TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.15K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ከዓለም ዙሪያ #1 ፦

➡️ #ሴኔጋል ፦ በምዕራብ ሴኔጋል ፤ ቲቫዋን በምትሰኝ ከተማ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰ ቃጠሎ 11 አዲስ የተወለዱ ህጻናት መሞታቸውን ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ተናግረዋል።

➡️ #አፍጋኒስታን ፦ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል እና ሰሜናዊ ከተማ ማዛር ኢ ሻሪፍ ከተከታታይ በደረሱ ፍንዳታዎች ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። ዳኢሽ ለጥቃቱ ኃላፊነት መውሰዱን ሮይተርስ ዘግቧል።

➡️ #ሩስያ ፦ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ ለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ወታደሮቻቸውን ወደ ሀገሪቱ ከላኩ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩክሬን ውስጥ በወታደራዊ ዘመቻው ከቆሰሉ ወታደሮች ጋር ተገናኝተዋል። በሌላ የሩስያ ጉዳይ ፤ ሀገሪቱ ያለባትን የውጭ ሀገራት እዳ በራሷ መገበያያ ገንዘብ “ሩብል” ለመክፈል ወስናለች ፤ እዚ ውሳኔ ላይ የደረሰችው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ከቀናት በፊት በሩሲያ በአሜሪካ ባንኮች በኩል የምትፈጽመውን የውጭ ዕዳ ክፍያ ፍቃድ መሰረዙን ተከትሎ ነው።

➡️ #ዩክሬን ፦ ወደ ሰቨሮዶንስክ ከተማ የሚወስደውን አውራ ጎዳና ለመቆጣጠር በሩስያ እና ዩክሬን ኃያሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተደረገ ነው። ሩሲያ ይህን ከተማ ለመቆጣጠር ተቃርቢያለሁ ብትልም አንድ ከፍተኛ የዩክሬን ባለሥልጣን ነገሩን አስተባብለዋል። ይህ ጎዳና ዩክሬን የምትቆጣጠራቸውን ከተሞች ሩሲያ ከያዘቻቸው ከተሞች ጋር የሚያገናኝ ከፍ ያለ ወታደራዊ ዋጋ ያለው ነው።

➡️ #ጋምቢያ ፦ የጋምቢያ መንግስት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ከ20 አመታት በላይ በዘለቀው የስልጣን ዘመናቸው ተፈጽመዋል በተባሉ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ማሰቃየት እና ሌሎች ወንጀሎች ላይ ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል።

#አልጀዚራ #ቲአርቲወርልድ #ስፑትኪን #ሮይተርስ

@tikvahethiopia
#Motta 📍

የሞጣ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ኮማንድ ፖስት ፤ በህግ የሚፈለጉ ግለሰቦች በሁለት ቀን ለመንግስት እጅ እንዲሰጡት አሳሰበ።

ኮማንድ ፖስቱ ይህን ያሳሰበው ትላንት ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ/ም በወቅታዊ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ ነው።

በህግ የሚፈለጉ ግለሰቦች ከሁለት ቀን ሞጣ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት በመቅረብ ለመንግስት እጅ እንዲሰጡ ያሳሰበው ኮማንድፖስቱ ግለሰቦቹ በተሰጣቸው እድል ባለመጠቀም ለሚወሰደው ርምጃ ሁሉ ሀላፊነት አልወስድም ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ኮማንድ ፖስቱ ፦

➡️ ማንኛውንም ህ/ሠብ በቡድን መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን ገልጿል።

➡️ ማንኛውም ማህበረሰብ በህግ የሚፈለጉ አካላትን ደብቆ ወይም አከራይቶ ቢገኝ ተጠያቂ መሆኑን አውቆ ችግር ፈጣሪዎችንና ተፈላጊዎችን አጋልጦ እንዲሰጥ አሳስቧል።

➡️ ከጠዋቱ 12:30 በፊትና ከምሽቱ 1: 30 በኋላ ስምሪት ከተሰጣቸው የጸጥታ ሀይሎች ውጭ የእንቅስቃሴ ገደብ ተቀምጧል። ይህ ሳይሆን ቢቀር የጸጥታ ሀይሉ እርምጃ ይወስዳል ተብሏል።

➡️ ስምሪት ከተሰጠው የጸጥታ ሀይል ውጭ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈጽሞ ተከልክሏል።

(ተጨማሪ ክልከላዎችን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
🫂 ከጭልጋና አካባቢው ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖች ወደ ቦታቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።

በጭልጋና አካባቢዋ ተፈናቅለው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሠራ እንደሚገኝ ተነግሯል።

ከትላንት አንስቶ ከአይከል እና በዙሪያዋ ተፈናቅለው የነበሩ 11 ሺህ 938 የህበረተሰብ ክፍሎች ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ሲሆን ወደ አይከል ከተማ ሲገቡ ማህበረሰቡ በነቂስ ወጥቶ ተቀብሏቸዋል።

ተፈናቃዮቹ ከዚህ በፊት በአይከል ከተማና በአካባቢዋ ይኖሩ የነበረ ሲሆን ከማንነት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከቦታቸው ተፈናቅለው በተለያዬ ቦታ ነበሩ። አሁን ላይ በተፈጠረው አንፃራዊ ሰላም ከትላንት አንስቶ ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል።

ፎቶ ፦ የጭልጋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#TemesgenDesalgn

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቢሮው ሲቪል በለበሱ በሁለት መኪና በመጡ የፀጥታ ሀይሎች መወሰዱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ አሳውቋል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፍትህ መፅሄት ማናጂንግ ዳይሬክተር መሆኑ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ መተግበርያን በመጠቀም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት ክፍያዎን ይፈጽሙ !

ክፍያ ለመፈፅም የሚከተሉትን ቀላል ሂደቶች ይከተሉ።
1. በአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ login ያድርጉ።
2. ዋና ሜኑ ውስጥ utility payment የሚለውን አማራጭ በመክፈት Ethiopian Airlines Ticket የሚለውን ይጫኑ።
3. የበረራ ትኬት መክፈያ ቁጥርዎን (PNR) አስገብተው አስፈላጊውን መረጃ ማሰገባትዎን ካረጋገጡ በኋላ pay የሚለውን ይጫኑ።

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://yangx.top/BoAEth
#እንድታውቁት

በአማራ ክልል የጦር መሳሪያ ምዝገባ ቀን ተራዝሟል።

የመሳሪያ ምዝገባው የተራዘመው ለሶስት ቀናት ማለትም እስከ ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ/ም ሲሆን በተለያየ ምክንያት ያላስመዘገቡ ግለሰቦች እድል ያገኛሉ ተብሎ ስለታሰበ ነው ተብሏል።

የተራዘመበት ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር በመኖሩ በበቂ ጊዜያት ማስመዝገብ ያልቻሉ እና በተሳሳተ መረጃ የተደናገሩ ግለሰቦች እንድል እንዲያገኙ በማሰብ ነው ተብሏል፡፡

ከምዝገባው በኋላ ሕገ ወጥ የመሳሪያ እንቅስቃሴ ላይ ቁጥጥር ስለሚኖር ሕዝቡ ያለውን መሳሪያ ያለምንም አይነት የመሳሪያ ገደብ ማስመዝገብ እና መታወቂያውን መያዝ እንደሚኖርበት ተገልጿል።

በቀጣይ የክልሉ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ከመሳሪያ አጠቃቀም፣ አያያዝ እና ኅላፊነት አንጻር ሥልጠና ይሰጣል ተብሏል፡፡

(የአማራ ክልል ሚሊሻ ፅ/ቤት)

@tikvahethiopia
#YayesewShimeles

ከጥቂት ወራት በፊት ታስሮ የተፈታው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በዛሬው ዕለት መታሰሩ ተሰምቷል።

ጋዜጠኛ ያየሰው ዛሬ ሀሙስ በፀጥታ ኃይሎች ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣባያ መወሰዱን ጠበቃው ገልፀዋል።

ጠበቃው አቶ ታደለ ገ/መድኅን የካ አባዶ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ፖሊስ መምጣታቸውን በተናገሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል።

ጠበቃው አቶ ታደለ ፤ ያየሰው ላለፉት 2 ዓመታት ትምህርት ላይ ማሳለፉን አስታውሰው፤ በአሁኑ ሰዓት በጋዜጠኝነት ሥራ ላይ አይገኝም ብለዋል፤ በተያዘበት ወቅትም ለመያዙ ምንም አይነት ምክንያት እንዳልተሰጠው አስረድተዋል።

ያየሰው በአሁኑ ወቅት በ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኝ ሲሆን በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት ይቀርባል ብለው እንደሚጠበቅ ጠበቃው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#RICA

አሽከርካሪዎች በ5 በመቶ የኮሚሽን ክፍያ የሚሰሩበት የኤሌክትሮኒክስ ትራንስፖርት ሞባይል መተግበሪያ ስራ ሊጀምር መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ አገልግሎት የሚጀምረው በሪካ ቴክኖሎጂ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲሆን ድርጅቱ የሞባይል መተግበሪያዎችን በማበልጸግ እና በማዳበር ፤ የበይነመረብ ግብይትን ማመቻቸት ላይ የሚሰራ ነው።

በዛሬው እለት ሪካ ድርጅቱ ስላበለጸጋቸው የሞባይል መተግበሪያ እና አገልግሎቶቹን በተመለከተ ትውውቅ አድርጓል።

ከመተግበሪያዎቹ መካከል ሪካ ትሪፕ እና ሪካ ሾፒንግ የተሰኙት በቅርቡ ስራ የሚጀምሩ ናቸው ተብሏል።

ሪካ ትሪፕ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ መተግበሪያ ሲሆን አሽከርካሪዎች እስከ ሐምሌ 10/ 2014 ዓ.ም ድረስ ያለ ኮሚሽን ክፍያ የሚሰሩበት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ከሐምሌ 10 በኋላ በ5 በመቶ የኮሚሽን ክፍያ እንደሚሰሩ ተገልጿል።

መነሻ ዋጋ 95 ብር እንዲሁም በኪ.ሜ 10 ብር ተመን አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቋል።

ሌላው ሪካ ሾፒንግ የተሠኘው የሞባይል መተግበሪያ ማንኛውም ግለሰብ እና ድርጅት ምርትና አገልግሎቱን ለሽያጭ የሚያቀርብበት እንዲሁም የሚሸምትበት የበይነመረብ ግብይት ስርአት ሲሆን ሐምሌ 10 ቀን 2014 አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሏል።

Via ኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

‘ US Embassy Addis Ababa ’ በሚል ስም ከ127 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የቴሌግራም ቻነል " አሜሪካ ኤምባሲ በጦርነት የተጎዳዉን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመደገፍና ከክፍለዘመን የዘለቀዉን የአሜሪካና የኢትዮጵያን ወዳጅነት ለማጠናከር ለ20 ሺህ ኢትዮጵያዉያን በአሜሪካ የስራ ዕድል ፈጥሯል " ብሎ መረጃ አጋርቷል።

የዕድለኞች የትራንስፖርት ፤ የመኖሪያ ቤትና የመኪና ወጪ በኤምባሲዉ እንደሚሸፈንም ጽፏል።

ስለዚህም የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን በቴሌግራም ቻነሉ አማካኝነት እንዲመዘገቡና ተመዝጋቢዎችም ሙሉ ስማቸዉን፤ ስልክ ቁጥራቸዉን እንዲሁም አድራሻና መሰል ግላዊ መረጃዎቻቸዉን እንዲልኩም ይጠይቃል።

ይህን በተመለከተ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እየተሰራጨ ያለድ መረጃ ሀሰተኛ እና ሰዎችን ለማጭበርበር እንደሆነ ገልጿል።

ኤምባሲዉ ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ አጣሪ ድረገፅ በሰጠው ቃል፤ በአሜሪካ የስራና የቪዛ ዕድሎችን በተመለከተ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተጋሩ መሆኑን አስታዉቋል።

" የአሜሪካ መንግስት በኢሜይል፤ ፌስቡክ ሚሴንጀር፤ ቴሌግራም ወይም ሌላ ማህበራዊ ትስስር ገጾች አማካኝነት ግላዊ መረጃዎችን አይጠይቅም " ሲል ኤምባሲው አስረድቷል

ትክክለኛ የስራ ዕድሎችን በድረ-ገጹ ላይ እንደሚለጥፍና ሰዎች ለአጭበርባሪዎች እንዳይጋለጡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኤምባሲዉ ጠይቋል።

Via Ethiopia Check

@tikvahethiopia