TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " በሁለት ሶስት ቀን ውስጥ ሽረ ላይ ስብሰባ ይደረጋል ፤ በአንዳንድ ቴክኒካል ጉዳዮች ዘሪያ የሁለቱም ጦር ተወካዮች ተገናኝተው ይወያያሉ " ትላንት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተካሄደውን የሰላም ድርድር / ስምምነቱን የመሩት የቀድሞው የናይጄሪያው ፕሬዜዳንት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የትግራይ መዲና ፤ #መቐለ መግባታቸው…
#Update #ሽረ

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፤ የትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚሠራው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ሽረ ላይ እየመከረ መሆኑን አሳውቋል።

" በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት ሕወሓት ትጥቅ የሚፈታበትን ዝርዝር ዕቅድ የሚያዘጋጀው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ከትናንት ሕዳር 21 ቀን ጀምሮ ሽረ ላይ ሥራውን ጀምሯል " ያለው የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፤ " ከፌዴራል መንግሥትና ከትግራይ ታጣቂዎች የተውጣጣው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ሥራውን ያጠናቅቃል ተብሎ ይታመናል " ብሏል።

ኮሚቴው የሚያወጣው ዝርዝር ዕቅድ ትጥቅ የማስፈታት፣ ካምፕ የማስገባትና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚመልስ እንደሚሆንም ተመላክቷል።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽ ፤ ዝርዝር ዕቅዱን የማውጣት ተግባሩ፣ በቴክኒክ ጉዳዮች ምክንያት መዘግየቱን ገልጿል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና  በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። መውጫ ፈተና በሁሉም  መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መርሀግብሮች የሚመረቁ ተማሪዎችን እንደሚመለከትና ፈተናውን   በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ገልጸዋል። የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከመደበኛ  ተማሪዎች ባሻገር  #የማታና #የርቀት ተመራቂ ተማሪዎችን…
#ExitExam

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ  ፦

" የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የቀን ፣ የማታ እና የርቀት መርሀ ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ  በመንግስትና ግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና #በኦንላይን ለመስጠት ታቅዷል ።

በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው ተገቢውን ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል ።  "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በናይሮቢው የሰላም ስምምነት ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት የትግራይ ኃይሎች አዛዥ ጄነራል ታደሰ ወረደ በናይሮቢው ስምምነት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ባለፉት ቀናት ለኃይሎቻቸው ኦረንቴሽን ሲሰጥ እንደነበር እና ይኸው ኦረንቴሽን በቀጣይ ሁለት ቀን እንቀሚያልቅ ገልፀዋል። ይህን የገለፁት በክልሉ ለሚገኙት የመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ነው። ጄኔራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ? " በናይሮቢው…
#Update #Peace

በሰላም ስምምነቱ መሰረት የትግራይ ታጣቂዎች በስራቸው ከነበሩ የውግያ ግምባሮች ለቀው መውጣት እንደጀመሩ ተገልጿል።

ታጣቂዎቹ ከደቡብ ፣  ማይ ቅነጣል፣ ዛላምበሳ፣ ነበለት ፣ ጨርጨር ፣ ኩኩፍቶ ፣ ሕጉምብርዳ ፣ በሪተኽላይ እና አበርገለ ለቆ ግንባሮች ነው መውጣት እንደጀመሩ ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን የተሰማው።

ከጥቂት ቀናት በፊት ጄነራል ታደሰ ወረደ (የትግራይ ኃይሎች አዛዥ) በሰጡት መግለጫ በናይሮቢው ስምምነት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለኃይሎቻቸው ኦረንቴሽን ሲሰጥ እንደነበር እና ይኸው ኦረንቴሽን እንዳለቀ ኃይላቸው ካለበት ቦታ Disengage አድርጎ / ተላቆ የውጊያ ግንባሮች #የማፍረስ እና ሰራዊቱ ወደ ተቀመጠለት ቦታ እንደሚጓጓዝ መግለፃቸው አይዘነጋም።

ጄነራል ታደሰ ፤ " የሎጅስቲክስ አቅማችን ወይም የማጓጓዝ አቅማችን እስከፈቀደ ድረስ በአንድ ጊዜም ልናነሳው እንችላለን ምናልባት የተወሰኑ ቀናት ሊወስድ ይችላል " ማለታቸውም የሚወስ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኦሮሚያ #ትኩረት በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች አሁንም በቀጠለው የፀጥታ ችግር በርካቶች ህይወታቸው እያለፈ ፣ አካላቸው እየጎደለ፣ ንብረታቸው እየወደመ እንደሚገኝ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል። ባለፉት ዓመት ህዝቡ በሰላም እጦት ብዙ ቢሰቃይም መፍትሄ ሳይገኝ አሁንም እየተባባሰ በመቀጠሉ ንፁሃን ክፉኛ እየተጎዱ እና ስቃያቸውም እየተባባሰ እንደሚገኝ ነው ቤተሰቦቻችን የገለፁት። ከጥቂት ቀን በፊት…
" የንጹሓን ደም በከንቱ መፍሰስን ማስቆም የሚችለው ሕሊና ያለው ሕዝብና ፈጣሪ ብቻ ነው " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ በላከልን መግለጫ ፤ ከሰሞኑ በምሥራቅ ወለጋ በጊዳአያና፣ ኪረሙና ሐሮ ቀበሌዎች በየቀኑ በሚባል ደረጃ የሰው ህይወት እያለፈ እንደሆነ አሳውቋል።

" የየቀኑ የሚፈሰው ደም የኢትዮጵያ ምድር ይህን ያህል ደም ተጠምቷልን ? ያሰኛል " ያለው ፓርቲው " እሥረኞች ተገድለዋል፣ ንጹሓን በእምነት ቦታዎች ጭምር ተጨፍጭፈዋል፣ ብዙ ሺዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል " ብሏል።

በመሆኑም፦

- መንግስት ለአካባቢው ልዩ ትኩርት በማድረግና በቂ የመከላከያ ኃይል በማሰማራት የንጹሓንን እልቂት በአፋጣኝ እንዲያስቆምና የአካባቢው ዘላቂ ሰላም እስከሚረጋገጥ ድረስ በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደር በአጽንዖት እናሳስቧል።

- ግጭቱ ከጊዜ ወደጊዜ መልኩን እየቀየረ የእርስ በእርስ ወደመሆን ከመሄዱ በፊት ያገባኛል የሚሉ አካላት በሙሉ ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

- እልቂቱን በዘላቂነት ለመፍታት ከአድሏዊነት በጸዳ መልኩ የአካባቢውን ማኅበረሰብ በማወያየትና ችግሩን በጥልቀት በመረዳት የመፍትሔ ሀሳብ እንዲፈለግም ጠይቋል።

ፓርቲው፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ የንጹሓንን መታረድ ዝም ብሎ ማየት ኃጢያትም ወንጀልም ነው ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ኹሉ የእነዚህን በየቀኑ የሚታረዱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹን ለመታደግ በሕሊናም በፈጣሪም ፊት ከተጠያቂነት ለመዳን በመወያየትና መፍትሔ እንዲፈልጉ፤ በኦሮምያ ክልላዊ መንግስትና በፌዴራል መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርጉ፤ ድርጊቱንም እንዲቃወሙ ጥሪ አቅርቧል።

" የንጹሓን ደም በከንቱ መፍሰስን ማስቆም የሚችለው ሕሊና ያለው ሕዝብና ፈጣሪ ብቻ ነው " ያለው እናት ፓርቲ "ይህን ተረድተን ኹላችንም የምንችለውን እንድናደርግ" ብሏል።

(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Mekelle

ትላንት 13 የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ኮንቮይናና 3 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የጭነት ተሽከርካሪዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ጭነው ትግራይ ክልል መቐለ ገብተዋል።

ተሽከርካሪዎቹ የዳይለሲስ እቃ እንዲሁም በኢትዮጵያ ስኳር ህሙማን ማህበር የተበረከተ ኢንሱሊንን ጨምሮ አጠቃላይ 200 ቶን የሚጠጋ ሰብዓዊ ድጋፍ ፣ምግብ እና መድሃኒት የጫኑ እንደሆኑ ከICRC ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
" ከትግራይ ህዝብ ጋር ተከባብረን የምንኖርበት እንጂ ለጦርነትና እልቂት የምንፈላለግበት ጉዳይ ሊኖር አይገባም " - ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት

የአማራ ክልል መንግስት በመደበው በጀት በጦርነት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የወደሙ መሰረታዊ አገልግሎት መስጫ ፕሮጀክቶች መልሶ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ዛሬ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ እየተካሄደ እንደሚገኝ የብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን) ዘግቧል።

በማስጀመሪያ ስነስርአቱ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን ዶክተር ይልቃል ፤ በጦርነቱ የደረሰውን ውድመት ቀስ በቀስ መልሶ ለመገንባት የክልሉ መንግስት በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።

" አሁን ላይ የተደረሰው የሰላም ስምምነት እንዲሳካ አበክረን እንሰራለን " ሲሉም ተናግረዋል።

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፤ " ከትግራይ ህዝብ ጋር ተከባብረን የምንኖርበት እንጂ ለጦርነትና እልቂት የምንፈላለግበት ጉዳይ ሊኖር አይገባም " ሲሉም ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከትግራይ ህዝብ ጋር ተከባብረን የምንኖርበት እንጂ ለጦርነትና እልቂት የምንፈላለግበት ጉዳይ ሊኖር አይገባም " - ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት የአማራ ክልል መንግስት በመደበው በጀት በጦርነት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የወደሙ መሰረታዊ አገልግሎት መስጫ ፕሮጀክቶች መልሶ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ዛሬ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ እየተካሄደ እንደሚገኝ የብሄራዊ ቴሌቪዥን…
#Amhara

ዛሬ በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ እየተካሄደ ባለ የመልሶ ግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስዩም መኮንን የተናገሩት ፦

- በጦርነቱ ከደረሰው ሰብአዊ ጉዳት ባሻገር 👉 291 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ቁሳዊ #ውድመት መድረሱ በጥናት መረጋገጡን ተናግረዋል።

- በክልሉ የደረሰውን ውድመት መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ፅ/ ቤት አቋቁሞ እየሰራ መሆኑ ገልፀዋል።

- ዛሬ የመልሶ ግንባታ የማስጀመሪያ መርሀግብር እየተካሄደ በሚገኝበት ራያ ቆቦ ወረዳ ብቻ ወደ 👉 9 ቢሊዮን ብር የሚገመት #ውድመት መድረሱም ጠቁመዋል።

- በዚህ አመት ብቻ 12 ቢሊዮን ብር በማሰባሰብ የመልሶ ግንባታ ለማከናወን የታቀደ ሲሆን የክልሉ መንግስት ለዚሁ ስራ 1 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አሳውቀዋል።

- ሶስት ሺህ (3000) የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች፣ 21 ትምህርት ቤቶች፣ 10 ጤና ጣቢያዎች፣ 1 ሆስፒታል፣ 31 የንፁህ መጠጥ ውሀ ተቋማትና ሌሎችም ፕሮጀክቶች እንደሚገነቡ ገልጸዋል።

- ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ለመልሶ  ግንባታው የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ካሰራጨው ዘገባ የተወሰደ።

(በጦርነት የወደመው ህንፃ ፎቶ - ፋይል)

@tikvahethiopia
" ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር ልሄድ ስል በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት ታግጃለው " - አቶ ስብሃት ነጋ

አቶ ስብሐት ነጋ የፌደራል ፖሊስን በፍ/ ቤት ከሰሱ።

አቶ ስብሐት " ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር ልሄድ ስል በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት ታግጃለው "  ሲሉ ነው ለፍርድ ቤት ክስ ያቀርቡት።

ክሱን ያቀረቡት በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት መሆኑ ተገልጿል።

አቶ ስብሐት በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ህክምና አድርገው ለመመለስ ወደውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ለችሎቱ በቀረበው ክስ ላይ ተጠቅሷል።

በዚህ በቀረበ ክስ ኢትዮጲያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን ህጎችን እና በህገመንግስቱ የተቀመጡ የዜጎችን የመቀሳቀስ መብት በሚጣረስ መልኩ ፍ/ቤት ባላዘዘበት ሁኔታ ፖሊስ ከስልጣኑ ውጪ የጉዞ እግድ መጣሉና አቶ ስብሐትን ከኤርፖርት እንዲመለሱ ማድረጉ የህግ አግባብ የሌለው ነው ሲል ጠበቃቸው ታደለ ገ/መድህን ለችሎቱ አቅርቧል።

የአቶ ስብሐት ነጋ ክስ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ ፖሊስ መልስ ባለማቅረቡ ምክንያት መልስ የመስጠት መብቱ እንዲታለፍ ብይን ሰጥቷል።

በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ህዳር 28 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

በትግራይ ክልል ከነበረው ጦርነት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍ/ቤት ሲታይ የነበሩት አቶ ስብሐት ነጋ እና እህታቸው ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ እንዲሁም አቶ አባይ ወልዱ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር፣ አቶ ኪሮስ ሐጎስ በምህረት እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ ከእስር መፈታታቸው ይታወሳል።

(ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ጥያቄ ምንድነው ? ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ምላሽስ ? • " እንደዚህ ዓይት ውሳኔ ላይ የተደረሰው አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ኃላፊዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው " - የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ፍቅረስላሴ አካሉ (ለአዲስ ስታንዳርድ) • " ማህበራችን የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አላቀረበም " - ዶ/ር በፍቃዱ ዘለቀ (ለዶቼ…
" የተሰራጨውን የአቋም መግለጫ አላውቀውም " - የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፤ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች ስም የተሰራጨውን አቋም አላውቀውም ብሏል።

ማህበሩ ይህን ያለው #ለኢዜአ በላከው መግለጫ ነው።

ማህበሩ ፤ ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምሀርት ድረስ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን በማደራጀት በአምስት ዓላማዎች እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጿል።

ከአምስቱ ዓላማዎች መካከል አንዱ የመምህራን መብትና ጥቅም ማስከበር ነው ያለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ መምራን ያነሱትን ጥያቄዎች ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሚመለክታቸው የፌዴራል መንግስት አካላት እያቀረበ ለመፍትሄው እየሰራ መሆኑን አመልክቷል።

" አንዳንድ ጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ ማግኘት የሚገባቸው መሆኑን " እናምናለን ያለው ማህበሩ " አንዳንዶቹ ደግሞ ጊዜ የሚፈልጉ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል " ብሏል።

ማህበሩ ከሰሞኑን " የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች የአቋም መግለጫ "  በሚል ርዕስ  " ከህዳር 26/2015 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሥራ ማቆም አድማ እናደርጋለን " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ አላውቀውም ብሏል።

እውቅና ያለው የማህበሩ መዋቅር ስም  " የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር "  መሆኑን የገለፀው ማህበሩ ፤ መምህራን ማህበራቸው ጉዳዩን በጥብቅ ይዞ እየሰራ መሆኑን አውቀው የተለመደውን የማስተማር የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት በሙያዊ ኃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ጥሪውን አቅርቧል።

#ኢዜአ

ማስታወሻ : https://yangx.top/tikvahethiopia/74911

@tikvahethiopia