TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፍትሕ በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እና ዝርፊያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ባለፉት ሳምንታት ብቻ 3 በዚሁ አገልግሎት ላይ በተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ዝርፊያን ጨምሮ ጥቃት ተፈፅሟል (በቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ብቻ ሪፖርት የተደረገ) ። ትላንት ግን ከዝርፊያም ባለፈ የሰው ህይወት ተቀጥፏል። በዚህ ዘርፍ የሚሰሩ ወገኖች…
" እያገለገልን መሞት ይብቃን "

የኮድ 3 ሜትር ታክሲ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች እና ባለንብረቶች ማኅበር ፕሬዜዳንት ሄኖክ ተስፋዬ ለጀርመን ሬድዮ ጣቢያ ከተናገሩት ፦

" በአዱስ አበባ እስካሁን ድረስ 6 አሽከርካሪዎች ተሳፋሪ ነን ብለው ጥሪ ባደረጉ አካላት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።

መንግሥት በየ ዓመቱ ከ 450 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ገቢ የሚሰበስብበት ዘርፍ ነው።

እስከ 45 ሺህ የሚደርሱ አሽከርካሪዎችን አቅፎ የያዘውን ዘርፍ በትኩረት ሊመለከተው ይገባል።

በኮድ 3 የግል አውቶሞቢል የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጡ ብዙዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸው።

ቴዲ ቡናማው ፣ አቤል አማርከኝ፣ ሳላሃዲህ ሀሰን ፣ አቶ ሀብቴ የተባሉ በእድሜ የገፉ ሰው፣ ይበልጣ እና  ተወልደ የተባሉ አሽከርካሪዎች እስካሁን ተሳፋሪ ነን ብለው በተሳፈሩ ሰዎች ተገድለዋል። 

... አሽከርካሪዎችን አቅፈው ከሚሰሩ የትራንስፖርት ኩባንያዎች መካከል ኢትዮጵያዊ ያልሆኑትን ሰዎች አቅፈው የሚሰሩ አሉ።

ኢትዮጵያዊነት ዜግነት የሌላቸው ይሄንን ወንጀል እየፈፀሙት ነው የሚልም ነገር አለ። በርካቶቹ አንገታቸውን ገመድ ሲታነቁ፣ በርካቶቹ በስለት ሲወጉ እንዲህ አይነት ምልክቶች ሊሰጡ የሚችሉ መረጃዎች ይደርሱናል።

ይሄንን እኛ ሳንሆን መንግስት ደህንነቱን ሊያስጠብቅ መርምሮና ፈትሾ ምላሽ እንዲሰጠን እንፈልጋለን። "

-----

የኤሌክሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ከዚህ ቀደም በለሊት ይፈፀም የነበረው ዝርፊያ፣ ጥቃት ፣ ግድያ አሁን በቀን (ሳልሀዲን ተገድሎ የተዘረፈው ቀን 10:00 ሰዓት ላይ ነው) እየተፈፀመ መሆኑ እጅግ እንዳሳሰባቸውና ለስራቸው ከፍተኛ የደህንነት ስጋት መደቀኑን እየገለፁ ይገኛሉ።

Photo Credit : Solomon Muchie

@tikvahethiopia
#CISCO

Training & Preparation for the Cisco CCNA Network Engineering Certification (Weekend program-Online)

#Registration: from July 18, 2022 to August 19, 2022 #Class_start_date: August 20/2022

Three (3) certificates of course completion and a coupon for a 58 percent discount for the international exam will be given to the trainees from Cisco

Contact
Information: 0902-340070, 0935-602563, or 0945-039478, 0111260194

Follow our Telegram channel @CiscoExams for further information.
ትላንት ምሽት ከ4 ሰዓት በኃላ በአዲስ አበባ አንድ ስማቸውን መግለፅ የማያስፈልግ ግለሰብ #ታርጋ_በሌለው 2 ሎንግ ቤዝ መኪና በመጡ ወደ 20 በሚጠጉ የፀጥታ ኃይል ልብስ በለበሱ እና አብረዋቸው ሲቪል በለበሱ ሰዎች ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደው ነበር።

በኃላም ዛሬ ንጋት አካባቢ በቪ8 መኪና መንገድ ላይ ጥለዋቸው ሄደዋል።

የፀጥታ ኃይል ልብስ የለበሱና የታጠቁት ግለሰቦች በቅድሚያ በር በማንኳኳት የግቢው ጥበቃ በሩን ሲከፍትላቸው ገፍትረው በመግባት እኚሁን ግለሰብ ከቤት እየደበደቡ አስወጥተው መኪና ላይ ጭነዋቸው እንደወሰዷቸው ቤተሰቦቻቸውን ገልፀዋል።

በወቅቱ ቤት ውስጥ የነበሩ የቤተሰብ አባላት ጉዳዩን በስልክ ለመቅረፅ ቢሞክሩም መሳሪያ ደቅነው እየዳበደቡ ስልክ እንደቀሙባቸው አስረድተዋል።

"እነዚህ ግለሰቦች ማንነታቸውን የሚገልፅ አንድም ነገር አልያዙም፤በትክክል የህግ አካል ከሆኑም የፍ/ቤት መጥሪያ አላሳዩም፤ ምንም ነገር የላቸውም ልንጠይቃቸው ስንሞክር ማሳሪያ ደቅነው #እንዳትጠጉን ነው ያሉት፤ እንዳይሄዱ ለመከላከል ስንጮህ መሳሪያ እየተኮሱ ነው የሄዱት" ብለዋል።

በአቅራቢያው ፖሊስ ጣቢያ ስለነበር ፖሊስ ይዘው ቢመጡም ፖሊስ ባለበት እየተኮሱ ነው የሄዱት።

ከእኚሁ ግለሰብ ጋር የቤቱ ጥበቃ እና መንገድ ላይ የተያዙ 2 የአካባቢው ልጆችም ተወስደው የነበረ ሲሆን ሁሉም ፊታቸው ተሸፍኖ አንድ መጋዘን የሚመስል ቦታ እንደነበሩ ድብደባም እንደተፈፀመባቸው አስረድተዋል።

ግለሰቡ ከፖለቲካ ሆነ ከሌላ ማንኛውም ጉዳዮች ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ነገር ግን በግል ጉዳይ የፍ/ቤት ቀጥሮ እንደነበራቸው ትላንትም ፍ/ቤት እንደነበሩ ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል።

ትላንት የተፈፀመውን ድርጊት በተመለከተ ፖሊስ ቤት መጥቶ ቃል የተቀበለ ሲሆን ለፌዴራልና አ/አ ፖሊስ እንዲያመለክቱ አሳውቋቸዋል።

@tikvahethiopia
#EOTC

ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሕከምና ከሀገር ውጪ እንደሚሄዱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

• ምእመናን በጸሎት እንዲያስቧቸው ጠይቀዋል፡፡


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለሕክምና ከሀገር ውጪ መጓዝ ማሰባቸውን በማስመልከት ዛሬ ከብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ለኢኦተቤ ቴቪ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስነታቸው በአስቸጋሪ የጤና ሁኔታ መቆየታቸውን ጠቅሰው ከሀገር ውጪ ለመታከም ማሰባቸውን ገልጸዋል፡፡

በተቻለ መጠን የተለየ ችግር ካልገጠማቸው ከ አንድ ወር ባላነሰ ጊዜ ሕክምናቸውን አጠናቀው ወደ በመንበረ ፕትርክናቸው እንደሚመለሱ የገለጹት ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ስለ ሀገርና ስለወገን እየጸለዩ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ እንዲቆዩ ጠይቀዋል፡፡

የዐይን ሕክምና ጨምሮ ሙሉ ሕክምናቸውን አጠናቀው አስኪመለሱ አባቶችና ምእመናን በጸሎት ያስቡኝ ያሉት ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቤተክርስቲያን ክብር አስጠብቀው ሥራቸውን በኃላፊነት እንዲያከናውኑ አደራ ብለዋል፡፡

ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ለሕክምና ሊሄዱ እንደነበር የተናገሩት ቅዱስ ፓትርያርኩ ሁኔታቻዎች ባለመመቻቸታቸው እንደቆዩ ገልጸው አሁን ግን ነገሮች ስለተስተካከሉ ሕክምናቸውን አጠናቀው እስኪመለሱ ምእመናንና ካህናት ተረጋግተው የሚጠበቅባቸውን ተግባር እያከናወኑ እንዲቆዩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

መረጃው የኢኦተቤ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethiopia
" ወደ 100 የሚጠጉ የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላት ተገድለዋል "

ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ ጥቃት የሰነዘረው የአልሻባብ የሽብር ቡድን በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

ይሄ የሽብር ቡድን በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ከመታቱ በፊት በንብረት እና ሰው ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ተነግሯል።

አልሸባብ ፤ ከሶማሊያ ጋር ወደ ሚዋሰነው ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን በመግባት ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ በሶማሌ ልዩ ኃይል ከባድ ምት መመታቱ ተሰምቷል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች በሐረገሌ ወረዳ ሁልሁል በተባለ ስፍራ ያታጣቂ ቡድኑን ከበውትም እንደሚገኙ ቢቢሲ ሱማልኛ ክፍል ፅፏል።

እስካሁን በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ፣ በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በኩል ሆነ በክልል ኮሚኒኬሽን የተሰጠ መረጃ ባይኖርም የሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ አልሸባብ የሽብር ቡድን ላይ በሶማሌ ክልል የፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ የማጥቃት እርምጃ 100 የሚደርሱ የሽብር ቡድኑ አባላት መገደላቸውን ዘግቧል።

የሶማሊያ ቴሌቪዥን አንድ ስማቸው ያልተገለፀ የአካባቢው ባለስልጣን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ባለፉት 24 ሰዓታት አፍዴር ዞን ውስጥ የሽብር ቡድኑ ጥቃት ከከፈተ በኃላ በተወሰደበት ጠንካራ ምት 100 የሚደርሱ ታጣቂዎቹን እንዳጣ ገልጿል።

Photo Credit : የሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ

@tikvahethiopia
#NEBE

የኢትዮጵያ ነጻነት ፓርቲ (ኢንፓ) ሚያዝያ 02 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ በተመለከተ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት ፦

" ... የጉባኤው ምልዓተ ጉባኤ በቁጥር ደረጃ የተሟላ ቢሆንም የቦርዱ ተወካዮች ከታዘቡት እና የጉባኤው ማገባደጃ አካባቢ ከተፈጠረው ግርግር መረዳት እንደቻሉት አብዛኛው የጉባኤ ተሳታፊዎች የፓርቲ አባል ስለሆኑ የተገኙ ሳይሆን በልመና ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና #በአበል የተገኙ ናቸው "

📎 ምርጫ ቦርድ ኢነፓ ያደረገውን ጠቅላላ ጉባዔ በተመለከተ ፓርቲው ያቀረባቸውን ሠነዶችና ሪፖርቶች እንዲሁም የቦርዱ ታዛቢዎችን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ፓርቲውን የማገድ ውሳኔ አሳልፏል። ሙሉ የቦርዱ የውሳኔ ሀሳብ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#ጥያቄ #የጋራመኖሪያ_ቤቶች

ብዙ ሲባልለት የነበረው የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ከብዙ መናጋገሪያ ጉዳዮች በኃላ ሙሉ በሙሉ መሰረዙ ይታወሳል።

በቀጣይ ዕጣው መቼ ይወጣል ? የሚለው ለጊዜው ባይታወቅም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ " ከገጠመን ችግር ተነስተን ተገቢውን ሁሉ ጥንቃቄ በማድረግ በፍጥነት ዳግም እጣ በማውጣት በፍትሀዊነት ተደራሽ ለማድረግ እንሰራለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

የቀጣዩ ዕጣ ከመውጣቱ በፊት ግን የተለያዩ አካላት ከወዲሁ እጅግ ልዩ ጥንቃቄ እንዲደረግ እና ታማኝነት ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ እየጠየቁ ይገኛሉ።

ቤት ይደርሰናል በማለት ረጅም ዓመታት እየተቸገሩ ቆጥበው በተስፋ የሚጠባበቁ ነዋሪዎች መካከል በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በቀጣዩ ዕጣ አወጣጥ ዙሪያ መልዕክታቸውን እየላኩ ጥያቄ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ከነዚህ መካከል በቀጣይ ዕጣው የመውጣት ሂደት ላይ ሁሉም ለዕጣው ብቁ ሆነው የተገኙት ቆጣቢዎች ዕጣ ከመውጣቱ በፊት የስም ዝርዝራቸው በይፋ እንዲገለፅ ፣ ከዕጣው መውጣት በፊት ቤቶቹ ያሉበት ሳይት ቤቶቹ ካሉበት ወለል ጋር እንዲገለፅ፣ በሂደቱ ዕጣ የማይወጣላቸው ቤቶች አጠቃላይ ምን ያህል እንደሆኑ በግልፅ እንዲብራራ ጠይቀዋል።

ሌላው የ20/80 የባለ 3 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች አሁን በሚወጣው ዕጣ ላይ እንዲካተቱ ጠይቀዋል።

ባለፈው ውድቅ በተደረገው የዕጣ አወጣጥ ከ1997 ተመዝጋቢዎች በአግባቡ እየቆጠቡ ያሉ ጥቂቶች መኖራቸው መግለፁ ይታወሳል (በቤት አስተዳዳሪው ቦርድ ውሳኔ ፕሮግራሙ ከሲስተም ውጭ ቢሆንም)።

እኚህ ቆጣቢዎች በባለፈው ዕጣ ውስጥ ያልተካተቱ ከመረጃ ውስንነትና በባለፈው ሲስተም ላይ የመረጃ መመሰቃቀልን ለመከላከል ሲሆን በልዩ ሁኔታ ለብቻቸው እንዲስተናገዱ መወሰኑ ይታወቃል።

የባለፈው ዕጣ አወጣጥ የ20/80 የባለሶስት መኝታ ቆጣቢዎች በቀጣዩ ላይ በዕጣው ላይ እንዲካተቱ ከወዲሁ እንዲሰራ ጠይቀዋል።

ሌላው የ2005 የ20/80 ባለሶስት መኝታ ቆጣቢዎች በርካታ ጥያቄ ያላቸው ሲሆን በ13ኛው ዙር ተጀምሮ በ14ኛው ዙር አለመካተቱ ጥያቄ እንደፈጠረባቸው ፤ ግልፅ የሆነ ማብራሪያም እንደሚፈልጉ በመግለፅ አስተዳደሩ በድጋሚ አጢኖት በቀጣይ ላይ እንዲካተቱ ጠይቀዋል።

በተለይ ማብራሪያውን እየጠየቁ የሚገኙት ላለፉት 9 ዓመታ እየቆጠቡ የሚገኙት ወገኖች በ13ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ወቅት በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሳይቀር በ1997 ለባለ3 መኝታ የተመዘገበ የለም ሁሉም በ2005 የተመዘገቡ ስለሆነ ወደእነሱ ይተላለፋል ተብሎ ነበር ነገር ግን በ14ኛው ዙር አለመካከተቱ ግልፅ ማብራሪያ የሚያስፈልገው መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ ተደርጓል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ/ም የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ውድቅ አድርጓል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ባሳለፍነው ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ/ም የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ…
" ውሳኔውን ማሳለፍ ከባድ ነበር " - ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣው ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንዲደረግ የተላለፈው ውሳኔ ከባድ እንደነበር ነገር ግን ውሳኔው ባይተላለፍ ተጎጂ የሚሆነው ህዝብ እጅግ ከፍተኛ እንደነበር የአዲስ አበባ ከንቲባ ገለፁ።

ይህ የገለፁ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ በቤቶች ዕጣ አወጣጥ ላይ የተፈፀመው ማጭበርበር እኛንም ጨምር በጣም ያሳዘነና ያሰደነገጠ ነበር ይህን ተከትሎ ዕጣው ውድቅ እንዲሆን የተወሰነውን ውሳኔ ማሳለፍ በጣም ከባድ ነበር ብለዋል።

" ህዝቡ በጣም ጓግቶ ነበር የጠበቀው፣ በቀጥታ ስርጭት ዕጣ ሲወጣ ሰው ያየበት ነበር፣ ግማሹ በቀጥታ ስርጭት ስሙን ያየ ፣ በዕለቱ የፕሮግራም አስተዋዋቂው ጭምር የሰው ስም ሲያስተዋውቅ ስለነበር እዛ ውስጥ በጤነኛ መንገድ ቆጥበው የመጡና ዕጣ የወጣላቸው ስላሉ ውሳኔ ማሳለፉ ከባድ ነበር " ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም " ውሳኔውን ለማሳለፍ ጉልበት የሆነን ባለፈው ዓመት ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ አስጠንተን ያየነው ውጤት እንድንደፍር አድርጎናል።

ሁለተኛ ውስጣችን ያለው ፍትሃዊነትን የማንገስ ፍላጎት ደፍረት ሆኖናል፣ ከፍተኛ የከተማውን አመራር ወዲያው ይሄን ዕጣ በምንም አይነት ተጣርጦ እንኪያልቅ ድረስ ህዝቡ እንዲታገሰን የመጨረሻ መግለጫ እናውጣ ፤ ማጣራቱን ተቋማቱ ፈጥነው እንዲጨርሱ ግፊት እናድርግ እየታየ እየመጣ ያለው ሂደት በአጠቃላይ አጠቃላይ ውጤቱን የሚያዛባ እንጂ የተወሰነ ስህተት ከውስጡ ማረም የሚያስችል ሆኖ አላገኘነውም " ብለዋል።

" ውሳኔውን ለህዝቡ ስንል፣ ለፍትሃዊነት ስንል ነው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረስነው ፤ በእርግጠኝነት ያንን 25,491 እነኚህ ናቸው የወጣላቸው ብለን ብናረጋግጥ ኖሮ የሚጎዳው ህዝብ ቀላል አልነበረም።

ሁለተኛ mess ይፈጠር ነበር፣ ባንክም ለእነኚህ ሁሉ ውል ያዋውላል ብዬ አላምንም ብዙ ናቸው eligible ያልሆኑ፣ መንግስት እና ህዝብ መካከል ያለውን ትምምን የፈለገ ቤት ብንገነባ በጣም ይጎዳው ነበር በዚህም ከተማ አስተዳደሩ ለህዝቡ የገባውን ቃል ታማኝነቱን ተመልሶ ያረጋገጠበት ነው የገጠመን ነገር።

ለምን ያጋጥማል አይባልም ፤ ሊያጋጥም ይችላል ካጋጠመን ግን ያ ማጭበርበር አልፎን እንዳይሄድ የተደረገውን ጥረት መመልከት ነው ያለበት " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ውሳኔውን ማሳለፍ ከባድ ነበር " - ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣው ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንዲደረግ የተላለፈው ውሳኔ ከባድ እንደነበር ነገር ግን ውሳኔው ባይተላለፍ ተጎጂ የሚሆነው ህዝብ እጅግ ከፍተኛ እንደነበር የአዲስ አበባ ከንቲባ ገለፁ። ይህ የገለፁ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ በቤቶች ዕጣ አወጣጥ ላይ የተፈፀመው ማጭበርበር እኛንም…
#Update

በቅርቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳውቁ።

ከንቲባዋ ትክክለኛ ቀኑን አስረግጠው ባይናገሩም የጋራ ቤቶች እጣ ባጠረ ጊዜ ውስጥ እንደሚወጣ ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ነው።

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ " የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ በቅርብ ለማውጣት ተመልሰን ሶፍትዌሩ መረጋገጥ አለበት ፤ #ሌላ_ሶፍትዌር ነው የምንጠቀመው ትንሽ መታገስ ያስፈልጋል።

ቤቱን የሚጠባበቀው ህዝባችን ለጥራት ቅድሚያ ይስጥ፤ በጥራት ለመስራት ሰው የሚችለውን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን። ጥንቃቄም እናደርጋለን። በሚመለከታቸው ተቋማት ሁሉ ማረጋገጫ እንዲሰጥበት የተለያየ አደረጃጀቶችን ፈጥረንላቸዋል ተቋማት ድርሻ ድርሻ እንዲኖራቸው።

የኢንዱስትሪ ስታንዳርድ አመራሩንም ጭምር በዚህ አጋጣሚ በደንብ ስላወቅነው እሱንም ጭምር የማስጠበቅ ሂደት እንከተላለን ነገር ግን አንዘገይም።

በጣም ለመፍጠን ብለን ስህተት ውስጥ አንገባም ፤ አዲስ ሶፍትዌር ነው በሚል በጣም complicated ነገር አድርገን ሰው የማይችለው ነገር አስመስለን ማዘግየትም አንፈልግም " ብለዋል።

አክለውም " በእርግጠኝነት የሰዎች አለመታመን ነው ይሄን ያመጣው (ባለፈው የተጭበረበረውን የቤት ዕጣ አወጣጥ ማለታቸውን ነው) ሶፍትዌሩን በትክክል አልምተውታል ካለሙ በኃላ ግን ለሚፈልጉት ነገር እንደሚጠቅም አድርገው አዘጋጅተውታል ፤ ሰዎች ያጠፉት ጥፋት ነው ይሄን ህግ በማስከበት ሂደታችን 16 የሚደርሱ ሰራተኞቻችን በህግ ቁጥጥር ስር ነው ያሉት ፍርድ ቤትም ቀርበዋል ፤ ሂደቱን ከስር ከስር የፌዴራል ፖሊስ ይዞታል እራሱ መግለጫ እየሰጠበት ይሄዳል። ሌላም መረጃ የሚመለከተው ሰው ካለም ይቀጥላል " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#ሐምሌ16

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ልክ በዛሬው ቀን በሐምሌ 16 ቀን 1939 ዓም ነው የተመሰረተው።

ምሥረታው ዛሬ አውቶቡስ ተራ በምንለው አካባቢ ነበር። አሁን በጉለሌ የተሠራው በ1961 ዓ/ም ነበር።

ኮሌጁ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት መልካም አሻራውን በማሳረፍ እዚህ ደርሷል።

ወደፊት የሕክምና ዩኒቨርስቲ ለመሆን እየሠራ ይገኛል።

@tikvahethiopia