የትግራይ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ ሆነ!
ዛሬ የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን ጳጉሜ 4/2012 ዓ/ም የተደረገውን 6ኛው ክልላዊ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ አድርጓል።
ከአጠቃላዩ 190 የክልሉ ምክር ቤት ወንበሮች 189ኙ በህወሓት የተያዙ ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ በምክር ቤቱ አንድ (1) ወንበር አግኝቷል፡፡
ባይቶና በአንድ ወንበር ምክር ቤት የገባ ፓርቲ ሆኗል፡፡
ምንጭ፦ ሚሊዮን ኃይለስላሴ (DW)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

September 14, 2020
#COVID19Ethiopia
መስከረም 4/2013 ዓ/ም
የተደረገ ላብራቶሪ ምርመራ - 9,256
በቫይረሱ የተያዙ - 485
ህይወታቸው ያለፈ - 9
ያገገሙ - 350
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስከረም 4/2013 ዓ/ም
የተደረገ ላብራቶሪ ምርመራ - 9,256
በቫይረሱ የተያዙ - 485
ህይወታቸው ያለፈ - 9
ያገገሙ - 350
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
September 14, 2020
#DrAbiyAhmed
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በነገው ዕለት ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጋር እንደሚወያዩ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በደረ ገፁ አስነብቧል።
ነገ ረፋዱን ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ለዚሁ ስብሰባ ፤ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በዛሬው ዕለት ጥሪ ተደርጎላቸዋል።
የነገው ውይይት ባለፈው ሐምሌ ወር ከተደረገው ተመሳሳይ ስብሰባ ወዲህ የነበሩ ሂደቶች የሚገመገሙበት እንደሆነ ተገልጿል።

TIKVAH-ETHIOPIA
አዲሱ የብር ኖት 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ታትሟል! አዲሱ የብር ኖት 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ታትሞ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ለስርጭት ዘግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ አዲሱን የብር ኖት በማስመልከት ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም አሁን ላይ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ታትሞ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የብር ኖት ቅያሬውን ለማከናወን…
ዛሬ ማምሻውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ከሰጡት መግለጫ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች ፦
- የብር ለውጡን ተከትሎ ህገ ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር ዝግጅት ተደርጓል።
- በተለያዩ ጎረቤት አገራት የኢትዮጵያ የብር ኖቶች ክምችት አለ ፤ ለብር ለውጡ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ቁጥጥር ይደረጋል። ለዚህም ከጸጥታና የደህንነት አካላት ጋር በመነጋገር የመቆጣጠርና የማምከን ተግባራት ይከናወናል።
- በድንበር አካባቢ የሚገኙ ባንኮች በብር ለውጡ ለህገ ወጥ ድርጊቶች እንዳይጋለጡ ጥብቅ ክትትል ይደረጋል።
- የብር ቅያሬውን ለማከናወን ማንኛውም ግለሰብ የብር ኖቶቹን ራሱ በባንክ መቀየር ሲገባው በሌላ ግለሰብ በውክልና መቀየር አይችልም።
- በ3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወጪ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን የብር ኖት ታትሟል፤ የመጠባበቂያ ክምችት እንዲኖር ተጨማሪ የብር ኖቶች እየታተሙ ነው።
- ባለፉት ጥቂት ወራት አዳዲሶቹን የብር ኖቶች ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የማጓጓዝ ስራ ተሰርቷል። አሮጌውን ገንዘብ መቀየር የሚያስችል በቂ ክምችት አለ።
- አዳዲሶቹ የብር ኖቶች እንዳይበላሹ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፤ ይሄም ኢትዮጵያ የተበላሸ ገንዘብ ለመተካት የምታወጣውን ብዙ ወጪ ያስቀራል።
- ህገ ወጥ ተግባራት የሚፈጽሙ ባንኮች እንደ ጥፋታቸው መጠን እና ልክ ቅጣት ይጣልባቸዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#ATTENTION
በኢትዮጵያ እና በሌሎች የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊጥል እንደሚችል የምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት የልህቀት ማዕከል አስጠነቀቀ፡፡
ማዕከሉ በተለይም በመካከለኛው እና ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊጥል ይችላል ብሏል።
በእነዚህ ሀገራት የሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋዎችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ የልህቀት ማዕከሉ አስጠንቅቋል፡፡
የዝናብ ትንበያው ከዛሬ ጀምሮ በሚቀጠሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የሚጠበቅ ሲሆን በምዕራብ እና መካከለኛው ኢትዮጵያ ጥቂት ቦታዎች ከ 200 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ ዝናብ ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እንዲሁም በጎረቤት ሀገራት ደቡብ-ምዕራብ ሱዳን ፣ ከሰሜን-ምዕራብ እስከ ደቡብ-ምዕራብ ደቡብ ሱዳን፣ በምዕራብ እና፣ ሰሜን-ምስራቅ ሶማሊያ እንዲሁም በሰሜን-ምዕራብ ዩጋንዳ እና ምዕራብ ኬንያ ከ 50 እስከ 200 ሚሊ ሜትር የሆነ መካከለኛ ዝናብ ይኖራል፡፡
በሰሜን ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ፣ በማዕከላዊ ሱዳን ፣ በሰሜን ምዕራብ ኤርትራ ፣ በምዕራብ እና ማዕከላዊ ደቡብ ሱዳን፣ በሰሜን እና በደቡብ ሶማሊያ ፣ በጅቡቲ የባህር ዳርቻዎች ፣ በማዕከላዊ እና በምስራቅ ዩጋንዳ አንዳንድ አካባቢዎች ከ50 ሚሊ ሜትር በታች የሆነ ቀላል ዝናብ ይኖራል ተብሏል፡፡
(ኢዜአ)

September 15, 2020
ጥቅምት እና ህዳር ውስጥ ብዙ ሰው በኮቪድ-19 ይሞታል ተብሎ ተሰግቷል!
በመጪዎቹ ጥቅምት እና ህዳር ወራት በኮቪድ-19 ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ይጨምራል ብለው እንደሚገምቱ የዓለም የጤና ድርጅት (WHO) የአውሮፓ ቅርንጫፍ ኃላፊ መናገራቸውን ቪኦኤ ዘገበ።
ሃንስ ክሉገ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት ቃል "እየከፋ ነው የሚሄደው፣ ጥቅምት እና ኅዳር ውስጥ ብዙ ሰው ይሞታል ብለን እንሰጋለን” ብለዋል።
የኮቪድ-19 ክትባት ቢገኝ እንኳን ዓለምቀፉ ወረርሽኝ አበቃ ማለት እንደማይሆንም አሳስበዋል።
"የሚገኘው ክትባት ለሁሉም ህዝብ የሚሆን ወይም ሁሉንም የሚረዳ እንደሚሆን አናውቅም። የተወሰነ የህዝብ ክፍል ቫይረሱን እንዲከላከል እንደሚረዳ ለሌላው ደግሞ ምንም ላይጠቅም እንደሚችል ከወዲሁ ፍንጮች እያገኘን ነው ፤ ያ ከሆነ ደግሞ የተለያዩ የክትባት ዓይነቶችን ማዘዝ ሊኖርብን ነው፤ እንደዚያ ሲሆን የሚኖረውን የማጓጓዣ እና የማከፋፈል መከራ ማየት ነው" ብለዋል።

ህፃናትን አስገድደው ደፍረዋል የተባሉ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ!
በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጃዊ ወረዳና ደብረ ማርቆስ ከተማ ህፃናትን አስገድደው ደፍረዋል ተብለው የተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች እስከ 25 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ።
መረጃ #1 ፦
ይሉሃል እንዳለው የተባለ ግለሰብ በጃዊ ወረዳ የ11 ዓመት እድሜ ያላትን ታዳጊ ህጻን ግንቦት 17/2012 ዓ.ም አስገድዶ ደፍሯል።
የ40 ዓመት እድሜ ያለው ይሄው ግለሰብ ከደፈራት ታዳጊ ህጻን እናት ጋር በአንድ ተቋም የሚሰሩና በጉርብትናም የሚቀራረቡ ናቸው።
ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሞ ከህጻኗ ጋር በመቀራረብ ደፍሯታል ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ለእናቷ ብትናገር እንደሚገላት ማስፈራራቱን በማስረጃ ተረጋግጧል።
ግለሰቡ በዚህ ሳያበቃ እንደገና ግንቦት 19/2012 ዓ.ም በድጋሜ አስገድዶ ሲደፍራት ወላጅ እናቷ ደርሳ ለፖሊስ አመልክታች።
ፈጽሞታል የተባለው የወንጀሉ ድርጊት በፖሊስ ከተጣራ በኋላ አቃቤ ህግ የመሰረተውን ክስ የተመለከተው የጃዊ ወረዳ ፍርድ ቤት በሰውና ሰነድ ማስረጃ አመሳክሮ ግለሰቡ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ጳጉሜን 4/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል።
መረጃ #2 ፦
በደብረ ማርቆስ ከተማ ህጻን አስገድዶ የመድፈር ሙከራ ባደረገ ግለሰብ ላይ በ12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል።
የከተማ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ህጻኗን ብር ልስጥሽ በማለት ከቤት አታሎ በመውሰድ ሐምሌ 7/2012 ዓ/ም የመድፈር ሙከራ ማድረጉን በሰውና ሰነድ ማስረጃ ተረጋግጧል።
ድርጊቱን ፈጽሟል የተባለው የሃያ ሰባት (27) ዓመት እድሜ ያለው ጳውሎስ ምህረቴ ጥፈተኛነቱ ተረጋግጦበት የከተማው ፍርድ ቤት ጳጉሜን 5/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔው ተላልፎበታል። (ኢዜአ)
@tikvahethiopiaBOT

ከግንቦት 28/2005 ዓ/ም ጀምሮ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ከነገ መስከረም 5/2013 ዓ/ም ጀምሮ ኃላፊነቱ እንደተነሳላቸው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት በተለመደው የዪኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ምልመላ እና ስምሪት መመሪያ መሠረት የሥራ ጊዜያቸውን አጠናቀው በክብር መሰናበታቸውን ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት በተሰጣቸው የኃላፊነት ጊዜ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፆ ምስጋና አቅርቦላቸዋል።
በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ከሃላፊነታቸው ተነሱ እየተባለ የሚሰራጨውና የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሚኒስቴሩ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት በተሰጣቸው የኃላፊነት ጊዜ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፆ ምስጋና አቅርቦላቸዋል።
በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ከሃላፊነታቸው ተነሱ እየተባለ የሚሰራጨውና የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
September 15, 2020
#SPHMMC
የቅዱስ ዻውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ (SPHMMC) ለ3 ወር ያህል አቋርጦት የነበረውን ህክምና መስጠት እንደጀመረ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።
ሆስፒታሉ የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከል ረገድ ምርመራዎች ማካሄድና ታካሚዎችን ከመንከባከብ ጋር ተያይዞ ወደ 25 ሺህ የሚጠጉ ምርመራዎችን እንዳከናወነ ነው የገለፀው።
270 አልጋዎችንም በማዘጋጀት ከኮሮና በሽታ ጋር ተያይዞ የተለየ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ታካሚዎች በመቀበል አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር ተጠቅሷል።
ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ እስከ 900 ሰዎችን በመቀበል 640 ድነው መውጣታቸውና አሁን ላይ ደግሞ 150 ሰዎች በህክምና ላይ የሚገኙ እንደሆኑ ተጠቁሟል።

አፋር ገዋኔ ወረዳ ገለዔ ለዶራ እና ገበያ ቦራ ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቻችን በጎርፍ አደጋ ተፈናቅለዋል።
ዜጎቻችን በጎርፍ ቤታቸው ውድሞባቸዋል ፣ ለፀሐይ ተጋልጠዋል እስከሁን የተደረገላቸው ምንም ዓይነት እርዳታ የለም።
በአደጋው ምክንያት ለረሀብ እና ለውሃ ጥም የተጋለጡ ለነዚህ ምስኪን ወገኖቻችን በፍጥነት እረዳታ መደረግ ይኖርበታል (Hassen Koke)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዜጎቻችን በጎርፍ ቤታቸው ውድሞባቸዋል ፣ ለፀሐይ ተጋልጠዋል እስከሁን የተደረገላቸው ምንም ዓይነት እርዳታ የለም።
በአደጋው ምክንያት ለረሀብ እና ለውሃ ጥም የተጋለጡ ለነዚህ ምስኪን ወገኖቻችን በፍጥነት እረዳታ መደረግ ይኖርበታል (Hassen Koke)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
September 15, 2020
ከ3 ሚሊዮን የሚበልጡ የሶሪያ ተማሪዎች ከእሁድ ጀምሮ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል።
ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ጥብቅ የሆነ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነም ተገልጿል።
ሶሪያ እስካሁ 3,506 ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዘባትንና 152 ሰዎች እንደሞቱባት ሪፖርት አድርጋለች።
ትክክለኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ግን ከዚህ እጅግ እንደሚልቅ ይታመናል። የሀገሪቱ የምርመራ አቅም ዝቅተኛ ነው።
በሶሪያ በግል ክሊኒክ ምርመራ ለማድረግ $60 (የአሜሪካ ዶላር) የሚያስፈልግ ሲሆን መንግስት በየዕለቱ ለቫይረሱ የተጋለጡ ናቸው ላላቸው 300 ሰዎች ነፃ ምርመራ ያደርጋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ጥብቅ የሆነ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነም ተገልጿል።
ሶሪያ እስካሁ 3,506 ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዘባትንና 152 ሰዎች እንደሞቱባት ሪፖርት አድርጋለች።
ትክክለኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ግን ከዚህ እጅግ እንደሚልቅ ይታመናል። የሀገሪቱ የምርመራ አቅም ዝቅተኛ ነው።
በሶሪያ በግል ክሊኒክ ምርመራ ለማድረግ $60 (የአሜሪካ ዶላር) የሚያስፈልግ ሲሆን መንግስት በየዕለቱ ለቫይረሱ የተጋለጡ ናቸው ላላቸው 300 ሰዎች ነፃ ምርመራ ያደርጋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
September 15, 2020
የ'ጥቁር ገበያ'ውን ለመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ ተጀመረ!
በአዲስ አበባ ከባንክ ውጭ የሚደረጉ የውጭ ሀገር ገንዘብ ግብይቶችን በድብቅ ያከናውናሉ ከተባሉ ሱቆች መካከል የተወሰኑት ከትላንት ጀምሮ እንዲታሸጉ መደረጋቸውን 'ኢትዮጵያ ኢንሳይደር' ድረ ገፅ ዘገበ።
የእርምጃው ሰለባ የሆኑት በይፋ ከሚታወቁባቸው አገልግሎቶች ባሻገር የውጭ ሀገር ገንዘቦች ምንዛሬን በተደራቢነት የሚሰጡ ሱቆች ናቸው ተብሏል።
በኢትዮጵያ ሆቴል እንዲሁም ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኙት እነዚህ ሱቆች “ታሽጓል” የሚል ጽሁፍ እና ማህተም የሰፈረባቸው ወረቀቶች በየበሮቻቸው ላይ መለጠፉቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ማረጋገጡን በዘገባው ጠቁሟል።

ሳዑዲ አረቢያ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምክንያት አግዳው የቆየችውን የአየር ፤ የብስና ባህር ትራንስፖርት ከታህሳስ 23/2013 ጀምሮ እንደምታነሳ አሳውቃለች፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዛሬ ጀምሮ የገልፍ ትብብር ምክር ቤት ሀገራት ዜጎች ወደ ሳዑዲ አረቢያ መግባት እንደተፈቀደላቸው ተሰምቷል።
ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሳኡዲ አረቢያ መግባት የሚችሉት የመኖሪያ ፈቃድ ኖሯቸው ከኮሮና በፊት ወጥተው ወደሳኡዲ ለመመለስ ያልቻሉ ፣ የጉብኝት፣ የስራ ቪዛ ያላቸው ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪ ከዛሬ መስከረም 5/2013 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ሳዑዲ አረቢያ መግባት የተፈቀደላቸው (የGCC ዜጎች) ባለፉት 48 ሰዓታት የኮሮና ምርመራ አድርገው ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
የGCC አባል ሀገራት፦
- ሳዑዲ አረቢያ
- ኦማን
- የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ
- ኳታር
- ኩዌት
- ባህሬን
የኡምራ እና ሀጅ ጸሎት ጉዞ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ታይቶ ደረጃ በደረጃ የሚፈቀድ ይሆናል ተብሏል።