TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዘንድሮ 164,242 ተማሪዎችን በሬሜዲያል እንቀበላለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ በዘንድሮው ዓመት 164,242 ተማሪዎች በአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም እንደሚታቀፉ አሳውቀዋል። እንዚህ ተማሪዎች በግልና በመንግሥት ተቋማት የሬሜዲያል ትምህርት የሚከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕ/ር ፕርሃኑ ነጋ ምን አሉ ? - በ2014 ዓ/ም…
#MoE

" አትሞክሩ፣ ባትደውሉ ነው የሚሻለው embarrassing ይሆናል "  - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ ፤ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ በአግባቡ እንደሚሰራበት አመልክተዋል።

" በምንም አይነትና መስፈርት አግባብ የሌለውና አድሎ ላይ የተመሰረተ ምደባ አይኖርም " ሲሉ ተናግረዋል።

" እያንዳንዱ ተማሪ በጠየቀው በችሎታው ፣ በሚገባው ቦታ እንዲመደብ እናደርጋል " ያሉት ሚኒስትሩ " አንድና ብቸኛው ከዛ የምንወጣበት አስቸኳይ የሆነና ቅርብ የሆነ ክትትል የሚያስፈልጋቸው የህክምና ጉዳይ ሲኖር ነው " ብለዋል።

" የህክምና ኬዞችንም ስንመለከት ከዶክተር ወረቀት ማምጣት ብቻ ሳይሆን በቦርድ ደረጃ ተነጋግረውበት ያ የህክምና ጉዳይ ሌላ ቦታ ሄዶ ለመማር የማያስችል ነው፤ ለህይወቱ/ቷ አስቸጋሪ ነገር ያመጣል ከተባለ ብቻና ብቻ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፤ " ለአንድ የመንግሥት ባለስልጣን ፣ አንድ የምክር ቤት አባል፣ አንድ ዝም ብሎ ሃብታም ነኝ ብሎ ለሚያስብ ሰው ከሚገባው ውጭ ለልጁ የሚሰጥ ምንም ነገር የለም " ብለዋል።

ከምደባ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ጥያቄዎች እየተጠየቁ መሆኑን ያልደበቁት ፕ/ር ብርሃኑ " ስልኮች ይደወላሉ ነገር ግን የምንሰጠው መልስ አንድ ነው ፤ ' ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው። በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው ከዛ ውጭ ባለ ሌላ መስፈርት ማንንም እድል አንሰጥም ' የሚል ነው " ብለዋል።

" ከዚህ ውጭ የተሰራና የሚሰራ ስራ ካለ አሳዩን፤ ንገሩን እናስተካክላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ለምደባ በሚል ጉዳይ እሳቸውም ጋር የሚመጡ እንዳሉ ገልጸው " ለሁሉም የምለው አትሞክሩ፣ ባትደውሉ ነው የሚሻለው embarrassing ይሆናል ፤ ትክክለኛ ጥያቄ አለን ካላችሁ በትክክለኛው ሂደት እለፉ ከዛ ውጭ ግን የሚመጣ የአቋራጭ መንገድ የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

#MoE #Tikvah_Ethiopia

@tikvahethiopia