TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.9K photos
1.52K videos
215 files
4.17K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
አውስትራሊያ የኢኮኖሚ ውድቀት አጋጠማት!

አውስትራሊያ ከሃያ ዘጠኝ (29) አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢኮኖሚ ድቀት እንዳጋጠማት ይፋ ማድረጓን ኤስ ቢ ሴስ ሬድዮ ዘግቧል።

ከባለፈው ጁን ወር ጀምሮ የነበረው የሶስት (3) ወር የመረጃ ውጤትም ያሳየው የአገር ውስጥ ምርት እድገት በሰባት በመቶ ዝቅ ማለቱን ነው።

የመጀመሪያው የኢኮኖሚ እድገት ማሽቆልቆል የታየው ባሳለፍነው ማርች ወር ሲሆን ይህውም 0.3 በመቶ ነበር፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሁለተኛው ዙር ማእበል ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ደረጃ እንደጎዳውም የቅርብ ጊዜው ውጤት ማመላከቱን ከኤስ ቢ ኤስ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አርቲስት ንብረት ገላው (እከ) በኮሮና ቫይረስ ተይዞ በየረር ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት እንደሚገኝ 'ታዲያስ አዲስ' ለተባለ የሬድዮ ፕሮግራም ተናግሯል።

አርቲስቱ 'ከሞት የተረፍኩት በእግዚአብሔር ተዓምር ነው ፤ እንደእድል ታመው በሽታውን በቀላሉ የተቋቋሙ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን በሽታው እጅግ በጣም ገዳይ ፣ አድካሚ ፣ በመንግስት ህክምና አገልግሎት ማግኘት ካልተቻለ በግል ህክምና በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ የሚወጣበት በጣም ከባድ በሽታ ነውና ሁሉም ሰው መዘናጋቱን ትቶ ይጠንቀቅ' ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መጠናቀቅ #1 በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ሲባል በሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው በከፊል የመጫን ዕገዳ ከዛሬ ጀምሮ መነሳቱ ተገልጿል። የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የአዋጁ ጊዜ መጠናቀቁን በማስመልከት ዕገዳው የተነሳ መሆኑን ዛሬ ለአማራ ክልል መንገድና ትራንስፖርት ቢሮው በላከው ደብዳቤ አሳውቋል። ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም የሕዝብ ትራንስፖርት…
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መጠናቀቅ #2

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ለአምስት (5) ወራት ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መጠናቀቁን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ቀድሞ ወደነበረበት መመለሱን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

ሀገር አቋራጭ አውቶብሶች ከትላንት ጀምሮ በወንበር ልክ መጫን መጀመራቸው የተገለፀ ሲሆን ተሳፋሪዎች ከአዋጅ በፊት ሲከፈሉ በነበረው ታሪፍ ልክ ይከፍላሉ ተብሏል።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ከአዋጁ በፊት ሲከፈል ከነበረው ታሪፍ ጭማሪ ማስከፈል እንደማይችሉ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መጠናቀቅ #2 የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ለአምስት (5) ወራት ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መጠናቀቁን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ቀድሞ ወደነበረበት መመለሱን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል። ሀገር አቋራጭ አውቶብሶች ከትላንት ጀምሮ በወንበር ልክ መጫን መጀመራቸው የተገለፀ ሲሆን ተሳፋሪዎች ከአዋጅ በፊት ሲከፈሉ በነበረው ታሪፍ ልክ ይከፍላሉ…
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መጠናቀቅ #3

በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ ማሻሻያ መደረጉን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ማሻሻያው ፦

- ሚኒባስ ፣ የአንበሳ አውቶብስ ፣ ሸገር እና ሀይገር ባሶች በወንበራቸው ልክ እንዲጭኑ ተወስኗል።

- የሚኒባስ ታክሲዎች ከኋላ ባለው መቀመጫ ከ2 ሰው በላይ መጫን አይችሉም።

- ባለ ሶስት እና ባለ አራት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪዎች እስከ ሹፌሩ 3 ሰው መጫን ይችላሉ።

- ቀላል ባቡር የመጫን አቅም ወደ 75 በመቶ ክፍ እንዲል ተደርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኒባስ ታክሲ ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ተደርጎበታል ፤ ዝርዝር መረጃውን (ማስተካከያውን) ከላይ ባለው ምስል ተመልከቱ!

@TIKVAHETHIOPIABOT
#AddisAbaba

ከተፈቀደው ሰው በላይ መጫን ከ1 ሺህ ብር ጀምሮ ከታሪፍ በላይ ማስከፈል 1 ሺህ 500 ብር ጀምሮ እንደሚያስቀጣ የአ/አ ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል።

ይህንም ለመቆጣጠር ከትራፊክ ፖሊስ በዘለለ የፖሊስ እና የፀጥታ አካላት ተሰማርተዋል።

ህብረተሰቡ ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉና ትርፍ የሚጭኑትን ለመጠቆም የሚጠቀምበት የስክል ቁጥር በቅርቡ ይፋ ይደረጋል መባሉን ከኤፍ ቢ ሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ሳይመን ማርክስን ጨምሮ 10 ሰዎች ወደ መቐለ እንዳሄዱ ታገዱ!

የብሉምበርግ ፣ ኒውዮርክ ታይምስ እና ለቪኦኤ እንግሊዘኛ የሚፅፈው ፍሪላንስ ጋዜጠኛ ሳይመን ማርክስን ጨምሮ ሌሎች አስር (10) የሚደርሱ ሰዎች ወደ መቐለ እንዳይሄዱ ታገዱ።

ጋዜጠኛውን ጨምሮ አስር (10) የሚደርሱት ሰዎች ወደ መቐለ ለመሄድ ቦሌ አየር ማረፊያ ቢገኙም በፀጥታ አካላት እንዳይጓዙ እንደታገዱ ተሰምቷል።

ጋዜጠኛ ሳይመን ማርክስ ወደ መቐለ ሊጓዝ የነበረው ጳጉሜ 4 በትግራይ ክልል የሚደረገውን 6ኛውን ክልላዊ ምርጫ ለመዘገብ እንደነበር ተገልጿል።

Via Elias Meseret (Associated Press)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ወደ መቐለ እንዳይሄዱ ከታገዱት ሰዎች መካከል ' የአውሎ ሚዲያ ' ጋዜጠኞች ይገኙበት እንደነበር የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው አረጋግጦልናል።

ጋዜጠኞቹ ወደ መቐለ ሊጓዙ የነበሩት ጳጉሜ 4 የሚደረገውን ክልላዊ ምርጫ ለመዘገብ ነበር።

ወደ መቐለ ከተማ እንዳሄዱ ከማገድ በተጨማሪ ጋዜጠኞቹ ተይዘው እቃዎቻቸው ተወስዶ አሁን እንደተለቀቁ የአውሎ ዋና አዘጋጅ ገልፆልናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የእነ አቶ ጀዋር መሃመድ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት በዛሬው ዕለት የእነ አቶ ጀዋር መሃመድን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ፡፡

አቶ ጀዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ አስር (10) ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ሕግ መስከረም 8 በከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ እንዲመሰርት ችሎቱ ውሳኔ ማሳለፉን ኢብኮ ዘግቧል።

በተጨማሪ ፍርድ ቤት ከአስራ አንደኛ እስከ አስራ አራተኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ በ5 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰርትባቸው ትእዛዝ ሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጤና ሚኒስትሯ ስጦታ ተበረከተላቸው!

ኔቶር ኢቨንትና ፕሮሞሽን እና አዱሊያን ማስታወቂያ ከዋልታ ቲቪ ጋር በመተባበር 'ክብር ለጤና ባለሞያዎቻችን' በሚል ርዕስ ባዘጋጁት የአዲስ አመት ዝግጅት ላይ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ስጦታ ተበረከተላቸው።

ስጦታውን ያበረከተው የከበሩ ማዕድናት አቅራቢዎች ማህበር ሲሆን ማህበሩን በመወከል የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ሳሙኤል ግዛዉ ስጦታውን ለዶ/ር ሊያ አበርክተዋል።

ለዶ/ር ሊያ የተበረከተላቸው ስጦታ በአለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊነት ያለቸዉ ኤመራልድ እና ሞንጋናይዝ የተባሉ የከበሩ ማዕድናት እንደሆኑም አዘጋጆቹ አሳውቀውናል።

በፕሮግራሙ ላይ የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል ፣ የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ ጨምሮ ሌሌች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተው ነበር።

ዝግጅቱ ለአዲስ አመት ዋዜማ በዋልታ ቲሌቪዥን ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ እንደሚተላልፈ ተገልጾልናል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ መንግስት ለ2 ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች የኦፕሬተርነት ፍቃድ ወስደው እንዲሰሩ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻ ለተመረጡት ኩባንያዎች የሚተላለፍ ሲሆን 5 በመቶ ድርሻ ደግሞ ለኢትዮጵያውያን ይሸጣል።

የ5 በመቶ አክስዮን ሽያጭም በጥቂት ግለሰቦች የሚያዝ ሳይሆን ሁሉም ዜጋ አቅሙ በፈቀደ መጠን የሚሳተፍበት መሆኑ ታውቋል።

የማሻሻያ ስራዎቹን በተመለከተ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የባለድርሻ አካላት ወይይት መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በፓኪስታን ትምህርት ቤቶች ሊከፈቱ ነው!

በፓኪስታን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተዘጉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 5/2013 ዓ.ም ጀምሮ ሊከፈቱ እንደሆነ ተሰምቷል።

የሀገሪቱ መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮቪድ-19 የሚያዙ እንዲሁም የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በመቀነሱ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጳጉሜ 2/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 684 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 690 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 28 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት፦
- 9 ከመንጌ ወረዳ
- 5 ከሸርቆሌ ወረዳ
- 4 ከሆሞሻ ወረዳ
- 1 ከአሶሳ ወረዳ
- 9 ከበሎ (ምዥጋ ወረዳ)

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 521 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 17 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 4,947 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 61 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል (ከደ/ብርሃን የኮሮና ህክምና ማዕከል)

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 20 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 14 ከሰ/ወሎ ዞን
- 14 ከጎንደር ከተማ ይገኙበታል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3,367 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 346 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 212 ከምስራቅ ሸዋ
- 31 ከምዕራብ ወለጋ
- 28 ከቢሾፍቱ ከተማ
- 14 ከጅማ ከተማ
- 12 ከሰበታ ከተማ
- 9 ከአርሲ ዞን ይገኙበታል።

@tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,449 የላብራቶሪ ምርመራ 976 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 482 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 59,648 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 933 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 21,789 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጳጉሜ 2/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,356 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ ስድስት (66) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ቫይረሱ የተያዙት፦
- ከወላይታ ዞን 17 (7 ከሶዶ ዙሪያ፣ 7 ከዱጉና ፋንጎ፣ 1 ከሶዶ፣ 1 ዳሞት ሶሬ እና 1 ከቦሎሶ ሶሬ) ፣
- ከደቡብ ኦሞ ዞን 12 ( 6 ከሳላማጎ እና 6 ከማሌ)፣
- ከቤንች ሸኮ ዞን 8 (8ቱም ከሚዛን ከተማ )፣
- ከሃዲያ ዞን 7(3 ከጊምቢቹ፣ 3 ከምስራቅ ባደዋቾ እና 1 ከሾኔ)፣
- ከደራሼ ልዩ ወረዳ 4፣
- ከጋሞ ዞን 3 (1 ከአርባምንጭ ፣ 1 ከዲታ እና 1 ከጨንቻ)፣
- ከዳውሮ ዞን 3 (3ቱም ከማረቃ)፣
- ከጉራጌ ዞን 3 (3ቱም ከምሁር አክሊል)፣
- ከአሌ ልዩ ወረዳ 2፣
- ከስልጤ ዞን 2 (1 ከጦራ እና 1 ከወራቤ ከተማ)፣
- ከጌዴኦ ዞን 2 (1 ከጨለለቅቱ እና 1 ከወናጎ)፣
- ከቡርጂ ልዩ ወረዳ 1፣
- ከከምባታ ጠምባሮ ዞን 1 ( ከዱራሜ ከተማ)፣
- ከሃላባ ዞን 1 (ዌራዲጆ) ናቸው።

#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 195 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 26 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,142 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 107 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ሰማንያ ሰባት ሰዎች ከማህበረሰቡ የተገኙ ናቸው።

@tikvahethiopiaBOT