#Update
ጋዜጠኞቹ በዋስትና እንዲፈቱ ተወሰነ።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሶሴትድ ፕሬስ (AP) ዘጋቢ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያ ቶማስ እንግዳ እያንዳንዳቸው በ60 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተለቅቀው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ወስኖላቸዋል።
ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኞቹ ከአገር እንዳይወጡ የጉዞ እገዳም አስተላልፎባቸዋል።
ጋዜጠኞቹ በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብለ የተፈረጀውን "ሸኔ" ን በዓለም አቀፍ ደረጃ አስተዋውቃችኃል ተብለው ተጠርጥረው መያዛቸው ይታወሳል።
የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ከታሰሩ ወዲህ ለአራተኛ ጊዜ የተካሄደ ነው።
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ የጋዜጠኞቹ የትዳር አጋሮችን ጨምሮ 5 የቤተሰብ አባላቶቻቸው በአካል ተገኝተው ሂደቱን መከታተላቸው ethiopiainsider.com ዘግቧል።
@tikvahethiopia

#ETHIOPIA
ከነገ ጀምሮ ዜጎቻችንን የመመለስ ስራ ይጀመራል ተብሏል።
ለረጅም ጊዜያት ሲጠበቅ የነበረው በሳዑዲ አረቢያ በከፋ ስቃይ ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ ነገ እንደሚጀመር ተገልጿል።
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ አረቢያ ሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ወደ አገራቸው የመመለስ ሥራ እንደሚጀመር አስታውቋል።
ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከ7 እስከ 11 ባሉት ወራት ውስጥ ለመመለስ እንደታቀደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

#Bichena📍
2 ታዳጊዎችን አግተው ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ የጠየቁ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በምስራቅ ጎጃም ዞን ብቸና ከተማ ቀበሌ 03 ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሀሊማ ሀሰን በቀን 19/07/2014 ዓ/ም ወደ ብቸና ከተማ ፖሊስ ፅ/ቤት ቀርበው የማያውቁት ሰው ስልክ እየደወለ " ልጅሽን አግተነዋልና ዛሬውኑ 400,000 ብር ካላመጣሽ እንገለዋለን " እያለኝ ነው የሚል መረጃ ለፖሊስ ይሰጣሉ።
የብቸና ፖሊስም አባላቱን ስምሪት ውስጥ በማስገባት በተጠርጣሪወች ላይ ክትትል ማድረግ ይጀምራል።
ፖሊስ በ " ስልክ ልውውጡ " መሰረት አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ማድረግ ሲጀምር እድሜያቸው 12 ዓመት እና 14 አመት የሆኑ 2 ወንድ ታዳጊዎች ታግተው የሚገኙበትን ቦታ መረጃ ያገኛል።
ፖሊስ ባገኘው መረጃ መሰረት ጥቆማ የሰጠውን ተጠርጣሪ እንዲመራ በማድረግ ታዳጊዎቹ ታግተዋል ተብሎ ወደተጠረጠረበት ቦታ ይጓዛል።
በዚህም አጎራባች ከሆነው " እነማይ ወረዳ " ውስጥ እድገት በአንድነት ቀበሌ ሁለቱ ታዳጊወች ሰው ከማይኖርበት ባዶ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው በ2ኛ ተጠርጣሪ እየተጠበቁ እንዳለ እጅ ከፈንጅ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።
የታገቱት ታዳጊዎች ወደ ፖሊስ ከቀረቡ በኋላ ሁኔታውን ፥ በመጫወት ላይ እንዳሉ ሁለት የማያውቋቸው ሰዎች ጠርተው " ወንጀል ፈፅማችኋልና ትፈለጋላችሁ " በሚል በባጃጅ አስገብተው ወደማያውቁት ቦታ በመውሰድ ባዶ ቤት ውስጥ እንደዘጉባቸው አስረድተዋል።
የብቸና ፖሊስ በእገታ ወንጀሉ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉት 2 ግለሰቦች ላይ ምርመራውን አጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ገልጿል።
መረጃው የብቸና ከተማ አስ/ፖሊስ ነው።

#NEBE
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አድርጓል።
በዚህም ምክክር ወቅት ይፋ ያደረገው ለፓርቲዎች የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ መጠን ከላይ ተቀምጧል።
የገንዘብ ድጋፉ ከዚህ ቀደም በፀደቀው መመሪያ ላይ በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት የተከናወነ መሆኑን ቦርዱ አሳውቋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
" የነዳጅ እጥረት ለስራችን እንቅፋት እየሆነ ነው " -የባጃጅ አሽከርካሪዎች በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ስራቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተጓጎለ መሆኑን አመልክተዋል። ለአብነት ከቡሌሆራ፣ ሀዋሳ፣ ወልቂጤ፣ አሶሳ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ ፣ አሳስ፣ አዶላወዮ፣ ሻኪሶ፣ አሳሳ ከሚገኙ አሽከርካሪዎች የመጡ መልዕክቶች ነዳጅ ለማግኘት አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳለ…
" የቤኒዚን አቅርቦት ችግርን በጥቂት ቀናት ለመፍታት እየተሰራ ነው " - የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ባለስልጣን
በአዲስ አበባ የተፈጠረውን የቤንዚን አቅርቦት ችግር በጥቂት ቀናት ውስጥ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።
የኢትየጵያ ነዳጅ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ለችግሩ መከሰት የተለያዩ ምክንያቶችን አንስቷል ፦
1ኛ. የዩክሬን – ሩስያ ጦርነትን ተከትሎ የተፈጠረውን ዓለማቀፋዊ ችግር ፤
2ኛ. የጅቡቲ መንገድ መበላሸቱና ከጅቡቲ አዲስ አበባ ከ2 ቀን እስከ 2 ቀን ተኩል ይወስድ የነበረው መንገድ አሁን 4 ቀን ድረስ በመውሰዱ መዘግየት መፈጠሩ ነው።
የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ባለስልጣን ከሎጂስቲክስና ከዓለማቀፋዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የተከሰተውን ችግር ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አሳውቋል።
ከባለፈው አርብ ጀምሮ 6 ሚሊየን ሊትር ቤንዚን ከጅቡቲ በመጓጓዝ ላይ ነው ያለው ባለስልጣኑ እስከመጭው #አርብ ድረድ ችግሩ ሙሉ በሙሉ ይፈታል ብሏል።
በጊዜያዊነት ችግሩን ለመቅረፍ ከመንግስት ቋት ቤንዚን እየቀረበ ነው ሲልም አሳውቋል።
ችግሩ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሌሎች ከተሞችም እንዳለ የተገለፀ ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ ቀጥሎ ለሁሉም ከተሞች መፍትሄ ይሰጣል መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከሀዋሳ ፣ ቡሌሆራ ፣ ሻሸመኔ፣ ቢሾፍቱ፣ አሶሳ ... በሌሎችም በርካታ ከተሞች የነዳጅ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ተፅእኖ እሳያደረ መሆኑን በተለይም ነዳጅ ለማግኘት ከለሊት ጀምሮ ተሰልፎ መጠበቅ ግድ እንደሚል መጠቆሙ ይታወሳል።
ሁኔታ በርካቶችን ከስራ እዲስተጓጎሉና ቀናቸውን ነዳጅ ለመቅዳት በመሰለፍ እንዲያሳልፉ እያደረጋቸው መሆኑ መገለፁ አይዘነጋም።

" ምዕራቡ ዓለም ወደ ድሀ አገራት የሚልከውን እርዳታ ወደ አውሮፓ ማዞሩን ያቁም " -የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት
የዩክሬን ስደተኞችን ለመርዳት የሚጣደፈው ምዕራቡ ዓለም ወደ ድሀ አገራት የሚልከውን እርዳታ ወደ አውሮፓ ማዞሩን እንዲያቆም የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት ጠየቀ።
የኖርዌይ የስደተኞች ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ያን ኢግላንድ " ዩክሬንን እርዱ ነገር ግን በሌላው የዓለም ክፍል ያለውን ቀውስም አትዘንጉ " ሲሉ ጠይቀዋል።
ሃላፊው ምዕራባውያን በጎ ፈቃደኞችና ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የዩክሬን ስደተኞችን ለመርዳት የሚያደርጉት ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው ለዩክሬን የተጠየቀው 1.7 ቢሊዮን ዶላር በቀናት ውስጥ ሲደርስ ለየመንም እንዲሰጥ የጠየቅነው ገንዘብ እንዲህ በፍጥነት ቢደረሰ ምንኛ ደስ ባለን ነበር ብለዋል።
ኢግላንድ እንዳሉት ፤ ለየመን እርዳታ ከተጠየቀው 4.2 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ የተገኘው ለዩክሬን ከተፈቀደው ያነሰ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ነበር ብለዋል።
የዩክሬን ጦርነት ሳህል አካባቢ ለሚኖሩ ሀገራት መጥፎ ዜና መሆኑን የገለጹት ኢገላንድ ዛሬ በነዚህ አካባቢዎች የምግብ እና የነዳጅ ዋጋ እንዲንር ማድረጉንም ተናግረዋል።
አንዳንድ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ለድሀ ሀገራት ይለግሱ የነበረውን እርዳታ ወደአውሮፓ ማዞራቸው ችግሩ ይበልጥ እንዲባባስ አድርጓል ብለዋል።
ኢግላንድ በአውሮጳ በተለይም በዩክሬን የሚፈለገውን እርዳታ ከመስጠት ጎን ለጎን የሌሎች ሀገራትን የእርዳታ ጥያቄዎችንም በእኩል ሁኔታ ማስተናገድ ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸውን AFPን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

#Oxfam " ኦክስፋም " ከአፍሪካ ቀንድ አስከፊ ድርቅ ጋር በተያያዘ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ኦክስፋም ፥ በአፍሪቃ ቀንድ በተከሰተው አስከፊ ድርቅ ለረሐብ ለተጋለጠው ሕዝብ መርጃ የሚዉል ገንዘብ ካልተገኘ ከፍተኛ ሰብአዊ ድቀት ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል። 👉ኢትዮጵያን፣ 👉 ሶማሊያን 👉 ኬንያን በመታዉ ድርቅ 13 ሚሊዮን ሕዝብ ለረሐብ መጋለጡን WFP ካስታወቀ 2 ወር ሊሞላ ነው። ድርጅቱ እንዳስታወቀዉ…
ለማስታወስ ...
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ፦
👉 በኢትዮጵያ 🇪🇹
👉 በሶማሊያ 🇸🇴
👉 በኬንያ 🇰🇪 ከተከሰተው ድርቅ ጋር በተያያዘ 13 ሚሊዮን ህዝብ ለከፋ ችግር መጋለጡን ከገለፀ ሁለት ወር ሊሞላው ነው።
ተመድ ለረሃብ ለተጋለጠዉ ሕዝብ መርጃ የሚዉል የምግብ እህል መግዢያ ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ዓለም አቀፉን ማህብረሰብ ተማፅኖ ነበር።
ነገር ግን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በ ' ዩክሬን ' ጦርነት ላይ ሙሉ ትኩረቱን ስላደረገ ላቀረበው ጥያቄ ተገቢ መልስ አላገኘም።
ከቀናት በፊት በወጣው መረጃ ማግኘት የቻለው 3 በመቶ ብቻ ነው።
በተለይም ደግሞ በጎረቤታችን ሶማሊያ ለረሃብ ለተጋለጠው 4.5 ሚሊዮን ህዝብ መርጃ ይሆን ዘንድ የተጠየቀው 1.46 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን እስካሁን የተገኘው 3 በመቶ ብቻ ነው።

#Update ዛሬ የአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የዉጪ ግንኙነት ኮሚቴ ኢትዮጵያን በሚመለከተዉ S.3199 በተባለዉ ረቂቅ ሕግ ላይ ይነጋገራል። በ2021 ላይ የተረቀቀዉ ሕግ የኢትዮጵያን ሠላም እና ዴሞክራሲን ለመደገፍ (ለማበረታት) ያለመ እንደሆነ አርቃቂዎቹ አስታዉቀዋል። ይህ S.3199 ረቂቅ ሕግ ከዚህ ቀደም ለአሜሪካ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት ከቀረበዉና H.R.6600 በሚል መለያ ከሚታወቀዉ…
#Update
በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ሮበርት ሜንዴዝ የቀረበው S.3199 ረቂቅ ህግ ዛሬ ማለፉ ተሰምቷል።
ኮሚቴው ፤ "በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማበረታታ " በሚል ርዕስ የቀረበው S.3199 ላይ ተወያይቶ ማማሻያ ካደረገ በኃላ ነው ማሳለፉ የታወቀው።
የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ ተመልክቶ ያሳለፈው S.3199 ረቂቅ ህግ በጠቅላላ የምክር ቤቱ አባላት እንዲፀድቅ የሚመራ ሲሆን ህግ ሆኖ ለመውጣት የህግ አውጪው ምክር ቤት ድምፅ እና የፕሬዜዳንቱን ፊርማ ማግኘት አለበት።
S.3199 ረቂቅ ህግ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ላይ ሲሆን ከዚህ ረቂቅ ጎን ለጎንም HR.6600 የተሰኘ " በኢትዮጵያ መረጋጋት፣ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማስፈን " በሚል ርዕስ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ በህግ አውጪው ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ እንዲያየው መላኩን ቪኦኤ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን ሊፀድቁ በመንገድ ላይ ናቸው የተባሉት S.3199 እና HR.6600 ፤ ኢትዮጵያን ከሌሎች አገራት ጋር የሚኖራትን የጸጥታ፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ግንኙነት በሌሎች ኃይሎች በጎ ፈቃድ እንዲንጠለጠል እና ራሷን የማትከላከል ሽባ አገር የሚያደርጋት በመሆኑ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ረቂቅ ህጎቹ እንዳይፀድቁ ከፍተኛ ዘመቻ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል።

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
#Sport ግብፅ እና ሴኔጋል ዳግም ተገናኝተዋል። ግብፅ እና ሴኔጋል ለኳታሩ የአለም ዋንጫ ለማለፍ የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ በግብፅ መዲና ካይሮ እያደረጉ ይገኛሉ። በደርሶ መልስ (መጋቢት 15 እና 19) ከሚደረገው ጨዋታ በኃላ ግብፅ ወይም ሴኔጋል / ሞሀመድ ሳላህ ወይም ሳድዮ ማኔን በ2022 ዓለም ዋንጫው የምንመለከታቸው ይሆናል። ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ላይ እልህ አስጨራሽ…
ሴኔጋል ለ2022 ዓለም ዋንጫ አለፈች።
የአፍሪካ ዋንጫ ባለድሏ ሴኔጋል በፍፃሜው ያገኘቻትን ግብፅን በድጋሚ በመለያ ምት በማሸነፍ ለኳታሩ 2022 ዓለም ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች።
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ሴኔጋል ካይሮ ላይ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፋ ነበር።
ዛሬ በሀገሯ ላይ በተካሄደው የመልስ ጨዋታ አንድ ጎል አስቆጥራ በመደበኛው እና ተጨማሪው ሰላሳ ደቂቃ በድምር ውጤት 1-1 ከተጠናቀቀ በኋላ ጨዋታው በመለያያ የፍፁም ቅጣት ምት በሴኔጋል 3-1 ውጤት ተጠናቋል።
ሴኔጋላዊው ኮከብ ማኔ በዓለም ዋንጫው ላይ የሚታይ ሲሆን ግብፃዊው ኮከብ ሳላህ በዓለም ዋንጫው ድንቅ ብቃቱን የሚያሳይበት ዕድሉ መክኗል።
@tikvahethsport

#ETHIOPIA ከነገ ጀምሮ ዜጎቻችንን የመመለስ ስራ ይጀመራል ተብሏል። ለረጅም ጊዜያት ሲጠበቅ የነበረው በሳዑዲ አረቢያ በከፋ ስቃይ ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ ነገ እንደሚጀመር ተገልጿል። የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ አረቢያ ሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ወደ አገራቸው የመመለስ ሥራ እንደሚጀመር አስታውቋል። ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን…
#ETHIOPIA
ኢትዮጵያ ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎቿን መቀበል ጀምራለች።
በዛሬው ዕለትም 157 ህፃናት እና 314 ሴቶች በድምሩ 498 ዜጎች በሰላም ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
በቀጣይ ከ7 እስከ 11 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎችን ለመመለስ እቅድ ተይዟል።
Via @tikvahethmagazine