TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ወልቂጤ

- " በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። ቤቶች ተቃጥለዋል " - የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር

- " በቦታው አድማ የመበተን ሥራ እየተሰራ ነው " - የጉራጌ ዞን ፓሊስ ኮሚሽን

- " ግጭቱ እንዲባባስ በሚፈልጉ አካላት ንብረት ወድሟል፣ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል " - የጉራጌ ዞን ኮማንድ ፓስት

አዲስ በተዋቀረው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማና ቀቤና ልዩ ወረዳ መከከል በተቀሰቀሰ ግጭት በንጹሐን ላይ አካላዊ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ነዋሪዎቹ በገለጹት መሠረት፣ ከጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት በንጹሐን ላይ ጉዳት ደርሷል፣ ቤት ተቃጥሏል ብለዋል።

ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ፣ እንደቆሰሉ፣ ተኩስ እንደቆመና እንዳልቆመ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረቡላቸው አንድ የአካባቢው ነዋሪ፣ " አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል  በጥይት ተመቶ ሞቷል። እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት 25 በላይ ሲቭል ሰዎች ቆስለዋል። ከትላንት 7 ጀምሮ ዛሬ ጥዋት 2 ሰዓት ድረስ ተኩስ ነበር አሁን ቆማል " ብለዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸውና ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣን፣ " በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። ቤቶች ተቃጥለዋል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ግጭቱ በቀቤና ልዩ ወረዳና በወልቂጤ ከተማ የወሰን ይገባኛል ጥያቄን መሠረት በማድረጉ ከዚህ በፊትም አለመረጋጋት እንደነበር ገልጸው፣ አሁንም እንዳይባባስ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በጥምረት እየሰሩ ነው ብለዋል።

ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የጉራጌ ዞን ፓሊስ ኮሚሽን ዋና ኢኒስፔክተር ገና በበኩላቹው፣ " በቦታው አድማ የመበተን ሥራ እየተሰራ ነው " ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ኮማንድ ፖስት ጥቅምት 03 ቀን 2016 ዓ.ም ጉዳያ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ፣ " በቀን 02 ቀን 2016 ዓ.ም በወልቂጤ ከተማ የተቀሰቀሰው አመጽ እንዲበርድ የጸጥታ ኃይላት በሆደ ሰፊነት ግጭቱ እንዲበርድ እና የሚደርሰው ቁሳዊና ሰብዓዊ ጉዳት ለመቀነስ በኃላፊነት ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል " ብሏል።

አክሎም ፣ " ይህን እንጅ ግጭቱ እንዲባባስ በሚፈልጉ አካላት ንብረት ወድሟል፣ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል " ሲል አስታውቋል።

" በዜጎች ላይ የሚደርሰው አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ለመቀነስ የዞኑ  ኮማንድ የሰዓት እላፊ ገደብ እንዲጣል ወስኗል " ያለው መግለጫው፣  " በመሆኑም ከዛሬ ጥቅምት 03/2016 ጀምሮ በተሽከርካሪዎች እና በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ የሰዓት ገደብ ተጥሏል " ሲል አስገንዝቧል።

" በዚህ መሰረት የትኛውም ተሽከርካሪ ማለትም ፦
-  ሞተር ሳይክል፣
- ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ)፣
- አነስተኛም ሆነ ከፍተኛ የህዝብ አመላላሽ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ሰዎች ላይ ከ11:00 እስከ ጠዋት 1:00 ድረስ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል " ብሏል።

መረጃው በአዲስ አበባ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia