TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በፕሪቶሪያ ፤ በኢትጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነትን በተመለከተ የወጣው የጋራ መግለጫ 12 ነጥብ የያዘ ነው። ከዚህም ስምምነት መካከል ፦ - የህወሓት ቡድን #ትጥቅ_እንዲፈታ ከስምምነት ተደርሷል። - የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት ለማረጋገጥ እና የኢፌደሪ ሕገ-መንግሥቱን ለማስከበር የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ተስማምተዋል። …
#ETHIOPIA🇪🇹

#በኢትዮጵያ_መንግስት እና #በህወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ይዘት የሚገልፅ 12 ነጥብ ያለው #የጋራ_መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

ነገ ሁለት ዓመት የሚደፍነውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲበጅለትና ህዝቡም እረፍት እንዲያገኝ ፤ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ፣ አርሶ አደሮችም ወደ እርሻቸው ፣ ሰራተኞችም ወደ ስራቸው፣ ነጋዴዎችም ወደንግዳቸው እንዲመለሱ አጠቃላይ የቀደመው ሁኔታ እንዲፈጠር  ሁሉም አካል ዛሬ ወደ ተደረሰው " የሰላም ስምምነት " #ተፈፃሚነት እና #ተግባራዊነት ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የአፍሪካ ህብረት ፤ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የዛሬው ስምምነት በስኬት እንዲጓዝ እና ሰላም እንዲሰፍን  የስምምነቱ ትግበራ " ወሳኝ ይሆናል " ሲሉ ነው ያስገነዘቡት።

በዚሁ አጋጣሚ ለሰላም መስፈን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከሚጫወቱት ሚና ባለፈ በዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጥላቻ እና እርስ በእርስ መራራቅን ከሚሰብኩ ንግግሮች በመቆጠብ በሰላም ማስፈኑ የራሳቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው።

@tikvahethiopia
የካንሰር ህክምና . . . #በኢትዮጵያ

#ጥቁር_አንበሳ

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፤ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ የካንሰር ሕክምና ለማግኘት ወረፋ የሚጠብቁ መኖራቸውን አስታውቋል።

የሆስፒታሉ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ክፍል ኃላፊ ኤዶም ሰይፉ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" የተለያዩ የካንሰር ሕክምና ለማግኘት የሚጠብቁ ከ2013 መጨረሻ፣ 2014 ዓ.ም. እና 2015 ዓ.ም. ወረፋ ያልደረሳቸው አሉ፡፡

ይሁን እንጂ በየዕለቱ የሚመጡ ድንገተኛ የካንሰር ታካሚዎች በመኖራቸው በቅድሚያ ለእነዚህ ታካሚዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል።

በሆስፒታሉ ቆይተው መታከም ይችላሉ ተብለው የተለዩት ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ሕክምና ለማግኘት እየተጠባበቁ ያሉትን ለማስተናገድ ጥረት እየተደረገ ነው።

ለዚህ ወረፋ መብዛት ዋነኛ ምክንያት ብለው ያቀረቡት በሆስፒታሉ የሚገኘው መሣሪያ #አንድ ብቻ መሆኑን ነው።

በዚህ ዓመት ብቻ በተደረገው ማጣራት የካንሰር ሕክምና ለማግኘት የሚጠበባቁ 5,000 ታካሚዎች ሲኖሩ፣ በማዕከሉ በቀን በአማካይ ከ300 በላይ ታካሚዎች ይስተናገዳሉ።

ከእነዚህ የካንሰር ታካሚዎች መካከል 70 በመቶ የጨረር ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ፣ ኬሞ ቴራፒ የሚያስፈልጋቸው የታካሚዎች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም ።

በማዕከሉ አገልግሎት ለማግኘት የ2014 ዓ.ም. እና በ2015 ዓ.ም. ሕክምና ለማግኘት የተመዘገቡ ደግሞ ከ10,000 በላይ ናቸው። "

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ_ስፔሻላይዝድ_ሆስፒታል

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክሊኒካል ኢንኮሎጂስት ዶ/ር አማረ የሺጥላ ምን አሉ ?

"  በሆስፒታሉ የሚሰጠው የካንሰር ሕክምና ኬሞ ቴራፒና ቀዶ ጥገና ነው።

የጨረር ሕክምና ለመጀመር የማሽን ተከላ ላይ እንገኛለን። 60 በመቶ የሚሆነው የካንሰር ታካሚ እስኪጠናቀቅ እየተጠባበቁ ነው።

በሆስፒታሉ ካንሰር ሕሙማን ሕክምና አንዱ የሆነው ኬሞ ቴራፒ ሕክምና ለማግኘት ወረፋ በዛ ከተባለ ከሳምንት አይበልጥም።

ይሁን እንጂ ለካንሰር ሕሙማን የሚሰጠው የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለመጠባበቅ ከስድስት ወራት እስከ አንድ ዓመት ያስፈልጋል። "

#በሐሮሚያ_ዩኒቨርሲቲ_ሕይወት_ፋና_ሆስፒታል

በሐሮሚያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ሆስፒታል በካንሰር ሕክምና ረዳት ፕሮፌሰር ሚካኤል ሻውል (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" በሆስፒታሉ የኬሞ ቴራፒና የጨረር ሕክምና ለካንሰር ሕሙማን እየተሰጠ ነው።

የጨረር ሕክምና ከተጀመረ ስድስት ወራት አስቆጥሯል ፤ የታካሚዎች መጠነ መጠበቅ ከሦስት ወራት አይበልጥም።

በሆስፒታሉ በዓመት እስከ 6000 የካንሰር ታካሚዎች ሕክምና ያገኛሉ። በተለይ ደግሞ ጨረር ሕክምና ከተጀመረ በኋላ የታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

ሆስፒታሉ በምሥራቅ ኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜያት ብቸኛው የካንሰር ሕክምና መስጫ በመሆኑ ከሶማሌላንድና ከሌሎች አገሮች እየመጡ አገልግሎት የሚያገኙ ነበሩ። "

Via Ethiopian Reporter

@tikvahethiopia
ቪድዮ፦ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በረራ ላይ ሳለ #መስኮቱ_መገንጠሉን ተከትሎ አንድ የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላኑን ከበረራ አግዶታል።

የአሜሪካው አላስካ አየር መንገድ በቁጥር 65 የሆኑ 737 ማክስ 9 አውሮፕላኖቹን አግዷል።

እገዳው በበረራ ወቅት የአንደኛው አውሮፕላን መስኮት ተገንጥሎ አውሮፕላኑ በአስቸኳይ ለማረፍ ከተገደደ በኋላ ነው።

አርብ ዕለት በኦሬጎን ግዛት ከፖርትላንድ ከተማ ተነስቶ ወደ ካሊፎርኒያ ሲበር የነበረው አውሮፕላን የገጠመውን አደጋ ተከትሎ ከ35 ደቂቃዎች በረራ በኋላ በመነሻው ለማረፍ ተገዷል።

አየር መንገዱ በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩት 177 ተሳፋሪዎች እና ሠራተኞች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው አውሮፕላኑ #በሰላም አርፏል ብሏል።

የአደጋው መንስዔ እስኪጣራ ድረስ ሁሉንም 737 ማክስ 9 አውሮፕላኖች በጊዜያዊነት ከበረራ እንዳገደ አየር መንገዱ አስታውቋል።

ይህ ቦይንግ ሰራሹ አውሮፕላን ባለፉት ዓመታት መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ከአምስት ዓመት በፊት #በኢትዮጵያ እና #ኢንዶኔዢያ ባጋጠመ አደጋ ምክንያት ከበረራ ታግዶ የነበረው ይህ ማክስ 737 ዝርያ መሆኑ ይታወቃል። #BBC

@tikvahethiopia
#ATTENTION🚨

“ የካንሰር ሕመም እየጨመረ ነው ” - ዶክተር አስቻለው ወርቁ

በኢትዮጵያ የካንሰር ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን፣ በተለይም ማኀበረሰቡ ትንቦሆ፣  አልኮል ነክ ነገሮችን ከመጠቀም እንዲታቀብ ጥሪ ቀረበ።

ለካንሰር ሕሙማን የሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ቢሆንም በተለይ በኢትዮጵያ በኩል የፋይናንስ እጥረት ችግር እንደፈተነው ማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ተቋሙ የ20ኛ ዓመት ምስረታውን በማስመልከት መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ካንሰር #በኢትዮጵያ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ? በበሽታው የተጠቂ ሰዎች ቁጥር ቀነሰ ወይስ ጨመረ ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

የተቋሙ የቦርድ አባልና የውስጥ ደዌ ባለሙያው ዶክተር አስቻለው ወርቁ ምን አሉ ?

“ በጣም እየጨመረ ነው ያለው። ለመጨመሩ የተለያዩ ምክንያቶች ይኖራሉ። በአጠቃላይ ተላላፊ ያልሆኑ በሽዎች እየጨመሩ ነው። የካንሰር ህመምም እየጨመረ ነው።

ለምሳሌ፦ የሳንባ ካንሰርን ብናዬው ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ነው ያለው። የምንመረምረው ጥቂት ሰዎችን ስለሆነ በዚያችው ዳታ ተመርኩዘን ነው የምንገልጸው። ማኀበረሰቡን ያማከለ የዳሰሳ ጥናት ካልሰራን ቁጥሩን በትክክል መግለጽ ከባድ ነው።

10 ሰዎችን መርምሮ 5 ሕሙማን ቢገኝ 50 በመቶ ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ያልተመረመሩ ብዙ ስለሚኖሩ። እንደ አጠቃላይ ካየነው ግን ፦
- የሳንባ፣
- የአንጀት፣
- የጉበት፣
- የማህፀን፣
- የደም ሴል ካንሰር ታማሚሞች ቁጥራቸው እጅግ ባጣም እየጨመረ ነው ያለው። ” ብለዋል።

ካንሰር ዋነኛ የሞት እና የስቃይ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን ቁጥሮች እንደሚያመላክቱ ተገልጿል።

ለአብነት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከሞቱ ሰዎች ካንሰር የመገኘት እድሉ ከፍ ብሏል። ምክንያቱም የሳንባ ካንሰር ካሉት የካንሰር ዝርዝሮች ወደ 6ኛ ደረጃ ላይ ነው ያለው ተብሏል።

የማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ምን አሉ ?

“ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትንባሆ መሸጥም መግዛትም እንዳይችል የሚነገርበት ጊዜ መቼ ነው ?

ትንባሆ ነክ ነገሮች፣ አልኮል በሽታውን እያስፋፉት ነው።
 
ከ3,000 በላይ የካንሰር ሕሙማንና ቤተሰባቸውን እረድተናል። በአሁኑ ወቅት 175 ለካንሰር ሕሙማንና ለቤተሰባቦቸው፦

° ከአገራቸው የሚመጡበት ሙሉ የትራንስፖርት፣
° ከውጪ የሚገዙ መድኃኒቶች፣ 
° በሆስፒታል ውጪ በግል ተቋማት ለሚሰሩ የላብራቶሪ ምርመራ፣ 
° ሆስፒታል ለተኙት ሕሙማን ለአንዳንድ ነገር መሸፈኛ በወር 1,000 ብር፣
° እየታከሙ ለሚማሩ ተማሪዎች በወር 1,000 ብር፣
° 24 አልጋ ባለው የካንሰር ሕክምና ማዕከል በየዕለቱ ለቁርስ፣ ምሳ፣ በክሰስና እራት ወጪዎችን እየሸፈንን ነው። ”

NB. ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ የአቶ ወንዱ በቀለ የ4 ዓመት ጨቅላ ልጃቸው በካንሰር በሽታ ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ የደረሰባቸውን መሪር ሀዘን “ ማቲዎስ ቢሞትም ብዙ ማቲዎሶችን ማዳን እንችላለን ” በሚል መልካም አስተሳሰብ በመቀየር በ15 መስራች አባሎች ሚያዚያ 9 ቀን 1996 ዓ/ም የተመሠረተ ለካንሰር ሕሙማን የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia