ/ሮ ሜላትወርቅ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኃላፊነት አዲስ አይደሉም። ቦርዱን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።

- ለሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሰርተዋል።

- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት ምርቋ ሜላትወርቅ የሥራ ሕይወታቸው የሚጀምረው በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ነው። በኮሚሽኑ ከጀማሪ የሕግ ኦፊሰርነት እስከ ኦፕሬሽን ኃላፊነት ድረስ ሰርተዋል።

- የኒው ጀኔሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተባባሪ መሥራችም ናቸው።

- የሕግ ማማከር አገልግሎት የሚሰጥ የሕግ ድርጅት አቋቁመው ነበር።

- ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ ከሰላም እና ደኅንነት ጥናቶች ተቋም (አይፒኤስኤስ) የማስተርስ ዲግሪያቸው ተቀብለዋል።

- ከአሜሪካ ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ኬኔዲ ትምህርት ቤት በሕዝብ አስተዳደር ሌላ የማስተርስ ዲግሪ አላቸው።

- በአካዳሚክ፣ በፖሊሲ እና በፐብሊክ ሴክትር ባለሙያነት፣ በሁለትዮሽ እና በዘርፈ ባለብዙወገን ስምምነቶች ተደራዳሪነት፣ በግልግል ዳኝነት አማካሪ በመሆን ሰፊ ልምድ እንዳላቸው በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ።

ቀጣይ ምን ይጠብቃቸዋል ?

* የቀድሞዋ ሰብሳቢ ወ/ሪ ብርቱካን ሚደቅሳ ያላጠናቀቋቸው የቤት ሥራዎች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።

* ቀዳሚው እና ትልቁ ያለፈው ምርጫ ባልተካሄደባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች ምርጫ ማካሄድ ነው።

* ለሁለት ዓመት ጦርነት ሲካሄድበት በቆየው የትግራይ ክልል የፓርላማም የክልል ም/ ቤት ምርጫ አልተካሄደም። ክልሉ ላለፉት 3 ዓመታት በሕዝብ ተ/ም/ቤት ተወካይ የለውም። ቦርዱ በተያዘው 2016 ዓ.ም. በክልሉ ምርጫ ለማካሄድ ዕቅድ መያዙን ለፓርላማ አስታውቆ ነበር። መጪው የቦርዱ ሰብሳቢ ይህን ዕቅድ ያሳኩታል ወይ የሚለው በሂደት የሚታይ ጉዳይ ነው።

- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም በተወሰኑ አካባቢዎች ምርጫ ያልተደረገባቸው ቦታዎች አሉ።

- በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞኖች በፀጥታ ችግር ምርጫ ያልተካሄደባቸው አካባቢዎችም አሉ።

-  የአካባቢ ምርጫም ዋነኛ የቤት ሥራ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከህ/ተ/ም/ቤት እና ከቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው ያሰባሰበው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

" ጠቅላላ ጉባኤው ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ ከተካሄደ  ቦርዱ ለዚህ ጉባኤም ሆነ በጉባኤዎቹ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና አይሰጥም "- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከህወሓት ጉባኤ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለድርጅቱ ደብዳቤ ጽፏል።

ቦርዱ ፥ ነሐሴ 3/2016 ዓ/ም ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ ፖርቲው በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን እና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትም እንደሰጠው አስታውሷል።

ፓርቲው የቦርዱ ደብዳቤ እና የምስክር ወረቀት ከደረሰው ቀን ጀምሮ የሚተዳደረው የኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011ና ይህን አዋጅ ባሻሻለው አዋጅ ቁጥር 1332/2016 እንዲሁም እነዚህን አዋጆች መሰረት ተደርገው በወጡ መመሪያዎችና የቦርዱ ውሳኔዎች መሰረት እንደሆነ አስገንዝቧል።

ቦርዱ ውሳኔ የሰጠባቸውና በደብዳቤ ከገለፃቸው በፓርቲው መተግበር ካለባቸው ተግባራት መካከል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ከማድረጉ ከ21 ቀን በፊት ለቦርዱ ማሳወቅና ፖርቲው በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤ የቦርዱ ታዛቢዎች መገኘት በዋናነት የተገለፁ ግዴታዎች እንደሆኑ አመልክቷል።

ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ፖርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ሊያደርግ መሆኑን ቦርዱ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን እየተዘገበ መሆኑ መመልከቱን ገልጿል።

በዚህም ቦርዱ " ለአንድ ጠቅላላ ጉባኤ መደረግ አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እንዲያውቅ ባልተደረገበት፣ ባልተከታተለበትና ባላረጋገጠበት እንዲሁም የቦርዱ ታዛቢዎች ባልተገኙበት ተጠራ የተባለው ጠቅላላ ጉባኤ ሊካሄድ አይችልም " ሲል አሳውቋል።

ጠቅላላ ጉባኤው ከቦርዱ ፍቃድ ውጭ ከተካሄደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዚህ ጉባኤም ሆነ በጉባኤዎቹ ላይ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ዕውቅና የማይሰጥ መሆኑን ለህወሓት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልጿል።

#TPLF #NEBE

@tikvahethiopia