TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
በታንዛኒያው የ " ሰላም ንግግር " ላይ እነማን እየተሳተፉ ነው ? በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለው) መካከል ትላንት የሰላም ንግግር በታንዛኒያ ከፊል ራስ ገዟ ዛንዚባር ተጀምሯል። ኢጋድ ይሄ የሰላም ንግግር ወደ ፖለቲካ ስምምነት እንደሚያመራ ተስፋ እንዳለው በቃል አቀባዩ በኩል ገልጿል። ለመሆኑ የታንዛኒያ የሰላም ንግግር ተሳታፊዎች / ተደራዳሪዎቹ እነማን…
#Update

በታንዛኒያ እየተካሄደ የሚገኘው የመንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራው) የሰላም ንግግር ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።

ቢቢሲ ለድርድሩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች አገኘሁት ባለው መረጃ ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ልዩነታቸውን በሰላም ለመቋጨት በሚያደርጉት ውይይት #ኬንያ እና #ኖርዌይ በዋነኛ የአሸማጋይነት ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ ገልጿል።

እየተካሄደ ባለው ውይይት አጀንዳዎችን የመቅረጽ ውይይቶች እየተካሄዱ እንደሆነም ተነግሯል።

ማክሰኞ የጀመረው ውይይት በሳምንቱ መጨረሻ ይጠናቀቃል የሚል ዕቅድ ተይዞ እንደነበር የተሰማ ቢሆንም ሊራዘም እንደሚችል ቢቢሲ ከስፍራው ዘግቧል።

ለውይይቱ መራዘም በዋነኝነት በኦሮሚያ ክልል ያሉ ጥያቄዎች በጣም ውስብስብ እና በቀላሉ እልባት ሊደረስባቸው ስለማይችሉም እንደሆነ ተመላክቷል።

እስካሁን ሁለቱ ወገኖች ውይይቱ እንደሚካሄድ ከመናገር ውጪ ዝርዝር መረጃዎችን ያልሰጡ ሲሆን ውይይቱ እየተካሄደበት ያለችው ዛንዚባር አስተዳደሮች ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።

የዛንዚባር ባለሥልጣናት ውይይቱ እየተካሄደ እንደሆነ ቢያረጋግጡም የድርድሩ አካል እንዳልሆኑ እና ከአዘጋጅነት የዘለለ ሚና እንደሌላቸው አመልክተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከትግራይ ክልል ወደ አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል የሚደረገው የየብስ ትራንስፖርት ዛሬ በይፋ መጀመሩ ተገልጿል።

ይህ የተገለፀው ፦
👉 የአማራ ክልል የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን
👉 የአፋር ክልል የትራንስፖርት እና መንገድ ቢቶ
👉 የፌዴራል የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

የአማራ ክልል የትራንፖርት እና የሎጀስቲክስ ባለስልጣን ምን አለ ?

- በአማራ ክልል አቅጣጫ ዛሬ 4ኛ ቀኑን የያዘ የሕዝብ ትራንስፓርት የሙከራ ጉዞ  ወደ አዲስ አበባ ተደርጓል።

- ሶስት (3) የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በአማራ ክልል በኩል ጉዞ አድርገዋል።

- ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ ይፋዊ ጉዞ ጀምሯል።

- የአማራ ክልል መንግሥት ለማንኛውም የትራንፓርት እና ሰላማዊ እንቅስቃሴ ድጋፍ ያደርጋል።

- የክልሉ ሕዝብ ለሰላማዊ እንቅስቃሴ በጎ አመለካከት ያለው በመኾኑ ጉዞው ላይ ችግር አያጋጥምም።

የአፋር ክልል የትራንፖርት እና መንገድ ቢሮ ምን አለ ?

- በአፋር ክልል በኩል በመጀመሪያው ቀን ብቻ ሁለት የሙከራ ጉዞዎች የተደረጉ ሲሆን ትራንስፖርት ከተጀመረ ዛሬ 6 ቀናት ተቆጥረዋል።

-  ክልሉ ማንኛውም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲኾን ያግዛል።  መንግሥት ብቻ ሳይኾን ሕዝቡም ሰላማዊ አንቅስቃሴውን ይደግፋል።

- ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ ይፋዊ የየብስ ትራንፖርት ጀምሯል።

የትራንፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ምን አለ ?

- ተቋርጦ የነበረው የየብስ ትራንፖርትን ለማስጀመር ሁለት የጥናት ቡድን በአማራ ክልል በኩል እና በአፋር ክልል በኩል በመላክ ጥናት ተደርጓል።

- በሁለቱም ክልሎች በኩል 19 የሙከራ ጉዞዎች ከአዲሰ አበባ ትግራይ ክልል እና ከትግራይ ክልል አዲስ አበባ ተደርጓል።

- ከዛሬ ጀምሮ  ይፋዊ የየብስ ትራንስፖርት ተጀምሯል።

የትግራይ ክልል የትራንፖርት ቢሮ ኀላፊዎች በአየር ትራንፖርት #መዘግየት ምክንያት በአዲስ አበባ በተሰጠው የጋራ መግለጫ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል።

#አሚኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና  ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን  አብራርተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 ዓ.ም የሚካሄደው ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸው የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@tikvahethiopia
አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደሉ።

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ዛሬ በሰሜን ሸዋ " መሀል ሜዳ " ላይ በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።

የአቶ ግርማን ግድያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል። " ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ የግድያውን ሁኔታ በተመለከተ #ዝርዝር_መረጃ ባይሰጡም " ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው " ሲሉ ገልጸውታል።

" ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው። " ሲሉ አክለዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደሉ። የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ዛሬ በሰሜን ሸዋ " መሀል ሜዳ " ላይ በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። የአቶ ግርማን ግድያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል። " ብለዋል። ዶ/ር ዐቢይ የግድያውን ሁኔታ በተመለከተ #ዝርዝር_መረጃ…
" አቶ ግርማ የሺጥላን ጨምሮ አምስት ሰዎች ተገድለዋል " - የአማራ ክልል መንግስት

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባወጣው የሀዘን መግለጫ በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመው ግድያ ዛሬ ከሰዓት በኋላ፤ የመንግሥትና የድርጅት ሥራዎችን ሠርተው ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን ሲመለሱ በመንዝ ጓሳ ላይ መሆኑንና ግድያው የተፈፀመው በታጠቁ ኢ-መደበኛ ኃይሎች እንደሆነ ገልጿል።

ከእሳቸው በተጨማሪ በግል ጥበቃዎቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ላይ ጥቃት መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን እስካሁን #የአምስት_ሰዎች ሕይወት ስለማለፉ መረጃው እንደደረሰው ክልሉ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

ክልሉ በመግለጫው፥ "ይህንን የሽብር ሥራ እየሠሩ ያሉ እንዲህ አይነት ኃይሎች ላይ የክልሉ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል፡፡ የጥቃቱን አድራሾችም ለሕግ ያቀርባል " ብሏል።

አክሎም፥ "የጥፋት ኃይሎች ከዚህ በላይ ዓላማ ያላቸው እና ክልሉን የማፍረስ ተልዕኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በኋላ የክልሉ መንግሥት እንደማይታገስ እና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ እናረጋግጣለን " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ቴክኖ_ሞባይል

እጅግ ዘመናዊ፣ ለአያያዝ እና አጠቃቀም ምቹ የሆነው አዲሱ ስፓርክ 10 ሲሪየስ ከቴክኖ ሞባይል ቀርቦሎታል !

ማራኪ ዲዛይን ያለው ባለ 6.8 ኢንች ስክሪን ልዮ ስታሪ ግላስ የተባለ ብርጭቆ ፓናል የተላበሰ ሲሆን ይህም ከፍተኛ ጭረት እንዲቋቋም እና ለእይታ ማራኪ  ያደርገዋል።

ሁለት ዋና ካሜራዎችን ከተጨማሪ የፍላሽ መብራት ጋር የያዘ ሲሆን ከፊት ለፊት ቁልጭ አርጎ ፎቶ ማንሳት የሚያስችል ባለ 32 ሜጋ ፒክስል ሰልፊ ካሜራ ይዞ ቀርቧል።

በየትኛውም የስልክ መሸጫ መደብሮቻችን ያገኙታል።
ለበለጠ መረጃ: Facebook, Instagram, Tiktok

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark10Series #TecnoMobile #Ethiopia #Spark10pro
#ExodusPhysiotherapy

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ለትክሻ፣ለወገብ ህመም;ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር፣ ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል፣ ለስፖርታዊ ጉዳቶች ፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች ፣ በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ !

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ     #ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት
አድራሻችን ፦ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን።

ስልክ ፦ 0979099909/ 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://yangx.top/ExodPhysioClinic
" የግጭቱ ምክንያት ነዋሪዎችን ለማወያየት ወደ ገጠር በመጓዝ ላይ በነበረ አንድ አመራር ላይ የተፈጸመ ግድያ ነው " - አቶ ታደሰ ካይ (የደቡብ ኦሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ)

በደቡብ ክልል ፤ ደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት የወረዳው አመራርን ጨምሮ 11 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 6 መቁሰላቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

የግድያ ጥቃቱ የደረሰው ከትናንት በስቲያ በመስክ ጉዞ ላይ የነበረ አንድ የወረዳ አመራር " ማንነታቸው ባልታወቁ " ሰዎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ተከትሎ ነው።

ግድያውን ተከትሎ በወረዳው በሚገኙ ቦዲ እና ደሚ በተባሉ የጎሳ አባላቶች መካከል ግጭት መቀስቀሱን የአይን እማኞች ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

በጎሳ አባላቱ መካከል የተነሳው ግጭት የሳላማጎ ወረዳ ማዕከል ወደ ሆነችው የሐና ከተማ መዛመቱና ፤ በከተማዋ ሕይወታቸው ካለፉት መካከል ሕጻናት እና ነፍሰ_ጡሮች እንደሚገኙበት የአይን እማኞች ተናግረዋል።

የዞኑ ባለስልጣናት በሳላማጎ ወረዳ ግጭት መከሰቱን አረጋግጠው ፤ በጥቃቱ 11 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 6 ደግሞ መቁሰላቸውን አሳውቀዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደሰ ካይ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል፤ ነዋሪዎችን ለማወያየት ወደ ገጠር በመጓዝ ላይ በነበረ አንድ አመራር ላይ የተፈጸመው ግድያ ለግጭቱ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።

የአመራሩን ሞት ተከትሎ " የእኛ ሰው ተገደለ " በሚል ሁለቱ ጎሳዎች ወደ ግጭት በመግባታቸው በተጨማሪ ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ሊደርስ መቻሉን ነው አቶ ታደሰ አመልክተዋል።

በአሁኑ ጊዜ ወረዳው እየተረጋጋ መምጣቱንና ጥቃት አድራሾችን ለሕግ አሳልፎ ለመስጠት ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ምክክር መደረጉን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
" ማኅበረሰቡ ፈፃሚዎችን ሊያወግዝና ተገቢው ማጣራት ተደርጎ ፍትኅ እንዲሰፍን የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል " - አቶ ክርስቲያን ታደለ

በአማራ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመው ግድያን " በማንም ለምንም ዓላማ ይፈፀም ተቀባይነት የሌለው ወንጀል " መሆኑን የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ገለፁ።

አቶ ክርስቲያን ፤ " በወንድማችን ግርማ የሽጥላ ላይ በተፈፀመው ግድያ በእጅጉ አዝኛለሁ " ብለዋል።

" ድርጊቱ በማንም ለምንም ዓላማ ይፈፀም ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ወንጀል ነው። " ያሉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ " ማኅበረሰቡ ፈፃሚዎችን ሊያወግዝና ተገቢው ማጣራት ተደርጎ ፍትኅ እንዲሰፍን የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል " ሲሉ አሳስበዋል።

አቶ ክርስቲያን፥ በሁሉም በኩል የሚደረጉ ፍረጃዎችና የሴራ ትንተናዎች ወንጀሉን በአግባቡ በመመርመር  ገዳዮችን ለፍትህ ለማቅረብ የሚደረገውን ጥረት እንዳይጎትቱ ብርቱ ጥንቃቄዎች ሊደረጉ ይገባል ብለዋል።

" የአማራ ሕዝብ ሰላሙንና አንድነቱን እንዲጠብቅ አሳስባለሁ " ያሉት አቶ ክርስቲያን ታደለ ፤ " ለመላው ለቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ " ሲሉ ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#ELPJC

" ... የሀገራችንን የፖለቲካ ችግሮችን የአመለካከት ልዩነቶችንና ስብራቶችን እርስ በርስ በመገዳደል ለውጥ ማምጣትና ማስተካከል አይቻልም " - ምክር ቤቱ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መገለጫ በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመውን ግድያ እንደሚያወግዝ እና በደረሰባቸውም አሰቃቂ ሞት በእጅጉ ማዘኑን ገልጿል።

ምክር ቤቱ " የሀገራችንን የፖለቲካ ችግሮችን፣ የአመለካከት ልዩነቶችንና ስብራቶችን እርስ በርስ በመገዳደል ለውጥ ማምጣትና ማስተካከል አይቻልም " ብሏል።

" ሥር የሰደዱ ግጭቶች እንኳን ቢሆኑ በአመጽ ሳይሆን በመነጋገር፣ በመወያየት፣ በመግባባትና በመደማመጥ፣ እንዲሁም በመተባበር ብቻ መፈታት ይኖርባቸዋል " ሲልም አስገንዝቧል።

በአቶ ግርማ ላይ የተፈፀመውን ግድያ በጽኑ እንደሚያወግዝ የገለፀው ምክር ቤቱ መንግስት ይህን አስነዋሪ ተግባር የፈጸሙ አካላትን በአፋጣኝ በቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢውን የህግ ተጠያቂነት እንዲያረጋግጥ ጠይቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia