TIKVAH-ETHIOPIA
#IOM እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መረጀ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቱርክ ዜጎችን ጨምሮ ከ3,500 በላይ ሰዎች በሱዳን ያለውን ከባድ ጦርነት ሸሽተው በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ከሚያዚያ 21 እስከ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ3500 በላይ የሆኑ የ35 ሀገራት ዜጋ ስደተኞች ተመዝግበዋል። ከተመዘገቡት አጠቃላይ ስደተኞች መካከል ከ40 በመቶ በላይ የቱርክ ዜጎች ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን 14…
#ኢትዮጵያ #ሱዳን #መተማ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ፤ በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በመሸሽ በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ድንበር አቋርጠው ወደ #ኢትዮጵያ እየገቡ እንደሆነ አሳውቋል።
ይህ ቁጥር አሁንም እየጨመረ ነው ብሏል።
እስካሁን በሱዳን ጦርነት ምክንያት #በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ዜጎች ቁጥርም በአጠቃላይ ከ12 ሺ በላይ መድረሱ ተመላክቷል።
ሱዳን እና ኢትዮጵያ በሚዋሰኑበት ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ በኩል ሕይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ካሉት መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የሌሎች አገራት ዜጎች እንደሚገኙበት የመንግሥታቱ ድርጅት መሥሪያ ቤት መረጃን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopia