#Update #USAID
የአሜሪካ መንግሥት በዓለም አቀፉ የተርድዖ ድርጅቱ USAID አማካኝነት በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ አካቢዎች ለሚገኙ ሰዎች ያቀርበው የነበረውና አቋርጦት የነበረውን የምግብ እርዳታ ከ15 ቀናት በኋላ ዳግም ሊጀምር እንደሆነ አስታውቋል።
አሜሪካ በኢትዮጵያ ስታቀርብ የቆየችው የምግብ እርዳታ ላልተገባ ዓላማ እንደዋለ ከገለጸች በኋላ ማስተካከያ እስከሚደረግ በሚል በሁሉም አካቢዎች የነበረውን የምግብ እርዳታ ባለፈው ዓመት አቋርጣ ነበር።
USAID ትናንት ባወጣው መግለጫ ተቋርጦ የቆየው እርዳታ ከኅዳር 21/2016 ጀምሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ድርጅቱ የምግብ እርዳታው ላልተገባ አላማ እንዳይውል ያደረገውን ማሻሻያ በቀጣዩ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙከራ ይደረግበታል ብሏል።
በዚህ የሙከራ ጊዜ በUSAID ፣ በኢትዮጵያ መንግሥትና በአጋሮች የሚተገበረውን የአዲሱን አሰራር ውጤታማነት በተከታታይ እንደሚቆጣጠርና እንደሚገመግም አስታውቋል።
በኢትዮጵያ አቋርጦት የቆየውን እርዳታ ለመጀመር ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችና ድርድር ሲደረግ መቆየቱን USAID ገልጿል።
አዲሱ አሰራር የእርዳታ ተደራሽነትን ለመቆጣጠርና ለመከታተል ያግዛል የተባለ ሲሆን ይህንኑ አሰራር ለመተግባር የሚያስችል ለውጦች ለማደረግ የኢትዮጵያ መንግሥት መስማማቱን ተገልጿል።
በተጨማሪ መንግሥት ያልተስተጓጎለ የእርዳታ አቅርቦት ተደራሽነት ለመፍቀድ ቁርጠኛ ነው ብሏል።
(መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

#ኢትዮጵያ
በፕሪቶሪያ የተፈረመው #የሰላም_ስምምነት ለዘላቂ ሰላም አስተዋፅኦ ያደርጋል ? ወይስ አያደርግም ? በሚሉት ነጥቦች ክርክር እና ውይይት እንዲደረግ ከ #USAID በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ " ሀበጋር " (የደበበ ኃ/ገብርኤል የህግ ክርክር ፕሮግራም) ባለፈው ቅዳሜ አንድ የውይይት እና ክርክር መድረክ ተዘጋጅቶ ነበር።
በመድረኩ ላይ የተጋበዙ ምሁራን ፣ የሕግና የፖለቲካ ባለሙያዎች ፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች በየፊናቸው ሀሳብ ሲሰጡ ፤ የተለያዩ ጥያቄዎችንም ሲሰነዝሩ ተስተውለዋል።
የታሪክ ምሁር እና የቀድም #የአብን ብሔራዊ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም (ዶ/ር) የፕሪቶሪያው ስምምነት " #ዘላቂ ሰላምን አያመጣም " በማለት፣ እንዲሁም የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አበበ ገ/ህይወት " ስምምነቱ ዘላቂ ሰላም ያመጣል " በማለት ክርክር አድርገዋል።
በአንድ ወገን ያሉት ተሳታፊዎች ስምምነቱ ከነችግሩም ቢሆን ዘላቂ ሰላም ያመጣል፣ በሌላ ወገን ደግሞ ስምምነቱ አሳታፊና ግልፅኝት፣ ተጠያቂነት መርሆችን ካላሟላ ዘላቂ የሆነ ሰላም ሊመያመጣ አይችልም ፣ ቀድሞውንም አሳታፊነት እና ግልጸኝነት የጎደለው ነው በማለት ሀሳባቸውን አቅርበዋል።
በመድረኩ ፦
- የፕሪቶሪያው ስምምነት ዘላቂ ሰላም ያመጣል ? አያመጣም ?
- የተፈናቃዮች ጉዳይ
- የራያ እና ወልቃይት ጉዳይ ተነስተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ክርክርና ውይይት መድረኩ የተሳተፉ አካላትም አነጋግሯል።
ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-19

Telegraph
Tikvah-Ethiopia
የፕሪቶሪያው ስምምነት አፈጻጸም ፦ " የፕሪቶሪያው ስምምነት ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ አይችልም። የማይችልበት ዋናው ምክንያት አሳታፊ ስላልነበረ ነው " - አቶ ታደለ ደርሰህ " የፕሪቶሪያው ስምምነት ህጸጾች ቢኖሩበትም ዘላቂ ሰላም ያመጣል " - አቶ አበበ ገ/ህይወት የፕሪቶሪያው ስምምነት ዘላቂ ሰላም አስተዋፅኦ ያደርጋል ? ወይስ አያደርግም ? በሚሉት ነጥቦች ክርክርና ውይይት እንዲደረግ ከUSAID በተገኘ…
"ጥበብ እንደ መፈወሻ መንገድ/ Art as a path to healing" ኦላይን የስዕል ኤግዚቢሽን
በትግራይ መቐለ ከተማ ከወርሃ የካቲት እስከ ሚያዝያ 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየውና ከ387 ተመዝጋቢዎች የተመረጡ 61 ታዳጊና ወጣት ሰአልያን የተሳተፉበት የቡድን የስእል ውድድር አሸናፊዎችን በመለየት ተጠናቋል።
በውድድሩ ወጣቶቹ በ10 ቡድን በመከፋፈል 10 ስዕሎችን ያቀረቡ ሲሆን፤ ስዕሎቹም ጦርነትን፣ ዘረኝነትን፣ የእርስ በርስ ግጭትና ጠባብነት በማውገዝ ሰላም አንድነት ስር እንዲሰድ የሚሰብኩ ነበሩ።
እነዚህን ስዕሎች ኦላይን በተዘጋጀው ኤግዚቢሽን እንድትመለከቷለቸው እንጋብዛለን።
ወደ ኤግዚቢሽኑ ጎራ ለማለት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ https://redeem.tikvahethiopia.net/paintings
#USAID #RTG #TikvahEthiopia

#USAID
ከስድስት ሳምንት ግምገማ በኋላ አሜሪካ 83 በመቶ የሚሆነውን የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ፕሮግራሞችን መሰረዟን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በX ገጻቸው አስታውቀዋል።
" በቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረግባቸው የነበሩ 5,200 ኮንትራቶች ተቋርጠዋል " ያሉት ሚኒስትሩ " እነዚህ ለብሔራዊ ጥቅማችን ምንም የማያገለግሉ አንዳንዶቹ እንደውም የሚጎዱ ጭምር ናቸው " ሲሉ ነው የገለጹት።
ቀሪ 18 በመቶ የሚሆኑት ፕሮግራሞች (1000 የሚጠጉ) በስቴት ዲፖርትመንቱ በአግባቡ እየተመራ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።
Via @tikvahethmagazine