TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል ! ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች። ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ። ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ…
" ኢፍትሃዊ እና ግብዝነት የተሞላበት ነው " - ኡጋንዳ

የዓለም ባንክ ለኡጋንዳ አዲስ ብድር አልሰጥም ብሏል።

ይህን ያለው ለምን የፀረ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ህግን አውጥተሽ ተግባራዊ አደረግሽ በሚል ነው።

የዓለም ባንክ ኡጋንዳ ያወጣችው ሕግ " መሰረታዊ ከሆኑ እሴቶቼ ጋር ይቃረናል " ብሏል።

ተቋሙ ለሁሉም ኡጋንዳውያን ያለምንም ልዩነት " ከድህነት እንዲወጡ፣ መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እና ሕይወታቸውን እንዲያሻሽሉ ለመርዳት " ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

በኡጋንዳ ከዚህ ቀደምም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነቶች ሕገ ወጥ የነበሩ ሲሆን ግንቦት ላይ በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሰረት ደግሞ የዕድሜ ልክ እስራትን ጨምሮ #ሞት ያስቀጣል።

በኡጋንዳ ተግባራዊ በተደረገው የፀረ ተመሳሳይ ጾታ ሕግ ፤ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ ሰው ጋር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የፈጸመና የኤችአይቪ ቫይረስ በደሙ ከሚገኝበት ሰው ጋር ግኝኑነት የፈጸመ ሰው እስከወዲያኛው ይሸኛል / የሞት ቅጣት ይፈረድበታል።

ዓለም ባንክ ይህ ሕግ ተግባራዊ ከተደረገ በኃላ አንድ ቡድን ወደ ኡጋንዳ አሰማርቶ የነበረ ሲሆን ሕጉ " በመሰረታዊነት የዓለም ባንክ ቡድን እሴቶችን ይቃረናል " ብሏል።

ራዕያችን " ዘር፣ ጾታ ወይንም ተመሳሳይ አፍቃሪነትን ሳይለይ ሁሉንም ያካተተ ነው " ሲል ገልጿል።

በሕጉ ውስጥ የተካተቱ አዳዲስ እርምጃዎች እስኪገመገሙ ድረስ " ለኡጋንዳ አዲስ ብድር እንዲጸድቅ ለሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አይቀርብም " የሚል ውሳኔ አሳልፏል።

ኡጋንዳ ምን አለች ?

የዓለም ባንክ የወሰደው እርምጃ ኢፍትሃዊ እና ግብዝነት ነው ብላለች።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኡጋንዳ አምባሳደር አምባሳደር አዶኒያ አየባሬ ፥ " የገንዘብ ተቋሙን እርምጃ በጣም የከፋ ነው። የዓለም ባንክ የአሰራር ዘዴ እና የቦርዱን ውሳኔ እንደገና የማጤን ጊዜው አሁን ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲኤታ ኦኬሎ በበኩላቸው ፤ እርምጃው ከሌሎች አገራት ጋር ሲወዳደር ወጥነት የለውም ብለዋል።

" የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የማይታገሱ በርካታ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት አሉ። ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችንም የሚቀጡት በመስቀልና በመግደል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" በአሜሪካ ውስጥ በርካታ ግዛቶች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚቃወሙ ወይንም የሚገድቡ ሕጎችን አውጥተዋል። ታዲያ ለምን ኡጋንዳ ላይ አነጣጠራችሁ ? "ሲሉም ጠይቀዋል።

ከዓለም ባንክ በተጨማሪ አሜሪካ በጸረ ተመሳሳይ አፍቃሪ ሕግ ምክንያት በኡጋንዳ ላይ ማዕቀብ ጥላለች። (ሮይተርስ/ቢቢሲ)

ኡጋንዳ ፤ ሕጉን ከማፅደቋ በፊት ከምዕራባውያን ሀገራት እና ተቋማት ብዙ ማስጠንቀቂያዎች ቢደርሳትም ሕጉ ለሀገሬ አስፈላጊ ነው በማለቷ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፈርመውት አፅድቀውታል፤ ተግባራዊም ሆኗል።

ከዚህ ቀደም የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፤ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ #በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ  " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ሲሉ ነበር የገለፁት።

ስለ ኡጋንዳ አዲሱ ሕግ ለማወቅ ፡ https://yangx.top/tikvahethiopia/78787

@tikvahethiopia