TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ExitExam

ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚተገበረው አስገዳጅ መመሪያ ምን ይላል ?

(የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን)

" ከቀጣዩ ዓመት 2016 ዓ/ም ጀምሮ እያንዳንዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመውጫ ፈተና ከሚያስቀምጣቸው ተማሪዎች በየትምህርት መስኩ ቢያንስ 25 በመቶዎቹ ማለፍ ይጠበቅባቸዋል።

የግል ተቋማቱ 25 በመቶ ተፈታኞቻቸውን ማሳለፍ ካልቻሉ የትምህርት ፕሮግራሙ #ይሰረዛል

በተጨማሪም የትምህርት ተቋማቱ ለማስተማር የሚመዘግቧቸውን ተማሪዎች የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው። "

NB. ዘንድሮ በተሰጠው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ 72 ሺህ ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ውጤት ያመጡት 12,422 ወይም 17.2 በመቶ ብቻ ናቸው።

Credit : #FBC

@tikvahethiopia
Final Exit Exam Schedule.xls
196.5 KB
#ExitExam

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከአርብ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል።

በኦንላይን ለሦስተኛ ጊዜ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናው፤ በድጋሜ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞችም ይሰጣል፡፡

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኳል። የተማሪዎቹ ውጤት ዛሬ ለተቋማቱ መላኩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል። በዚህም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የዘንድሮው የመውጫ ፈተና ለ57 የመንግሥት እና ለ124 የግል ከፍተኛ የትምህርት…
#ExitExam

የግል የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት መቼ ይፋ ይሆናል ?

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2016 ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ላይ የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤት ግን እስካሁን ይፋ አልተደረገም።

ይህን ተከትሎ የግል ተፈታኞች በርካታ ጥያቄዎችን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድርሰዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልገሎት ዴስክን ጠይቀናል።

" ከግል ተፈታኞች ውጤት ጋር በተያያዘ ያልተጠናቀቁ ነገሮች በመኖራቸው ውጤቱ ይፋ አለመደረጉን " የዴስኩ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ቀሪ መጠናቀቅ ያለባቸው ጉዳዮች እንዳለቁ የግል ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ይደረጋል " ብለዋል።

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ በበኩላቸው ፥ " ከግል ተፈታኞች አጠቃላይ መረጃ እና ክፍያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሲጠናቀቁ ውጤቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚለቀቅ " ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ማኅበሩ 178 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በአባልነት ይዟል፡፡

የግል ተቋማት ተማሪዎች የፈተና ውጤት ለተቋማቱ አለመላኩን ከተቋማት በኩል ባገኘነው መረጃ የተረዳን ሲሆን ከሰሞኑን የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ተልኳል፣ እየተላከ ነው ፣ ውጤት ሊለቀቅ ነው " የሚሉ መረጃዎች ሀሰተኛ እንደሆነ ተገንዝበናል።

በሌላ በኩል ፥ በዚሁ ጉዳይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተማሪዎች ተወካይ አነጋግሯል።

ይኸው ተወካይ በውጤት ጉዳይ ከተማሪዎች ጫና ሲበዛ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር እንደሄደና አንድን ኃላፊ እንደጠየቀ የተሰጠው ምላሽም ፥ " ለመፈተኛ ይከፈል የተባለውን በክፍያ (በተማሪ 500 ብር) አጠቃለው ያልፈጸሙ ተቋማት አሉ " የሚል እንደሆነ ገልጿል።

ክፍያውን ሙሉ በሙሉ የከፈሉ እንዳሉ ሁሉ ያልከፈሉ በመኖራቸው ውጤቱ እንደዘገየ እንደተነገረው አስረድቷል።

ተማሪዎች የፈተናው ውጤት መዘግየቱ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ተረድተናል።

ተማሪዎቹ ፥ " ያልከፈለውን አለማስፈተን ነው እንጂ የሚጠበቀውን ክፍያ ከፍሎ የተፈተነን ተማሪ ውጤት ማዘግየት እና ተማሪውን በጭንቀት ማሰቃየት ፍጹም ተገቢ አይደለም " ብለዋል።

ውጤታቸው በፍጥነት እንዲላክና እንዲገለጽ ሌላው ጉዳይ እነሱን የሚመለከት ባለመሆኑ ይህን ያህል ውጤት በመጠበቅ ለጨነቁ እንደማይገባቸው አስገንዝበዋል።

ዘንድሮ 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ማስፈተናቸው ይታወቃል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ExitExam

🔴" የተፈተነው ፈተና ኮንተንቱ(ይዘቱ) ህክምና ያልሆነ ነው በትምህርት ሊገኝ የማይችል ነው " - ተፈታኝ ተማሪዎች

🔵" የተማሩት ነው የሚወጣው የተፈተኑትም ይህን መሰረት አድርጎ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

ሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና (Exit Exam)  ከጥር 26-30/2017 ዓም በ 87 የፈተና ማዕከላት መሰጠቱ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ " ፈተናው ለፈተና ዝግጅት ከሚያግዘው ' ብሉፕሪንት ' ውጪ ነው ይዘቱም ከተማርነው ትምህርት ጋር የማይገናኝ ነው " የሚሉ ቅሬታዎችን ከተፈታኞች ተቀብሏል።

ከተለያየ የትምህርት ክፍል ፈተናውን የወሰዱ ተፈታኞች ፈተናውን ከብሉ ፕሪንት ውጪ የመጣ መሆኑን በመግለጽ ትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ ይስጠን ብለዋል።

ቅሬታውን ካቀረቡ ተፈኞች መካከል የሆኑ የህክምና ተማሪዎች " የመጣው ፈተና በጣም ከስታንዳርዱ የወጣ የህክምና ተማሪዎችን የማይመጥን ነበር " ብለዋል።

አክለውም " የተፈተነው ፈተና ኮንተንቱ (ይዘቱ) ህክምና ያልሆነ ነው በትምህርትም ሊገኝ የማይችል ነው " ያሉ ሲሆን " የሚመለከተውን አካል ለማናገር ብንሞክርም ከውጤት በፊት ንግግር እንደማይኖር ተነግሮናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከእኛ በፊት አምና የተመረቁ ተማሪዎች የተፈተኑትን ፈተና ተመልክተናል ሰርተንም ስለገባን እናውቀዋለን ትክክለኛ ፈተና ነበር የተፈተኑት ይዘቶቹም ጥሩ ነበሩ  ዘንድሮ ምን እንደተፈጠረ አናውቅም የወጣው ፈተና ከህክምና ጋር የማይገናኝ ጥያቄ ይበዛው ነበር " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪ ከጤና ተማሪዎች ውጭ የፊዚክስ ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ከብሉ ፕሪንት ውጪ ተፈትነናል የሚለው ቅሬታ " ውሸት ነው " ብለዋል።

" ከስልጠና ፕሮግራም ብቃት (Competency) ውጪ የሚዘጋጅ አንድም ጥያቄ የለም " ያሉት ስራ አስፈጻሚው የተባለው ቅሬታ " ውሸት ነው ሪፖርትም አልቀረበልንም እንደዚህ ብሎ የጠየቀንም የለም ከኮምፒተንሲ ውጭ የሚወጣ ፈተና የለም " ነው ያሉት።

አክለውም "ፈተናው ከብቃት ጋር የተገናኘ ከሁለተኛ ዓመት እስከ መጨረሻ ዓመት የተማሩት ነው የሚወጣው የተፈተኑትም ይህን መሰረት አድርጎ ነው " ብለዋል።

" ጥያቄው ከዚህ ውጪ ወጣ የሚል ቅሬታ ከሱፐር ቫይዘር፣ ፈታኝ ፣ተማሪ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች የቀረበልን አንድም ሪፖርት የለም መረጃው የለንም ሪፖርቱም አልቀረበልንም " ሲሉ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ሃገር አቀፉ የመውጫ ፈተና ውጤት ነገ አልያም ከነገ በስቲያ ይፋ እንደሚደረግ ከትምህርት ሚኒስቴር መስማቱን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡

ህብረቱ ፥ ሚኒስቴሩ ከComprehensive Nursing የመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ የቀረበ ቅሬታን እያጣራ እንደሚገኝ አስረድቷል።

ረቡዕ ወይም ሐሙስ አጠቃላይ የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ እንደገለጸለት ህብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia