TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Kenya #USA

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከኬንያ ጋር ተነጋገሩ።

ትላንትና የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ
መወያየታቸው ገልፀዋል።

ብሊንከን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ ፥ “በኢትዮጵያ እየተባባሰ በመጣው ወታደራዊ ግጭቶች አሜሪካን እንደሚያሳስባት ለፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አሳውቄያለሁ” ብለዋል።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ግጭት የምስራቅ አፍሪከ ቀጠናን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በግጭቱ እየተሳፉ ያሉ ሁሉም አካላት የሀገሪቱን ሉአላዊነት እና አንድነት ባስጠበቀ መልኩ ወደ ሰላም ለመምጣት ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስዱም ጥሪ አቅርበዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኒድ ፕራይስ ውይይቱን አመስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ በውይይቱ ወቅት በግጭቱ የሚሳተፉ አካላት በአፋጣኝ ወደ ድርድር እንዲመጡ አሜሪካ ጥሪ ማቅረቧን አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ኬንያታ እና አንቶኒ ብሊንከን በግጭቱ ለተጎዱ ማህበረሰቦች ያልተቋረጠ የሰብአዊ ድጋ አቅርቦት አስፈላጊነት ላይ መምከራቸውን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲደረግ አሜሪካና ኬንያ ድጋፍ ለማድረግ መስማማታቸውንም ቃል አቀባዩ ማስታወቃቸውን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጥቂት ቀናቶች በፊት ኬንያ መጥተው ስለኢትዮጵያ እና ሌሎችም ጉዳዮች ከኬንያ ጋር ውይይት አድርገው መመለሳቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

አዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታዉ ጠመንጃ ያዥ አካባቢ የተለያዩ መሣሪያዎች ቱቦ ዉስጥ ተጥለው መገኘታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ቦታዉ ጠመንጃ ያዥ አካባቢ ቱቦ ውስጥ ተጥለው የተገኙት የተለያዩ መሣሪያዎች ፦

- ታጣፊ ከላሽ ብዛት 1 የውግ ቁጥር 24096 የጥይት ብዛት 114 እና 4 ካዝና፤
- ማካሮፍ ሽጉጥ ብዛት 1 የውግ ቁጥሩ የማይታይ የጥይት ብዛት 7 ፍሬ፤
- አንድ የአፋር ጊሌ የሚመስል ሳንጃ ናቸው።

የጦር መሳሪያዎቹ ላንቻ ለፖሊስ ጣቢያ ገቢ መደረጋቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ኅብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት እንዲቃኝ እና የተለየ ነገር ሲመለከት ለፖሊስ እንዲያመለክት የአ/አ ፖሊስ አሳስቧል።

Credit : ኢፕድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲን አስጠነቀቀች። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እንዲሁም ድርጅቶች የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት መቀጠላቸውን የኢትዮጵያ መንግስት አስታውቋል። ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ ተከባለች የሚል መረጃን ያሰራጩ እንደነበር ያስታወሰው መንግስት አሁን ደግሞ የሽብር ጥቃት ይፈፀማል የሚል ሀሰት መቀጠሉን ገልጿል። ኤምባሲው እና የአሜሪካ መንግስት የሀሰት መረጃዎችን ከማስተላለፍ እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ…
የኤሜሪካ ኤምባሲ ?

እዚህ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አሁንም የአሜሪካ ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መወትወቱን ቀጥሎበታል።

ትላንትም ከሰሞኑ ሲያስተላልፋቸው የነበረውን መልዕክት ደግሟል።

ኤምባሲው የአሜሪካ ዜጎች ሀገር ለቀው እንዲወጡ እየወተወተ ያለው የፀጥታ ሁኔታው እየተባባሰ ነው በሚል ነው።

ከትላንት በስቲያ የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት የአሜሪካ ኤምባሲ እና መንግስት በኢትዮጵያ ጉዳይ ሀሰተኛ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ በጥብቅ አስጠንቅቆ እንደነበር አይዘነጋም።

በተጨማሪ ደግሞ ይህ ማስጠቀቂያ ከመሰጠቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፥ አንዳንድ ሀገራት ዜጎቻቸውን ከኢትዮጵያ እንዲወጡ በተደጋጋሚ ቢናገሩም ኤምባሲዎቻቸውን ጨምሮ ዜጎቻቸው አሁንም ድረስ በሰላም እየሰሩ መሆኑን ተናግረው ነበር።

የአሜሪካ ኤምባሲም ሆነ ሌሎች ኤምባሲዎች ደህንነት አልተሰማንም ፤ ለሰራተኞቻችንም ምቹ ሁኔታ የለም ካሉ በየትኛውም ጊዜ መውጣት መብታቸው እንደሆነና 24 ሰዓት በሩ ክፍት መሆኑን ዶ/ር ለገሰ ቱሉ አሳውቀው ነበር።

ነገር ግን ኢትዮጵያ ሰላሟን፣ ደህንነቷን ይዛ እንደምትቀጥል እና የኤምባሲዎቹ መኖር የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት እንደማያረጋግጥ አስገንዝበው ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኤሜሪካ ኤምባሲ ? እዚህ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አሁንም የአሜሪካ ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መወትወቱን ቀጥሎበታል። ትላንትም ከሰሞኑ ሲያስተላልፋቸው የነበረውን መልዕክት ደግሟል። ኤምባሲው የአሜሪካ ዜጎች ሀገር ለቀው እንዲወጡ እየወተወተ ያለው የፀጥታ ሁኔታው እየተባባሰ ነው በሚል ነው። ከትላንት በስቲያ የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት የአሜሪካ ኤምባሲ እና መንግስት…
" 24 ሰዓት በሩ ክፍት ነው "

የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ (15/03/2014 ዓ/ም) ፦

" የትኛውም ሀገር የትኛውም አካባቢ ያለ ኤምባሲ በአንድ ሀገር ላይ ደህንነት አልተሰማኝም ዜጎቼ በጥሩ ሁኔታ ላይ ሊሆኑ አይችሉም ባሉበት በማንኛውም ጊዜ መውጣት መብታቸው ነው።

ስለዚህ የአሜሪካ ኤምባሲም ሆነ ሌሎች ኤምባሲዎች ደህንነት አልተሰማንም ካሉ ፤ ለሰራተኞቻቸው ምቹ ሁኔታ የለም ካሉ በየትኛውም ጊዜ መውጣት መብታቸው ነው ስለዚህ 24 ሰዓት በሩ ክፍት ነው የሚከለክል የለም።

ኢትዮጵያ ግን ሰላሟን፣ ደህንነቷን ይዛ ትቀጥላለች። የኤምባሲዎቹ መኖር የኢትዮጵያን ደህንነት አያረጋግጥም።

ኢትዮጵያውያን ደህንነታቸውን ፣ሰላማቸውን፣ አንድነታቸው የሚያረጋግጡት ኤምባሲዎቹ በመኖራቸው አይደለም። በራሳቸው ጥረትና በክንዳቸው ብቻ እንደሆነ መታወቅ አለበት። "

@tikvahethiopia
" ቱርክ ግጭቱን ለማስቆም እና በውይይት ለመፍታት ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት " - ሜቭሉት ካቩሶግሉ

በትላንትናው ዕለት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አናዱሉ ዘግቧል።

ውይይቱ በኢትዮጵያ ስላለው ውቅታዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ እንደነበር የቱርክ መንግስት የዜና ወኪል የሆነው አናዶሉ ገልጿል።

ለመገናኛ ብዙሃን የመናገር ገደብ በመኖሩ ሳቢያ አናዶሉ ማንነታቸው ያልተገለፁ የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ካቩስግሉ ለአቶ ደመቀ መኮንን ፥ ቱርክ በኢትዮጵያ ውስጥ እየቀጠለ ያለውን ግጭት ለማስቆምና ችግሩን በውይይት ለመፍታት ማንኛውንም ድጋፍ ለማድርግ ዝግጁ መሆኗን ገልፀውላቸዋል።

ውይይቱን በተመለከተ እስካሁን በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የተሰጠ መረጃ የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰን ጨምሮ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የሰራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ወደ ግንባር ለመዝመት ውሳኔ አሳለፉ። " በግንባር ተገኝቼ ጦሩን እመራለሁ " ብለው ወደ ግንባር ያቀኑት የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብይ አህመድ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የሰራ አስፈጻሚ…
#BenishangulGumuz

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ግንባር ዘምተው ጦሩን እንደሚመሩ በይፋ ካሳወቁ በኃላ " እኛም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደ ጦር ግንባር እንዘምታለን " ያሉት ከፍተኛ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለስልጣናት መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙ ታውቋል።

ከትላንት አርብ አንስቶ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጠናት መሠረታዊ የውትድርና ስልጠና እየወሰዱ ሲሆን ስልጠናው ዛሬ ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው የክልሉ መንግስት ያስታወቀው።

ባለስልጣናቱ ዛሬ አካላዊ የስፓርት እንቅስቃሴ ጨምሮ ፣ መሠረታዊ የቦታ አያያዝ፣ ዒላማና የተኩስ ልምምድ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በስልጠናው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ባለስልጣናት ፥ " ከስልጠናው በኋላ ህወሓትና ተላላኪዎቹ አገራችን ለማፍረስ የከፈቱትን ጦርነት ለመቀልበስ በግንባር ተገኝተን ፊት ለፊት ጦርነቱን ለመምራት ቁርጠኛ ነን " ሲሉ ተናግረዋል።

ለ ክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እየተሰጠ የሚገኘው መሠረታዊ የውትድርና ስልጠና ለቀጣዮቹ 5 ቀናት እንደሚቀጥልም ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በሁለት ቦታዎች በተደረገ ፍተሻ የጦር መሳሪያ እና ወታደራዊ ቁሳቁስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

ፖሊስ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፖፑላሬ ተብሎ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ባደረገው ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ወታደራዊ ቁሳቁሳችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተገልጿል።

በቁጥጥር ስር የዋለው 1 ክላሽ ከ186 መሰል ጥይት ጋር፣ 3 የጥይት ካዝና፣ 1 የዲሽቃ ጥይት፣ 18 አሮጌው የመከላከያ ልብስ፣ 19 የመከላከያ ቦኔት፣ 1 የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ልብስ፣ 1 የአፋር ጊሌ፣ 3 የሰላም ማስከበር ልብስ፣ 4 የመከላከያ አዲሱ ልብስ፣ 3 የዝናብ ልብስ፣ 5 የመከላከያ ቀበቶ፣ 2 የመጀመሪያ ህክምና መስጫ ነው።

በተጨማሪም በርካታ የወታደር ባጅ፣ የካናቢስ እፅ፣ 10 የተለያየ ቼክ እና 2 ማህተም በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ጨው በረንዳ አካባቢ በሚገኝ ጅንአድ ድርጅት ውስጥ በፖሊስ በተደረገ ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

በፍተሻ የተገኘው የጦር መሳሪያ 1 ክላሽ፣ 7 ኤስኬስ፣ 1 ፒፒኤስ፣ 9 ዲሞፍተር፣ 3 ቤልጂግ፣ 14 ምንሽር፣ 1ራሽ፣ 2360 የክላሽ ጥይት፣ 72 የሽጉጥ ፣ ጥይት እና 3 ሳንጃ ነው።

መረጃው ከኢፕድ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#Mekelle

በዚህ ሳምንት ምግብና ሌሎች ህይወት አድን የሆኑ ሰብዓዊ አቅርቦቶችን የጫኑ 79 ተሽከርካሪዎች መቐለ መግባታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ዛሬ አሳውቋል።

ሌሎችም የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በጉዞ ላይ መሆናቸውን ድርጅቱ ገልጿል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ምግቡን ትግራይ ውስጥ ያሉ ድጋፍ የሚፈልጉ የማህበረሰብ ክፍሎች እጅ እንዲገባ እና የ5.2 ሚሊዮን ሰዎችን ፍላጎት ሊያሟሉ የሚችሉ ኮንቮይዎች በየቀኑ መግባታቸውን ለማረጋገጥ ያለማቋረጥ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia