TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.9K photos
1.52K videos
215 files
4.17K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
ውጤቶች : ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስገብቶ ባስፈተነው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተመዘገቡ ውጤቶች በጥቂቱ ከላይ ተያይዘዋል። More : @tikvahuniversity #TikvahFamily @tikvahethiopia
ውጤቶች : ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት / ዩኒቨርሲቲ አስገብቶ ባስፈተነው የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና የተመዘገቡ ውጤቶች በጥቂቱ ከላይ ተያይዘዋል።

እስካሁን ድረስ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በኩል በታየው የጥቂት ተማሪዎች ውጤት ብቻ ዝቅተኛው ውጤት 120 ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 666 ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር በአጠቃላይ ከውጤት ጋር በተያያዘ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

More : @tikvahuniversity

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ውጤቶች : ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት / ዩኒቨርሲቲ አስገብቶ ባስፈተነው የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና የተመዘገቡ ውጤቶች በጥቂቱ ከላይ ተያይዘዋል። እስካሁን ድረስ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በኩል በታየው የጥቂት ተማሪዎች ውጤት ብቻ ዝቅተኛው ውጤት 120 ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 666 ነው። የትምህርት ሚኒስቴር በአጠቃላይ ከውጤት…
#Update

" ብዙም አይርቅም "

የትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤት ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል።

የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ትላንት ለሊት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

ከውጤቱ ጋር በተያያዘ አጠቃላይ መግለጫ ዛሬ ከሰዓት 8:00 በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) እንደሚሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

" የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ውጤታቸው ከ50 በመቶ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከ28 ሺህ እንደማይበልጥ" በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እየተዘገበ ይገኛል ፤ ይህን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች አሐዝ ከ28 ሺህ " #ብዙም_እንደማይርቅ " ቲክቫህ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።

እስካሁን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ያልተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia