#Amhara #Bahirdar
በአማራ ክልል መዲና ባሕር ዳር ክልከላ ተጣለ።
ክልከላው የተጣለው በከተማው የጸጥታ ምክር ቤት ነው።
ከክልከላዎቹ ምንድናቸው ?
- የቤት መኪና ፣ ታክሲ ፣ የመንግሥት መኪና ፣ ማንኛውም የጭነት መኪና ተሽከርካሪ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኃላ እንዳይንቀሳቀሱ ክልከላ ተጥሏል። ከተፈቀደው ሰዓት እላፊ ሲያሽከረክሩ መገኘት በሕግ ያስቀጣል።
- ከምሽቱ 3 ሰዓት በኃላ ማንኛውም የሰው እንቅስቃሴ ተከልክሏል።
- ማንኛውም ተሽከርካሪ ታርጋ ሳይኖረው ወይም ሳያስር መንቀሣቀሥ አይችልም።
- ከተፈቀደላቸው ተሽከርካሪዎች ውጭ ስቲከር መለጠፍ ተከልክሏል።
- ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ባጃጅ መጋረጃ እና የግራ ጎን ሸራን ሳያነሱ ማሽከርከር ተከልክሏል።
- የባጃጅ ተሽከርካሪ ማኀበራት ከተሰጣችው የሥምሪት ቦታ ውጭ ማሽከርከር አይችሉም።
- በማኀበራት ተደራጅተው ስምሪት ከተሰጣቸው ባጃጆች ውጭ ማሽከርከር ተከልክሏል።
- የባጃጅ ተሸከርካሪዎች የባሕር ዳር አስተዳደር ትራንስፖርት ጽ/ቤት በአዲስ የሚሰጠውን መለያ ወይም ባር ኮድ ግልጽ እና በሚታይ መንገድ የመለጠፍ ግዴታ አለባችው።
- የባጃጅ ባለ ንብረቶች ለቀን ገቢ ወይም ለተለያዩ የጊዜ ገደብ ለሚያከራዮቸው ግለሰቦች የውል ስምምነት በመያዝ ለፓሊስ እና ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ማሳወቅ አለባቸው።
- ባጃጆች ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ማሽከርከር ተከልክሏል።
- ባለ 2 እግር ሞተር ተሽከርካሪ ላልተወሰነ ጊዜ ማሽከርከር ተከልክሏል።
ክልከላው የማይመለከታቸው እነማንን ነው ?
ክልከላ የማይመለከታቸው ተሽከርካሪዎች ፦
° በጸጥታ ሥምሪት ላይ የሚገኙ፣
° አንቡላሶች፣
° የእሳት አደጋ መኪናዎች ናቸው። ነገር ግን በማንኛውም ሰዓት በአንቡላንስም ኾነ በሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ ፍተሻ ይደረጋል ተብሏል።
በሌላ በኩል ፤ ከጸጥታ መዋቅሩ አባላት እና ለጸጥታ ሥራ ተሰማርተው የመንቀሣቀሻ ፈቃድ ከተሰጣቸው ሰዎች ውጭ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሣቀሥ ተከልክሏል።
ማንኛውም የጸጥታ አባል ከተሰጠው ስምሪት ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ሲቪል ለብሶ የጦር መሣሪያ ይዞ መንሳቀስ እንዳይችል ክልከላ ተጥሏል።
#AmharaRegion
@tikvahethiopia