#ETHIOPIA😷
የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 4,805
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 374
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 8
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 825
• ፅኑ ታማሚዎች 👉 364
ዛሬ ፣ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ አጠቃላይ 1,505 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 32 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
@tikvahethiopia

#ይበቃል
ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ያሉ ዜጎቻችን ፍትህን እንዲያገኙ የሚጠይቅ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ተመልክተናል።
ዘመቻው ሳዑዲ ያሉ ዜጎቻችን እምነበረድ ላይ ለብሰው የሚተኙትን ጥቁር ፌስታል በመልበስ አጋርነት የሚገለፅበት ነው።
ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በርካታ ዜጎቻችን እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል።
የሳኡዲ አረቢያ መንግስት መሰረታዊ የእስረኛ አያያዝ ህግን እንዲተገብር፣ ፍትሃዊ የሆነ ምላሽም እንዲሰጥ የሚጠየቅበት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ነው እየተካሄደ ያለው።
#ይበቃል
#ጥቁር_ፌስታል
#الحرية_للسجناء_الاثيوبيين
#العدالة_للسجناء_الاثيوبيين
Credit : Ali Amin & Social Media

" መኪናው በግምት 200 ሜትር ከሚሆን ገደል ውስጥ ነው የገባው። ... በደረሰው አደጋ 20 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 6 ሰዎች ቆስለዋል " - ኢንስፔክተር ሲሳይ አበራው
ከባሕር ዳር ከተማ ወደ ሰቆጣ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
ለግዳጅ ከባሕር ዳር መነሻውን ያደረገው የሕዝብ ማመለሻ አውቶብስ በደረሰበት አደጋ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ፣ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉም ታውቋል፡፡
የድሃና ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሲሳይ አበራው ለአሚኮ በሰጡት ቃል ፥ ለግዳጅ ከባሕር ዳር የወጣው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በመንገድ ላይ ያገኛቸውን ሰዎች ጭኖ ሲጓዝ አደጋው እንደደረሰ ተናግረዋል።
አደጋው የደረሰው መለያ ቁጥሩ 11300፣ የጎን ቁጥሩ 2527 የሆነ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ጉዳቱ የደረሰው ከአምደወርቅ ወጣ ብሎ አቦ መገጠንያ መንገድ በምትባል ሥፍራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በግምት 200 ሜትር ከሚሆን ገደል ውስጥ መግባቱንም ተናግረዋል፡፡ በደረሰው አደጋም 20 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 6 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ነው የተናገሩት፡፡
ከአደጋው ከተረፉ ሰዎች ጋር ቆይታ እንዳደረጉ የተናገሩት ኃላፊው ከእብናት ወደ አምደ ወርቅ ሲጓዝ ብዙ ሰው እንደነበርና ከአምደወርቅ ሲያልፉ ግን ሰው ያልነበረባቸው ወንበሮች እንደነበሩ ነግረውኛል ነው ያሉት፡፡
ለአደጋው ምክንያት ፍጥነት እና የመንገዱ መጎዳት ሳይሆን እንዳልቀረም ተናግረዋል፡፡ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ፦ አሚኮ
@tikvahethiopoa

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ12ኛ ክፍል ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናውን የሚወስዱበት ቀን ይፋ ተደረገ። በ2013 የጸጥታ ችግር በተከሰተባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ከጥር 24 እስከ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ፈተናው እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል። በሁለተኛ ዙር የሚሰጠውን ፈተና 58 ሺህ 936 ተማሪዎች እንደሚወስዱም የአገልግሎቱ ምክትል…
#የ12ኛ_ክፍል_ፈተና
ከመጪው ጥር 24 እስከ ጥር 27 የሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ይሰጣል።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያደረሰው ተፅእኖ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል።
በተለይም ወረርሽኙ ወደሀገር ከገባ በኃላ እና በትግራይ ክልል ጦርነት ከተነሳ በኃላ የዓመቱ መርሀግብር በእጅጉ ተናግቷል።
ከጥቂት ወራት በፊት ብሄራዊ ፈተና የወሰዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እስካሁን ውጤት ያልተነገራቸው ሲሆን በዚህም ያለትምህርት ወራትን ለማሳለፍ ተገደዋል።
እስካሁን የፈተናው ውጤት ይፋ የሚደረግበትም ቀን አልታወቀም።
በትግራይ ክልል ፈተና መቀመጥ የነበረባቸው ተማሪዎች በጦርነት ምክንያት ላለፉት ዓመታት በአግባቡ ለፈተና መቀመጥ አልቻሉም።
በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በፀጥታ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ከመጪው ጥር 24 እስከ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ለፈተና ይቀመጣሉ።
ይህ ፈተና ሁለተኛ ዙር ሲሆን 58 ሺ 936 ተማሪዎች ፈተናው ይወስዳሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

#Update ቅዱስ ሲኖዶስ የብፁዕ አቡነ ሚካኤል የኢሉባቡር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር ጥር 16/2014 ዓ.ም በታላቁ የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እንዲፈጸም ወሰነ። ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል። ብፁዕ አቡነ ሚካኤል በሀገረ ስብከታቸው ርዕሰ መንበረ ጵጵስና መቱ በአገልግሎት…
#Update
የብፁዕ አቡነ ሚካኤል የኢሉባቡር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ጥር 16/2014 ዓ.ም በታላቁ የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ይፈፀማል።
ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል።
ትላንት የብፁዕ አቡነ ሚካኤል የኢሉ አባ ቦራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሽኝት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም መከናወኑን ለማወቅ ተችሏል።
በሽኝት የጸሎት ሥነ ሥርዓቱ ላይም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የበላይ የአርሲና ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የሲዳማ ጌዴኦ አማሮና ቡርጅ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቤተሰቦቻየውና በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ተገኝተው እንደነበር ከኢኦተቤ ቴቪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ የኤልክትሪክ አውቶቡስን ስራ ላይ ለማዋል ፋይናንስ የማፈላለግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።
ቢሮው በውጭና ሀገር ውስጥ ከሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት ለአውቶቡስ ግዥ የሚውል ፋይናንስ የማፈላለግ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
የኤልክትሪክ አውቶቡሶች ሌሊት ቻርጅ አድርገው ቀኑን በሙሉ ያለምንም የጊዜ ብክነት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋሉ ያለው ቢሮው።
አውቶቡሶቹ የሙከራ ትግበራ የሚደረግባቸው በሸገር እና አንበሳ አውቶቡሶች ሲሆን ፥ ከሸጎሌ ዴፖ ቅርበት ያላቸው አራት ኮሪደሮች ልየታ መከናወኑም ተገልጿል።
የመጀመሪያው ኮሪደር ከአዲሱ ገበያ - ቄራ ሲሆን፥ ሁለተኛው ኮሪደር መነሻውን ዊንጌት አድርጎ መዳረሻው አየር ጤና ይሆናል።
እንዲሁም ሶስተኛው ኮሪደር ከለገሃር ተነስቶ መዳረሻው ድል በር እንዲሁም አራተኛው ኮሪደር ከአውቶቡስ ተራ - አስኮ ይሆናል፡፡
ከዴፖው ያላቸው ርቀት፣ ከBRT ኮሪደሮች ጋር ያላቸው ትስስር እና ገበያ አካባቢዎች መሆናቸው ለኮሪደሮች የሙከራ ትግበራ መመረጥ እንደመስፈርት ተቀምጧል፡፡
በቀጣይ በከተማዋ ሌሎች ተጨማሪ ኮሪደሮችን በማጥናት የተደራሽነት አድማሱን የማስፋት ስራ እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።

#BenishangulGumuz
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ዞኖች በፀጥታ ችግር ምክንያት ከ2 ዓመት በላይ ምንም አይነት የመብራት አገልግሎት አላገኙም።
የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መለሰ በየነ ለአሐዱ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፥ ባለፉት ዓመታት በመተከል እና ካማሽ ዞኖች በታጣቂዎች የተስተጓጎለው የመብራት አገልግሎት መፍትሔ ሳያገኝ እስካሁን ድረስ ዘልቋል ብለዋል፡፡
በዚህም ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት ተዳርጓል ፤ በተለይም በከተሞች አካባቢ በመብራት ኃይል ብቻ ስራቸውን የሚሰሩ ዜጎችን ለስራ አጥነት ተጋላጭ አድርጓቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።
ችግሩ መቼ ይፈተል በሚል ከቴሌቪዥን ጣቢያው ለቀረበላቸው ጥያቄ ፥ " በቀጣይ የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ሲስተካከል እግር በግር በመከተል ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመመለስ ይሰራል " ሲሉ መልሰዋል።
ምንጭ ፦ አሐዱ ቴሌቭዥን

ፕሬዝዳንት ካቦሬ በወታደሮች ታስረዋል።
የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት በሀገሪቱ ወታደሮች መታሰራቸው ተነግሯል።
ፕሬዝዳንት ሮች ካቦሬ የታሰሩት በአማጺ ወታደሮች ሲሆን፤ በሀገሪቱ መዲና ኡጋዱጉ ባለ አንድ ወታደራዊ ማዘዣ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል።
የቡርኪና ፋሶ መንግስት በትናንትናው ዕለት የወታደሮቹ እንቅስቃሴ መፈንቅለ መንግስት አለመሆኑን ገልጾ ነበር።
በቡርኪና ፋሶ ወታደሮች ውስጥ ጥያቄ እንዳነሱ የሚነገርላቸው አማጺ ወታደሮች አዛዦቻቸውን ጨምሮ መሪዎችን ገድለዋል።
ይሄንን ተከትሎም የቡርኪና ፋሶ መንግስት ከትናንት ምሽት ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ጨምሮ የሰዓት ገደብ ጥሎም ነበር፡፡
በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት መፈንቅለ መንግስት ማድረግ የተለመደ ሲሆን አሁን ደግሞ ተራው የቡርኪና ፋሶ ሆኗል።
የማሊ ወታደሮች በኮለኔል አስሚ ጎይታ የተመራ መፈንቅለ መንግስት በማድረግ አሁን ላይ የሽግግር ጊዜያዊ መንግስት መስርተው ማሊን በማስተዳደር ላይ ይገኛል።
ኢኳቶሪያል ጊኒም መፈንቅለ መንግስት በማድረግ የሀገሪቱን ሲቪል አስተዳድር በማስወገድ ወታደረዊ መንግስት የመሰረተ ሲሆን እነዚህ ወታደራዊ መሪዎች ስልጣናቸውን በህዝብ ለተመረጡ መንግስታት እንዲያስረክቡ ኢኮዋስን ጨምሮ አፍሪካ ህብረት እና ሌሎች ተቋማት በማሳሰብ ላይ ናቸው።
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ / ሮይተርስ